ለሚኩራ ወረዳ 13 ፕሬስ/Lemikura Woreda 13 Press

ለሚኩራ ወረዳ 13 ፕሬስ/Lemikura Woreda 13 Press

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ለሚኩራ ወረዳ 13 ፕሬስ/Lemikura Woreda 13 Press, Public & Government Service, Addis Ababa.

Photos from ለሚኩራ ወረዳ 13 ፕሬስ/Lemikura Woreda 13 Press's post 19/08/2021

ሆያሆዬ ሆ!ሆያሆዬ ሆ!እንኳን ለቡሄ በዓል በሰላም አደረሳችሁ/ሰን።
አዲስ አበባ፣ለሚ ኩራ፣ወረዳ 13(ነሃሴ 13/2013ዓ.ም)በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 አስተዳድር ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ጽ/ቤት አዘጋጅነት የ2013ዓ.ም የቡሄን በዓል በአስተዳድሩ የወጣቶች ማዕከል አዳራሽ የአስተዳድሩ ሠራተኞችና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸዉ አካላት በተገኙበት ደማቅ ኘሮግራም የተካሄደ ሲሆን በዚህ ኘሮግራም የተለያዩ ባህላዊ ይዘት ያላቸዉ የቡሄ ጭፈራ ሆያ ሆዬ፤የስነጹፍና የሙዚቃ ድግስ ኘሮግራሙን ያደመቁና የበዓሉን በዓላዊ ይዘት የሚዘክሩ ዝግጅቶች ለታዳሚያን ቀርበዋል።እንዲሁም በዓሉን የሚገልጹ የተለያዩ በራሪ ወረቀቶችና ብሮሸሮች ለታዳሚያን ተሰራጭተዋል።

Photos from ለሚኩራ ወረዳ 13 ፕሬስ/Lemikura Woreda 13 Press's post 19/08/2021

የመሠረታዊ ድርጅትና የህዋስ አመራሮች ዉይይት ተካሄደ።
አዲስ አበባ፣ለሚ ኩራ፣ወረዳ 13(ነሃሴ 13/2013ዓ.ም)በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳድር የወረዳ 13 አስተዳድር ድርጅት ጽ/ቤት የመሠረታዊ ድርጅትና የህዋስ አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮችና በህዋስና በአባላት መልሶ መደራጀት እንዲሁም በ6ኛዉ አገር አቀፍ ምርጫ አፈጻጽም ዙሪያ ሰፊ ዉይይት አካሂደዋል።
በዉይይቱ የተለያዩ ሃሳቦች እንዲሁም ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን በመድረክ አወያዮች ማብራሪያና ምላሽ ተሠጥተዋል።

Photos from ለሚኩራ ወረዳ 13 ፕሬስ/Lemikura Woreda 13 Press's post 18/08/2021

አስተዳድሩ የሀገር መከላከያ የሃብት ድጋፍ አሰባሰብ፤ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታና የክረምት የበጎ አድራጎት ስራዎችን ገመገመ።
አዲስ አበባ፣ለሚ ኩራ፣ወረዳ 13(ነሃሴ 12/2013ዓ.ም)በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 አስተዳድር የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሃብት አሰባሰብ ድጋፍ፣በአካባቢዉ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታና የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎች ሁሉም አመራሮች በተገኙበት የጋራ በማድረግና በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ዉይይት ተካሂዷል።በተመሣሣይ የህዋስ መልሶ ማደራጀትና የአዲስ አባላት ምልመላ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ በመገምገም ተጠናክሮ መቀጠል በሚችልበት ሁኔታ ዙሪያ ዉይይት ተካሂዷል።የመከላከያ ድጋፍ በማሰባሰብና በቀጥታ በመሣተፍ ህዝቡ የጸጥታ ስራን በባለቤትነት በመሣተፍ ሁሉም አካባቢዉን በንቃት መቃኘትና መጠበቅ እንደሚገባና በየብሎኩ የፀረ-ሰላም ሃይሎችን የመለየት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርብናል።የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎች የቤት እድሳትን ጨምሮ የያዝነዉ የክረምት ወራት ሳይጠናቀቅ ስራዎችን መጨረስ በሚቻልበት ሁኔታ ዉይይት በማካሄድ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

Photos from ለሚኩራ ወረዳ 13 ፕሬስ/Lemikura Woreda 13 Press's post 07/08/2021

አስተዳድሩ ከአዳማ የከተማዉ የከፍተኛ የሥራ ግምገማና የእቅድ ዉይይት በሏላ የመንግስትንና የድርጅትን የሥራ እንቅስቃሴ ገምግሟል።
አዲስ አበባ፣ለሚ ኩራ፣ወረዳ 13(ነሃሴ 1/2013ዓ.ም)በለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳድር የወረዳ 13 አስተዳድር ከፍተኛ አመራሮች በአዳማ ከተማ የስራ ግምገማና የ2014ዓ.ም የእቅድ ዉይይት በሏላ የመንግስትና በድርጅት ሥራዎችን ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ በመገምገም ፤የአገልግሎት አሰጣጥን በሚሻሻልበት ሁኔታ ሁሉም የወረዳዉ አመራሮችና የክ/ከተማ አስተባባሪዎች ዉይይት ተካሂዷል።
በተጨማሪም በቀን 02/12/2013ዓ.ምን በከተማ ደረጃ በመስቀል አደባባይ ለሚካሄደዉ ኘሮግራም የወረዳ አስተዳድሩ ያለዉን ሁሉን አቀፍ ዝግጅት በመገምገምና የጋራ በማድረግ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

Photos from ለሚኩራ ወረዳ 13 ፕሬስ/Lemikura Woreda 13 Press's post 07/08/2021

አስተዳድሩ የሃገር መከላከያ ሰራዊት የሃብት አሰባሰብና የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎችን እንዲሁም የመደበኛ መደበኛ ያልሆኑ ስራዎችን ያሉበትን ሁኔታ በመገምገም ችግሮችን በመለየት የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጧል።
አዲስ አበባ፣ለሚ ኩራ፣ወረዳ 13(ሃምሌ 30/2013ዓ.ም)በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 አስተዳድር ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የሃብት አሰባሰብን፣የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎችን እንዲሁም የመደበኛና መደበኛ ያልሆኑ የሥራ እንቅስቃሴን ያሉበትን ደረጃ በመገምገም የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጧል።የሃገር መከላከያ ሠራዊት ከምንም በላይ ህዝባዊ ድጋፍን የሚሻ ጊዜ ላይ በመሆናችን በመገንዘብ እንደከዚህቀደሙ ህዝባዊ ደጀን በመሆን በሎጅስቲክና በሠዉ ሃይል ድጋፍ የማድረጉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገልጿል።የክረምት የበጎ ፍቃድ የቤት እድሳትን ጨምሮ በቀጣይ አንድ ሳምንት በሁሉም ቀጠናዎች መጠናቀቅ እንዳለበት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።የቀጣይ ትምህርት ዘመን የተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ማሠባሠብና ለአዲስ ዓመት የማዕድ ማጋራት የሃብት ማሰባሰብ ከወዲሁ ስራ መሥራት ይኖርብናል የሚል የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

Photos from ለሚኩራ ወረዳ 13 ፕሬስ/Lemikura Woreda 13 Press's post 27/07/2021

አስተዳድሩ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የድጋፍ አሰባሰብና የክረምት የበጎ ፍቃድ ሥራዎችን ገመገመ።
አዲስ አበባ፣ለሚ ኩራ፣ወረዳ 13(20/2013ዓ.ም) በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 አስተዳድር የሀገር መከላከያ ሠራዊት የድጋፍ አሰባሰብንና የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎችን እንዲሁም ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታን ያሉበትን ሁኔታ በመገምገም ያሉ ክፍተቶችን በመለየትና የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ሁሉም አመራሮች በተገኙበት ዉይይት ተካሂዷል።

Photos from ለሚኩራ ወረዳ 13 ፕሬስ/Lemikura Woreda 13 Press's post 27/07/2021

በወረዳ አስተዳድሩ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት የሴፍትኔት ተጠቃሚ የነበሩ ዜጎች ተመረቁ።
አዲስ አበባ፣ለሚ ኩራ፣ወረዳ 13(ሃምሌ 20/2013ዓ.ም)በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 አስተዳድር ለሦስት ዓመታት የሴፍትኔት አገልግሎት ተጠቃሚ የነበሩ 172 አባወራዎችና 876 እማወራዎች ተመርቀዋል።በአጠቃላይ ዛሬ የተመረቁት እማወራዎችና አባወራዎች በስራቸዉ ወ=1568,ሴ=2110,ድ=3644 የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የነበሩ ሲሆን፣በቀጣይ ተመራቂዎች ወደ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርኘራይዞች ተሸጋግረዋል።
በኘሮግራሙ ላይ የተገኙት የወረዳዉ ም/ዋና ስራ አስፈጻሚና የት/ት ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ኢብሳ ተመስጌን የተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ፤ተመራቂዎች ባለፈዉ ሦስት አመታት በቆጠባችሁት ገንዘብ በመነሳት፣የቁጠባና የሥራ ባህልን በማጠናከር ወደ ቋሚ የሥራ እድል ፈጠራ መሸጋገር እንዳለባቸዉ መልዕክት አስተላልፈዋል።በሦስት ዓመታት ዉስጥ የተከፈለ አጠቃላይ የገንዘብ መጠን 31,599,480 ብር ሲሆን የተቆጠበ የገንዘብ መጠን ደግሞ 6,384,354 ብር መሆኑን የጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ጸጋአብ ገልጸዋል።

Photos from ለሚኩራ ወረዳ 13 ፕሬስ/Lemikura Woreda 13 Press's post 23/07/2021

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የከተማ ሴፍትኔት ተጠቃሚዎችን ለመመልመል ፣የመልማዮች ስልጠና መሰጠት ተጀመረ።
አዲስ አበባ፣ለሚ ኩራ፣ወረዳ 13(ሃምሌ 16/2013ዓ.ም)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በሁሉም ክ/ከተሞችና ወረዳዎች በአዲስ የከተማ ሴፍትኔት ተጠቃሚዎችን ለመለየት ፣የመልማዮች ስልጠና ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በቦሌ ማንፋክቼሪንግ ኮሌጅ ስልጠና የጀመረ ሲሆን፤እንደ ወረዳ 13 ከሁሉም ቀጠናዎች የተዉጣጡ 63 የምልመላ ሰልጣኞች ስልጠና እየወሰዱ ሲሆን የወረዳዉ የሴፍትኔት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጸጋአብ በከተማችን የከተማ የሴፍትኔት አገልግሎት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የከተማችን ነዋሪዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ አገልግሎት ሲሰጥ የቆዬ ሲሆን በዋናነት ተጠቃሚዎች በቋሚነት ራሳቸዉን የሚያስተዳድሩበት የሥራ ዘርፍ ማሸጋገር ዋናዉ አላማ ነዉ።
በመሆኑም ሠልጣኞች በስልጠና ወቅት ያገኛችሁትን ልምድ በመጠቀም ያለምንም አድሎ ተጠቃሚዎችን መመልመል እንዲችሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘገባዉ የወረዳዉ ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ነዉ።

Photos from ለሚኩራ ወረዳ 13 ፕሬስ/Lemikura Woreda 13 Press's post 22/07/2021

ሃምሌ 15/2013 ዓ.ም የህወሃት ጁንታን በመቃወምና የመከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በደማቅ ሁኔታ ከጥዋቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል።በሰልፍ ላይ በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጅ መልዕክቶች የዉስጥ ጁንታን የ፣የዉጭ ጠልቃገብነትን የሚያወግዙ መልዕክቶች በመተላለፍ ላይ ናቸዉ።

Photos from ለሚኩራ ወረዳ 13 ፕሬስ/Lemikura Woreda 13 Press's post 20/07/2021

አስተዳድሩ የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎችን በመገምገም በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ዉይይት አካሄደ።
አዲስ አበባ፣ለሚ ኩራ፣ወረዳ 13(ሃምሌ 13/2013ዓ.ም)በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 አስተዳድር የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎች ያሉበትን ተግባራዊ እንቅስቃሴ በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጧል።
በዘህም ዉይይት የክረምት የአረንጓዴ ልማት፣የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት፣የሃገር መከላከያ የህዝብ ድጋፍ፣የደም ልገሳ፣የትራፊክ ትምህርት፣የተማሪዎች የሚሆን የትምህርት ቁሳቁስ ማሰባሰብ የመሣሠሉትን ተግባራት በክረምት ከሚከናወኑ ተግባራት በእቅድ ተይዘዉ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ናቸዉ።በመሆኑም በሂደቱ ላይ ያጋጠሙ ክፍቶችን በመለየት በቀጣይ የሚሠሩ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

19/07/2021

የወረዳ 13 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ደረሰ እንዳለ ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አዲስ አበባ፣ለሚ ኩራ ፣ወረዳ 13(ሃምሌ 12/2013ዓ.ም)በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 13 አስተዳድር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ደረሰ እንዳለ ለእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
ሁሉም የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል-አድሃ በዓል በሠላም አደረሳችሁ ያሉ ሲሆን በዓሉ የሠላም፣የፍቅር፣የመተሳሰብ፣የአብሮነት በዓል እንዲሆን የተመኙ ሲሆን፤በተለይም በዚህ ወቅት በዓሉን ስናከብር የግድባችን የሁለተኛ ዙር የዉሃ ሙሊት በተሳካ ሁኔታ ባጠናቀቅንበት ማግስት በመሆኑ በዓሉን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል።በመሆኑም ሁሉም የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን ስናከብር በአንድ በኩል አገራችን ያለችበትን የዉስጥና የዉጭ ጫናንን በጽናትና በአብሮነት የምንታገልበት በሌላ በኩል የሚታዩ የብልጽግና ተስፋዎችን የምናስቀጥልበት ወሣኝ ምዕራፍ ላይ በመሆናችን በመተባበርና በአንድነት ወደ ማይቀረዉ የተስፋ ጉዟችን መገስገስ ይኖርብናል።
በዓሉን ስናከብር የታመሙትን፤የደከሙትን በመጠየቅና በማካፈል በፍቅር እንድናከብረዉ እያሳሰብኩ በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እፈልጋለሁ፤መልካም በዓል!!

Photos from ለሚኩራ ወረዳ 13 ፕሬስ/Lemikura Woreda 13 Press's post 13/07/2021

አስተዳድሩ ከንግዱ ማህበረሰብና ባለሃብቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዉይይት አካሄደ።
አዲስ አበባ፣ለሚ ኩራ፣ወረዳ 13(ሃምሌ 6/2013ዓ.ም)በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 አስተዳድር ከንግዱ ማህበረሰብና ባለሃብቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዉይይት አካሂዷል።
ዉይይቱን መድረክ የመሩት የአስተዳድሩ ም/ዋና ስራ አስፈጻሚና የትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ኢብሳ ተመሥጌን እንደገለጹት በዚህ ወቅት የንግዱ ማህበረሰብ እንዲሁም ባለሃብቶች የአገራችንንና የከተማችንን ወቅታዊ ሁኔታዎች በትክክል በመገንዘብ ፤ትክክለኛ መረጃ እንዲኖረዉ ማስቻል፤አገራችን አሁን ባለንበት ወቅታዊ ሁኔታ ብዙ ድሎችን እያስመዘገበች ቢሆንም በአንጻሩ ደግሞ በበርካታ አስቸጋሪ ሁኔታዎች እያለፈች ያለች በመሆኗ ማህበረሰባችን ነገሮችን በሰከነ ሁኔታ በመገንዘብና ውዥንብርን በማጥራት በጋራና በመተባበር መንፈስ ያሳካናቸዉ ድሎች እንዳሉ ሁሉ ያሉብንን ችግሮች አሁንም በጋራና በተለመደዉ ድል የማድረግ መንፈስ ማሳካት ይኖርብናል ያሉ ሲሆን በተለይም ከሰላም ማስከበርና በዙሪያዉ ያሉ እዉነታዎች ምን እንደሚመስሉ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣የሁለተኛዉ የግድባችን የዉሃ ሙሊት በስኬት ማጠናቀቅ፤የዉስጥ ባንዳዎችና የዓለም አቀፍ ሚዛናዊነት የጎደለዉን እይታና የመንግስታችንን አቋም ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በቀጣይም ለአገራችን ሁለንተናዊ ብልጽግና የንግዱ ማህበረሰብና በለሃብቶቾ ግብርን በወቅቱና በአግባቡ ከመክፈል ጀምሮ ፤የአካባቢያችንን ሰላም በትኩረት በባለቤትነት መከታተል፤አገራችን በምትጠይቀዉ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ የበኩላቸዉን አስተዋጾኦ እንዲያደርጉ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለባቸዉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘገባዉ የወረዳዉ መንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ነዉ።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Ababa