የኢትዮጲያ ወጣቶች ምክር ቤት Ethiopian Youth Council

የኢትዮጲያ ወጣቶች ምክር ቤት Ethiopian Youth Council

Share

The official representative voice of more than 41 million young people in Ethiopia.

Photos from የኢትዮጲያ ወጣቶች ምክር ቤት Ethiopian Youth Council's post 22/04/2026

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ፉአድ ገና በቼንጅ ሜከርስ አዋርድ በ”Inspiring journey of the year”ዘርፍ እጩ ሆነው ቀርበዋል።

ወጣት ፉአድ ገና የኢትዮጵያ ወጣቶች በአገራቸው ሁለንተናዊ ፓለቲካዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ባለቤት ሆነው እንዲሳተፉና ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ መደላደሎችን ከመፍጠር ጀምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ብቁ ተወዳዳሪና አሸናፊ ሆነው እንዲወጡ ጠንካራ የአመራርነት ሚናቸውን እየተወጡ ያሉ የወጣት መሪ ናቸው።

ፉአድ ገና በስትራቴጂካዊ ራዕያቸውና እና ሁሉን አቀፍ በሆነው የአስተዳደር መርሀቸው የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤትን በተጨባጭ ውጤቶች አየመሩ ይገኛሉ።

በመሆኑም እጩ ሆነው በቀረቡበት የሽልማት ዘርፍ አሸናፊ ይሆኑ ዘንድ የእርስዎ ድምጽ ዋጋ አለውና ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ድምጽዎን ይስጡ።

Fuad Gena, President of the Ethiopian Youth Council, has been nominated for the Change Makers Award, Inspiring Journey of the Year category. This recognition is a testament to his unwavering commitment to delivering quality leadership for Ethiopian youth.

Through strategic vision and inclusive governance, Fuad has transformed the council into a dynamic force that prioritizes youth-driven solutions, ensuring that young Ethiopians are not just heard but actively shaping the nation’s future.

Ethiopian youth are now more empowered than ever to participate meaningfully in political, social, and economic affairs of the country. His work is building a generation of confident, capable young leaders ready to drive Ethiopia forward.

Beyond national borders, Fuad has been instrumental in facilitating platforms for Ethiopian youth on international stages allowing them to showcase their potential, share their stories, and build global partnerships.

Now, it’s time to honor this inspiring journey. Vote for Fuad Gena using the link below and help celebrate a leader who truly empowers Ethiopian youth.

Cast your vote here: https://changemakeraward.com/share/id-mo4c9ste62pyyogazh.html?cat=cat_inspiring_journey

Photos from Ethiopian Broadcasting Corporation's post 09/04/2026
Photos from የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር   Ministry of Women and Social Affairs's post 26/03/2026
Photos from የኢትዮጲያ ወጣቶች ምክር ቤት Ethiopian Youth Council's post 08/02/2026

"ወጣቶችን ወደ ጎን ያደረገ ማንኛውም ሰላም፣ ልማትና አስተዳደር ጎዶሎ ብቻ ሳይሆን ዴሞክራሲያዊ ህጋዊነትም ይጎለዋል" የኢትዮጲያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ፉአድ ገና

የአፍሪካ ቀንድ የወጣቶች ፎረም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ይገኛል።

"ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እና የአየር ንብረት ለዉጥ መፍትሔዎች ወጣት መር ጥረቶችን ማበረታታት " በሚል መሪ ሀሳብ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት የአፍሪካ ቀንድ የወጣቶች ፎረም በዛሬው እለት ተጀምሯል ።

በፎረሙ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሙና አህመድ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ወጣቶች በዚህ መልኩ መሰባሰባቸዉ ለቀጠናው ሁለንተናዊ ሰላም፣ልማትና እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

በመረሀ-ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ፎረሙ ቀጠናዊ ሰላምን ለማስፈን ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸው የቀጠናው ወጣቶች እርስ በርስ የሚግባቡበትና ለጋራ አላማ የሚሰለፉበትን መደላደል እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።

የኢትዮጲያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ፉአድ ገና በፎረሙ ላይ ባደረጉት ንግግር ወጣቶችን ወደ ጎን ያደረገ ማንኛውም ሰላም ልማትና እድገት ፣ደህንነትና አስተዳደር ጎዶሎ ብቻ ሳይሆን ዴሞክራሲያዊ ህጋዊነት የጎደለው በመሆኑ ወጣቶች በእያንዳንዱ አጀንዳ ላይ ተገቢው ቦታ ሊሰጣቸው እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በወጣቶች እምቅ አቅምና ሀይል የታደለውን የአፍሪካ ቀንድ ለማጠናከር፣የቀጠናውን ወጣቶች ለጋራ አላማ ለማሰለፍና ቅንጅታዊ አሰራርን ለመዘርጋት መሰል የግንኙነት መድረኮች ሚናቸው የጎላ እንደሆነ ያመላከቱት ፕሬዚደንቱ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ወጣቶች ከቀጠናው አልፎ ለአህጉሪቱ ሁለንተናዊ ሰላምና ልማት የድርሻቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።

የድሬዳዋ ከተማ የወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ወጣት ሃሚድ አብደላ በበኩላቸው ፎረሙ በዋነኝነት በአየር ንብረት ለዉጥና ቀጠናዊ ሰላም ላይ ያተኮረ ስለመሆኑ አመላክተው ድሬዳዋ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነትና የብዝሀነት መናገሻ መሆኗን ለሌሎች ሀገራት ለማሳየትም ጥሩ እድል ፈጥራል ብለዋል።

በፎረሙ ላይ የጂቡቲ ፣ የሶማሊያ ፣ የሶማሌላንድ ፣ የደቡብ ሱዳን ፣ የኢጋድ እና የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች እየተሳተፍ ሲሆን በቀጠናው ሰላምና ደህንነት፣የአየር ንብረት ለውጥ፣ የወጣቶችና ቀጠናዊ ትስስር፣ቀይ ባህርና የወጣቶች አመራርነት ላይ አትኩሮ እየተካሄደ ይገኛል።

የኢ/ወ/ም/ቤት

05/02/2026

Opportunity for Ethiopian traditional music instrument players

*Don't miss the opportunity to shine at the BRICS Melody International Music Festival!* 💃🕺

The Russia-BRICS Youth Project Office is looking for professional performers who masterfully play traditional musical instruments of the BRICS countries (Brazil, Russia, India, China, South Africa, United Arab Emirates, Iran, Ethiopia, Egypt, Indonesia)!

📌 *About the project:*
"BRICS Melody" is a cultural bridge aimed at strengthening dialogue and mutual understanding between our countries through music. We believe that traditional instruments are the living history and soul of a people, and they can speak to the whole world without words.

*Program Components and Opportunities:*
✨International Festival in Moscow. The culmination of the project will be a grand concert on April 25, 2026 at the "Rossiya" National Center stage.
✨Creation of the international music album "BRICS Melody". Each participant will record a song on a traditional instrument, after which all the tracks will be combined into a single album.
✨The organizers cover the flight and accommodation costs for the selected participants.

*How to Participate ?*
✅Fill out the competition application via the link: https://forms.gle/iLYAQ4nTuGG4oESD8 ( *by February 15* )

🔗 *Details and contact with the organizers* : https://bricsmelody.com/main_page_en/

Organisers: the Ulyanovsk Regional Branch of the Russian Youth Union in partnership with the Russia BRICS Youth Cooperation Project Office with the support of the Presidential Foundation for Cultural Initiatives.

Photos from Dire Dawa Youth Council  የድሬዳዋ ወጣቶች ምክር ቤት's post 04/02/2026
Photos from የኢትዮጲያ ወጣቶች ምክር ቤት Ethiopian Youth Council's post 25/01/2026

ሁለተኛው የሶማሌ ክልል የወጣቶች ፎረም በጅጅጋ ከተማ ተካሄደ።

የሶማሌ ክልል የወጣቶች ምክር ቤት ከክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው አመታዊው የሶማሌ ክልል የወጣቶች ፎረም ለሁለተኛ ጊዜ በጅጅጋ ከተማ ተካሂዷል።

ፎረሙ "ወጣቶችን ለዲጂታል አለም ማብቃት" በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደ ሲሆን በዲጂታል ዘመን የወጣቶችን ሚና፣ አቅም እና ተሳትፎ ለማጎልበት አላማ ያደረገ ስለመሆኑም ተመላክቷል።

በመድረኩ የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኢብራሂም ኡስማን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የፌዴራል መንግስት ተወካዮችና ከሶማሌ ክልል ሁሉም ዞኖችና የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከአጎራባች ክልሎች የተወከሉ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል።

የኢት/ወ/ም/ቤት

Photos from የኢትዮጲያ ወጣቶች ምክር ቤት Ethiopian Youth Council's post 23/01/2026

ወጣት አሸናፊ መብራቱ የኢጋድ ሊደርሺፕ አካዳሚ አልሙናይ ኔትዎርክ ሰብሳቢ ሆኖ ተመረጠ።

በኢጋድ አደረጃጀቶች ስር ከሚገኙ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነውና መቀመጫውን ኬንያ ያደረገው የኢጋድ ሊደርሺፕ አካዳሚ የቀጠናውን አገራት ወጣቶች በአመራር ልህቀት የማሰልጠንና የማብቃት ተልእኮ አንግቦ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነው።

ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ወር አጋማሽ ላይ የኢጋድ ሊደርሺፕ አካዳሚ አልሙናይ ኮንፈረንስ በናይሮቢ መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን በኮንፈረንሱም የኢጋድ ሊደርሺፕ አካዳሚ አልሙናይ ኔትዎርክ በይፋ ተመስርቷል።

በዚሁ ኮንፈረንስ ላይም ኢትዮጵያ የኢጋድ ሊደርሺፕ አካዳሚ አልሙናይ ኔትዎርክ ሰብሳቢነት ሚናን ተረክባለች።

በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የሶሾሎጂ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ የሆነው ወጣት አሸናፊ መብራቱ ከፍተኛ ፍክክር የነበረበትን ምርጫ በማሸነፍ የኢጋድ ሊደርሺፕ አካዳሚ አልሙናይ ኔትዎርክ ሰብሳቢ ሆኖ ተመርጧል።

ምክትል ሰብሳቢ ከኬንያ እንዲሁም ዋና ጸሀፊ ከሶማልያ ተመርጧል።

ወጣቶች የነገ ብቻ ሳይሆን የዛሬ መሪዎች መሆናቸው በተስተጋባበት በዚሁ መድረክ የቀጠናውን አገራት ወጣቶች ሁለንተናዊ ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ ተመላክቷል።

ወጣት አሸናፊ ከ13 አመታት በላይ በማህበራዊ ሳይንስ መምህርነትና ተመራማሪነት ያገለገለና ወጣቶችን በማብቃት የካበተ ልምድ ያለው ባለሙያ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

የኢ/ወ/ም/ቤት

01/01/2026
Photos from የኢትዮጲያ ወጣቶች ምክር ቤት Ethiopian Youth Council's post 04/12/2025

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ፉአድ ገና በቻይና ዣመን ከተማ ከተካሄደው የብሪክስ ወጣቶች ሳይንስ፣ቴክኖሎጂና የፈጠራ ስራዎች ሰብሰባ ጎን ለጎን "ከBrics Partnership on New Industrial Revolution Innovation Center" የአለም አቀፍ ትብብር ዲቪዥን ዳይሬክተር ቻይ ቻካኮ ጋር ተወያይተዋል።

ድርጅቱ በብሪክስ አባል አገራት ለሚገኙ የቴክኖሎጂና ስራ ፈጣሪዎች እንዲሁም ስታርትአፓች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን ይሰጣል።

መሪዎቹ ኢትዮጵያውያን የቴክኖሎጂና ስራ ፈጣሪዎችን እንዲሁም ስታርትአፓች የዚህ እድል ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መደላደል ማመቻቸት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ተቋማቱ የውይይቱን ፍሬ ሀሳቦች ወደ መሬት ለማውረድ የሚያስችል ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለመፈጸምም ከስምምነት ደርሰዋል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Bambis Area
Addis Ababa