Ethiopian Statistical Service-ESS

Ethiopian Statistical Service-ESS

Share

Ethiopian Statistical Service collects, processes, and disseminates official statistical data.

Photos from Ethiopian Statistical Service-ESS's post 29/05/2026

ተቋሙ በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ
ግንቦት 21/2018 ዓ.ም፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች ከ8 መቶ ሺ ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
ተቋሙን ወክለው በጋሞ ዞን ተገኝተው ድጋፉን ያስረከቡት የተቋሙ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብነት ሐዋዝ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስታቲስቲክስ መረጃዎችን በማመንጨትና በማሰራጨት ሙያዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ከህዝብ ጎን የሚቆም ተቋም መሆኑን ገልፀው፣ በጋሞ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ወገኖቻችንን መልሶ ለማቋቋምና ለመደገፍ ከዋናው መ/ቤትና ከ26 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የሚገኙ አመራሮችና ሰራተኞችን በማስተባበር ከ8 መቶ ሺ ብር በላይ የሰበሰበ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ይህንን ለማስረከብ በቦታው መገኘታቸውን ገልፀዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ተስፋፅዮን ዘነበ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በዞናቸው ለደረሰው ጉዳት ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

26/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛ የኢድ አል-ዓደሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ ኢድ ሙባረክ!

Photos from Ethiopian Statistical Service-ESS's post 26/05/2026

በ55ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔ ካስተላለፈባቸው ጉዳዮች ውስጥ የስታቲስቲክስ ረቂቅ አዋጅ አንዱ መሆኑ ተገለፀ
ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ረቂቅ አዋጅ ምክር ቤቱ የተወያየበት ሌላው አጀንዳ ነው፡
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሞያዊ ነፃነትን ለማረጋገጥ፣ የተቆጣጣሪ እና የፈጻሚ አካላትን የቁጥጥር እና የአሠራር ተግባራትን ሚና በግልፅ ለመለየት፣ በሁሉም ኦፊሽያል ስታቲስቲክስ አመንጪዎች መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር፣ የመረጃ ምስጢራዊነትን ለመጠበቅ፣ የስታቲስቲክስ ውጤቶችን ጥራት ለማሻሻል፣ ተደራሽነታቸውን ለማረጋገጥ እና ሀገራዊ አሠራሮችን ከዓለም አቀፍ የስታቲስቲክስ መርሆዎች እና ደረጃዎች ጋር ለማጣጣም እንዲያስችል ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡

Photos from Ethiopian Statistical Service-ESS's post 26/05/2026

በተቋሙ የስራ አፈፃፀምና ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተደረገ
ግንቦት 18/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ባለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት ባከናወናቸው የስታቲስቲክስ ልማት ፕሮግራም የጥናትና ቆጠራዎች አፈፃፀም ቀርቦ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ላይ ከተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት መላ ፈፃሚ ጋር ውይይት ተደረገ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የስታቲስቲክስ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ዶ/ር ሜሮን ክፈለው ተቋማችን ባለፉት ሶስት ዓመታት ያከናወናቸውን ጥናቶችና ቆጠራዎች በስኬት መጠናቀቅ የሁሉም ባለሙያ የጎላ ተሳትፎ ውጤት መሆኑ እና ቀጣይ ከዚህ በተሻለ ለመስራት በስራ ክፍሎች መካከል የዕውቀት ሽግግር እንዲኖር በማድረግና የበለጠ በቅንጅት ለመስራት ለመዘጋጀት ታስቦ የተፈጠረ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል።

በመድረኩ ከጥናቶች ስነ ዘዴ፣ ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም አንፃር፣ ከመረጃ አሰባሰብና አመዘጋገብ፣ አማራጭ የመረጃ ምንጮች ፣ የመረጃ ተደራሽነት፣ ከመረጃ አስተዳደር ማዕቀፍ አንፃር የተሰሩ ዋና ዋና ስራዎች ላይ ገለፃዎች ቀርበው ግንዛቤ ተፈጥሯል።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በመድረኩ ማጠቃለያ ተቋሙ በስታቲስቲክስ ልማት ፕሮግራም የታቀዱ ስራዎችን ለመፈፀም የተቻለው የአመራሩ እና ፈጻሚው ርብርብ ፣ የባለድርሻ አካላት በቅንጅት በመስራት ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች መታገዝ ፣ አማራጭ የመረጃ ምንጮችን በመጠቀም የተሰጠውን ኃላፊነቱን የተወጣ መሆኑን ገልፀዋል።

በተጨማሪም ይህን ስኬት መነሻ በማድረግ በየደረጃ ያሉት ፈጻሚዎች በቀጣይ የበለጠ በመነሳሳት ፣የተሻሉ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም ወደ ልህቀት የምናደርገውን ጉዞ ለማሳካትና የሀገራችንን የመረጃ ሉዓላዊነት ለማፅናት እና ለማላቅ ሁሉም አካላት በጋራ መስራት አለብን ሲሉ የስራ አቅጣጫ ተሰጥተዋል። ተሳታፊዎቹም ዝግጁነታቸውን የገለጹ ሲሆን የተፈጠረውን ተነሳሽነት ወደ ተሻለ ደረጃ ማሻገር እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

23/05/2026
Photos from Ethiopian Statistical Service-ESS's post 23/05/2026

ተቋማቱ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
ግንቦት 14/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በሀገራችን በምርምርና ልማት ዘርፍ ያለውን የመረጃ ክፍተት የሚሞላ ብሔራዊ የምርምርና ልማት ጥናት በጋራ ለማካሄድ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ እና የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ በጋራ ፈርመውታል።

የጥናቱ ዋና ዓላማ የምርምርና ልማት ወጪን ከሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት አንፃር ለመለካት፣ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችን ብዛት ለማወቅ፣ የምርምር ዓይነቶችን ለመለየት፣ የአሠራር ፈተናዎችንና ክፍተቶችን በማጥናት መነሻ አመልካች መረጃ ለማዘጋጀትና ከጥናቱ ከተገኙት መረጃዎች በመነሳት ተግባራዊ የሚሆኑ የፖሊሲ ምክረ-ሀሳቦችን ማቅረብ ሲሆን መረጃው ከንግድ ድርጅቶች፣ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ለትርፍ ያልተቋቋሙ የግል ድርጅቶች እንደሚሰበሰብ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

ጥናቱ ለ2030 የዘላቂ ልማት ግቦች (ለኢንዱስትሪ፣ ፈጠራና መሠረተ ልማት)፣ ለአፍሪካ አጀንዳ 2063 የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ስትራቴጂ)፣ ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ለኢትዮጵያ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

Photos from Ministry of Innovation and Technology - Ethiopia's post 22/05/2026
22/05/2026
Photos from Ethiopian Broadcasting Corporation's post 22/05/2026
Photos from Abiy Ahmed Ali's post 22/05/2026
Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Piassa
Addis Ababa