TOM TOM

TOM TOM

Share

i need love and peace

Photos from TOM TOM's post 23/09/2021

እስከ ዶክትሬትነት የዘለቀ
ጏደኝነት ከልጅነት አስከ ጅማ
ዩኒቨርስቲ የህክምና ዶክትሬት::

23/09/2021

መልካም ምሽት

02/09/2021

ማርታ ጎይቶም 😍😍
በተለይ ኪያ የተሰኘው ፊልሟ እስከዛሬ ከሰራቻቸው ፊልሞች ጋር ቢደመሩ የአንድ የሱን ያህል አያክሉም ።
ጎበዝ እና ቆንጃ አክተርስ ።

14/04/2021

‹‹ዘመነ መሳፍንት›› የተባለውን የየግዛት ባላባቶች ዘመን በማስቆም ኢትዮጵያን በአንድ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት ስር ለማስተዳደር የሞከሩት ንጉሰ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ቴዎድሮስ ያረፉት ከዛሬ 153 ዓመታት በፊት (ሚያዝያ 6 ቀን 1860 ዓ.ም) ነበር፡፡

14/04/2021

አሜሪካ ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የ23 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያዎችን ልትሸጥ መሆኗን አስታወቀች

ሽያጩ ይፋ የሆነው ፕሬዝደንት ባይደን ለዩኤኢ የጦር መሳሪያ እንይሸጥ ጥለውት የነበረውን እገዳ በማንሳታቸው ነው፡፡የጦር መሳሪያ ሽያጭ ስምምነቱ በዘመነ ትራምፕ የተደረሰ ነው፡፡

11/01/2021

የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሌሎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ዋነኛ የጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ
የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱና ምክትል ፕሬዚዳንትን ዶክተር አብርሃም ተከስተን ጨምሮ አገር ለመበታተን ሲሰሩ ቁጥጥር ስር የሕወሃት ጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ።
የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ጥምር ሃይል አገር በመከላኪያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በማድረስ አገር ለመበታተን ሲሰሩ የነበሩ የአሸባሪው ህወሃት አባላትን ለሕግ የማቅረብ ተልዕኮ እንደቀጠለ ነው።
ኢቢሲ

Photos from TOM TOM's post 10/01/2021

በማዳም ልጅ በጥይት ተመትታ የነበረችው ኢትዮጵያውያን ሰደተኛዋ እህታችን ሀብታሟ ይመር ስጦታው

512 ሺህ ብር ካሳ ተከፈላታል::

ክዌት 🇰🇼

በኩዌት የኢፌዲሪ ኤምባሲ ሀብታሟ ይመር ስጦታው የተባለች ዜጋችንን የግማሽ ሚሎዮን ብር የጉዳት ካሳ በዛሬው ዕለት (ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲከፈላት አድርጓል።

ዜጋችን ጠፍታ በምትራበት ቤት እያለች መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም በአሰሪዋ ልጅ በሽጉጥ ተመትታ ጉዳት ደርሶባት ነበር።

በዚህም ምክንያት በፈርዋንያ ሆስፒታል ህክምና ስትከታተል የነበረ ሲሆን፣ ለደረሰባት ጉዳት ከሳ እንዲከፈላት ለማድረግ ኤምባሲው ከፖሊስ ጋር በመሆን ጉዳዩን በጎ ፈቃደኛ ጠበቃ አቁሞ ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።

በመሆኑም ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው የፍርድ ቤት ቀጠሮ በመገኘት KWD 4000.00 ( ETB 512,000.00 (አምስት መቶ አስራ ሁለት ሽህ ብር) እንዲከፈል አድርጓል።

የጉዳት ካሳ እንዲከፈላት የተደረገችው ዜጋችን ሀብታሟ ይመር ስጦታው ወደ ሀገሯ እስክትሳፈር ድረስ በመንግስት መጠለያ እንዲትሆን ተደርጓል። ኤምባሲው በሂደቱ ለተባበሩ ሁሉ ምሥጋናውን ያቀርባል።

ምንጭ :- በኩዌት የኢፌዲሪ ኤምባሲ

19/12/2020

ከቤተሰቦቻቸው ሊቀላቀሉ ነው!!
ላለፉት 30 አመታት አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ተጠልለው በቁም እስር ላይ የቆዩት ሁለቱ ከፍተኛ የደርግ ባለስልጣናት ምህረት ተደርጎላቸው ከቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ ተወሰነ፡፡

በኤምባሲው ተጠልለው የሚገኙት የ85 አመቱ ሌተናል ኮለኔል ብርሃኑ ባየህና የ77 አመቱ ሌተናል ጄነራል አዲስ ተድላ ከቁም እስር ወጥተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ የሚያስችላቸውን የምህረት ውሳኔ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ መፈረማቸው ምንጮች ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል፡፡

ከ4 ዓመት በፊት ሁለቱ የቀድሞ ባለስልጣናት ከእስር እንዲለቀቁ በተለያየ አካላት ጥረት ሲደረግ የቆየ ሲሆን በሀገሪቱ ብሔራዊ መግባባትና እርቅ የሚፈጠርበትን ሁኔታ እንዲያመቻች የተቋቋመው የብሔራዊ እርቀ ሠላም ኮሚሽን፣ ከመንግስት ጋር በመነጋገር መንግስት እንዲለቀቁ ውሳኔ ማሳለፉን ምንጮች ጠቁመዋል።

ባለስልጣናቱ ከተጠለሉበት የጣሊያን ኤምባሲ የሚወጡት ሙሉ ምህረት ተደርጎላቸው ሲሆን ከሰሞኑ አስፈላጊውን ሂደት አጠናቀው ከቤተሰቦቻቸው ይቀላቀላሉ ተብሏል፡፡

ሌተናል ኮለኔል ብርሃኑ ለበርካታ ዓመታት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ ሲሆን የ77 አመቱ የእድሜ ባለፀጋው ሌተናል ጀነራል አዲስ ተድላ በበኩላቸው የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም እንደነበሩ ይታወቃል፡፡

27/11/2020

በማይካድራ ተጨማሪ የጅምላ መቃብሮች ተገኙ።

ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም በንጹኃን የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ዘርን መሠረት ያደረገ ጥቃት በማይካድራ ከተማ መፈፀሙ ይታወቃል። ይህን አስነዋሪ ተግባር የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቦታው በመገኘት ባደረገው ጥናት እና ይፋ ባደረገው መረጃ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 600 እንደሆነ ገልጾ ነበር።
ግድያውም ዘርን መሠረት ያደረገና በተለይም የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጅምላ ጭፍጨፋ መሆኑን ገልጿል። ይሁን እንጂ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 600 ነው ተብሎ የተገለጸው በማይካድራ ከተማ በየቤቱ ህይወታቸው አልፎ የተገኙ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ የተቀበሩትን ብቻ መሠረት ያደረገ ነው።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጥናት አድርጎ ከተመለሠ በኃላ ከማይካድራ ከተማ ወጣ ባሉ የገጠር አካባቢዎች በርካታ የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ጋዜጠኞች በቦታው በመገኘት አረጋግጠዋል።
በአንድ ቦታ 18 ሰው በጉድጓድ ውስጥ በጅምላ የተጣሉ ሲሆን በሌላ የገጠር አካባቢ ደግሞ 57 ሰዎች በጎርፍ ማፋሰሻ ቦይ ውስጥ በጅምላ ተገድለው እና ተጥለው ተገኝተዋል።
በዛሬው ዕለትም በማይካድራ ሌላ የገጠር ቀበሌ ውስጥ 17 ሰዎች በጅምላ ተገድለው በጉድጓድ ውስጥ ተጥለው ተገኝተዋል። አሁንም ሴንትራል፣ ደሮ እርባታ፣ በረኸት በሚባሉ አካባቢዎች ላይ አሠሳ እየተደረገ እንደሚገኝ እና ቁጥሩ እንደሚጨምር የማይካድራ ነዋሪዎች ገልጸውልናል።
በዚህ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተሳታፊ ናቸው የሚባሉት ተጠርጣሪዎች በብዛት ሱዳን ሐሻባ በሚባል የስደተኞች መጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ ይነገራል።
ከዚህ በተጨማሪ በማይካድራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ላይ ተሳታፊ ናቸው በሚል ተጠርጥረው ከተያዙት 60 ግለሠቦች ውስጥ 17ቱ በቀጥታ የወንጀሉ ተሳታፊ መሆናቸውን የማይካድራ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ገልጾልናል።
ትህነግ በወልቃይትና አካባቢው ተወላጆች ላይ በአስር ሽህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ገድሏል፤ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ደግሞ ከአካባቢያቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል፡፡

Photos from TOM TOM's post 18/11/2020

ይሄ ነገር 👂

ከሰማይ

63 ሚሊዮን 569 ሺህ 112 ብር የወረደለት በአንድ ቀን ከመቃብር ሳጥን ሰሪነት ወደ ሚሊዮነር የተቀየረው ይህ ኢንዶኔዥያ የ33 ዓመቱ ጆሽዋ

ይህ የምትመልከቱት ድንጋይ meteorite የተባለ በአሜሪካ ሳይንቲስቶች የሚፈለግ ስፔስ ውስጥ የሚገኝ ድንጋይ ሲሆን

ይህ ድንጋይ ስፔስ ውስጥ የሚገኝ ነገር ግን ይህን ለማግኘት እጅግ አዳጋጅ የሆነ ነው

የድንጋዩ እድሜው ከ4.4ቢሊዮን ዓመት በላይ ያለው ሲሆን

2.1 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ይህ ድንጋይ በዚህ በኢንዶኔዥያው ጇሸዋ በሚባል ወጣት ከቤቱ አቅራቢያ የመቃብር ሳጥን እየስራ እያለ ነበር ከሰማይ እጅግ ከባድ ድምፅ ባለው እንዲህ እንደምታዩት ቤቱን ሰርጉዶ የገባው

ጆሽዋ ምንድን ነው ብሎ መሬት ውስጥ ገብቶ የነበረውን ድንጋይ ቆፍሮ ሲያወጣው ድንጋዩ እጅግ በጣም የሚያቃጥል የነበረ ቢሆንም እስኪበርድ ጠብቆ አውጥቶታል

ይህን የሰሙት አሜሪካን ሳይንቲስቶች ለድንጋዩ 1.4 ሚሊዮር ዩሮ

ወደ ብር ሲመነዘር 63 ሚሊዮን 569 ሺህ 112 ብር

ለጆሽዋ አቅርበውላታ ጆሽዋም ይህን ድንጋይ ሽጦ በገንዘቡም ለአባቱ ና ለእናቱ ቤት ለመስራት እንዲሁም በስፍራው ለህብረተሰቡ ቤተክርስቲያን አሰራለው ብሏል::

ኢትዮጵያውያን አንድ አባባል አለን " አትሩጥ አጋንጥ " የሚባል እንግዲህ ይሄ ነው

ቸር ዋሉ 🙏❤️

ምንጭ :- Daily mail

17/11/2020

የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን የኒጀር አቻውን አሸነፈ።

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታድየም ያለተመልካቾች ለአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታውን ያካሄደው የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን የኒጀር አቻውን በ3 ለ 0 አሸንፏል።

ጎሎቹንም አማኑኤል ገ/ሚካኤል ፣ መስኡድ መሀመድ እና ጌታነህ ከበደ አስቆጥረዋል።

በዚህ ውጤት ምክንያትም በስድስት ነጥብ ከምድቡ ሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚያስቀምጣቸውን ውጤት አስመዝግበዋል።

በአቤል ጀቤሳ
ሕዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Address


Addis Ababa