በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶአደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን

በአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር አርሶአደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን

Share

በመዲናዋ የከተማ ግብርናን ማስፋፋት እና ማዘመን እንዲሁም በልማት ምክንያት ከይዞታቸው የለቀቁ አርሶ አደሮችን መልሶ ማቋቋም ዋነኛ ተግባራችን ነው፡፡

02/06/2026
Photos from በአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር አርሶአደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን's post 02/06/2026

17,627 አርሶ አደሮች በግል ይዞታቸው ላይ እንዲያለሙ ተደርጓል፡፡
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ
17,627 አርሶ አደሮች በግል ይዞታቸው ላይ እንዲያለሙ የተደረገ ሲሆን ካላቸው ይዞታ ላይ አነስተኛ ቦታ ያላቸው 80 በመቶ እንዲያለሙ እንዲሁም ሰፊ ይዞታ ካላቸው 20 በመቶ ይዞታቸውን ለከተማ ግብርና ስራ እንዲያውሉ በማድረግ አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን ሰፊ ሥራ ተሰርቷል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ በከተማ ግብርና ተሳታፊ ከሆነው 1.2 ሚሊዮን ተጠቃሚ ውስጥ ከተገኘው 478,567.18 ቶን ምርት አርሶ አደሩ በተሰማራበት ስራ ከራስ ፍጆታ አልፎ የገበያ ማረጋጋት ስራ ላይ ከፍተኛ ድርሻ አበርከተዋል፡፡
በሌላ በኩል በግል ይዞታቸው ላይ ሰፊ የልማት ሥራ ማከናወን የሚችሉ 168 አርሶ አደሮች ወደ ኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሸጋገሩ ምቹ ሁኔታዎች መፍጠር ተችሏል፡፡

Photos from በአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር አርሶአደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን's post 02/06/2026

300 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች በትምህርት ዘርፍ መንግስት ባመቻቸላቸው ዕድል በ6 ማኅበራት ተደራጅተው ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ

ባለፉት የለውጥ ዓመታት በልማት ምክንያት ከይዞታቸው የተነሱ አርሶ አደሮችን መልሶ በማቋቋም እና በቀጣይም የከተማው ልማት አካታችነቱን ጠብቆ አርሶ አደሩ አብሮ እንዲለማ በርካታ ሥራዎች ተሰርቷል፡፡

ከነዚህ የልማት ሥራዎች አንዱ በመሆነው የትምህርት ዘርፍ በአቃቂ ቃሊቲና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች 2 ትምህርት ቤቶችን በመገንባትና ግብዓት በማሟላት 300 አርሶ አደሮች በ6 ማኅበራት ተደራጅተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል፡፡

ለውጡ ያመጣላቸውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በቅርበት እየተከታተላቸው በዘርፉ አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ እጅግ ተመራጭ እና ወደ ኢንቨስትመንት ዘርፍ እየተሸጋገሩ ያሉ ውጤታማ ማህበራት መሆን ችለዋል፡፡

Photos from በአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር አርሶአደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን's post 02/06/2026

በ104 ማኅበር የተደራጁ 540 አርሶ አደሮች በእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ግ/ል/ኮ

አርሶ አደሮች ከከተማው ልማት ጋር አብረው እንዲለሙ ከማድረግ አንፃር ከለውጥ በኋላ በልማት ምክንያት ይዞታቸውን የለቀቁ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች በተለያዮ የሥራ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ ዘርፈ ብዙ መልሶ የማቋቋምና የማልማት ሥራ ተሰርጧል፡፡

ከነዚህ የልማት ሥራዎች መካከል አንዱ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በ14 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባው የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ሲሆን የወተት፣ የከብት ማደለቢያ፣ የዶሮ እርባታ፣ የመኖ ማቀነባበሪያና 32 ሱቆችን በማሟላት 104 ማኅበራትንና 540 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ Addis Ababa City Communication's post 02/06/2026
02/06/2026

ኢትዮዽያ አሸነፈች!!!

የሀገረ መንግስቱን ግንባታ ከዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አቅጣጫ ውጭ ባንዳና ባዳ ጥምረት ፈጥረው በአመፅና በኃይል ሀገራችንን ወደ ጥፋት መንገድ ለመክተት ያሴሩትን ደባ ሕዝቡ በዴሞክራሲያዊው ምርጫ እምቢተኝነቱንና ለሀገር ያለውን ፅኑ ፍቅር በተግባር በማሳየት አክሽፎታል።

በተለይ በአዲስ አባባ ረጃጅም ሰልፍ ቢፈጠርም ህዝቡ በእንቅልፍ እና በብርድ ሳይበገር ተራ እስኪደርሰው እስከ ለሊቱ 10:30 ሰአት ድረስ ተሰልፎ በሚገርም ጨዋነት፣ መሰጠት፣ ቁርጠኝነትና ፅናት መርጧል።

የሀገራችን ፖለትከኞችና ልሂቃን ይህንን ታላቅ ጽኑ ጨዋና ቆራጥ ሕዝብ የምንረዳውና የሚንመጥነው መሆን ይጠበቅብናል።

ፈጠሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

02/06/2026
Photos from Mayor Office of Addis Ababa's post 02/06/2026
Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Hayahulet
Addis Ababa