የብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን

የብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን

Share

ጠንካራ ኢንስፔክሽን ፤ ለጠንካራ ፓርቲ!

Photos from Southwest Ethiopia People's Region Prosperity Party Branch Office's post 17/02/2026

Photos from የብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን's post 16/02/2026

ሰኞ፣ የካቲት ፣ 09፣ 2018(ኢሥኮዋጽ) - የየካቲት ወር 2ኛ ሳምንት የኮሚሽኑ ዓበይት ክንውኖች፦

1. ኮሚሽን ዋና ጽ/ቤት- ​“ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታ” በሚል መሪ ቃል የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት፤ ለዞን፣ ለከተማ፣ ለልዩ ወረዳና ለወረዳዎች የኮሚሽኑ አባላት ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ የስልጠና መድረክ ላይ የብልጽግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ጸሀፊና የጽ/ቤት ኃላፊ ተገኝተው ስልጠና በመስጠት ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን እርሳቸዉም በስልጠናው ላይ እንዳሳሰቡት የፓርቲው መዋቅር ካለው ግዝፈት አኳያ በሁሉም እርከኖች ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

2. ኦሮሚያ ክልል የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- የክልሉ ኮሚሽን በክልሉ ለሚገኙ የብልፅግና ህብረቶች በፓርቲዉ መተዳደሪያ ደንብና መመሪያዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል። በተጨማሪ ለተለያዩ ዞኖችና እና ከተማ አስተዳደሮች፣ ለወረዳ የኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አመራሮች እና ለብልፅግና ህብረት አመራሮች የጸረ-ሙስና ትግልና የፓርቲ አባላትና አካላት ሚና ፣የአባላት ምልመላ፣ ግንባታና ስንብት የአፈጻጸም መመሪያ እንዲሁም በስትራቴጂክ ዕቅዱ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

3. ጋምቤላ ክልል የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- የክልሉ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በጥር ወር የ2018 ሁለተኛ ሩብ ዓመት በሦስት ዞኖች፣ በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር እና በክልል ሴ/መ/ቤቶች ያካሄደውን የሱፐርቪዥንና የኢንስፔክሽን ሪፖርት ገመገመ፡፡ በመድረኩም በኢንስፔክሽን የተገኙ ግኝቶችን በጥንካሬና በድክመት የተለዩትን ለፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ግብረ መልስ እንዲሰጥ አቅጣጫ ተቀምጧል። በተጨማሪ የክልሉ ኮሚሽን ሥራ አመራር ኮሚቴ አባላት ለምዘና መነሻ እንዲሆን በተዘጋጀው የስድስት ወራት አፈፃፀም ሰነድ መሰረት አካላዊ ግምገማ አድርገዋል።

4. ቤን-ጉሙዝ ክልል የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- የክልሉ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት፤ ለዞን፣ ለከተማ፣ ለልዩ ወረዳና ለወረዳዎች የኮሚሽኑ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል። በዚህ ​“ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታ” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው የስልጠና መድረክ ላይ የብልጽግና የምክር ቤት አባልና የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ባስተላለፉት መልዕክት "የኮሚሽኑ አደረጃጀት መጠናከር ለፓርቲው ጥንካሬና ለሀገር ግንባታ ወሳኝ ነው" ብለዋል። የብልጽግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ፀሐፊና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ በስልጠናው ላይ ተገኝተው ስልጠናውን በመስጠት ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በተጨማሪ "ዉጤታማ ምርጫ ለተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል 7ተኛ ሀገራዊ ምርጫ በሚመለከት በየወረዳዉ ላሉት የኮሚሽን አመራርና አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ተፈጥሯል። በየደረጃዉ ያሉት የኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የአንደኛ መንፈቅ ዓመት ምዘና አካሂደዋል።

5. ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- የክልሉ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የ1ኛ መንፈቅ ዓመት የሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽን ሪፖርቱን ገምግሟል። በሪፖርቱ በየደረጃዉ የፓርቲውን ራዕይ ለማሳካት በመንፈቅ ዓመቱ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርበዉ ዉይይት ተካሂዶባቸዋል። በግምገማ መድረኩ ላይ የክልሉ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ በቀጣይ ዉጤታማ ተቋማትን በመለየት ተሞክሮዎችን መቀመርና ማስፋት፣ በአመራርና አባላት የዲሲፕሊን መመሪያ መሠረት ክፍተት የተስተዋለባቸዉን የማረምና ተጠያቂ የማድረግ ስራ እንደሚሰራም አመላክተዋል።

6. አማራ ክልል የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- የክልሉ የብልጽግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን በአስራ አራት ዞንና ከተማ አስተዳደር ኮሚሽን ለሚገኙ ለወረዳ እና ለህብረት አመራሮች፣ የኮሚሽን አባላት እንዲሁም በወረዳዎች ለቀበሌ እና ለህብረት አመራሮችና አባላት በኮሚሽን መመሪያዎች ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልጿል።

7. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- የክልሉ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ቁጥራቸው 280 ለሚደርሱ ለክልል፣ ለዞን፣ ለልዩ ወረዳዎችና ከተማ አስ/ር የኮሚሽን አመራሮችና አባላት በቡታጅራ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ። በዚህ ለሁለት ቀናት በተካሄደው ስልጠና ማጠቃለያ ላይ የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ ባስተላለፉት መልዕክት ከሠልጣኞች በየደረጃ ያለውን ከተግባር አፈጻጸም ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ጉድለቶችን አድምጠው ፓርቲው በቀጣይ መደገፍ በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳብ ተቀብለው የኮሚሽኑን የ3 ''መ'' ህጎችን የማመን ፣የመደገፍና የመተግበር የኮሚሽኑ የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም በሚያጎለብት መልኩ ትርጉም ያለውን አቅጣጫ አስቀምጠዋል።


8. አፋር ክልል የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- የክልሉ ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት የአንደኛ መንፈቅ ዓመት ምዘና ማካሄድ ጀምሯል። ምዘናዉ በየደረጃዉ ባሉት የኮሚሽን መዋቅሮች ወጥነት ባለዉ መልኩ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

9. ድሬደዋ አስተዳደር የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- በአስተዳደሩ ኮሚሽን በህብረት ደረጃ ለሚገኙ የኮሚሽን አባላት በመመሪያዎች ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

Photos from Benishangul Gumuz  Prosperity Party-ብልጽግና's post 13/02/2026

Photos from የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን-Commssion's post 13/02/2026

Photos from South Ethiopia Region Prosperity Party - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ's post 12/02/2026

Photos from አዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ቅ/ጽ/ቤት's post 12/02/2026

Photos from Central Ethiopia Region - Prosperity Party - ብልፅግና's post 12/02/2026

12/02/2026

የሳምንቱ ዓቢይ መልዕክት
===============
የብልፅግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ተልዕኮ፤
===============
የኮሚሽኑን ተቋማዊ አቅም በማጠናከር፣ ውጤታማ ኢንስፔክሽንና ሱፐርቪዥን በማድረግ፤ የፓርቲውን የፖለቲካ ጥራት፣ የሥነ-ምግባር ጤናማነት፣ የአባላት መብት መከበሩን እና የፓርቲ ሀብት አስተዳደር ውጤታማነት በማረጋገጥ ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታ የላቀ አስተዋጽኦ ማድረግ ነው፡፡

ጠንካራ_ኢንስፔክሽን_ለጠንካራ_ፓርቲ!

Photos from በጋምቤላ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት's post 11/02/2026
Photos from የብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን's post 09/02/2026

ሰኞ፣ የካቲት ፣ 02 ቀን 2018(ኢሥኮዋጽ) - የየካቲት ወር 1ኛ ሳምንት የኮሚሽኑ ዓበይት ክንውኖች:-

1. ኮሚሽን ዋና ጽ/ቤት- በአስተዳደር ክላስተር የብልጽግና ወረዳ "ውጤታማ ምርጫ ለተምሳሌት ሀገር" በሚል ቃል የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ኮንፈረንሱን በፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ሲያካሂድ "ሥነ-ምግባራዊ እሴትን በመላበስ ሙስናን በፅናት መታገል" በሚል ርዕስ የብልጽግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ጸሀፊና የጽ/ቤት ኃላፊ ስልጠና ሰጥተዋል። በተጨማሪ የኮሚሽኑ ዋና ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የአንደኛ መንፈቅ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና ምዘና አካሂዷል። በመድረኩ የሁለቱ ዳይሬክቶሬቶች እና የጽ/ቤቱ የበጀት ዓመቱ የመንፈቅ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በKPI ላይ የተመሰረተ ምዘና ያደረገ ሲሆን የጽ/ቤቱ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች አፈፃፀም ምዘናም ተካሂዷል።

2. ኦሮሚያ ክልል የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት-በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ዞኖችና እና ከተማ አስተዳደሮች የኮሚሽን አባላት፣ የ3ኛ ሩብ ዓመት 2018 ቼክ ሊስት ላይ ተወያይተው አቅጣጫ ሰጥተዋል። በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቶች ለኮሚሽን አባላት፣ ለወረዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አመራሮች እና ለፓርቲ አባላት በመመሪያዎች እና ደንቦች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል። በተጨማሪ የክልሉ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ማኔጅመንት ኮሚቴ ባለፉት 15 ቀናት ውስጥ የተከናወኑ ስራዎች ላይ ግምገማ አካሂዷል።

3. ሐረሪ ክልል የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- የክልሉ ኮሚሽን ማኔጅመንትና የስራ አመራር ኮሚቴ ድሬዳዋ ከተማ በተካሄደው የብልፅግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን የስድስት ወር ግምገማና በተሰጡ ቀጣይ አቅጣጫዎች፣ በአዳማ ከተማ በተዘጋጀው ስልጠና የክልላችን ተሳትፎ ሁኔታና በቀጣይ ስልጠናውን ለሁሉም የኮሚሽን አባላት ስለሚወርድበት ሁኔታ፣ የ2018 የሁለተኛው መንፈቅ አመት እቅድ ክለሳ፣ በ2018 የመጀመሪያው መንፈቅ አመት የኮሚሽን አመራርና አባላት የኮሚሽን ስራዎች ምዘና ክንውን ያለበት ደረጃና በቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች፣ እንዲሁም በልሳነ ብልፅግና ቁጥር 1 ቅፅ 7 ዙሪያ በየደረጃው በሚደረገው ውይይት የኮሚሽኑ አባላት የነቃ ተሳትፎ በሚያደርጉበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡

4. ፌተአ የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- የፌዴራል ተቋማት አደረጃጀት ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡ በውይይቱ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት አጠቃላይ አፈፃፀም፣ የአካል ግምገማና የአባላት ምዘና ለማካሄድ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት አድርጓል፡፡ በተጨማሪ በፌተአ ኮሚሽን ስር የሚገኙ የማህበራዊ፣ የአስተዳደር እና የኢኮኖሚ ክላስተሮች እና በስራቸው የሚገኙ ወረዳዎች ኮሚሽኖች የኮሚሽን አመራር ምዘና ያካሄዱ ሲሆን በተካሄዱ የወረዳ ኮንፈረንሶችም ላይ የ6 ወራት የኮሚሽን አፈፃፀም ቀርቦ በፓርቲ አባላት ውይይት ተደርጎበታል፡፡

5. ጋምቤላ ክልል የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- የብልፅግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ቅ/ጽ/ቤት ሀብት አስ/ር ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈጻጸም በየደረጃዉ ከሚገኙ ቅ/ጽ/ቤቱ ሀብት አስ/ር ዘርፍ ጋር ባካሄደዉ የጋራ መድረክ የክልሉ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች ተገኝተዉ ከሀብት አሰባሰብ ጋር ተያይዞ ያለዉን ክፍተት በማንሳት ከ2017 ዓ.ም ሳይሰበሰቡ የቀሩ የአባላት ቁርጥ መዋጮ የአርሶ አደር፣ ነጋዴና ተማሪ ያደሩ ዕዳዎች በአስቸኳይ ማስገባት እንዲችሉ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

6. ቤን-ጉሙዝ የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- "ዉጤታማ ምርጫ ለተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል 7ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ በሚመለከት በየወረዳዉ ላሉት የኮሚሽን አመራርና አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ተፈጥሯል። በየደረጃዉ ያሉት የኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የአንደኛ መንፈቅ ዓመት ምዘና አካሂዷል። በተጨማሪ የአንደኛ መንፈቅ ዓመት አፈፃፀም ላይ የታዩ ጉድለቶችን የክልሉ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ተወያይቶ ዉሳኔ አሳልፏል።

7. ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- በክልሉ የጎፋ ዞን የኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በስሩ የሚገኙ መዋቅሮች የርስ በርስ የልምድ ልውውጥ እንዲያካሄዱ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በሦስት ማዕከል ማለት በደምባ ጎፋ ወረዳ ፣ በዛላ ወረዳ እና በቡልቂ ከተማ ማዕከል የሁሉም መዋቅር የኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ም/ኃላፌዎች በመገኘት ልምድ ልውውጡን አድርገዋል። በሦስቱም ማዕከል የተሣተፉት የወረዳና የከተማ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጥሩ ልምድ እንደቀሰሙ ገልጸዋል፡፡

8. አማራ ክልል የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- ከብልጽግና ኮሚሽን ለክልሎች የተሰጠውን ስልጠና በክልሉ ለሚገኙ ወረዳዎች ለመስጠት 14 ዞኖች/ከተሞች በስራቸው የሚገኙ ወረዳዋችን የጠሩ ሲሆን ሌሎች የምስራቅ ጎጃም፣ የሰሜን ጎጃም፣ የማእከላዊ ጎንደርና የደቡብ ወሎ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቶች በስራቸው ለሚገኙ ወረዳዎች በንቅናቄ ስልጠና መስጠት ጀምረዋል፡፡

9. ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- የክልሉ ኮሚሽን የ6ወራት የተግባር አፈፃፀም የፅሁፍ ግብረመልስ ለዞኖች ተልኳል፣ በዞኖች የቀሪ የ6ወራት ዕቅድ ክለሳ ተደርጓል፣ በቤንች ሸኮ ዞን የተቋም ህብረቶችን ቼክሊስት በማዘጋጀት የኢንስፔክሽን ስራ እየተሰራ ይገኛል። በተጨማሪ በክልሉ በምዕራብ ኦሞ ዞን የሁለተኛ ሩብ ዓመት ኮንፈረንስ ላይ የኮሚሽኑን ሪፖርት በማቅረብ የተጓደሉ የኮሚሽን አባላትን በኮንፈረንስ በማስመረጥ ማሟላት ተችሏል።

10. ድሬደዋ አስተዳደር የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- በአስተዳደሩ በየደረጃው የሚገኙ የኮሚሽን አባላት እና የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎች የ2018 በጀት ዓመት የአንደኛ መንፈቅ ዓመት ምዘና ተካሂዷል፡፡

11. አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- የከተማ አስተዳደሩ ኮሚሽን የኢንስፔክሽን ቡድን የየካ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ በ2018 ዓ.ም በጀት አመት የ6ወር ያከናወነውን የፐርፎርማንስ ኢንስፔክሽን ግብረመልስ ሰጠ፡፡ በተጨማሪ የልደታ ክፍለ ከተማ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን 6 ወር የአካል ግምገማ ማካሄዱን አስታውቋል።

12. አፋር ክልል የኢሥኮ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት- በክልሉ የኮሚሸን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አማካኝነት በአራት ዞን የኮሚሸን አመራርና አባላት የወረዳ እና የከተማ አሰተደዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች እና የኮሚሸን አባላትን በአዳማ የስልጠና አላማና ዋናው የትኩረት አቅጣጫ ላይ በቂ ግንዛቤ የተጨበጠበት ዉይይት ተደርጎል። በመጨረሻም ስልጠናው ወደ ታችኛው መዋቅር ተደራሽ ለማድረግ አቅጣጫ በማስቀመጥ ከዋናው ኮሚሽን የተሰጡ የሰባት ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ ስነድ ላይ በመወያየት እና የስነድ ርክክብ በማድረግ ስልጠናው ተጠናቋል ።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Addis Ababa