26/10/2021
ለትራፊክ ፖሊሶች እና የመንገድ ደህንነት ቁጥጥር አመራሮች የትራፊክ ማኔጅመንት ስልጠና ተሰጠ።
*********
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ኤንቲዪ (NTU) ከተባለው የዴንማርክ ድርጅት ጋር በመተባበር በአምስት የመንገድ ኮሪደሮች ላይ በፓይለት ደረጃ የቁጥጥር ስራንና ከአደጋ በኃላ አፋጣኝ የህክምና አገልግሎት በማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በተመረጡ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ቁጥጥር ተቋማት መሪዎችና ለትራፊክ ፖሊሶች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናዉንም የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ምክትል ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አሰፋ ሐዲስ ያስጀመሩት ሲሆን፣ በሀገራችን የትራፊክ ግጭት የበርካታ ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የአካል እና የንብረት ጉዳት እያደረሰ ይገኛል በማለት ይህ በቅንጅት የሚሰጥ ሰልጠና ችግሩን ለመቅረፍ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፅዋል ።
የኤንቲዪ(NTU) አማካሪ ድርጅት ቡድን መሪዉ ድርጅቱ በመንገድ ደህንነት እና በትራፊክ የሚደርሱ አደጋዎች እንዲቀንስ የሚሠራ መሆኑን ገልጸው አደጋው በዓለም አቀፍ ያለበትን ደረጃ ገልፀዋል።
የትራፊክ ማኔጅመንት ሥልጠናው ለሁለት ቀን የተሰጠ ሲሆን የብሔራዊ መንገድ ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዮናስ በለጠ በማጠናቀቂያ መርሀ ግብር በመገኘት ለተሳታፊዎች ሰርተፍኬት አበርክተዋል፡፡
26/10/2021
ደህንነቱ የተጠበቀ የከተማ መንገድ ዲዛይን ላይ ስልጠና ተሰጠ::
******
የኢፌዴሪ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በከተሞች አካባቢ የሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ እንዲሁም የከተማ መንገዶች ለሁሉም የመንገድ ተጠቃሚ ምቹ ሆነዉ እንዲሰሩ የሚያግዝ Global Street Design Guide የተባለ ማንዋል በሃገር አቀፍ ደረጃ በመቀበል በስራ ላይ እንዲዉል ተደርጓል፡፡
በዚህም መሰረት በከተማ መንገድ ስራ ላይ እና በማንዋሉ ላይ በ National Association of City Transport Official (NACTO) አለምአቀፍ ባለሙያዎች እና በሚኒስቴር መስሪያቤታችን ትብብር የአንድ ቀን ስልጠና በሃዋሳ ከተማ ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናዉ ላይ የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር የስራ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች፣ የደቡብ ብ/ብ/ህ/ብ/ክ/መ የስራ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች፣ የሲዳማ ብ/ክ/መ የስራ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች፣ የትራፊክ ፖሊሶች እና የትራስፖርት ቁጥጥር ባለሙያዎች እንዲሁም የሃዋሳ ዩንቨርስቲ መምህራን ተካፋይ ሆነዋል፡፡
ስልጠናዉ የከተሞች መንገዶች ከዲዛይን ጀምሮ የመንገድ ደህንነትን እና ሁሉንም የመንገድ ተጠቃሚዎች ከግምት በማስገባት ለእግረኞች፣ ብስክሌተኞች እና አካል ጉዳተኞች ምቹ ሆነዉ እንዲገነቡ ለማስቻል በትራንስፖርት ዘርፍ ላሉ ባለሙያዎች እና የስራ ሃላፊዎች በቂ ግንዛቤን እንዲይዙ ለማድረግ መሆኑ ተገጿል፡፡
11/10/2021
በጋምቤላ ብ/ክ/መ 13ኛው የብስክሌተኞችና እግረኞች ቀን በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ተከበረ።
***********
የጋምቤላ ብ/ክ/መ ትራንስፖርት ቢሮ ከኢፌዴሪ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር 13ኛው የብስክሌተኞችና እግረኞች ቀን በተለያዩ መርሀ ግብሮች አካሂዷል።
በእለቱ የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊና የዕለቱ የክብር እንግዳ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ መርሀ ግብሩን አስጀምረዋል፡፡
በመርሀግብሩ የብስክሌት እና የእግር ጉዞ ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣የሰርከስ ትርኢቶችና የተለያዩ አዝናኝ ፕሮግራሞችን በማካተት በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።
11/10/2021
በኦሮሚያ ብ/ክ/መ 13ኛው የብስክሌተኞችና እግረኞች ቀን በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ተከበረ።
***********
የኦሮሚያ ብ/ክ/መ ትራንስፖርት ባለስልጣን ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር 13ኛው የብስክሌተኞችና እግረኞች ቀን በተለያዩ መርሀ ግብሮች ተካሂዷል።
11/10/2021
የእግረኞች እና ብስክሌተኞች ቀን ለ13ኛ ጊዜ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከበረ።
*****************************
"ከጳጉሜን እስከ ጳጉሜን እንደርሳለን" በሚል መሪ ቃል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ የእግረኞች እና ብስክሌተኞች ቀን ለ13ኛ ጊዜ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከበረ።
ዕለቱን በማስመልከት በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ለተሳታፊዎች መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን የትራንስፖርት ዘርፍ ም/ኃላፊ የሆኑት አቶ ለሜሳ ዋውያ የእግረኞች እና ብስክሌተኞች ቀን ማክበር ያስፈለገበት ዋና ዓላማ በ2012 ዓ.ም የፀደቀውን የሞተር አልባ ትራንስፖርት ስትራቴጂ ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅና ለማበረታታት፣ የብስክሌት ተጠቃሚዎችን ደህንነት ለማሳደግ እና አዳዲስ ተጠቃሚነትን ለመሳብ፣ እግረኞችን ለማበረታታት እና በተሽከርካሪ መጨናነቅ የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስና ህብረተሰቡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ጤንነቱን እንዲጠብቅ ነው ብለዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ አቶ ለሜሳ ያነሱት የመንገድ ደህንነት ችግሮችን ለመፍታት በተከታታይ ሳይቆራረጥ በዘላቂነት የመንገድ ደህንነት ዘመቻ ስራዎች መሠራት አለባቸው ብለዋል። ለዚህም እንደ ማሳያ በ2014 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የደረሠው የትራፊክ አደጋ ሲታይ 36 ያህል ሲሆን ከዚህ ውስጥ 5 ሞት፣ 40 ከባድ የአካል ጉዳት፣ 37 ቀላል የአካል ጉዳትና 301,500 ብር የሚገመት የንብረት ውድመት መሆኑንና አምና ከደረሠው አደጋ ጋር ሲነፃፀር መቀነሱን መረጃዎች የሚጠቁሙ ቢሆንም አሁንም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በጋራ መረባረብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም ለፕሮግራሙ መሳካት የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትን ሁሉ ም/ኃላፊው ምስጋና በማቅረብ ህብረተሰቡ በእግር መጓዝ እና ብስክሌት መጋለብን እንደ ትራንስፖርት አገልግሎት አማራጭ በመጠቀም አካባቢውን ከአየር ንብረት ለውጥ እንዲጠብቅ እና ባሁኑ ወቅት የበርካታ ዜጎችን ህይወት ለህልፈት እየዳረገ ካለው የኮሮና ቫይረስ ሳንዘናጋ ራሳችንን እንዲጠብቅ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
11/10/2021
13ኛው ዙር #የብስክሌተኞችና #የእግረኞች ቀን መርሀግብር ድሬደዋ ላይ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል፡፡
************************
በመርሀ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ እንደተናገሩት ማህበረሰቡ አማራጭ የሞተር አልባ ተሽከርካሪዎችንና የእግር ጉዞ ባህልን እንዲያጎለብት ግንዛቤን በመፍጠር እየደረሰ ያለውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ታስቦ መርሀግብሩ በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ጋር በመተባበር ወር በገባ የመጨረሻው እሁድ በማካሄድ 13ኛ ዙር መድረሱን ገልጸዋል፡፡ በዚህም በማህበረሰቡ ላይ ግንዛቤን ለመፍጠር መቻሉን ነው ዋና ዳሬክተሯ የተናገሩት፡፡
አሁን ላይ ከትራፊክ አደጋው ባልተናነሰ ፈተና ከሆነው የኮሮና ወረርሽኝ በተለይ ትራንስፖርትን በየትኘውም አጋጣሚ ስንጠቀም የአፍና አፍኝጫ መሸፈናን ባግባቡ በመጠቀም እና አስፈላጊውን የጥንቃቄ መርህ በመከተል ራሳችንን እንጠብቅ ሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ አያይዘውም አሁን ላይ በተለይ ከትራፊክ አደጋ መጨመር ጋር ተያይዞ እንደሚኒስቴር መስሪያቤትና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከሚሰረራው የማስገንዘብ ስራ በተጓዳኝ የማህበረሰቡና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ባዲሱ አመት ከምንጊዜውም በላይ እንዲጨምር ጥሪ ያቀረቡ ሰሆን በተለይ አሽከርካሪዎች ከፍጥነት በላይ ባለማሽከርከር ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ጉልማ ታዬ በበኩላቸው በመድረኩ ላይ ማህበረሰቡ በትራፊክ አደጋ እንዳይጎዳ ህግን አክብሮ መንገዱን ባግባቡ እንዲጠቀምና የሞተር አልባ ተሽከርካሪንና የእግር ጉዞን ባህል እንዲያደርግ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በተያያዘም የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ፣ ሞተር አልባ ትራንስፖርትን ባህል እንዲሆን ለማድረግ አሁንም ጉዳዩ የሚመለከተን ተቋማት ብስክሌትንና እግረኛን ታሳቢ ያደረገ መንገድ ለማስፋፋት፣ ለሌላ አገልግሎት እየዋሉ ያሉ የእግረኛ መንገዶችንም ለእግር ጉዞ ብቻ እንዲውሉ በማድረግ ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ፣ አሽከርካሪዎችም ለህግና ደንብ ተገዢ ሆነን ለእግረኞች ቅድሚያ በመስጠት ያለውንም መንገድ ተሳስበን በመቻቻልና በትዕግስት መንፈሰ ልንጠቀምበት፣ ሚዲያዎችም ማህበረሰቡን በማስገንዘብና ተቋማቱም የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ጫና በመፍጠር ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡ በስተመጨረሻም የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በማድረግና በተመረጡ ጎዳናዎች ላይ የሳይክልና እግር ጉዞ በማካሄድ መርሀግብሩ ተጠናቋል፡፡
11/10/2021
በአዲስ አበባ 13ኛው የብስክሌተኞችና እግረኞች ቀን በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ተከበረ።
*****
መስከረም 30 ቀን 2014 በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ አበባ 13ኛው የብስክሌተኞችና እግረኞች ቀን በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ተከበረ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንፖርት ቢሮ ከኢፌዴሪ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር 13ኛው የብስክሌተኞች እና እግረኞች ቀን ከጀሞ እስከ ለቡ ባለው ጎዳና ንቅናቄ ተካሂዷል።
በእለቱ ንግግር ያደረጉት በቢሮው የብዙሃንና ሞተር አልባ ትራንስፖርት ቡድን መሪ (ተወካይ) ኢንጂነር ቤተልሔም ታደሰ እንደተናገሩት ባሳለፍነው 2013 በጀት ዓመት በድምቀት ሲከበር የነበረው የብስክሌተኞች እና እግረኞች ቀን ውጤት በሚያመጣ መልኩ መከናወን ተችሏል ብለዋል፡፡
በዚህ ረገድ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ብስክሌት መንዳት እና በእግር ጉዞ ማድረግን በነዋሪዎች ዘንድ ማሳደግ መቻሉንም ጠቅሰዋል፡፡
ቢሮው ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመስራት የተሻለ እንቅስቃሴ መደረጉን የገለፁት ኢ/ር ቤተልሔም ድጋፍ በማድረግ አብረው ለሰሩ ተቋማትና አካላትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ብስክትሌን መጠቀም እና በእግር መንቀሳቀስ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስም ሆነ ፍሰቱን ለማሳለጥ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው አማራጭ የትራንስፖርት ስልት መሆኑን ያስታወሱት ቡድን መሪ ተወካይዋ የብስክሌት ትራንስፖርትን ለማስፋፋት ቢሮው በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
አክለውም በተያዘው በጀት ዓመትም የበለጠ በመጠናከር ህብረተሰቡ ብስክሌት መንዳትን እና የእግር ጉዞ ማድረግን ባህሉ አድርጎ እንዲጠቀምም ጥሪ አስተላልፈዋል፡
11/10/2021
13ኛ ዙር የእግረኞችና የብስክሌት ቀን በሀረር ህ/ብ/ክ/መ በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ፡፡
*******
በአገር አቀፍ ደረጃ በየወሩ የመጨረሻ ሳምንት እሁድ ቀን የሚካሄደው የእግረኞችና ብስክሌተኞች መርሀ ግብር መስከረም 30 ቀን 2014 ዓ.ም በሀረሪ ከተማ ተካሂዷል።
የሀረሪ ብ/ህ/ክ/መ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ከኢፌዴሪ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በክልሉ አፈ ጉባኤ ፅ/ቤት ፊለፊት በሚገኘው አደባባይና ጎዳናዎች ላይ በተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች፣በብስክሌት እና እግር ጉዞ በማከናወን እንዲሁም የማርሻል አርት ክለቦችም የተሳተፉ ሲሆን የማርሽ ባንድን ጨምሮ የተለያዩ አዝናኝ ፕሮግራሞችን በማካተት በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።
በዕለቱ ፕሮግራም የክልሉ ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አብዲ መሀመድ ሊማይ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል እንዲሁም የመንገድ ትራፊክ ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ በለጠም የፕሮግራሙን አላማ ለተሳታፊዎች ገለፃ አድርገዋል።
12/08/2021
በመንገድ ደህንነት ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚረዳ አውደ ጥናት ተካሄደ፡፡
***************************
የትራንሰፖርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ጋር በመሆን በመንገድ ደህንነት ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚረዳ አውደ ጥናት አካሄደ፡፡
በአውደ ጥናቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሲቪል ምህንድስና መምህራን ፣የድህረ ምረቃ እና የድግሪ ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በትራንስፖርት ሚኒስቴር የመንገድ ደህንነት ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ኢ/ር ሰመረ ጅላሎ በመንገድ ደህንነት ዙሪያ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ዘርፎች ፣የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታዎች እና በተለይም ደህንነቱ የተጠበቀ መንገድ ግንባታ ላይ በሚታዩ ተግዳሮቶች ዙሪያ ለተሳታፊዎች ገለጻ አቅርበዋል፡፡
የአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎችና የዩኒቨርስቲው መምህራን ውይይቱ ለተማሪዎቹ በቀጣይ በስራ መስክ ሲሰማሩ በተለይ በመንገድ ደህንነት ዙሪያ ትኩረት መስጠት በሚኖርባቸው ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ መፍጠሩን በመግለጽ፤ተመሳሳይ መድረኮች በቀጣይነት እንዲዘጋጁ ሀሳባቸውን አቅርበዋል፡፡
11/08/2021
የትራንስፖርት ሚኒስቴር ለወጣት በጎ ፈቃደኞች ድጋፍ አደረገ፡፡
**************************
የትራንስፖርት ሚኒስቴር በክረምት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ ትራፊክ ማስተናበር ስራ ለሚያከናውኑ የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ያዘጋጀውን የዝናብ ልብስ እና አንጸባራቂ ጃኬት
የብ/መ/ደ/ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዮናስ በለጠ ለአዲስ አበባ ወጣቶችና በጎ ፈቃደኞች ማስተባበሪያ አበርክተዋል፡፡
02/08/2021
11ኛው ዙር #የብስክሌተኞችና #የእግረኞች ቀን በሀረሪ ክ/ት/መ/ል ቢሮ እና በምስራቅ ኦሮሚያ ዞን ት/ባ ጋር በጋራ ተካሂዷል፡፡
**************************
11ኛው ወርሀዊ የእግረኞችና የብስክሌተኞች ከተሽከርካሪ ነፃ ቀን የሀረሪ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ እና የምስራቅ ኦሮሚያ ዞን ትራንስፖርት ባለስልጣን ጋር በጋራ በደማቅ ሁኔታ አካሂደዋል ።
መርሀ ግብሩ የትራንስፖርትና ትራፊክ አደጋ ጉዳይ በባሕሪው ድንበር ዘለል መንስሄውም ተያያዥ በመሆኑ ለየብቻ በሚደረግ ጥረት ብቻ አደጋውን መቀነስ ስለሚከብድ አጎራባች ክልሎች ተቀናጅተው እንዲሰሩ ከፍተኛ እድል የፈጠረ በመሆኑ በልዮ ሁኔታ ተካሂዷል።
ባሳለፍነው ዓመት በምስራቁ ኢትዮጰያ ክፍል ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ ሞት የተመዘገበ ሲሆን በምስራቅ ኦሮሚያ ዞን ባለው መረጃ ከ186 በላይ ዜጎች በትራፊክ አደጋ ለሞት ተዳርገዋል፡፡ በሀረር ከተማም ከ28 ዜጎች በላይ በትራፊክ አደጋ ውድ ህይወታቸው እንዳጡ በመግለጽ ግንዛቤ በመፍጠር እና በጋራ የትራፊክ ደንብ በማስከበር አደጋውን ለመቀነስ መስራት አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በመርሀ ግብሩ የእግርና የብስክሌት ጉዞ እንዲሁም የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተከናውነዋል፡፡
በዋዜማውም በትራፊክ አደጋ ምክንያት በምስራቅ ኢትዮጰያ ውድ ህይወታቸውን ያጡ ዜጎችን ለማሰብ የሻማ ማብራት ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡
01/08/2021
11ኛው የብስክሌተኞችና የእግረኞች ቀን በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ተካሄደ፡፡
*********************
በአዲስ አበባ ከተማ 11ኛው የብስክሌተኞችና እግረኞች ቀን በዛሬው ዕለት በተለያዩ ዝግጅቶች ተካሂዷል፡፡
የትራንስፖርት ቢሮ ከኢፌዲሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር 11ኛው የብስክሌተኞችና እግረኞች ቀንን ከፒያሳ እስከ ለገሃር ባለው ቸርችል ጎዳና በደማቅ ሁኔታ አካሂዷል፡፡
በትራንስፖርት ቢሮ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማረጋገጫ ዳይሬክተር ኢንጂነር ቀጀላ መኮንን በየወሩ በ4ኛው ሳምንት የሚከበረው የብስክሌትና እግረኞች ቀን በከተማዋ የሞተር አልባ ትራንስፖርት አገልግሎትን ማስተዋወቅ እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡
ኢንጂነር ቀጀላ አክለውም ቀኑ መከበሩ ማህበረሰቡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ጤናውን እንዲጠብቅ ከማስቻሉ ባለፈ ብስክሌት አማራጭት የትራንስፖርት ስልት እንዲሆን ግንዛቤ ለማስጨበጥ እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡
በዕለቱ ብስክሌተኞች፣ የአካል ብቃት ስፖርተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተው የመርሃ ግብሩ ተሳታፊ ሁነዋል፡፡ ተሳታፊዎችም ከትራፊክ አደጋና ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ለመከላከል የብስክሌተኞችና የእግረኞች ቀን መርሃ ግብሮች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ጠይቀዋል፡፡ማህበረሰቡም የእግር ጉዞን በማዳበርና ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ጤናውን መጠበቅ እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በመዲናዋ ከለቡ መብራት ሀይል እስከ ጀሞ 1፣ ከቤቴል ሚካኤል እስከ አንፎ ስላሴ፣ ከአያት አደባባይ እስከ ኖህ ሪል ስቴት፣ ከፓስተር እስከ መድሃኒዓለም እና ከስድስት ኪሎ እስከ ፈረንሳይ በተለያዩ ዝግጅቶች በተመሳሳይ ተከብሯል፡፡
አዲስ አበባ ት/ቢሮ