21/10/2024
በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ በተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት እጅግ አዝነናል።
የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ከእሳት አደጋ እና ስጋት መከላከል እንዲሁም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ርብርብ እየተደረገ ሲሆን አደጋውን ቶሎ ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለዉን ጥረት አዳጋች ያደረገዉ የአካባቢው መንገድ የእሳት አደጋ መኪና በተሟላ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት በሄሊኮፕተር ለመጠቀም እየጣርን ነው። ይህንን አደጋ ለመቀነስ ርብርብ እያደረጋችሁ ያላችሁ አካላት ሁሉ ጥረታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ አሳስባለሁ።
Balaa abiddaa Markaatoo, naannawa Shaamaa Taraatti uumameen miidhaa qaqqabeef baay'ee gaddineerra!
Balaa abiddaa uumamee too'achuuf, Ittisa abiddaa fi sodaa balaa akkasumas hawaasa naannichaa waliin ta'uun tattaaffiin godhamaa kan jiru yennaa ta'u balicha saffisaan too'achuuf tattaaffii taasifamaa jiru ulfaataa kan taasise daandiin naannichaa makiinota balaa abiddaa haala guutuu ta'een fayyadamuuf rakkisaa sababa ta'eef Helekooptaraa ayyadamuuf yaalaa jirra. Balaa kana hir'isuuf qaamoleen deeggarsa taasisaa jirtan hundi yaalii keessan cimsitanii akka itti fuftan isin yaadachiisa.
18/10/2024
ተቋማት የአደጋ መከላከል ተግባርን በመደበኛ ዕቅዳቸዉ አካተዉ መተግበር እንዳለባቸዉ ተገለጸ።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከሚገኙ ሴክተር ተቋማት ጋር የአደጋ መከላከል ተግባርን ከመደበኛ እቅዳቸዉ ጋር እንዲያካትቱ በሚያስችላቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ ከተቋማት ተወካዮች ጋር ዉይይት አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የአደጋ ቅነሳ ዘርፍ ኃላፊ ተወካይ አቶ ቴዎድሮስ በቀለ እንደተናገሩት የአደጋ መከላከል ተግባር የኮሚሽን መ/ቤቱ ኃላፊነት ብቻ እንዳልሆነ ጠቅሰዉ ሁሉም ተቋማት የአደጋ መከላከል ተግባርን ከመደበኛ ዕቅዳቸዉ ጋር አካተዉ በመተግበር ሰላማዊና ከአደጋ የተጠበቀ አካባቢን መፍጠር እንደሚገባቸዉ አሳስበዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ እንደተናገሩት የአደጋ ቅነሳ ስራ በሚፈለገዉ ደረጃ ትኩረት እንዳልተሰጠዉ ጠቅሰዉ አደጋን ተከላክሎ ስራን ማከናዉን ዉጤታማ የሚያደርግ በመሆኑ በቀጣይ ጊዜያት ከኮሚሽን መ/ቤቱ ጋር በትብብር እንደሚሰሩ አስታዉቀዋል።
በዉይይት መድረኩ የ27 ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
07/10/2024
የመሬት መንቀጥቀጥ በሚያጋጥም ጊዜ መደረግ የማገባቸዉ የጥንቃቄ እርምጃዎች
📌 ከቤት ውጭ ከሆኑ - ከዛፎች፣ ከሕንፃዎች፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።
📌 በቤት ውስጥ ከሆኑ - በበር መቃኖች፣ በኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።
📌 በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ- ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።
📌 መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ- የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
12/09/2024
በጎርፍ ሊወሰዱ የነበሩ እናትና ልጅ በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ህይወታቸዉን መታደግ ተቻለ።
ዛሬ መስከረም 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ገደማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ጀርመን ድልድይ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በጎርፍ ሊወሰዱ የነበሩ እናትና ልጅ በአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጥረት ህይወታቸዉን ማትረፍ ተችሏል።
እናትና ልጇ በወንዝ ዳርቻ ካለዉ የጎመን ማሳቸዉ ዉስጥ ጎመን በመሰብሰብ ላይ ሳሉ በድንገት ደራሽ ጎርፍ ሊወስዳቸዉ የነበረ ቢሆንም በወንዝ መሀል ባለ ድንጋይ ጫፍ ላይ ሆነዉ ህይወታቸወን ማቆየት ችለዋል።
ይሁንና የጎርፉ መጠን እየጨመረ በመምጣቱ እናትና ልጁ በጎርፉ ሊወሰዱ በተቃረቡበት ሰዓት የኮሚሽኑ ጠላቂ ዋናተኞች ደርሰዉ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸዉ የእናትና ለጇን ህይወት መታደግ ችለዋል።
በአካባቢዉ ቀደም ሲል በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የስምንት ሰዎች
ህይወት የአለፈበት ሲሆን በዚህ አካባቢ ከወንዙ የሚገኘዉን ዉሀ በመጠቀም የጎመንና ሌሎች ተክሎች ማሳ የሚገኝበት ነዉ።
በአሁኑ ሰዓት የክረምቱ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ባለመጠናቀቁ ባለማሳዎች ተክሎቹን ለመሰብሰብ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የጎርፍ አደጋ ሊያጋጥም የሚችል በመሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ ኮሚሽን መ/ቤቱ ያሳስባል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
12/09/2024
በሚቀጥሉት 10 ቀናት በሰሜንና ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች የዝናብ መጠን ስርጭት እየቀነሰ ይሄዳል
አዲስ አበባ፤ መስከረም 2/2017(ኢዜአ)፦ በሚቀጥሉት 10 ቀናት በሰሜንና ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች የዝናብ መጠን ስርጭት እየቀነሰ ሲሄድ በሌሎች ቦታዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊኖራቸው እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለኢዜአ በላከው መግለጫ በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ የኢትዮጵያ ክፍል የዝናብ መጠኑ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችል አመላክቷል።
የኢትየቶጵያ ደቡባዊው ክፍል ሁለተኛውን የዝናብ ወቅት ቀስ በቀስ ማግኘት እንደሚጀምሩም ጠቁሟል።
የሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እንዲሁም መካከለኛው የሀገሪቱ ክፍል ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ይመዘገባል ሲልም ነው የተነበየው።
በፀሐይ ሀይል የሚጠናከሩ የደመና ክምችቶች በአንዳንድ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ሊያስከትሉ እንደሚችሉም የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በትግራይ፣ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ኦሮሚያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች እንዲሁም አዲስ አበባ ከቀላል እስከ ከባድ ዝናብ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በአንፃሩ አፋር፣ ኦሮሚያ ምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ ዞኖች፣ አማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ጋንቤላ ክልል፣ ትግራይ ክልል ደቡብና ደቡብ ምስራው ዞኖች ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ሱማሌ እና ሀረሪና ክልሎች እንዲሁም ድሬዳዋ ከፍ ያለ ዝናብ ያገኛሉ ተብሏል፡፡
በአብዛኞቹ የመኸር ሰብል አብቃይ አካባቢዎች ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ እርጥበት እንደሚኖራቸውም ይጠበቃል።
በመሆኑም በማፍራት ላይ ላሉ፤ ዘግይተው ለተዘሩ ሰብሎች እንዲሁም ለአትክልትና ፍራፍሬዎች የላቀ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል ከአዋሽ ተፋሰስ የቆቃ፣ ተንዳሆና ከሰም ግድቦች፤ ከዓባይ ተፋሰስ ጣና በለስ፣ ርብና ፊንጫ ግድቦች፤ ከውሀ ብዛት ጋር በተያያዘ በታችኛው የተፋሰሱ አካባቢዎች ጫና እንዳያሳድሩ ክትትል ማድረግ ይገባል ሲል አሳስቧል።
07/09/2024
ኮሚሽን መ/ቤቱ አገልግሎቱን ለማዘመን በሙከራ ትግበራ ላይ ያዋላቸው የቴክኖሎጂ ስራዎች በከተማው አስተዳደሩ ስራ አሰኪያጅ ጽ/ቤት አመራሮች ተጎበኘ፡፡
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂው ለማዘመን የሚያስችለው የቴክኖሎጂ የሙከራ ትግበራ ስራ በአዲስ አበባ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ጳጉሜ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ተጎብኝቷል ፡፡
በጉብኝት መርሀ ገብሩ ላይ ወ/ሮ ቆንጂት ደባላ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ስራ አሰኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ስራ አስኪያጅ ኮሚሸነር ፍቅሬ ግዛውና የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም አቶ ሰለሞን አማረ የአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊና የቢሮው ስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በሙከራ ላይ የሚገኘው ቴክኖሎጂ ትግበራ አደጋ በደረሰበት ቦታ የሚደረግ በረራንና በአደጋው ቦታ ያለውን የአደጋ ሁኔታ በቀጥታ በቪዲዮ የሚያስመለከት እንደሆነ በሙከራ ትግበራዉ እንዲታይ ተደርጓል ፡፡
በሌላ በኩልም ለኮሚሽኑ ሰራተኞች አገልግሎት እየሰጠ ያለው ክሊኒክ ከወረቀት አሰራር ነጻ የሆነ ቴክኖሎጂን ለመተግበር በሙከራ ስራ ላይ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡
አመራሮቹ ከጉብኝቱ በኃላ በሰጡት አስተያየት አዲስ አበባ ከተማ አሁን ከደረሰችበት ዕድገት አንጻር አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ ማከናወን መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ጠቀሰው በዚህ መነሻም የኮሚሽን መ/ቤቱ የሪፎርም አካል በሆነው በቴክኖጂዉ ዘርፍ እያከናወናወኑ ያሉ ተግባራት ለውጥ ማምጣቸውን ጠቅሰው ቀሪ ስራዎች ተጠናቀዉ በፍጥነት ወደ ሙሉ ትግበራ እንዲገባም አሳስበዋል ፡፡
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነው ያሳውቁ!
07/09/2024
ዛሬ ጳጉሜ 1/2016 ዓ/ም የመሻገር ቀን በደማቅ ዝግጅት ተከብሮ ዋለ፡፡
በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፍ የማዕከል አደጋ ስጋት ጥናትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት በኮሚሽኑ ከተለያዩ ስራ ክፍሎች እና ከአራዳ ክፍለ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር እና በመቀናጀት በጊዮርጊስ አደባባይ ዳስ አውደርዕይ በማዘጋጀት እንዲሁም በከተማው ልዩ ልዩ ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች በአፍንጮ በር መነን ሽሮ ሜዳ ወደ ቀጨኔ፣ ከቀጨኔ ወደ አዲሱ ገበያ በሾላ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ በመዘዋወርና ትዕይንት በማሳየት፣የተለያዩ የህትመት ውጤቶችን ( 6500 በራሪ ወረቀትና 250 ፖስት ካርዶች) ለህብረተሰቡ ማሰራጨት ተችሏል፡፡
በዕለቱ በተደረጉ ትዕይንትና አውደ-ርዕይ ስራዎች በአጠቃላይ 40,000 በላይ ለሚሆን የከተማው የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤና ስርፀት ቅ/ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል ተብሎ ይገመታል፡፡ መሰል ተግባራት በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና በማዕከል የሚገኙ ባለሙያዎች ጳጉሜ 2 ትን በተመደቡበት ቅርንጫፍ በመገኘት አስፈላጊውን እገዛ ሲያርጉ እንዲውሉ ስምሪትም ተሰጥቷል፡፡
የአደጋ ስጋት ጥናትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት
07/09/2024
ቀን 2/13/2016ዓ.ም
በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሸን በለሚ ኩራ ቅ/ጽ/ቤት
በአደጋ ስጋት ጥናትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት
የዳስ አውድ ርዕይ አያት አደባባይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን