28/05/2026
ከዛሬ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. (በጥሞና ወቅት) ጀምሮ ምን ምን ማድረግ አይቻልም?
1. በአካልና በዐደባባይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች
👉ፖለቲካ ተኮር የሕዝብ ስብሰባዎችና ሠልፎች
👉የቤት ለቤትና የዐደባባይ ላይ ቅስቀሳዎች
👉የቅስቀሳ ኅትመቶችን እና ቁሳቁሶችን መለጠፍና ማሠርጭት
👉የቅስቀሳ አልባሳትን መልበስ
2. የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት
👉የቀጥታም ሆነ የተቀረጹ የዕጩ ወይም የፓርቲ ፕሮግራሞች ሥርጭት
👉የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾችን በመጠቀም ቅስቀሳ ማድረግ
👉ፕሮጀክት ማስጀመር እና ማስመረቅ
"የጥሞና ጊዜን ማክበር የምርጫውን ተዓማኒነት ያረጋግጣል! መራጩም ያለ ምንም ውጫዊ ተፅዕኖ፣ ግርግርና ቅስቀሳ በሰላም አስቦ እንዲወሥን ይረዳል።"
የተረጋገጡ መረጃዎችን ይፋዊ የቦርዱን የፌስቡክ ገጽ እንዲሁም በሌሎች የቦርዱ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ አማራጮች አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ ሲል ምርጫ ቦርድ አስታውቋል::
27/05/2026
ዛሬ በየደረጃው የሚገኙ የከተማችን የፖሊስ አመራሮች እና አባላት ያካሄዱት በ100 ቀናት እቅድ የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች ማጠቃለያ ግምገማ ላይ ተገኝቼ በርቱ ብያለሁ።
በሪፎርም በተያዙት በመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ባለፉት 100 ቀናት እቅድ ትግበራዎች፣ እያደገችና እየዘመነች ከመጣችው የአፍሪካ እና 3ኛዋ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነቸው መዲናችን አዲሰ አበባን የሚያገለግል የፖሊስ ሰራዊት ገለልተኛ ሆኖ በህግ እና በህዝብ የተጣለበትን አደራ በአግባቡ የሚወጣ ተቋም ሆኖ እንዲጠናከር፤ በሥነምግባር ክብሩ የተጠበቀ፣ በሰው ሃይል አቋም ብቁ የሆነና በአሰራርም ከዘመኑ ጋር የዘመነ እየሆነ እንዲሄድ ውጤታማ ስራ እየተሰራ ነው ።
የከተማ አስተዳደሩና ነዋሪው ህዝብ አንዳንዶች የሚፈጽሙትን የተቋሙንና የሰራዊቱን ስም የሚያጠለሹ ስህተቶችን እያረማችሁ፤ ጥሩ የሚሰሩትን እያበረታታችሁ ለምትሰሩት መልካም ስራዎች በርቱ እያለ ይደግፋችኋል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
27/05/2026
ተዘጋጅተዋል?
👇👇👇👇👇👇👇
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
https://linktr.ee/AddisMediaNetwork
27/05/2026
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 24ኛ የሀገር ውስጥ መዳረሻ የሆነውን እና አዲሱን የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያን በይፋ መርቀናል። እንደ ቦይንግ 737 ማክስ ያሉ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን የማስተናገድ አቅም ያለው ይህ ዘመናዊ አውሮፕላን ማረፊያ፤ የአካባቢውን እንዲሁም ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ልውውጥን እና ቱሪዝምን የማሳደግ ርዕይን ሰንቆ በሳምንት ሦስት በረራዎችን ያስተናግዳል። የምንገነባው እያንዳንዱ አዲስ የአውሮፕላን ማረፊያ ርቀትን በማጥበብ ትስስር ይፈጥራል፣ የክልሎችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ያነቃቃል፣ እንዲሁም ሕዝባችንን ይበልጥ ያቀራርባል።
የአፍሪካ ኩራት የሆነውና 80ኛ ዓመቱን የያዘው አየር መንገዳችን በእርግጥም`የአፍሪካ አዲሱ መንፈስ” (The New Spirit of Africa!”) ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
26/05/2026
የኢድ አል አድሀ (ዐረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ በነገው ዕለት ለተሽከሪካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ
**********************
1447ኛው የኢድ አል አድሀ (ዐረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በዚህ መሰረት፦
👉ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ቅ/ዑራኤል አደባባይ
👉ከቦሌ በአትላስ መብራት ወደ ቅ/ዑራኤል አደባባይ አትላስ እና ፒኮኪ መብራት
👉በቦሌ መንገድ ወደ መስቀል አደባባ ኦሎምፒያ አደባባይ
👉ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ መብራት አጎና ሲኒማ መስቀለኛ
👉ከቡልጋሪያ መብራት ወደ ገነት ሆቴል ሜክሲኮ አደባባይ ቡልጋሪያ መብራት ላይ
👉ከልደታ ፀጠል ወደ ሜክሲኮ አደባባይ AU ሚካኤል መታጠፊያ
👉ከጦር ኃይሎች ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ከፍተኛ ፍ/ቤት
👉ከአብነት አካባቢ ወደ ጨፌ ሜዳ መብራት ፈረሰኛ መብራት
👉ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር መውረጃ ሞላ ማሩ መታጠፊያ
👉ከመርካቶ አካባቢ ወደ ጥቁር አንበሳ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ
👉ከፒያሳ ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ባንኮድሮማ መብራት
👉ከሲግናል ወደ ካዛንቺስ ሴቶች አደባባይ ላይ የሚሄዱ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።
ከበዓሉ ዋዜማ ምሽት ጀምሮ ከላይ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረጅም ሠዓት ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
አሽከርካሪዎች ከፖሊስ የሚሰጠውን መረጃ በመገንዘብ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።
26/05/2026
በአዲስ አበባ ከተማ የጤና አገልግሎት ላይ የተጨመረ ትልቅ እመርታ!
የላፍቶ ሆስፒታል ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ዘርፍ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ሆስፒታሉ አዲስ አበባን የህክምና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተቀመጠውን ሀገራዊ ግብ ከመደገፉም በላይ ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ይኖረዋል።
የተቋሙ አሁናዊ አቅም እና ርዕይ:-
በ5.4 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ግዙፉ ሆስፒታል 17 ዘመናዊ ህንጻዎችንና 500 አልጋዎችን ይዟል። ተቋሙ የተገነባው የኢትዮጵያን የህክምና አቅም ለማጠናከር፣ የላቁ የህክምና አገልግሎቶች ተደራሽነትን ለማስፋት እና የልዩ ህክምና መዳረሻ እንድትሆን የተጀመረውን ጥረት ለመደገፍ ነው።
የላቀ የህክምና ቴክኖሎጂ:-
ሆስፒታሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ የዲጂታል የቅድመ ካንሰር እና ድህረ ካንሰር የምርመራ ማሽን ጨምሮ የሚከተሉትን ዘመናዊ
ህክምና ቴክኖሎጂዎች አካቷል፦
• ባለ 3-ቴስላ ኤም.አር.አይ (3-Tesla MRI) ማሽን
• ባለ 640-ስላይስ ሲቲ ስካን (640-slice CT scan)
• በድምጽ የሚታዘዝ የካቴተራይዜሽን ላብራቶሪ (Cath Lab)
• የ3ዲ (3D) ማሞግራፊ መሳሪያ
• የሮቦቲክስ ላብራቶሪ (TLA) መሳሪያ፤
እነዚህ ቴክኖሎጂዎች በሀገር ውስጥ ውስብስብ የሆኑ የጤና እክሎችን የመመርመር እና የማከም አቅምን በእጅጉ ያሻሽላሉ ተብሎ ይጠበቃል።
A MAJOR STEP FORWARD FOR HEALTHCARE SERVICES IN ADDIS ABABA
The completion of Lafto Hospital marks an important milestone in Ethiopia’s healthcare sector. The hospital is expected to support the country’s broader goal of positioning Addis Ababa as a center for medical tourism while helping reduce the foreign currency spent on medical treatment abroad.
Facility Scale and Vision:-
Built on 5.4 hectares of land, the hospital consists of 17 modern buildings and 500 beds. The facility was developed to strengthen Ethiopia’s healthcare capacity, expand access to advanced medical services, and support the country’s ambition to become a destination for specialized healthcare in East Africa.
Advanced Medical Technology:-
The hospital includes an AI-assisted digital PET scan system, alongside a range of advanced medical technologies, including:
- A 3-Tesla MRI system
- A 640-slice CT scan
- A voice-controlled Cath Lab
- 3D Mammography equipment
- Robotics Laboratory (TLA) equipment
These technologies are expected to improve the diagnosis and treatment of complex medical conditions within the country.
26/05/2026
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛ የኢድ አል-ዓደሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ ኢድ ሙባረክ!
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ፤ ኢድ ሙባረክ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን አና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
26/05/2026
ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
55ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 55ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው በሁለት የፋይናንስ ድጋፍና ብድር ስምምነቶች ላይ ነው፡፡ የመጀመሪያው ለአርብቶ አደር ምግብና የኑሮ ዘይቤ ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ከአፍሪካ ልማት ባንክ የአርባ ስድስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ (46,300,000) የአሜሪካን ዶላር ብድር ስምምነት ነው፡፡ ሁለተኛው ለስድስተኛ ምዕራፍ ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ከዓለም ዓቀፍ የልማት ማህበር የአንድ መቶ አርባ ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሺ (146,100,000) ኤስ ዲ አር ብድር ስምምነት ነው፡፡ ምክር ቤቱ ሁለቱም የብድር ስምምነቶች ከአገራችን የብድር አስተዳደር ፖሊሲ ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን በማረጋገጥ የብድር ስምምነት ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆቹ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ለማሻሻል በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 ወጥቶ ሲሰራበት የቆየ ቢሆንም ባለፉት አመታት በሀገራችን በርካታ የኢኮኖሚ ለውጦች የተደረጉ በመሆኑ የታክስ አስተዳደር ሥርዓቱን ከዘመናዊ ዓለም አቀፍ ልምዶች ጋር ለማጣጣም፤ የታክስ አለመግባባቶችን በፍትሐዊነት፣ በሰላማዊ መንገድና በቅልጥፍና ለመፍታትና የተጠያቂነትና ግልጸኝነት አሰራር ለማስፈንና የታክስ ሕጎችን በተጠናከረ መልኩ ለማስፈጸም እንዲያስችል ተደርጎ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ሀዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
3. ከዚያም ምክር ቤቱ የተወያየው የግብርና ቢዝነስ ኩባንያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የግብርና ዘርፍን ከተለምዶአዊ አሰራር ወደ ቢዝነስ መር ሥርዓት ለማሸጋር፤ አነስተኛ አምራቾችን የገበያ የመደራደር አቅም ለማሳደግ፣ የእሴት ጭማሪና የኢንዱስትሪ ግብዓት ትስስርን ለመፍጠር፤ የተሻለ አቅም ያላቸው ወደ መካከለኛ አልሚነት የሚደርጉትን ሽግግር በሕግ ለመደገፍ፤ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የሥራ ዕድል ለመፍጠር የህግ ማዕቀፍ ሆኖ እንዲያገለግል ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ሀዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
4. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት የኢትዮጵያ የካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጅ ነው፡፡ የኢትዮጵያን የካርበን ገበያ ስትራቴጂ ወደ ተግባር ለመለወጥ፣ ለአረንጓዴ ኢንቨስትመንት እና ለቴክኖሎጂ ሽግግር ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር፣ የካርበን ግብይት አሰራሮችንና ሂደቶችን በግልፅ ለመደንገግ፣ በካርቦን ፕሮጀክት አካባቢ በሚኖረው ማህበረሰብና አካባቢው ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አሰራሮችን ለመዘርጋት፤ ከካርበን ንግድ የሚገኘው ገቢ በመንግስት፣ በአልሚዎች፣ በአካባቢው ማህበረሰብ እና በባለድርሻ አካላት መካከል በፍትሃዊነት የሚከፋፈልበትን አሰራር ለመዘርጋት እና ኢትዮጵያ የፈረመቻቸውን ዓለም አቀፍ ውሎችና የገባቻቸውን የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀት ቅነሳ ቃል ኪዳኖች ከሌሎች ጋር በትብብር እንድትወጣ የህግ ማዕቀፍ ሆኖ እንዲያገለግል ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ሀዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
5. የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ረቂቅ አዋጅ ምክር ቤቱ የተወያየበት ሌላው አጀንዳ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሞያዊ ነፃነትን ለማረጋገጥ፣ የተቆጣጣሪ እና የፈጻሚ አካላትን የቁጥጥር እና የአሠራር ተግባራትን ሚና በግልፅ ለመለየት፣ በሁሉም ኦፊሽያል ስታቲስቲክስ አመንጪዎች መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር፣ የመረጃ ምስጢራዊነትን ለመጠበቅ፣ የስታቲስቲክስ ውጤቶችን ጥራት ለማሻሻል፣ ተደራሽነታቸውን ለማረጋገጥ እና ሀገራዊ አሠራሮችን ከዓለም አቀፍ የስታቲስቲክስ መርሆዎች እና ደረጃዎች ጋር ለማጣጣም እንዲያስችል ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ሀዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
6.አስከትሎም ምክር ቤቱ የተወያየው የኢነርጂ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ ፖሊሲው ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ ከአሥር አመቱ የልማት ዕቅድ፣ ከአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ስትራቴጂ፣ ከምዕተ አመቱ የልማት ግቦች እና ከሌሎች ፖሊሲዎች ጋር ተጣጥሞ የአገራችንን የኢነርጂ ሀብት በአነስተኛ ዋጋ በማልማት ዘላቂ፣ አስተማማኝ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ በዋጋ ተመጣጣኝና ተወዳዳሪ የኢነርጂ አቅርቦት እንዲኖርና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲያስችል ረቂቁ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል በምክር ቤቱ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
7. ከዚያም ምክር ቤቱ የተወያየው ብሄራዊ የሴቶች ማብቃት እና የስርዓተ ጾታ እኩልነት ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ ፖሊሲው ለስርአተ ጾታ መዛባት ስር ነቀል የሆኑ ጉዳዮች ላይ በቂ ትኩረት ለመስጠት፣ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን በአግባቡ ለመከላከል እና ጥበቃና ምላሽ ለመስጠት፣ ልዩ ትኩረት ለሚሹ ሴት አካል ጉዳተኞች እና ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች ምላሽ ለመስጠት እንዲያስችል ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ስርአተ-ጾታን መሰረት ካደረጉ አለም አቀፍና አህጉራዊ ስምምነቶች ጋር በማጣጣም ረቂቁ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል በምክር ቤቱ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
8. ቀጥሎም ምክር ቤቱ የተወያየው የኢንሹራንስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የኢንሹራንስ ገበያውን ተኣማኒነት የሚያጠናክር፣ ፍትሃዊ፣ ደህንነቱ ተረጋገጠ እና የተረጋጋ የኢንሹራንስ ገበያ እንዲኖር የሚያበረታታ፣ የመድን ገቢዎችን እና የመድን አገናኞችን ደንበኞች ጥቅም የሚያስጠብቅ፣ የኢንሹራንስ ገበያውን ለመቆጣጠርና ለመምራት የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ሆኖ እንዲያገለግል ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ሀዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
9. በማስከተል ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ የንግድ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የንግድ ስርአትን በአግባቡ ለመምራት፣ በተመረጡ የገበያ ክፍተት ባለባቸው ዘርፎች ክፍተቶችን ለመሙላት የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር፣ የሀገራችንን የወጪ ንግድ በግብርና ምርቶች ያለውን ጥገኝነት በማላቀቅ የወጪ ምርትና አገልግሎት ብዝሃነትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ፣ የምርት ደህንነት መስፈርቶችን ለማውጣት እና ፍትሃዊ የንግድ አሰራርን ለመዘርጋት፣ የአገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪነትን እንዲገነቡ፣ ምርታማነትን እንዲያሳድጉና የአካባቢ አቅምን እንዲያዳብሩ ድጋፎችን በመስጠት በዘርፉ ያሉ ተግዳሮችን ለመፍታት እንዲያስችል ረቂቅ ፖሊሲው ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል በምክር ቤቱ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
10. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣንን አደረጃጀት፤ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የቀረበ ማሻሻያ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ ባለስልጣኑ በህግ የተሰጠውን ተግባርና ሃላፊነት በብቃት ለመወጣት እንዲያስችለው ማሻሻያ ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል ደንቡ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
11. ከዚያም ምክር ቤቱ የተወያየው በህግ የሰውነት መብት የተሰጣቸው አካላት ተጠቃሚ የሚሆኑ ባለቤቶችን መረጃ ግልጸኝነት ለመደንገግ የቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ በአግባቡ ለማስፈጸም እንዲያስችል ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል ደንቡ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
12. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየው የምግብ ስርዓት እና ስርዓተ ምግብ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ከሥርዓተ ምግብ መዛባት ጋር የተያያዙ በሽታዎች በጤና፣ በትምህርት፣ በአካባቢያዊ፣ በምርታማነትና በማህበራዊ መስተጋብር እና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድሩትን አሉታዊ ተጽእኖ ለመቀነስና ለማጥፋት የሚያስችሉ ተግባራትን ለማከናወን፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ይህን ስራ የሚያስተባብር አደረጃጀት ለመፍጠር፤ ሀብት በዘላቂነት ለመመደብና የማህበረሰቡን ተሳትፎ ለማሳደግ፣ ሀገራችን የገባቻቸውን አለም አቀፍ ስምምነቶችና የተቀመጡ የምግብ ስርዓትና ሥርዓተ ምግብ ግቦችን ለማሳካት የህግ ማዕቀፍ ሆኖ እንዲያገለግል ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ሀዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
13. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው ለራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት የሚሰጥ የበጀት ድጋፍ አፈጻጸምን ለመደንገግ በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ ለራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት የሚሰጥ የበጀት ድጋፍ በታወቀ ጥቅል የበጀት ድጋፍ ስርዓት ላይ የተመሰረተ ለማድረግ፣ የፋይናንስ ተጠያቂነት፣ ፍትሃዊነት እና ውጤታማነትን ለማረጋገጥ፣ የራስን ወጪ በራስ የመሸፈን ድርሻን ከጊዜ ወደ ጊዜ ለማሳደግ፣ በተቋማቱ መካከል ተመጣጣኝ የመማር-ማስተማር፣ የአገልግሎት ጥራት እና ፍትሃዊነትን ባረጋገጠ ሁኔታ ሀላፊነት የተሞላበት ስራዎችን እንዲያከናውኑ ለማስቻል ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡
//