17/12/2021
በማዕድን ሚኒስቴር ሁለተኛው ምዕራፍ የፀረ-ሙስና ቀን ተከበረ
በሃገራችን ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረው ሃገር አቀፍ የፀረሙስና ቀን “ በሥነ-ምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና የፀዳች ኢትዮጵያ “ በሚል መሪ ቃል በማዕድን ሚኒስቴር ሰራተኞች በሙሉ ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም የመጀመሪያውን ምዕረፍ የበዓል አከባበር በየስራ ክፍሉ ያሉ ውዝፍ ስራዎችን ሰርቶ በመጠናቀቅ ለተሰሩት ስራዎች ለበላይ አመራር ሪፖርት በማሳወቅ መከበሩ ይታወቃል ፡፡ ሆኖም ግን በዛሬው ዕለት ደግሞ ታህሳስ 08 ቀን 2014 ዓ.ም የሚኒስቴር መ/ቤቱ ሰራተኞች እና ተጠሪ ተቋም በሆነው ጂኦሎጆካል ኢንስቲትዩት ሰራተኞች በጋራ በመሆን ሁለተኛውን ምዕራፍ የፀረ-ሙስና ቀን በፅዳት ዘመቻ እና በሃገራችን ላይ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ በሚደረገው የፀጥታ ማስከበር ስራ የውጭ ሃገራት በሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት እና የሚዲያዎቻቸው የሃሰት ዜናዎች ትርክት በመቃወም የበቃ ( # NO MORE ) የንቅናቄ ዘመቻ በማካሄድ የፀረ-ሙስና ቀን ተክብሮ ውሏል ፡፡
በዕለቱም የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ዳይቴክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አራጋው አደመ በዓሉን አስመልክተው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ከምንም በላይ ስነ-ምግባር ትልቁ ዕሴታችን መሆን ያለበትና በተቋማችን ዉስጥ ይህንን አስተሳሰብ መገንባት ለፀረ- ሙስና ትግሉ የማይተካ ሚና እንዳለው ገልፀው ሙስና የልማትና የብልፅግና ፀር መሆኑን ተረድተን ይህን አፀያፊ ተግባር ማንኛውም ዜጋ ሊታገለው ይገባል ብለዋል ፡፡
በተጨማሪም ሙስና ለአንድ ሀገር ዕድገት ጠንቅ ከመሆኑም ባሻገር ለሰላምና መረጋጋት አይነተኛ ስጋት በመሆኑ ጠንካራ የሥራ ባህልን በመላበስ ሀገራችንን ወደ ልማትና ብልፅግና ጎዳና በሚደረገዉ ጉዞ የማተካ ሚና በመጫወት ከሙስና ድርጊትና አሰተሳሰብ በመራቅ የታሪኩ ባለቤት መሆን ይገባናል ሲሉ አፅንኦት ሰጥተው የዕለቱን መልዕክት አስተላልፈዋል ፡፡
በተጨማሪም የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ኪሮስ አለማየሁ የመ/ቤቱን የበላይ አመራር በመወከል የዕለቱን የበዓል አከባበር አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ኃላፊው እንደገለፁት በዕለቱ በሁለት ፕሮግራሞች በዓሉ እንደተከበረ ገልፀው ሙስና ከአስተሳሰብ ይጀምራል አካባቢያችንን እንዳፀዳን ሁሉ ሁላችንም ከዚህ አፀያፊ ተግባር ተላቀን ከብልሹ አሰራር የፀዳ አስተሳሰብ በመላበስ ለሃገራችን ልማት ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል በማለት አክለውም በሃገራችን ላይ ባለው ወቅታዊ ጉዳይ የተደረገው የንቅናቄ ስራ በቀጣይ ሃገራችን የጀመረችውን የሰላም ጉዞ ከዳር እስኪደርስ ድረስ ትግሉን የበለጠ በማቀጣጠል በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ትግሉ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በመግለፅ የበዓሉን አከባበር የመዝጊያ ንግግር አድርገዋል ፡፡

09/12/2021