Yeka Wereda 06 Urban Beauty and Green Development Office

Yeka  Wereda 06 Urban Beauty and Green Development Office

Share

Enderas

Photos from Yeka  Wereda 06 Urban Beauty and Green Development Office's post 20/02/2025

የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ቢሮውን ለአገልግሎት ምቹ በማድረግና በማዘመን በዛሬው ዕለት ሥራችን በራዕያችን ይመራል በሚል መሪ ቃል ስማርት ፅ/ቤት አስመርቋል::

የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም
የካ ወረዳ 06 አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት

በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ቢሮውን ለአገልግሎት ምቹ በማድረግና በማዘመን በዛሬው ዕለት የማስመረቂያ መርኃ-ግብር አካሂዷል።

በመርኃ ግብሩ ላይ የየካ ክ/ከተማ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ከበደ፤ የወረዳ 06 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ምስጋነው ህንጂሉ ፣ የም/ቤት መሬት ግንባታ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ባለድርሻ አካላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችን ጨምሮ የወረዳው አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የወረዳው የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ላለፉት 3 ዓመታት በወረዳም ሆነ በክ/ከተማ ስኬታማ የስራ ጊዜዎችን በማሳለፍ ከ 4 ዋንጫዎች በላይ በማምጣት እንዲሁም ሞዴል የነበረውን ቢሮ በቴክኖሎጂ የማዘመን፣ ውብ፣ ማራኪ እና አረንጓዴ በማድረግ እና በቁጥር 12 የሚሆኑ ተሞከሮዎች በመፍጠር ቢሮውን ወደ ስማርት ጽ/ቤት የተሸጋገረበትን ቀን ማስመረቅ ችሏል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የየካ ክ/ከተማ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ከበደ ተቋሙን ስማርት በማድረግ የተሰራው ስራ እጅግ የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ በ2022 ዓ.ም እንደ ተቋም የተያዘውን ውብ፣ማራኪና አረንጓዴ ስማርት ተቋም እና ከተማን የመፍጠር ራዕይን ቀድሞ ያሳከ ብቻኛ እና ድንቅ ጽ/ቤት መሆኑን የክ/ከተማ እና ወረዳ ተቋማት ልምድ እንዲወስዱ እንደሚደረግ በመግለጽ የከተማ አስተዳደሩ በወረዳው የተሰራውን ስራ ለሌሎች ክ/ከተማ እና ወረዳዎች የማስፋፋት ስራ እንዲሰራ እንደሚደረግ ተናግረዋል ።

በመጨረሻም በቢሮ ማዘመን ስራ አስተዋጽኦ ላደረጉ የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል።
እንዲሁም በ2016 በጀት ዓመት እና በ2017 በጀት ዓመት የመጀመረያ 6ወር ጥሩ የስራ አፈፃፀም የነበራቸው ባለሞያዎች የእውቅና ሽልማትና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል ። የፅ/ቤቱ ሀላፊዎች የሽኝትና የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃግብር ተካሂዷል ።

Photos from Yeka  Wereda 06 Urban Beauty and Green Development Office's post 12/12/2024

"የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ!!"

ታህሳስ 03 ቀን 2017 ዓ.ም
የካ ወረዳ 06 የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት

የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት "የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ!!" በሚል መሪ ቃል የግንዛቤ መስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

በዕለቱም በየካ ክፍለ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት የተፋሰስ ባለሙያ አቶ ውብሸት ወ/ሚካኤል ሰነድ የቀረበ ሲሆን በአረንጓዴ ልማትና ፣ ስለችግኝ አተካከልና እንክብካቤ፣ በቅንጅታዊ አሰራር፣ በዜጎች ቻርተር ዙሪያ እንዲሁም በከተማ ደረጃ የችግኝ ጠቀሜታን ጨምሮ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ ቀርቧል።

አቶ ውብሸት አክለው ግንዛቤው ማህበረሰቡ የተከላቸውን ችግኞች በባለቤትነት ስሜት እየተንከባከበና ጥቅሙን በመረዳት የጊቢውን ውበት በመጠበቅና ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞችን በአግባቡ እንዲንከባከቡ እንደረዳቸው ገልፀው በቀጣይ ግንዛቤውን በማጠናከር የወረዳው ማህበረሰብ ከዚህ በበለጠ በአረንጓዴ አሻራ ላይ ይበልጥ ተሳትፎ ይደረጋል ብለው እንደሚያስቡም ተናግረዋል።

በስልጠናው ላይም የሴፍቲኔት፣ ሴት ሊግ፣ ወጣት ሊግ፣ አካል ጉዳተኛ፣ ከ22 ሴክተር ጽ/ቤት የተወጣጡ ሠራተኞች እንዲሁም በወረዳው የሚገኙ ተቋማት ተሳትፈዋል።

Photos from Yeka  Wereda 06 Urban Beauty and Green Development Office's post 06/12/2024

ህዳር 27/2017 ዓ.ም
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ፅ/ቤት
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ፅ/ቤት የከተማውን ውበትና አረንጓዴ ሽፋን ለማሳደግ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ። በመሆኑም በብርሃን ጉዞ የመጀመረያ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት የተተከሉ ችግኞች በመንከባከብ የዜግነት ግዴታችን እንወጣ በሚል መሪ ቃል ችግኞችን የመንከባከብ ፣የመኮትኮት፣ ውሃ የማጠታት ፣የመከርከም ስራ ተሰርቷል ። በመረሃ ግብሩም ላይ የአስተዳደር ሰረተኞች፣መምህራን ፣ተማሪዎችና ባለድረሻ አካላት ተሳታፊ ነበሩ ።በቀጣይም ችግኞችን የመንከባከብ ስራ በሌሎች ትምህርት ቤቶችና ተቋማት ላይተጠናክሮ ይቀጥላል::

Photos from Yeka  Wereda 06 Urban Beauty and Green Development Office's post 04/12/2024

ህዳር 25/2017 ዓ.ም
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት

የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት የበጋ ወቅትን ምክንያት በማድረግ በወረዳው የሚገኙ አረንጓዴ ቦታዎች ላይ ቀይ አፈር እና ኮምፖስት የመበተን ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል::
እንደ አረንጓዴ ተክሎች ሁሉ ሣር የፀሐይ ብርሃንን እና ክሎሮፊልን በመጠቀም ኃይልን ወደ ሥሩ ይልካል፣ ይህም በአፈር ውስጥ እርጥበት እና ንጥረ ምግቦችን በማምረት አዲስ እድገትን ያመጣል። ለዛም ነው ከስር ጥሩ አፈር መኖሩ ልክ እንደሌላው ተክል ለጤናማ ሳር አስፈላጊ የሆነው:
በሌላ በኩልኮምፖስት ካርቦን በመጨመር የአፈርን መዋቅር ለማሻሻል እና የተክሎች ንጥረ ነገሮችን ለማቅረብ ያገለግላል። እንደ ናይትሮጅን (N)፣ ፎስፎረስ (P) እና ፖታሲየም (K) ያሉ የእፅዋት ንጥረ ነገሮች ምንጭ ከመሆኑ በተጨማሪ የአፈርን ፊዚኮ-ኬሚካላዊ እና ባዮሎጂያዊ ባህሪያትን ያሻሽላል።
በዚህም የለሙ አረንጓዴ ቦታዎች ላይ ቀይ አፈር እና ኮምፖስት በመጨመር አረንጓዴነቱን የማስቀጠል ስራ በጋራ እንስራ ።
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት

Photos from Yeka  Wereda 06 Urban Beauty and Green Development Office's post 26/11/2024

ህዳር 17/ 2017 ዓ.ም
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ፅ/ቤት

የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ፅ/ቤት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ፅ/ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ አካሂደዋል። በልምድ ልውውጡ ላይ የተለያዩ ተሞኩሮዎች ያገኙበት እንደሆን የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ፅ/ቤት የቡድን አስተባባሪው እና ባለሞያዎች ገልጿል ።

Photos from Yeka  Wereda 06 Urban Beauty and Green Development Office's post 12/11/2024

ህዳር 3/2017 ዓ.ም
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ፅ/ቤት
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ፅ/ቤት የከተማውን አረንጓዴ ሽፋን ለማሳደግ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ። በመሆኑም በ ወረዳው በ ቀበሌ 29 ወንዝ ዳርቻ ላይ የተተከሉ ችግኞች በመንከባከብ የዜግነት ግዴታችን እንወጣ በሚል መሪ ቃል እና ወንዞቻችንን ከብክለት እንጠብቃቸው በሚል መሪ ቃል ችግኞችን የመንከባከብ እና ወንዝ ዳርቻን የማፅዳት ስራ ተከናውኗል ። በመረሃ ግብሩ ላይ የተለያዩ የብሎክ አደረጃጀቶችና ሴፍትኔት ተሳታፊ ነበሩ ።በቀጣይም ችግኞችን የመንከባከብ ውሃ የማጠጣት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል::

Photos from Yeka  Wereda 06 Urban Beauty and Green Development Office's post 11/11/2024

ህዳር 2/2017 ዓ.ም
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ፅ/ቤት
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር የከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ፅ/ቤት የከተማውን አረንጓዴ ሽፋን ለማሳደግ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ። በመሆኑም በ ወረዳው በ ሁሉም ቀጠናዎች የ20/50 ራድየስ ቦታዎች የግንዛቤና የእንክብካቤ ስራዎች ወቅቱን በጠበቀ ሁኔታ ተጠናክሮ ቀጥሎዋል::

Photos from Yeka  Wereda 06 Urban Beauty and Green Development Office's post 05/11/2024

ጥቅምት 26/ 2017 ዓ.ም
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ፅ/ቤት አስተባባሪነት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ውይይት አካሂደናል ::በውይይቱም ላይ ቅንጅታው አሰራራችንን በደንብ ማጠናከር እንዳለብን ስራዎችን በጋራ ተናበንና ተደጋግፈን መስራት እንዳለብን የጋራ ውይይት ተደርጓል :: በውይይቱም ላይ የፅዳት አስተዳደር፣ ደንብ ማስከበር ፣ት/ት ፅህፈት ቤት ፣በጎፍቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ፣ከተማ ግብርና እና ሴፍትኔት ተሳታፊ ነበሩ።

Photos from Yeka  Wereda 06 Urban Beauty and Green Development Office's post 18/10/2024

የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት 2016በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀምና የ2017 የእቅድ ውይይት አካሂደናል።

መስከረም 08 ቀን 2017 ዓ.ም

የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈፀፃም በመገምገም የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂደናል፡፡

የከተማ ውበት ከመጠበቅ አንፃር አደባባዮችን ተቋማትን የመኖሪያ አካባቢዎችን በማስዋብ ምቹና አረንጓዴ አካባቢን በመፍጠር እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ ከዕቅድ በላይ ማከናወን መቻሉን በሪፖርቱ በዝርር ቀርቧል፡፡

በቀረበው ዕቅድ እና ሪፖርት ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከተሳታፊዎች ለቀረቡ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ከመድረክ ሰፋ ያለ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

Photos from Yeka  Wereda 06 Urban Beauty and Green Development Office's post 07/09/2024

ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት ለህብረተሰቡ ሙሉ ቀን አገልግሎት እየሰጠን እንገኛለን፡፡

ጳጉሜ 2/2016 ዓ.ም
የካ ወረዳ 06 የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት

በዛሬው እለት እየተከበረ ያለው የጳጉሜ 2 የሪፎርም ቀን ምክንያት በማድረግ በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 06 የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት በሚል መሪ ቃል ለህብረተሰቡ ሙሉ ቀን አገልግሎት እየሰጠን እንገኛለን፡፡

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Ababa