የአሊይ መስጂድ ወጣቶች ጀምዓ/ Aliy mesjid youth association

የአሊይ መስጂድ ወጣቶች ጀምዓ/ Aliy mesjid youth association

Share

��� ሁሉም የሚፈልገውን ወጣትነታችንን ለአላህ እንዲሁም ለ?

05/08/2022

🖋🖋ታላቅ ኮርስ
✒️✒️በ ታላቅ ርዕስ......

🎙🎙 ኮርሱ የሚያውጠነጥነው መትኑል- አል ሃኢያ የሚለውን በኢብኑ አቢዳዉድ የተፃፈውን የአቂዳ ኪታብ ሲሆን ........
🍂በሸይኽ ተውፊቅ ራህመቶ

🌬🌬 ኑ... አብረን ቀርተን አብረን አቂዳችንን እንወቅ!!!!!🌬🌬

⚡️በ ኮርሱ. ........ የማይወላውለውን የ ሱና አቂዳ የምንቃኝበት, ከ አቂዳው ማህደር የምንማትርበት, ከ ጊዜው ፊትና መጠለያ ይሆነን ዘንድ ትክክለኛውን አቂዳ የምንገነዘብበት.......
🍂 ኮርስ የሚጀመርበት ቀን :-
ሐምሌ 30/2014
🧭 ቋሚ ኮርሱ የሚሰጥባቸው ቀናት :-
ቅዳሜ እና እሁድ
🕰ሰዓት :-ከ ቀኑ 8:00-10:00
📍አድራሻ :-ዓለምባንክ ስልጤ ሰፈር
አሊይ መስጂድ
ለሴቶችም በቂ ቦታ አለን.

19/04/2022

✍የጥርስ ቡሩሽ መጠቀም እና ሲፍቁ ደም መውጣት

❔ጥያቄ፡

💫የጥርስ ቡሩሽ ሲዋክ ስጠቀም ጥርሴ ይደማል፤ ይህ ደም ፆሜን ያፈርሳልን?

✅መልስ፡

⚡️የደሙ መውጣት ብቻ ፆምን አያፈርስም -ኢንሻኣላሁ ተዓላ-። ደም ወጥቶ ሆን ብለው እና መዋጡ እደሚያፈርስ እያወቁ ደሙን የዋጡት እደሆነ በዚህ ፆም ይፈርሳል። የደም መዋጥ ፆም ማፍረስ አለማፍረሱ እንዳለ ሁኖ መዋጡም የተከለከለ ነው ፤አይቻልም። ፆመኛ በቀኑ ክፍለ-ጊዜ የትኛውም ወቅት ላይ ማለትም የቀኑ ጅምር ላይ፣ከሰዓት በኋላም ይሁን ከዑሱር ቡኋላ ምሽት ላይ, ማምሻ ላይ መፋቂያ መጠቀም ይቻላል። ከሰዓት ቡኋላ አይቻልም ያሉ ሰወች አሉ፤ (ነገር ግን) ግልፅና በቂ የሆነ "ደሊል" /(ማስረጃ) የላቸውም። ቡርሽን በተመለከተ፡ፆመኛ የጥርስ ቡሩሽ ,የጥርስ ሳሙና ቢጠቀም በመሰረቱ ችግር የለውም ፤ሳሙናው እዳይዋጥበት ጥንቃቄ ከማድረግ ጋር ማለት ነው። ሆኖም በጥርስ ሳሙና ጥርስን መፋቁን ወደ ማታ ቢያዘገዩት የተሻለ ነው። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ግን እዳይዋጥ ጥንቃቄ ከማድረግ ጋር ቡሩሽን እስከነ ሳሙናው ቢጠቀሙ ችግር የለውም።

በሸይኽ አህመድ ሸይኽ አደም(حفظه الله)

Join us on telegram
https://t.me/ALIYMESJIDYOUTH

18/04/2022

✍ነስር ፆምን ያበላሻልን

❔ጥያቄ፡

💫ነስር ፆምን ያፈርሳልን?

✅መልስ፡

⚡️ነስር መውጣቱ ብቻ ፆምን አያፈርስም። ነስሩ በአፍንጫ በኩል ወደ አፍ ሄዶ ወደ ሆድ የወረደ እንደሆነ (እና) ይሄን አውቀው ካደረጉት ፆምን ያፈርሳል። ሳያውቁ ከሆነ ፆምን አያፈርስም። በአፍንጫ በኩል ቀጥታ ከሆነ የወጣው በዚህ ፆም አይፈርስም። በተቻለ ያክል ነስሩን መቆጣጠርና እንዳይወጣ ማድረግ ተገቢ ነው። መቆጣጠር ካልተቻለና በራሱ ጊዜ ከወጣ {َ لاُ يَكِّلُف الَّلُهَ نْفًساِ إَّلاُ وْسَعَها} ነው ፤ ከአቅማችን በላይ በሆነ ነገር አሏህ አይጠይቀንም ፤ ፆሙም በዚ አይበላሽም።

በሸይኽ አህመድ ሸይኽ አደም(حفظه الله)

Join us on telegram
https://t.me/ALIYMESJIDYOUTH

15/04/2022

✍አዛን ሳይሰሙ ፀሐይ በመጥለቋ ብቻ ማፍጠር

❔ጥያቄ፡

💫የምኖረው ጧኢፍ ነው ፤ መግሪብ አዛን የሚለው ለአንድ ሰዓት አምስት ጉዳይ ነው ፤ጓደኛዬ ቀደም ብሎ አዛን ሳይል ያፈጥራል። አይሆንም ስለው ፀሐይ ከጠለቀች ይቻላል ይላል። ይህ ትክክል ነውን?

✅መልስ፡

⚡️ማፍጠሩ በመሰረቱ ከአዛኑ ከራሱ ጋር የተያያዘ አይደለም። ፆምን መፍታት የተያያዘው ከፀሐይ መጥለቅ አለመጥለቅ ጋር ነው። እያንዳንዱ ሰው ፀሐይ መጥለቋን በራሱ ዐይን, በራሱ ማረጋገጥ ከቻለ አረጋግጦ ማፍጠር ይችላል። ይህን ማድረግ ለሁሉም ላይሳካ ይችላልና ታማኝ የሆነ፣ አዋቂ የሆነ ሙአዚን ካልለ በአዛኑ መሰረት ማፍጠር ይጠበቅብናል። ስለዚህ ጓደኛህ በትክክል የፀሐይን መጥለቅ የሚያረጋግጥበት መንገድ ካለው ፣ የሚያውቅ ከሆነ፣ ለዲኑ የሚጠነቀቅ ሰው ከሆነ፣ ፀሐይ መጥለቋን ካረጋገጠ ቢያፈጥር ችግር የለውም ፤በተለይ ሙአዚኑ ይዘገያል ካለ ወይም ሰዓታቸው ትክክል አይደለም ካለ። ነገርግን ይሄን የሚያደርገው በግዴለሽነት እና በድፍረት ከሆነ ተገቢ አይደለም ፤አዛን ጠብቃችሁ ማፍጠር ይገባችኋል።

በሸይኽ አህመድ ሸይኽ አደም(حفظه الله)

Join us on telegram
https://t.me/ALIYMESJIDYOUTH

14/04/2022

✍ጀናባ ላይ ሆኖ ፈጅር አዛን ቢል

❔ጥያቄ፡

💫ጀናባ ላይ ሆነን ፈጅር አዛን ቢል ፆማችን ይበላሻልን?

✅መልስ፡

⚡️ፆምን ለመጀመር ከጀናባም ይሁን ከወር አበባ ደም መታጠብ "ሸርጥ"/ (መስፈርት) አይደለም። አዛን ከማለቱ ከተወሰኑ ሴኮንዶች ደቂቃዎች በፊት ሐይዷ የቆመላት ሴት፤ አዛን ከማለቱ ከተወሰኑ ሴኮንዶች ደቂቃዎች ግኑኝነት አድርጎ ጀናባ የሆነ ሰው ልክ ፈጅር ሲገባ ፆምን ነይቶ ከዛ በኋላ ለሶላተል ፈጅር ታጥበው መስገድ ይችላሉ።
የነብዩ-ዐለይሂሶላቱ ወሰላም -ባለቤቶች "ነብዩ-صلى الله عليه وسلم - የረመዷን ሌሊቶች ላይ ጀናባ ሆነው ፆማቸውን ይጀምሩ ነበር"ብለዋል። ፆምን ከጀመሩ በኋላ ጀናባ መሆኑ ነው ፆሙን ሊያፈርስ የሚችለው። ፆም ከጀመሩ በኋላም ፆምን የሚያፈርሰው ጀናባ በራስ ፍላጎት ከሆነ ነው እንጂ በተኙበት የዘር ፈሳሽ ቢወጣ ፆም አይፈርስም።

በሸይኽ አህመድ ሸይኽ አደም(حفظه الله)

Join us on telegram
https://t.me/ALIYMESJIDYOUTH

12/04/2022

✍ዊትር ላይ ቁኑትን ሁልጊዜ ማድረግና እጅን አንስቶ አሚን ማለት

❔ጥያቄ፡

💫ቁኑት ላይ ኢማሙ ዱዓእ ሲያደረግ እጅን ዘርግቶ፣ ድምጽን ከፍ አድርጎ አሚን ማለት በሸሪዓ እንዴት ይታያል?

✅መልስ፡

⚡️ዊትር ላይ ቁኑት ማድረግ ከረመዷን ውጪም ይሁን ረመዷን ላይ ይቻላል። ነገር ግን ሁሌ እያንዳንዱ ዊትር ላይ ባይደረግ የተሻለ ነው፤ አንዳንዴ ማድረግ አንዳንዴ መተው የተሻለ ነው። እንደዚሁ ደግሞ የቁኑቱን ዱዓ እአንዳንዴ ከሩኩዕ በፊት ሌላ ጊዜ ከሩኩዕ በኋላ ማድረጉም የተሻለ ነው። ለምንድ ነው አንዳንዴ ማድረግ፤ አንዳንዴ መተው ተገቢ ነው ,የተሻለ ነው? ያልነው ነቢዩ -ዐለይሂሶላቱ ወሰላም- በዚህ መልኩ ያደርጉ እንደነበረ አልተነገረም። ለልጃቸው ልጅ ለሐሰን የቁኑትን ዱዓ አስተምረዋል፤ የቁኑትን ዱዓእ ማስተማራቸው ቁኑት እንደሚደረግ እንደሚቻል "ደሊል"/ (ማስረጃ) ነው። ሁሌ ያደርጉ እንደነበረ አለመነገሩ ደግሞ አንዳንዴ መትተው እንዳለበት ያሳያል። መእሙሞች (ተከታዮች) ከኢማሙ ኋላ ሆነው በመካከለኛ ድምጽ አሚን ማለት ይችላሉ። እጅን ማንሳት በተመለከተ በዲን ሊቃውንት መኃል "ኺላፍ" /(ልዩነት) ያለበት ሲሆን "ራጂሑ" /(ከማስረጃ አንፃር ሚዛን የሚደፋው አስተያየት) እጅን ማንሳት ይቻላል፤ በርካታ ሶሓቦች ይሄን ስላደረጉ (ማለት ነው)። ዑመር ኢብኑል ኸጧብ, ዑሥማን, አቡሁረይራ እንዳደረጉ ተነግሯል። የቁኑት ዱዓእ ላይ እጅ ይነሳል፤ ነገር ግን እጅ በሚነሳበት ጊዜ እስከ ደረታችን አከባቢ መሆን አለበት። በጣም ከፍማለት የለበትም ፤በጣምም ዝቅ ማለት የለበትም። እንደዚሁም ደግሞ መዳፎቻችን እርስ በርሳቸው ተገጣጥመው መሆን አለበት።

በሸይኽ አህመድ ሸይኽ አደም(حفظه الله)

Join us on telegram
https://t.me/ALIYMESJIDYOUTH

11/04/2022

✍ቢድዓ የሚሰራበት መስጂድ ተራዊሕን መስገድ

❔ጥያቄ፡

💫ወንድሜ የሚኖርበት ሃገር መስጂድ ተራዊሕ ሲሰገድ በየአራት ረከዓው እጃቸውን እያነሱ ዱዓ ያደርጋሉ፤ ብዙ ቢድዓዎች ይስሰራሉ። ከዚህ መስጂድ ሄዶ መስገዱ እንዴት ይታያል?ወይስ ቤቱ ነው መስገድ ያለበት?

✅መልስ፡

⚡️ቢድዓቸው የሚያከፍር ቢድዓ እስካልሆነ ድረስ፤ እዚህ ጋር የተነገረው ዐይነት ከሶላቱ በኋላ የሚያደርጉት ዐይነት ቢድዓ እስከሆነ ድረስ፤ ሄዶ ከእነሱ ጋር ቢሰግድ ችግር የለውም። በተለይ መሄዱ ጥቅም ካለው ፣እነሱን የሚመክራቸው ከሆነ፣ ሱንናን የሚያስተምራቸው ከሆነ መሄዱም የተሻለ ነው። የረሱልን (-صلى الله عليه وسلم -) መንገድ ሱናን የሚያውቅ ሰው እንዲህ ዐይነት ቦታዎች ላይ ሄዶ ሊያስተምር፣ በእርጋታ ከምክንያት ጋር, ከ"ደሊል"/(ማስረጃ) ጋር ይሄን ስሕተት ሊያወግዝ እና ሠዎችን ሊመክር ይገባዋል። ይቀበሉኛል የሚልተስፋ እስካለው ድረስ ምንም ሳይሰላች ሁሌም ሊመክራቸው ይገባል።ነገርግንለረዥም ጊዜ መክሮ ማይቀበሉት ከሆነ፤ ሄዶ በመስገዱ እነሱ በሚስሩት ቢድዓ ቀልቡ ተረብሾ ምንም ዐይነት የሶላት ጣዕም የማያገኝ ከሆነ፤ ተራዊሕ ለብቻም መስገድ ይቻላልና ቤት ቢስግድ ይቻላል። ነገር ግን ሱንናው ተራዊሕን ከሙስሊሞች ጋር መስጂድ ሄዶ በጀመዓ እና በጋራ መስገድ ነው። ይህን እንዲያደርግ የሚከለክለው ነገር ካለ ቤት ቢስግድ ችግር አይኖረውም። "ፈርዱን"/(ግዴታውን) ሶላት እንኳ ቢድዓ ከሚሰራ ሰው ጋር ቢድዓው ካላከፈረ መስገድ ይቻላል፤ ሱንና ሲሆን ነገሩ ይበልጥ ይቀላል። ለእንደዚህ ዐይነት ምክንያቶች እያሉ "ፈርዱንም" ሶላት ጭምር ጀመዓ መስገድ እየተዉ ከመስጅድ የሚርቁ ሰዎች አሉ፤ ሶላትን የሚያዘገዩ ሰዎች አሉ፤ ተራዊሕም ላይ ቢሆን ከእንዲህ አይነት ሰው (ጋር) አልስግድም ብሎ ቤት የሚተኛ ሰው አለ፤ ቢድዓው ከሶላቱ ከራሱ ጋር እስካልተያያዘ ድረስ ሄደን ከእነርሱ ጋር መስገዱ የተሻለ ነው። መክረህ የማይቀበሉ ከሆነ፣ ተስፋ ከሌለ፣ በመሄድህ የምትረበሽ ከሆነ ቤትህ ለብቻህ የቻልከውን ያክል መስገድ ትችላለህ።

በሸይኽ አህመድ ሸይኽ አደም(حفظه الله)

Join us on telegram
https://t.me/ALIYMESJIDYOUTH

10/04/2022

✍ተራዊሕን ከኢማም ጋር ሲሰግዱ ፋቲሓ መቅራት

❔ጥያቄ፡

💫ተራዊሕ ሶላት ከኢማም ጋር ስንሰግድ ፋቲሓን ከሱ ጋር ነው የምንቀራው ወይስ ኢማሙ ከጨረሰ በኋላ ነው የምንቀራው? ቢያብራሩልኝ?

✅መልስ፡

⚡️ይሄ ከጥንት ጀምሮ እስካለንበት ጊዜ ድረስ በፊቅህ ዑለሞች መኃል "ኺላፍ"/(ልዩነት) ያለበት ጉዳይ ነው። የተወሰኑት የኢማሙ ድምጽ ከተሰማ የኢማሙን ማድመጥ ነው ግደታ የሚሆነው መቅራት አይቻልም ብለዋል። የተወሰኑት ምን ጊዜም "ኢማምም" (አሰጋጅም) ,"መእሙምም"/(ተከታይም), ብቻውን የሚቀራ ሰው ፋቲሓን መቅራት አለበት ብለዋል። ሌሎቹ የቀን ሶላቶች ላይ የኢማሙ ድምጽ የማይሰማባቸዉ ረከዓወች ላይ ይቀራል፤ የኢማሙ (ድምፅ) የሚሰማባቸው ላይ አይቀራም ብለዋል። (ከዚህም ውጭ ያሉ ሌላ አባባሎች ተብለዋል..) (ከማስረጃ አንፃር ቅርብ የሚሆነው አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው) የኢማሙ ድምጽ የሚሰማ ከሆነ አይቀራም ፤ ዝም ተብሎ ነዉ የሚሰማው። ኢማሙ ሲቀራ የማይሰማበት ሁኔታ ካለ ይቀራል። ከኺላፍ ለመውጣትና አስተያየቶችን ለማቀራረብ ኢማሙ ዝም የሚልበት አጋጣሚ ካለ በነዚህ ክፍተቶች (ላይ) ፋቲሓን ቢቀሩ የተሻለ ነው። ዝም የማይል ከሆነ ኢማሙ የቀራው ለመእሙሙም ጭምር ይሆናል። ይሄን የሚያሳዩ በርካታ "ደሊሎች"/ (ማስረጃዎች)አሉ። ኢማሙ አሽሸዕቢ -ረሒመሁሏሁ ተዓላ- ሰባ የሚደርሱ የበድር ዘመቻን ከነብዩ(-صلى الله عليه وسلم -) ጋር የተሳተፉ ሶሓቦች ከኢማሙ ኃላ መቅራትን ሲከለክሉ አይቻለሁ ወይም ሰምቻለሁ ብለዋል። ያለፋቲሓ ሶላት የለም የተባለው ኢማም ከሆኑ ወይም ለብቻ ሲሰግዱ ነው። ኢማም ያለው ሰው የኢማሙ ቂረአት ለሱም ቂረአት ይሆናል የሚል ኢብኑ ማጀህ የዘገቡትም "አሰር"/(ፋና) አለ። ኢብኑ ተይሚያ -ረሒመሁሏሁ ተዓላ- ኢማሙም ከቀራ መእሙምም ከቀራ የኢማሙ ጮክ ብሎ መቅራት ፋይዳው ምንድን ነው? ሸሪዓ ከእንዲህ አይነት ህግ የጠራ ነው፤ ወይም ሊጠራ ይገባዋል ብለዋል። በተለይ ተራዊሕ ላይ በተደጋጋሚ ፋቲሓዎች የሚሰሙበት ከመሆኑ አንፃር መጨናነቅን ወይም መረበሽን ሊያስከትል ይችላል፤ ፋቲሓን ጨርሰው ኢማሙን ለመስማት እየተጨናነቁ እየተሽቀዳደሙ ማለት ነው። ስለዚህ ዝም ብሎ ማድመጡ የተሻለ ነው። (እውቀቱ ያለው አላህ ዘንድ ነው።)
⚡️ከዚሁ ተያይዞ ስለ "ኢስቲፍታሕ" የሚጠይቁ ሰዎች አሉ። በእያንዳንዱ ረከዓ(ላይ) "እስቲፍታሕ" ማድረግ አለብን ወይስ የለብንም ይላሉ፤ ተራዊሕም ይሁን ከተራዊሕ ውጭ ያሉ ሶላቶች (ላይ) ኢማሙ ጮክ ብሎ መቅራት ከጀመረ እስቲፍታሕ አይደረግም። ኢማሙ ፋቲሓን ከመጀመሩ በፊት ከሆነ መእሙም "ኢስቲፍታሕ ቢቀራ ሱንና ይሆንለታል። ነገር ግን ኢማሙ ዋጂብ የሆነውን ፋቲሓን እየቀራ ከኋላ "ኢስቲፍታሕን" መቅራት ተገቢ አይደለም።

በሸይኽ አህመድ ሸይኽ አደም(حفظه الله)

Join us:-
on Facebook
http://fb.com/AliyMesjidYouth/
And telegram
https://t.me/ALIYMESJIDYOUTH

09/04/2022

✍የተራዊሕ ሶላትን ፋቲሓን ብቻ በመቅራት መስገድ

❔ጥያቄ፡

💫በረመዷን ተራዊሕ መስገድ ፈልጌ ነበረ፤ ብዙ ቁርአን አላውቅም ፤የማውቀውን የቁርአን አያህ ብቻ እየደጋገምኩኝ እየቀራሁ መስገድ እችላለሁ ወይ? ወይስ ረዣዥም ሱራዎችን መቅራት ግዴታ ነው?

✅መልስ፡

⚡️ማንኛውም ሶላት ላይ በመሰረቱ ከፋቲሓ ውጪ መቅራቱ ግደታ የሚሆን ሱራ የለም። ሁሉም ሶላት ላይ ፋቲሓን ብቻ ቀርቶ ሩኩዕ ማድረግ ይቻላል። ነገርግን ከፋቲሓ ዉጪ ሌላ ሱራ መቅራት እየቻሉ ሁሌ በቋሚነት ፋቲሓን ብቻ እየቀሩ ሩኩዕ ማድረጉ የተጠላ ነው ፤ከነብዩ-ዐለይሂሶላቱ ወሰላም -ሱንና ጋር ስለማይሄድ (ማለትነው)። ውስን ሱራዎችን እንጂ ያልሓፈዘ ሰው እነዚህ የሚያውቃቸው ሱራዎችን ሁሉም ረከዓዎች ላይ ቢደጋግም ምንም ችግር የለውም።

በሸይኽ አህመድ ሸይኽ አደም(حفظه الله)

Join us:-
on telegram
https://t.me/ALIYMESJIDYOUTH

የአሊይ መስጂድ ወጣቶች ጀምዓ/ Aliy mesjid youth association Send a message to learn more

07/04/2022

✍ተራዊሕ እና ተሀጁድ በአንድ ሌሊት መስገድ

❔ጥያቄ፡

💫በአንድ ሌሊት ተራዊሕ እና ተሃጁድ መስገድ ቢድዓ ነው ፤ በአንድ ሌሊት ሁለት ጊዜ ሶላት የለም ይላሉ፤ ይህ እንዴት ይታያል?

✅መልስ፡

⚡️በመሰረቱ በዲኑ የተፈቀደ ነቢዩ (-صلى الله عليه وسلم -) ያደረጉትን ነገር ቢድዓ ነው አንልም። ነብዩ -ዐለይሂሶላቱ ወሰላም -ተራዊሕ ሰግደዋል፣ ሶሓቦቻቸው ተራዊሕ ሰግደዋል፣ ሱሑር ያመልጠናል ብለው እስኪሰጉ ድረስ በረዥሙ ይስግዱ ነበር፤ እንደዚሁ ደግሞ ሶሓቦች ተራዊሕን ሲሰግዱ መኃል ላይ ያርፉ ነበር። አንዳንድ ዘገባዎች ላይ እንዳለው ዑመር -ረዲየሏሁ ዐንሁ ወአርዷህ- በሳቸው ዘመን ተራዊሕ እየተሰገደ መኃል ላይ ሰዎች እንዲያርፉ ያደርጉ ነበር። የእረፍቱን ጊዜ ሲገልፁ አንድ ሰው "ሰልዕ" የሚባለው ጋራ ጋር ሄዶ መመለስ የሚችልበትን ያክል ጊዜ ያሳርፉን ነበረ ብለዋል። ከነብዩ (-صلى الله عليه وسلم -) መስጅድ 500 ሜትር አካባቢ ርቀት ያለው ቦታ ነው። የግድ ተራዊሑን አንድ ላይ ጨርሰሀው ወደ ቤትህ መግባት አለብህ አይባልም። የተወሰነ ሰግደው ከዛ በኋላ መስጂድ የተወሰነ ቢያርፉ፤ አልያ ደግሞ ቤት ሄደው አርፈው ቢመለሱ ከዛ በኋላ ሶላታቸውን ቢቀጥሉ ችግር የለውም። በተለይ "ሶላተ-ተራዊሕ"/(የተራዊሕ ሶላት) እራሱን የቻለ የቁጥር ገደብ የለውም ብለናል። አንድ 8 ረከዓ ሰግደው ከዛ የተወሰነ አርፈው መልሰው ስምንትም ይሁን አራት ረከዓ ቢሰግዱ የሚከለክል ነገር የለም ። የመካ ሰዎች በተራዊሕ መኃል ጠዋፍ አድርገው የሚመለሱበት አጋጣሚ ነበር። ስለዚህ ኢማሙ አሕመድ -ረሒመሁሏሁ ተዓላ- ስለ "ተዕቂብ"፡ ተራዊሕ ካለቀ በኋላ ሌላ ሱንና ሶላት ስለመስገድ ሲጠየቁ ችግር የለውም ብለው አነስ-ረዲየሏሁ ዐንሁ ወአርዷህ |ما يرجعون إلالخير يرجونه، أو لشر يحذرونه|- ብለዋል ብለው የአነስን ንግግር አቅርበዋል። ሰግደው አርፈው ከዛ በኋላ ተመልሰው ቢሰግዱ ምንም ችግር የለውም። ተመልሰው መጥተው የሚሰግዱት "ኸይር" (መልካም ነገር) ፈልገው ,ተስፋ የሚያደርጉትን "ኸይር" ለማግኘት ብለው ,ጀነትን ,ሌሎችም "ኸይር" ነገሮችን (ለማግኘት) ፤የሚፈሩትን ነገር ለመተው እንጂ ለሌላ አይደለም ብለዋል። ከ"ኸይር" ወደ "ኸይር" መመለስ ምንም ችግር የለውም።

በሸይኽ አህመድ ሸይኽ አደም(حفظه الله)

Join us:-
on Facebook
http://fb.com/AliyMesjidYouth/
And telegram
https://t.me/ALIYMESJIDYOUTH

07/04/2022

✍የተራዊሕ ሶላት የረከዓ ብዛት

❔ጥያቄ፡

💫የተራዊሕ ንሶላት ግማሹ 20 ረከዓ ነው ፤ ግማሹ 8 ረከዓ ነው እያሉ በየዓመቱ ጭቅጭ ቅ እና ፀብ ይነሳል። 20 ረከዓ መስገድ ቢድዓ ነው, ሓራም ነውም ይላሉ፤ ይህ እንዴት ይታያል?

✅መልስ፡

⚡️በመጀመሪያ ደረጃ ንትርክ እና ጭቅጭቅ, ክርክር በዲኑ የተወገዙ ናቸው። ክርክር ያበዛ ሰው ዲኑ ላይ ፅናት አይኖረውም። ነቢዩ -ዐለይሂሶላቱ ወሰላም - [ሓቀኛ እንኳን ብሆን፤ ሐቁ እንኳን ያለው እሱጋር ቢሆን መከራከርን የተወ ሰው ጀነት እንደሚገባ እኔ ኃላፊ እሆነዋለው ]ብለዋል ነቢዩ -ዐለይሂሶላቱ ወሰላም። ሓቅን ተናግሮ ማለፍ እንጂ መከራከር አያስፈልግም, መጨቃጨቅ አያስፈልግም። እንደዚሁ ደግሞ "ኺላፍ" ያለበት, የሓሳብ ልዩነት ሊከሰት የሚችልበት ነጥብ ላይ እዚህ ደረጃ የደረሰ ፀብን ሊያስከትል የሚችል "ኺላፍ" ውስጥ መግባት አያስፈልግም። "ኺላፍ" መብዛቱ የቀልብን መራራቅ ያስከትላል። የፊቅህ ጉዳይ ላይ "መኻለፍ"/(መለያየት) ከሶሓቦች ዘመን ጀምሮ ያለ ነው። "ኢነማ" የሚወገዘው በሶሓቦች ዘመን ያልነበረው የዐቂዳ "ኺላፍ" ነው ያልነበረው። ዉዱእ የሚያፈርሱ ነገሮችን በተመለከተ፣ አንዳንድ መብላት የሚቻል እና የማይቻል ነገሮችን በተመለከተ፣ ፊቅህ ነክ ነጥቦች ላይ ከጥንት ጀምሮ "ኺላፍ" አለ። ልባችን ሰፊ ሊሆን፣ የሌላኛውን ወገን ማስረጃ ልናደምጥ ፣ልንረጋጋ ዓላማችን ለሰዎች ሓቅን ማሳወቅ ሊሆን ይገባናል። የተራዊሕ ሶላትን ቁጥር በተመለከተ ሰዎች ለሁለት ተከፍለዋል, በተለይ አላዋቂዎች። የተወሰኑት ከ11 ረከዓ በላይ መጨመር ስሕተት ነው ,ወንጀል ነው , ቢድዓ ነው ያሉበት ሁኔታ አለ። ሌሎች ደግሞ 11 ብቻ መስገድን ያወገዙበት አጋጣሚ አለ፤ ሁለቱም ስሕተትነው። ጥያቄው ላይከ 11 በላይ መጨመር ቢድዓ ነው, ሓራምም ነው ሁሉ እያሉ ነው የሚል ቃል አለ፤ እንዴት ተብሎ ነው 11 ላይመጨመር ሓራም የሚሆነው? ቢድዓ የሚሆነው? ነቢዩ-ዐለይሂሶላቱ ወሰላም -ስለ "ሶላተ-ለይል"/(የሌሊትሶላት) ሲጠየቁ [የሌሊት ሶላት ሁለት ሁለት ረከዓ ነው፤ ይነጋብኛል ብሎ የፈራና የሰጋ ሰው አንድ ረከዓ ይጨምር ዊትር ይሆንለታል።] ብለው ሳለ። ጠያቂው የለይል ሶላትን አሰጋገድ ብዛቱንም ጭምር ነው የጠየቃቸው። ነቢዩ (-صلى الله عليه وسلم) ይህን ያክል ሰግደህ አቁም አላሉትም፤ የሌሊት ሶላት ሁለትሁለትረከዓነው ያሉት፤ጥጉን አልነገሩትም። በዚህ መሰረት ከፈለጉ 20ረከዓ, ከፈለጉ 40ረከዓ, ከፈለጉ 80 እና 100 ረከዓም ቢሆን መስገድ እንደሚቻል ነው ሓዲሱ የሚያሳየው፤ የሌሊት ሶላት ገደብ የለውም። በመሆኑም ነገሩን ልናጠበው, ልናጠብቅ አይገባም። ከደጋግ ቀደምቶች ውስጥ እጅግ በጣም በርካታ የዲን መሪዎች ከ11 በላይ መጨመር እንደሚቻል ተናግረዋል። ከ11በላይ ሰግደዋል; አሰግደዋል። ከ11 በላይ መስገድ አይቻልም እያሉ10 ከተሰገደ በኃላ ጥለው የሚወጡ ወይም እዛው ቁጭ ብለው ሶፍፉ ክፍት እንዲሆን የሚያደርጉ ወይም ወደ ኋላ ሄደው ወሬ እያወሩ ሰውን የሚረብሹ ሰዎች ትልቅ ስሕተት ላይ ወድቀዋል። እንደዚሁም ደግሞ ትልቅ አጅርም አልፏቸዋል። ኢማሙ ሶላቱን እስኪጨርስ አብሮ የሰገደ ሌሊቱን በሙሉ ሲሰግድ እንዳደረ ይቆጠርለታል በሚለው በነቢዩ (-صلى الله عليه وسلم -) ሓዲስ የተነገረው ትሩፋት ይቀርባችዋል። እንደዝሁ ደግሞ ከ11 በላይ መጨመርም አይቻልም ብለው በማመናቸው ፤ይህ ቢድዓ ነው በማለታቸው ስሕተተኛም ይሆናሉ። ይህ እንዳለ ሆኖ 11 ብቻ የሚሰግዱ ሰዎችንም የሚያወግዙ አሉ፤ ይሄም ስሕተት ነው። ነቢዩ-ዐለይሂሶላቱ ወሰላም - ዓኢሻ (-ረዲየሏሁዐንሃ-) እነደተናገሩት፦ "ረመዷንም ይሁን ከረመዷንውጪ 11 ረከዓ ነበር የሚሰግዱት"። 11 መስገድ ይቻላል፤ ሱንናም ነው። ከ11 መጨመርም ይቻላል፤ ሁለቱም ትክክል ነው። እንዴት ነቢዩ-ዐለይሂሶላቱ ወሰላም -ከ11 በላይ ሰግደው የማያውቁ ከመሆኑም ጋር ሁለቱም ይቻላል ይባላል? (ከተባለ) ነቢዩ-ዐለይሂሶላቱ ወሰላም -ቂያሙን፣ ሩኩዑን፣ ሱጁዱን እያረዘሙ ነበር የሚሰግዱት። እንደነብዩ (-صلى الله عليه وسلم -) አርዝሞ መስገድ የቻለ ሰው "መእሙሞቹ"/(ከኋላ የሚሰግዱት ተከታዮቹ) ፍቃደኛ ከሆኑ11 መስገዱ በላጭ ነው ይባላል። ነገርግን ይሄን ማድረግ ለመእሙሞች የሚከብዳቸው ከሆነ አጠር አድርገው እየቀሩ ብዙ ረከዓ ቢሰግዱ ምንም ችግር የለውም። ነብዩ (-صلى الله عليه وسلم -) በተግባራቸው 11 ቢሰግዱም በንግግራቸው የሌሊት ሶላት ሁለት ሁለት ረከዓ ነው ብለዋል አልገደቡትም። 11 መስገዳችው ከ11 በላይ መስገድ እንደማይቻል የሚያሳይ "ደሊል"/(ማስረጃ) አይደለም። የነብዩ(-صلى الله عليه وسلم -) ንግግር እና ተግባራቸው ከተጋጨ የሚቀደመው ንግግራቸው ነው። የሌሊት ሶላት ሁለት ሁለት ረከዓ ነው ብለዋል፤ እዚህ ጋር ደግሞ ተጋጨ የሚያስብል ደረጃም የደረሰ አይደለም። ሓዲሱን ደጋግ ቀደምቶች, ዑለሞች በተረዱት መልኩ ነው ልንረዳት የሚገባው። 11 ብቻ መስገዳቸው ከዚያ በላይ መስገድ እንደማይቻል የሚያሳይ ነው ብለው አልተረዱትም ደጋግ ቀደምቶች። ከሓነፍዮች፣ ከሻፍዕዮች፣ ከማሊኪዮች፣ ከሓንበልዮች ከአራቱም የዲን መሪዎች ታላላቅ የዲን ሊቃውንት ከ11 በላይ መስገድ እንደሚቻል ገልፀዋል። ሓነፍዮች ስለ ተራዊሕ ሲናገሩ |'فإنهاعشرون ركعة سواى الوتر عندنا'|ብለዋል|" ተራዊሕ እኛ ዘንድ ከዊትሩ ውጪ 20 ረከዓ ነው የሚሰገደው "ብለዋል። ኢማሙ -ነወዊም በሻፍዕያ መዘሃብ ዘንድ ተራዊሕ 20 ረከዓ እንደሆነ ተናግረዋል። ከሓንበልዮችም እብኑ ቁዳማም እንደዚሁ ኢማሙ አሕመድ የመረጡት ሶላቱ-ተራዊሕ 21ረከዓ እንደሚሰገድ ነው ብለዋል። ኢማሙ ማሊክ ረሒመሁሙሏሁ ተዓላ 36 መስገድ እንደሚቻል ተናግረዋል፤ማሊኪዮችም ይሄንያደረጉነበር። ስለዚህ ሶላተ-ተራዊሕ በመሰረቱ ሱንና ነው። ቁጥሩን በተመለከተ ገደብ የለውም። አራቱም መዘሃቦች ከ11 ረከዓ በላይ መስገድ እንደሚቻል ተናግረዋል። ደጋግ ቀደምቶች ከ11 በላይ ሰግደዋል፤ የረሱልን (-صلى الله عليه وسلم -) ሓዲስ ሓሳባቸውን ከኛ በላይ እነሱ ናቸው የሚያውቁት። በመሆኑም ከ11 በላይ መስገድ ቢደዓ ነው ፤ ከ20 መቀነስ ቢደዓ ነው ,ስህተት ነው ልንል አይገባም። ሁሉም ያስኬዳል፤ ዋናው ነገር በሱንናው መሰረት ሌላ ነገር ሳይጨምሩ መስገድ ነው።
አላህ ይበልጥ ኣዋቂ ነው!!!

በሸይኽ አህመድ ሸይኽ አደም(حفظه الله)

https://t.me/ALIYMESJIDYOUTH

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Addis Ababa