ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወ09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት NFSLK w09 JEIDB

ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወ09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት NFSLK w09 JEIDB

Share

This page is created in order to share timely information regarding job, enterprise and industry development bureau to enterprises and work colleagues.

Photos from ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወ09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት NFSLK w09 JEIDB's post 24/08/2022

፨፨ ተቋሙ የ2015 በጀት ዓመት የተቋሙን እቅዶች ግምገማ አደረገ፨
✍...የስራ ኢን/ዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የ2015 በጀት ዓመት እቅድ የስራ ኢንተርፕራይዝ ሃላፊ አቶ ዳግም ጸጋዬ ከቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ጋር በጋራ በመሆን የገመገመ ሲሆን መስተካከል ያለበትን ነገር አስተያየቶችን በማስቀመጥ ተጠናቀቀ።
ቀን 18/12/2014 ዓ.ም

Photos from ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወ09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት NFSLK w09 JEIDB's post 24/03/2022

.....✍️በቀን 15/7/14ዓ.ም በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ከአከባቢ ጥበቃ ጋር በጋራ በመሆን የምግብ ዋስትና የሴፍትኔት ተጠቃሚዎች በከተማ ግብርና ዘርፍ በጓሮ አትክልት ለ 3ዓመት ሲያለሙበት የነበረበትን ቦታ ልኬት በማድረግ ህጋዊ አደረጃጀቱን ጠብቀዉ ዉል ተዋዉለዉ ወደ ስራ እንዲገቡ እንደተደረገ የወረዳ 09 ምክትል ስራ አስፈጻሚ እና የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ዳግም ጸጋዬ አሳወቁ፡፡
ገጻችንን እየገባችሁ like, follow and Join በማድረግ ፈጣን ትክክለኛ እና ትኩስ መረጃዎችን ይከታተሉ፡፡
ቴሌግራም ግሩፓችንን:- https://t.me/+YjAxvZlMCgRjYmNk
ፌስቡክ ፔጃችን:- https://www.facebook.com/nslakkw09jeidb
ኢሜይል አድሬስ፡- [email protected]
የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 የስራ ኢን/ዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቡድን

Photos from ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወ09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት NFSLK w09 JEIDB's post 25/02/2022

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ከኤስ.ኦ.ኤስ ጋር በመተባበር በወረዳ 09 የስራ ፈላጊዎችን ከቀን 11/6/2014 ዓ.ም እስከ 17/6/2014ዓ.ም በንግድ ክህሎት ዙሪያ በማሰልጠን፣ የስምምነት ሰነድ በመፈረም እና የሚደራጁበትን ዘርፍ እንዲመርጡ በማድረግ ስልጠናዉ ተጠናቋል፡፡
ገጻችንን እየገባችሁ like, follow and Join በማድረግ ፈጣን ትክክለኛ እና ትኩስ መረጃዎችን ይከታተሉ፡፡
ቴሌግራም ግሩፓችንን:- https://t.me/+YjAxvZlMCgRjYmNk
ኢሜይል አድሬስ፡- [email protected]
የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 የስራ ኢን/ዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቡድን

Photos from ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወ09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት NFSLK w09 JEIDB's post 21/02/2022

፨፨፨፨፨የወረዳ 09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት፨፨፨፨፨፨
✍በቀን 14/6/2014 የስራ ኢንተ/ዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ለወረዳ 09: 31 ለወረዳ 07: 37 እና አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 06: ለ30 ስራ ፈላጊዎችን የወረዳ 09 ም/ስራ አስፈጻሚ እና የስራ ኢንተ/ዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዳግም ጸጋዬ በማወያየት በፓርኪንግ እና በተለያዩ ዘርፎች በጊዜያዊ የስራ እድል ፈጠራ የሚደራጁበትን ዘርፍ በመምረጥ የሚጠበቅባቸውን መረጃ በመሟላት እንዲደራጁ ግንዛቤ ተፈጥሮላቸዋል።

Photos from ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወ09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት NFSLK w09 JEIDB's post 14/02/2022

***የወረዳ 09 የስራ ኢን/ዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት***
✍️በ ቀን 7/6/2014 በን/ስ/ላ/ክ/ከ ወረዳ 09 የስራ ኢን/ዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ እና ባለሙያዎች በጋራ በመሆን የ6ወር የፈጻሚዎች የቢ.ኤስ.ሲ ምዘና በ1 ባለሙያ ልዩነት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል እንዲሁም የጥር ወር ሪፖርት ግምገማ በማድረግ በድክመት የተነሱትን በቀጣይ መስተካከል እንዳለበት በመተማመን ዉይይቱ ተጠናቋል።

Photos from ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወ09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት NFSLK w09 JEIDB's post 12/02/2022

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍል ከተማ ወረዳ 9 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ አድርጎል። በስብሰባው ላይ የቀጣይ 6 ወራት የስራ እድል ፈጠራ እቅድ ላይ ተወያይቷ በተጨማሪ በፕሮጀክት ባለሙያዎች የተለዩ ጸጋዎችን ተወያይቷ እና ተጨማሪ ቦታዎችን አካቷ ጽ/ቤቱ ለክፍለ ከተማ መላክ ያለበትን እንዲሊክ እና እንዲያጽድቅ ሌሎቹን በወረዳ ለስራ ፈላጊ ዜጎች ተጠቃሚ እንዲያደርጉ የውሳኔ ሃሳብ በመስጠት አጽድቋል።

Photos from ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወ09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት NFSLK w09 JEIDB's post 12/02/2022

በዛሬ ቀን 3/6/2014 ዓ.ም የአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ07 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ከወረዳ 09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ጋር የልምድ ልዉዉጥ ያደረጉ ሲሆን በልምድ ልዉዉጥ ወቅት የተሻሉ የሚባሉ ተሞክሮዎችን በመዉሰድ ቡድን መሪዎችንና ባለሙያዎችን ስላደረጉት የመረጃ ልዉዉጥ አመስግነዉ ተጠናቋል፡፡....✍🏿

Photos from ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወ09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት NFSLK w09 JEIDB's post 12/02/2022

የንፋስ ስልክ ቴክንክ እና ሙያ ኮሌጅ
በግብርና ዘርፍ ስልጠና ላይ ያሉ ሰልጣኞችን ወረዳ 09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት በእፃዋት ዘርፍ የተሻለ ስራ እየተሰራ በመሆኑ ለሰርቶ ማሳያ የተግባር ስልጠና ከከተማ ግብርና ባለሙያ ጋር በመሆን በቀን 3/6/14 የመስክ ቦታ ላይ በመገኘት ስልጠና ሰጥተዋል ።

Photos from ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወ09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት NFSLK w09 JEIDB's post 12/02/2022

የንፋስ ስልክ ቴክንክ እና ሙያ ኮሌጅ
በግብርና ዘርፍ ስልጠና ላይ ያሉት ሰልጣኞች በወረዳ 09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት በእጽዋት ዘርፍ የተሻለ ስራ እየተሰራ በመሆኑ ለሰርቶ ማሳያ የተግባር ስልጠና ከከተማ ግብርና ባለሙያ ጋር በመሆን በቀን 3/5/14 የመስክ ጉብኝት አድርገዋል።

Photos from ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወ09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት NFSLK w09 JEIDB's post 03/02/2022

በቀን 26/5/2014ዓ.ም የን/ስ/ላ/ክ/ ከተማ የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የሱፐርቭዥን ባለሙያዎች የወረዳ 09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ተቋምን የ6ወር አፈጻጸም መዝነዋል በምዘናዉ ወቅት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዳግም ጸጋዬ፣ 6ቱም ስራ ሂደቶችና ባለሙያዎች መረጃዎችን ያቀረቡ ሲሆን እንዳጠቃላይ የጽ/ቤቱ የ6ወር አፈጻጸም የተሻለ መሆኑን እንደሚያሳይ መዛኞቹ ተናግረዋል፡፡

Photos from ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወ09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት NFSLK w09 JEIDB's post 31/12/2021

በቀን 21/4/2014ዓ.ም የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ሰራተኞችና እና የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳግም ጸጋዬ በተገኙበት በጋራ የ6ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት 6ቱም የስራ ሂደቶች ሪፖርታቸዉን ያቀረቡ ሲሆን በባለሙያዎች ጥያቄዎች፣ አስተያየቶች እንዲሁም ከስራተኛ ዲስፕሊን አንጻር የነበረዉ ሁኔታ የተነሱ ሲሆን የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳግም ጸጋዬ በቀጣይ በድክመት አፈጻጸማቸዉ ዝቅ ያሉ ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት እና የተሻለ ዉጤት መመዝገብ እንዳለበት በመግባባት ዉይይቱ ተጠናቋል

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Bole
Addis Ababa
SARIS