07/03/2024
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሎጎ መቀየሩን አስታወቀ።
***********************************
የአዲስ አበባ ከተማ የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ከተቋቋመበት አላማና ከሚያከናውናቸው ተግባራት እንዲሁም ከተሰጠው ተግባርና ሀላፊነት አንጻር ባለስልጣኑን ሊወክለው የሚችል ሎጎ መቀየሩን አስታውቋል።
ሎጎው በሶስት ቀለማት ማለትም በሰማያዊ ፣ቀይ እና ነጭ ቀለሞች የተዋቀረ ሲሆን ባለስልጣኑን ወካይ ምልክቶችንም አጠቃሎ ይዟል። በሎጎው የተቀመጡ ምልክቶችም የማረጋገጫ ምልክት የሎጎው አብዛኛው ክፍል በእንግሊዘኛ ሲ (C) ቁጥጥርን /control/የሚለውን የሚወክል ( Check marks/ / approval ቁጥጥር የሚያደርግባቸው ተቋማትና የሙያ ብቃት ትክክለኛቱን አረጋጋጭ መሆኑን ሲያመላክት በማረጋገጫ ምልክት ውስጥ ያለው በክብ የተቀመጠው ደግሞ የሚሠጠው አገልግሎት በእኩልነትና ከእድልዎ የፀዳ መሆኑን የሚያንጸባርቅ ነው፡፡ የመጨረሻው ምልክት እጁ የዘረጋ ሰው ምልክት ሲሆን ጤናውና ደህንነቱ የተረጋገጠለት ማህበረሰብ መፈጠሩን የሚያመለክት ወካይ ተምሳሌት እንደሆነም ተብራርቷል፡፡
የሎጎው ይዘትም በሎጎ እሳቤና ፍልስፍና መሰረት ሰማያዊ ቀለም የዓለም አቀፍ ጤና ድርጅት በመውሰድ የባለስልጣኑ ተልእኮና ስምሪት እንዲሁም መርህ ከዓለም አቀፍ ጤና መርሆዎችና ደረጃዎች ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ፤ ከዚህ በተጨማሪም ይህ ቀለም ከኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴርና ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን መ/ቤቶች የተቆራኘ የህብረቀለም ይዘት እንዲኖረው ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን ተቆጣጣሪና እርምጃ የመውሰድ ስልጣን ያለው መሆኑና የራሱ መለያ እንዲኖረው በማሰብ ደግሞ በቀጭኑ ቀይ ቀለም እንዲኖረው ተደርጎ ተዘጋጅቷል፡፡ የቀለማት ምርጫችንና የሎጎው ቅርፆች የባለስልጣኑ መርሆዎችና ዓለም አቀፍ የጤና እና የሃይጅን መርሆዎችን የሚገልፁ ናቸው፡፡

06/09/2023
06/09/2023
03/08/2023
17/07/2023
17/07/2023
24/03/2023
23/03/2023