Paartii Badhaadhinaa Damee Kutaa Magaalaa Addis Katamaa Annaa5

Paartii Badhaadhinaa Damee Kutaa Magaalaa Addis Katamaa Annaa5

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Paartii Badhaadhinaa Damee Kutaa Magaalaa Addis Katamaa Annaa5, Government Organization, Addis Katema, Addis Ababa.

06/05/2024

እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሠላምና በጤና አደረሳችሁ! አደረሰን!

የትንሳኤ በዓል እየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች መከራ የተቀበለበት በመጨረሻም ሞትን ድል አድርጎ በመነሳት ሰላምን ያበሰረበት በመሆኑ በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በሃይማኖታዊ ስነስርዓቶች ታጅቦ በታላቅ ድምቀት የሚከበር በዓል ነው፡፡

የመከራዉ ግዝፈት ትንሳኤውን እንዳላስቀረዉ ሁሉ የሀገራችንን ብልፅግናም ወቅታዊ ችግሮች እንደማያስቀሩት እዉን እንደሆነ ግልፅ ነዉና እንደተለመደው በዓሉን በኢትዮጵያዊ ጨዋነታችን በወንድማማችነትና እህትማማችነት እሳቤ ተደጋግፈን፣ የተቸገሩ ወገኖችን በመጠየቅ ያለንን እየተጋራን ማሳለፍ ይኖርብናል፡፡

በዓሉ የደስታ፣ የፍሰሃና የፍቅር እንዲሆንልን እመኛለሁ፤ መልካም የትንሳኤ በዓል!!

አቶ ሙስጠፋ ትኩ
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

Photos from አዲስ ከተማ ወረዳ 5 ብልፅግና ፓርቲ's post 03/03/2024
10/01/2024

ብልጽግና ፓርቲ ሀገር በቀል፣ ገቢራዊ ፣ አካታች፣ ተደራሽ አና በኢትዮጵያ ተጨባጭ አቅሞች ላይ በተመሠረተ የፖለቲካ እሳቤ የሚመራ ፓርቲ ነዉ።

ብልፅግና የኢትዮጵያን አቅሞች በመደመር እሳቤ በማሰባሰብ ፣ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል፣ ሰህተቶችን በማረም፣ የተዛቡ ትርክቶችን በማረቅ በጋራ የመልማትን፣ በትብብር የማደግን አቅጣጫ ይከተላል።

ይህ አዲስ ፖለቲካዊ እይታ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ ማሸጋገሪያ ሀዲድ ፤ የተጀመረዉን ለዉጥ ለማፅናትም አቅም ነዉ።

10/01/2024

የአድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም የመደመር ትውልድ የታሪክ አሻራ!

ብልጽግና ታሪክ ከመዘከር ባሻገር ዘመኑን የዋጀ አዳዲስና ለትውልድ ምንዳ የሚሆኑ ታሪኮችንም እየሰራ ይገኛል።

ኢትዮጵያዊያን በህብር ደመቀን በአንድነታችን ፀንተን በአብሮነት ያስመዘገብናቸውና በዓለም አደባባይ በከፍታ ያቆሙን አኩሪ ታሪኮች አሉን። በሀገራዊ አርበኝነት የቆሙ አባት/እናቶቻችን አለት ፈልፍለውና ድንጋይ ጠርበው ታሪካዊ ቅርሶችን፣ ለዳር ድንበር በጋራ በተከፈለ የደምና አጥንት መሰዋትነት ድልና ነፃነትን አውረሰውናል።

በጋራ ከምንኮራባቸውና ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ ጫፍ ተመው በጀግንነት ካስመዘገቧቸው ታሪካዊ ገድሎች አንዱና ዋናው የአደዋ ድል ነው።

አድዋ የመላው ጥቁር ህዝቦች የከፍታ ምልክት ሆኖ የሚዘከር የፅናትና አይበገሬነት ተምሳሌት በመሆን ለብዙዎች የነፃነት መነሻ ድል ነው።

ኢትዮጵያዊያን በህብር ደምቀው በፍፁም ወንድማማችነትና እህትማማችነት የጀግንነት ወኔ ሰንቀው በአንድነታቸው በመጽናት ያስመዘገቡት ታላቅ የድል አሻራ ነው አድዋ!

የአድዋ ድል የሀገር ልዑዓላዊነት እና ነፃነት የማስከበር ተጋድሎ ከኢትዮጵያ ምድር ተሻግሮ፤ ለጥቁር ህዝቦች ነፃነት መከበር ለፈጠረው ንቅናቄ የድል አድራጊነት ውሃልክ ያሰመረ ደማቅ የታሪክ ምዕራፍ ጭምር ነው።

ብልጽግና ፓርቲ በመርህም ሆነ በተግባር ኢትዮጵያ የነበራትን አኩሪ ታሪኮች ጠብቃ አዳዲስና ደማቅ አሻራዎችን በማሳረፍ የሚታይና የሚጨበጥ በትውልድ የሚዘከር ታሪኮችን እየሰራ ይገኛል።

ከዚህ አንፃር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተገነቡ ካሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው የአድዋ 00 ኪ.ሜ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

ብልጽግና የኢትዮጵያዊያንን ህብረ ብሔራዊ አንድነት በማጽናት ነባር ታሪካዊ ዳራዎችን መሰረት አድርጎ የአደዋ 00 ኪ.ሜ ጨምሮ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ወዘተ... የመሳሰሉትን ታላላቅ የታሪክ አሻራ እያሳረፋ ይገኛል።

Photos from Addis Ababa Prosperity Party - ብልፅግና's post 10/01/2024
03/01/2024

ታሪክ ከመዘከር ባለፈ ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ ሆኖ የተገነባ በሁሉም መመዘኛ ምልዑነትን የተላበሰ የኛ ትውልድ አሻራ!

ኢትዮጵያዊያን እንደ ድር ተጋምደን ያስመዘገብናቸው በዓለም አደባባይ ከፍ ያደረጉን አንፀባራቂ ታሪኮች አሉን።

ለአፍሪካውያን እንዲሁም ለመላው ጥቁር ህዝቦች የነፃነት፣ የእኩልነትና የአትንኩኝ ባይነት አብነት የሆነው የአድዋ ድል የብሔር፣ የሀይማኖት እና መሰል ልዩነቶች ሳይገድቧቸው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን አሻራቸውን ያሳረፉበት የወል ታሪካችን ነው።

አባት እናቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው በጋራ ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ ታሪክ ሰርተዋል፤ የጋራ ታሪካችንን በአብሮነት ለመዘከር ግን በረባ ባልረባው ስንነታረክ ቆይተናል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቧራ ተነስንሶበት የነበረው የአድዋ ድል ታሪክ ተገልጦ ወርቅነቱ እንዲታይ ለማድረግና በዓመት አንድ ጊዜ ከመዘከር ባለፈ ዓመቱን ሙሉ እንዲወሳ የሚያደርገውን ግዙፉን የአድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ላለፉት የለውጥ ዓመታት ሲገነባ ቆይቷል።

ሙዚየሙ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የአድዋን ድል ታሪክ በአብሮነት እንዲዘክር የሚያስችል ቦታ ላይ ያረፈ ከመሆኑም በላይ ታሪኩን በተሟላ መልኩ እንዲዘክር ተደርጎ የተሰራ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቀጥሎ ግዙፉ አገራዊ ፕሮጀክት ነው።

የአድዋን የድል ታሪክ ከአርበኞችና ከመሪዎች ነጥሎ ማየት ስለማይቻል በአድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም በተገቢው መልኩ የሚዘከሩበት ዕድል ተፈጥሯል።

የአድዋን ድል ስናነሳ የፈረሶቻችን ውለታ ባናወሳ የአድዋ ተራሮችም ጭምር ይታዘቡናል። በመሆኑም በሙዚየሙ የፈረሶቻችንን አሻራ የሚዘክሩ የጥበብ ስራዎችም ተካተዋል።

የአርበኞቻችንን ድል ከፍ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል ዘመናዊ ጦር ታጥቆ የመጣውን ወራሪ ሀይል ጦር፣ ጋሻ፣ እና ጎራዴን በመሳሰሉ መሳሪያዎች በልበ ሙሉነት ገጥመው ድል ማድረጋቸው ነው።

በአድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየምም የመሰባሰቢያ አዋጁ የተጎሰመበትን ታሪካዊ ነጋሪት ጨምሮ ጋሻ እና ጦራችን በሚገባ እንዲዘከሩ ሆኗል።

የአርበኞቻችንን መውጣትና መውረድ ለማሳየት በአድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች አምሳል የተገነባው የአድዋ ሙዜም ባረፉበት የጥበብ አሻራዎች ታሪክ ከመዘከር ባለፈ ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ ሆኖ የተገነባ በሁሉም መመዘኛ ምልዑነትን የተላበሰ የኛ ትውልድ አሻራ ነው!

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት

28/12/2023

ብሔራዊ ገዥ ትርክትን በማስረጽ ህብረ- ብሔራዊ አንድነት ማጽናት !

የብልፅግና ፓርቲ የነደፋቸው የፖለቲካ ተልኮና ዓላማዎች ይሳኩ ዘንድ በትኩረት ከሚሰራባቸው ነገሮች አንዱና ዋናው የሀገራዊ መግባባት ጉዳይ ነው። ፓርቲው ህብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን ለማጠናከር፣ ለዴሞክራሲ ስርዓት ማበብና አጠቃላይ ሀገራዊ የተረጋጋ የኢኮኖሚ ዕድገት ይመጣ ዘንድ ከተቃርኖ ትርክት በመላቀቅ ገዥ ብሔራዊ ትርክትን በማጽናት ሀገራዊ መግባባትን ለማዳበር በጽኑ እየሰራ ይገኛል።

የብልፅግና ፓርቲ በሀገሪቱ ለረጅም ዓመታት የገነገነ በልሂቃን መካከል የሚታይ ዋልታ-ረገጥ የጠቅላይነትና ተገጣይነት ጤናማ ያልሆነ ትርክት በህዝቦች መካከል አለመተማመንን እየፈጠረ መሆኑን ይገነዘባል። በብልጽግና ፓርቲ እምነት የሃሳብ ልዩነቶችም ሆኑ የጥቅምና የፍላጎት አለመጣጣሞች ተፈጥሯዊ በመሆናቸው ልዩነቶችን ዴሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ ማስተናገድ ጠቃሚና ገንቢ ናቸው። ፓርቲያችን ሀገራዊ መግባባትን ለማዳበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ ቅድሚያ ሰጥቶ ከሚሰራቸው ተግባራት አንዱ በሀገራችን የቂምና የጥላቻ ታሪክ ምዕራፍ እንዲዘጋና በብሔራዊ አርበኝነት የተገነባ ብዝሃነትን ያማከለ አካታች የፖለቲካ ስርዓት ይኖር ዘንድ ነው ።

የብልፅግና ፓርቲ በሀገራችን የምንፈጥረው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን የጠበቀና የሁሉም ማንነቶች ነፀብራቅ የሆነ፤ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ባህልና ማንነት ያከበረ መሆን እንዳለበት በጽኑ ያምናል። ለዚህም ብሔራዊ አርበኝነትን የሚያፀና አሰባሳቢ ገዥ ትርክት ወሳኝ ነው። ብሔራዊነት ስንፈልግ የምንይዘው ሳይመቸን የምንጥለው ሳይሆን ኢትዮጵያዊያን ከተቃርኖ የጠቅላይነትና የተገንጣይነት ነጠላ ትርክቶች ተላቀው ጠቃሚ የሆኑ የስልጣኔና የአብሮነት ዕሴቶቻቸውን በማዳበር የወል እውነትን በማጽናት በህብረ -ብሔራዊ አንድነት ፀንታ የምትበለጽግ የጋራ ሀገር ኢትዮጵያን ዕውን ማድረግ ይገባል።

ብልጽግና ፓርቲ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከድህነት ጋር የምታደርገዉን ትንቅንቅ ለመጨረሻ ጊዜ ለመቋጨት ኢትዮጵያዊያን ተፈጥሯዊ ልዩነቶችን እንደፀጋ በመውሰድ ለጋራ ሀገራቸው በጋራ በአብሮነት መቆም ሲችሉ ነው ብሎ ያምናል። ኢትዮጵያዊያን በጋራ ሲቆሙ አስደማሚና ለዓለም ሁሉ ትግርት የሆኑ ታሪኮች ማስመዝገብ እንደሚችሉ አስመስክረዋል። ጀግኖች አባት/እናቶቻችን በአድዋ የጥቁሮች ሁሉ ቀዳሚ የሆነ ድልን አስመዝግበው፣ አክሱም፣ ላሊበላ፣ ሀረር ግንብ፣ አባጅፋርና የጥያ ትክል ድንጋይን የመሳሰሉ ታሪካዊ አሻራዎችን በማኖር ኩራትና ምንዳ አሳርፈዋል።

ኢትዮጵያዊያን በዚህ ዘመንም የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ኮይሻ፣ ጎርጎራና ሀላላ ኬላን የመሳሰሉ ሀገራዊ ገፅታን የሚቀይሩ ፕሮጀክቶችንና የዓለም ሪከርድን የሰበርንበት አረንጓዴ አሻራን ማሳረፍና በአንድ ስንቆም መበልጸግ እንደምንችል አስመስክረናል። ለዚህም ነው ብልጽግና ፓርቲ ኢትዮጵያዊያን በህብር ሲቆሙ አርበኞች ናቸዉ ብሎ በጽኑ የሚያምነው! ሁሌም በድል ለመራመድና ሀገራዊ የብልጽግናን ጉዞ ለማረጋገጥ በህብር ሀገራዊ ገዥ ትርክት የሆነውን ብሔራዊ አርበኝነት ማጽናት ይገባል። ብልጽግና ዜጎች ተደምረው የጋራ የምትሆን የበለፀገች ኢትዮጵያን መገንባት የሚችሉበት እርሾ አለ ብሎ በማመኑ የነበሩብንን ያለመግባባት ዕዳዎች በውይይትና እርቅ በመፍታት ነባር ምንዳዎቻችንን በማስቀጠል በሀገራዊ ገዥ ትርኮታችችን በመገባባት ከዕዳ ወደ ተትረፈረፈ ምንዳ መሻገር አለብን ብሎ ያምናል።

ፓርቲያችን ብልፅግና ብሔራዊነት ገዢ ትርክት እንዲሆን የፈለገበት ዋና ምክንያት አብሮነትን ክዶ ልዩነት ላይ ብቻ የሚያተኩር ወይም ብዝኃነትን ደፍጥጦ ፍፁማዊ አንድነት የሚፈልግ ትርክት ለምናስበው ሀገራዊ ብልፅግና አንድነት አይጠቅመንም በሚል አቋም ነው። በአጠቃላይ ብሔራዊነት አማካይ የሆነ ኅብረ ብሔራዊነትን የሚያፀና አካታች ፍትሀዊና እኩልነትን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚያረጋግጥ አሰባሳቢ ትርክት ከመሆኑ አንጻር ሁሉን አቀፍ አካታች ብሔራዊ አርበኝነትን መፍጠሪያ መንገድ ነው።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Katema
Addis Ababa
POW5