03/01/2023
በጎነት ለህልናችን እረፍት፣ለመንፈሳችን ደግሞ እርካታ ይሰጣል‼
የሚንሰጠው ከተረፈልን ሳይሆን ካለን ነው የሚናካፍልው።
በአራዳ ክፍለ ከተማ የገና በዓል ማዕድ ለማጋራት የተለያዮ ማህበራት፣መንግስታዊና መንግሰታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች፣ ነጋዴዎች፣ሴቶች ወጣቶችና ሌሎች በቅንጅት ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው።
26/12/2022
በጎነት ለህልና እረፍት‼
በበጎ ፈቃድ ስራ እንትሳተፉ እናበረታታለን።
ለመሳተፍ የሚትፈልጉ አራት ኪሎ በሚገኘው የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንጻ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ በጽ/ቤት ተገኝታችሁ አስፈላጊ ድጋፍ ማግኘት ትችላላችሁ።
26/12/2022
ይህ የአራዳ ክፍለ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት የፌስቡክ አድራሻ ነው።
24/12/2022
" በበጎ ፈቃደኞች የነቃ ተሳትፎ በክረምት ወቅት የተተከሉ ችግኞች እንክብካቤ አጠናክረን እንቀጥላለን ‼"
አቶ አለማየሁ አራጋው
የአራዳ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ
የአራዳ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የበጋ በጎ ፈቃድ መረሃ ግብር አካል የሆነውን በወንዝ ዳርቻ የተተከሉ የፍራፍሬ ችግኞችን የማንከባከብ ስራ በባሻ ወልዴ ወንዝ ዳርቻ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ።
"በጎ ፈቃደኝነት ለማህበራዊ መስተጋብር" በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ የሚገነው የበጋ በጎ ፈቃድ በክረምት ወቅት የተተከሉ ችግኞች እንድጸድቁ ለማድረግ የእንክብካቤ ስራው በበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች አማካይኝነት እየተከናወነ እንደሚገኝ የገለጹት የአራዳ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አለማየሁ አራጋው በንቅናቄ ችግኞችን እንደተከልን ሁሉ በንቅናቄ እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ በይፋ በተጀመረው የችግኝ እንክብካቤ መረሃ ግብር ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ እየተከናወነ እንደሚገኝ ያስታወሱት ሀላፊው በጎ ፈቃደኝነት የወጣቱ ባህል እንድሆን ለማድረግ የሚታዩ ሰራዎች እየተሰሩ ይገኛልም ብሏል።
ከሁሉም ወረዳ የተወጣጡ የአረንጓዴ ልማት ችግኝ እንክካቤ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን መረሃ ግብሩ ቀጣይነት እንደሚኖረው ተገልጿል ሲል የኢዜአ ዘግቧል።
24/12/2022
በህብረተሰባችን ተሳትፎ የ90 ቀን እቅዳችን እናሳካለን !!
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳዳር በ90 ቀን እቅድ ተይዞለት ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የወረዳው አስተዳደር ግቢ ሳቤዝና ቴራዞ ንጣፍ ፕሮጀክት እንዲሁም የጥበቃ ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሔደ ።
ታህሳስ 13/2015 ዓ.ም
ይህ ፕሮጀክት ግቢውን በተለያዩ አትክልቶች የማስዋብ ስራን የሚጨምር ሲሆን በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል ።
የእለቱ የክብር እንግዳ የአራዳ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶአለማየሁ አራጋው እንደገለፁት ህብረተሰቡን በማሳተፍ የምንሰራቸው ስራወች የህዝቡን ጥያቄ የሚመልሱ ስለሆነ እንደነዚህ አይነት ፕሮጀክቶችን ህብረተሰቡ በገንዘብ በእውቀትና በጊዜም ጭምር መደገፍ እንዳለበት ተናግረዋል ።
የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አበበ ሃይሉ በበኩላቸው በ90 ቀን የምንሰራቸው የልማት ስራወች በተደጋጋሚ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የነበሩና ዛሬ የተጀመረው የግቢ የቴራዞ ንጣፍ በተለይ አገልግሎት ፈልገው ለሚመጡ ባለጉዳዪች ምቹ ሁኔታ ያልነበረውና አሁን ግን ይህንን ችግር አይተን ህዝባችን አሳትፈን ባጭር ጊዜ አጠናቀን ለአገልግሎት ክፍት አናደርጋለን ብለዋል ።