26/09/2021
መላው የከተማችን ነዋሪዎች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!
Addis Ababa city government Public enterprise regulatory authority is one of the organization establ
26/09/2021
መላው የከተማችን ነዋሪዎች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!
10/09/2021
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ወ.ሮ ዘይነባ ሽኩር የዘመን መለወጫ በዓል አስመልክቶ ያስተላለፉት መልዕክት
ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ የመሸጋገሪያው እለት በየዓመቱ እንቁጣጣሽ በመባል ይታወቃል፡፡
እንቁጣጣሽ!!
ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች አመራሮችና ሰራተኞች፣ ለባለስልጣኑ ሰራተኞች እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ2014 አዲስ ዓመት በሰላም በጤና በፍቅር አደረሰን አደረሳችሁ!!
ሀገራችን በአሮጌው ዓመት በ2013 ከባድ ፈተና ያጋጠማት ቢሆንም በጀግኖች ልጆቿ ጥረት በርካታ ስኬቶችን እንደሀገር ያስመዘገበችበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከእነዚህም አገራዊ ድሎች መካከል 6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ ያካሄድንበት እንዲሁም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ውሃ ሙሌት ማካሄዳችንና ሌሎች ታላላቅ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች የጀመርንበትና ያጠናቀቅንበት ዓመት ነው፡፡
ሌላው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አሸባሪው እና ፀረ-ሰላም ሀይሉ የህወሃት ቡድን በኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ላይ በፈፀመው ክህደት የተጀመረው ህግ የማስከበር ዘመቻ የአሸባሪው ሕወሓት ሃይል ዳግም ላይመለስ በሚያስችል ሁኔታ እየተቀበረ ያለበት ዘመን መሆኑ በታሪክ ሊመዘገብ ይገባል፡፡
አሮጌው አመት በተቋማችን ልናከናውናቸው ካቀድናቸው ተግባራት አኳያ መልካም አፈፃፀሞች የተመዘገቡበትም ሆኗል፡፡
በዚህም ባለስልጣን መስሪያቤቱ በዋነኛነት ከተቋቋመበት አላማ አኳያ የልማት ድርጅቶች ምቹ ተወዳዳሪና ትርፋማ እንዲሆኑ የሚያስችል ክትትልና ድጋፎች ተደርገዋል፡፡
በተለይም ድርጅቶቹ ዘመናዊ የፋይናንስ ሪፖርት ስርዓት (IFRS) እንዲተገብሩ የሚያስችል ስልጠናዎችን እንዲያገኙ እንዲሁም ወደ ተግባር እንዲገቡም ተደርጓል፤ ከዚህ ቀደም በድርጅቶቹ ያልተከናወኑ በሶስተኛ ወገን ኦዲት የማድረግ ተግባራት እየተከናወኑ ነው፤ የልማት ድርጅቶቹ ምቹና፣ ቀልጣፋ አገልግሎት ለህብረተሰቡ እንዲሰጡ የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራሮችን የመዘርጋትና ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር በበጀት እንዲደጎሙ ተደርጓል፡፡
ይህም በዋናነት ለከተማችን ማህበረሰብ እንግልትን እንዲቀንስና እርካታዎችን እንጨምር ያለሙ ተግባራት ናቸው፡፡
ባለስልጣኑም በመጪው አዲስ ዓመት የሚያከናውናቸው ተግባራት እቅዶ ወደ ተግባር የገባ ሲሆን በተለይም የከተማችንን ነዋሪ እርካታ የሚያሳድጉ፣ የልማት ድርጅቶቹ ይበልጥ ተወዳዳሪና ዘመናዊ አገልግሎቶችን ለነዋሪው ተደራሽ የሚያደርጉባቸውን አሰራሮች ዘርግቶ ለተግባራዊነቱ በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ስገልፅ በታላቅ ኩራት ነው፡፡
እቅዶቻችን ይሳኩ ዘንድ የከተማችን ማህበረሰብ፣ እንዲሁም የባለስልጣኑ እና የልማት ድርጅቶች አመራሮችና ሰራተኞች በየደረጃው የሚጠበቅባችሁን ሃላፊነት ትወጡ ዘንድ ጥሪዬን እያስተላለፍኩ መጪው አዲስ ዓመት የሰላም የልማት የብልፅግና የስኬት ዓመት እንዲሆንልል እመኛለሁ፡፡
በድጋሜ መልካም አዲስ ዓመት !!
ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
08/09/2021
#መልካምነትለሀገሬለወገኔ
#የመልካምነትቀን
ጳጉሜ 3
07/09/2021
#ማገልገልክብርነው
ጳጉሜ 02
የአገልጋይነት ክብር ቀን
06/09/2021
ጳጉሜ 1
የኢትዮጵያዊነት ቀን
#ኢትዮጵያዊነቴክብሬ
25/08/2021
ባለስልጣኑ የመንግስት ልማት ድርጅቶችን የ2014 በጀት ዓመት የፊዚካልና ፋይናንሻል እቅድ ተወያይቶ አፀደቀ
በመድረኩም የ2013 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን በአዋጅ ከተሰጡት ስልጣንና ተግባር አንዱ ነው፤ የልማት ድርጅቶችን የኢቨስትመንትና ዓመታዊ እቅድ መርምሮ ማፅደቅ።
በዚህም መሰረት የአንበሳ ከተማ አውቶብስ ድርጅት፣ የሸገር ብሁሃን ትራንስፖርት ድርጅት፣ ኤግዚብሽን ማዕከልና ገበያ ልማት ድርጅት፣ የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት፣ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት፣ የቄራዎች ድርጅት፣ እንዲሁም የግንባታ ኢንተርፕራይዝ የ2014 በጀት አመት እቅዶቻቸውን አቅርበዋል፡፡
ድርጅቶቹም በእቅዶቻቸው በበጀት ዓመቱ ትኩረት የሚሰጡባቸውን ተግባራት አመላክተዋል፡፡ በዚህም የአገልግሎት ተደራሽነት ሽፋን ማሳደግ፣ ፈጣንና ምቹ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያስችሉ አሰራሮችን መተግበር፣ ትርፋማነትንና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በውይይቱም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ወሮ. ዘይነባ ሽኩር በ2013 በጀት ዓመት በልማት ድርጅቶቹ ውጤታማ አፈፃፀም መመዝገቡን ገልፀው የታዩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል የተገልጋዮችን እርካታ ማሳደግ የሚችሉ ተግባራት በእቅዱ እንደተካተቱ ተናግረዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎችም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የባለስልጣኑ ክትትልና ድጋፍ ውጤታማ መሆኑን አንስተው አሁንም ድርጅቶቹ ትርፋማና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ድጋፎች ሊደረጉላቸው እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
በመጨረሻም ባለስልጣን መስራቤቱ በ2014 በጀት ዓመት የሚያከናውናቸውን ዋና ዋና ግቦችና ተግባራትን የያዘ የመግባቢያ ሰነድ ከልማት ድርጅቶች ጋር ተፈራርሟል፡፡
24/08/2021
is a terrorist group
Weaponizing Aid
TPLF
prevails
negotiation with TPLF
, Libya, Somalia, and Afghanistan were destroyed based on pretexts
#“Tigray famine” is a false narrative to destabilize Ethiopia.
world needs to know that we r fighting an army of intr'l aid agencies.
is a Genocider not a victim.
Adhanom is disseminating misinformation & clearly showing us partiality For TPLF against WHO Oath.
is Ethiopia’s fragmentation.
foreign policy fails in Afgan, Syria and Libya Iraq. What about Ethiopia?
about Maikadra and Afar Genocide??
cannot be another Afghanistan.
17/08/2021
ባለስልጣኑ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባርና ሃላፊነት ለመወጣት ተግዳሮት የሆኑበትን አሰራሮች ለማስተካከል የሚያስችል ጥናት አዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል መላኩን አስታወቀ
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #
በጥናቱም የልማት ድርጅቶች ባህርይ ያላቸዉ ተቋማትን ተቆጣጣሪ ባለስልጣኑ እንዲከታተላቸው የሚያስችል የማሻሻያ ሃሳብ መካተቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 64/2011 መሰረት ለባለስልጣኑ ከተሰጠዉ ተግባርና ኃላፊነት አንዱ የልማት ድርጅቶች የኮርፖሬት አስተዳደርን የመከታተልና የመቆጣጠር ተግባር ቢሆንም ተግባሩ በሌሎች ተቋማት የሚመራ በመሆኑ ተግዳሮት መፍጠሩን ዋና ስራ አስኪያጅዋ ይገልፃሉ፡፡
ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ጥናት በማካሄድ ለሚመለከተው አካላት መላኩን ዋና ስራ አስኪያጇ ወሮ ዘይነባ ሽኩር ተናግረዋል፡፡
በተያያዘም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከተቋቋመ በኋላ የልማት ድርጅት ባህሪ ያላቸው ተቋማት የተመሰረቱ በመሆኑ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንዲከታተላቸውና በአሰራር እንዲደገፍ የሚያስችል ሃሳብ በጥናቱ ውስጥ አካቶ ለሚመለከተዉ አካል ምላሽ እንዲሰጥባቸው መላኩን ገልፀዋል፡፡
14/08/2021
የመንግስት የልማት ድርጅቶችን አገልግሎት አሰጣጥና ትርፋማነት ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ
የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን በ2014 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ከሰራተኞቹ ጋር ተወያይቷል።
በውይይቱም የባለሥልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ወሮ ዘይነባ ሽኩር በ2014 በጀት ዓመት የልማት ድርጅቶቹን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በማሳደግ አገልግሎት አሰጣጡን ማዘመን የሚያስችሉ ተግባራት ትኩረት ተሰጥቶባቸው እንደሚተገበሩ ተናግረዋል።
ዋና ስራ አስኪያጇ አያይዘውም በበጀት ዓመቱ ዘመናዊ የኮርፖሬት ፋይናንስ አሰራር ስርአት መዘርጋት፣ ውጤታማ የሃብት አጠቃቀም ማሳደግ እንዲሁም ትርፋማነትና ዘላቂነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ግቦችና ተግባራት እንደታቀዱ ተናግረዋል።
ሰራተኞቹም በእቅዱ አፈፃፀም ላይ ውይይት በማድረግ እቅዱን ለማስፈጸም የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች እና ስጋቶች በመለየት የጋራ መግባባት ፈጥረዋል።
ባለስልጣን መስሪያቤቱ አንበሳ የከተማ አውቶብስ፣ የሸገር ብዙሃን ትራንስፖርት፣ ሲኒማቤቶች አስተዳደር ጨምሮ የከነማ መድሐኒትቤቶች አስተዳደር እና ሌሎች የልማት ድርጅቶችን እንደሚቆጣጠር ይታወቃል።
03/08/2021
በአንበሳ የከተማ አውቶቡስ እና በሸገር ብዙሃን ትራንስፖርት ድርጅቶች ላይ የተካሄደ የተገልጋይ እርካታ ጥናት ይፋ ሆነ።
**********************************************
ጥናቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ያካሄደ ሲሆን ከ4 መቶ በላይ የድርጅቶቹ ተገልጋዮች እንዲሳተፉበትም ተደርጓል።
የተገልጋይ እርካታ ጥናት የተካሄባቸው ድርጅቶችን ጨምሮ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሚቆጣጠራቸው የልማት ድርጅት የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት መድረክ ጥናቱ እንዲቀርብ ተደርጎ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል ።
የባለስልጣን መስሪያቤቱ የጥናትና አቅም ግንባታ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ሀብቱ አርብሴ ጥናቱን ባቀረቡበት ወቅት የጥናቱ ዋና አላማ ድርጅቶቹ የሚሰጧቸው አገልግሎቶችን ጥራት እና ተደራሽነት ማሳደግ መሆኑን ተናግረዋል።
የቡድን መሪው አቶ ሀብቱ አያይዘውም በጥናቱ ላይ ከ400 በላይ የድርጅቶቹ ተጠቃሚዎችን በቀጥታ ማሳተፍ መቻሉን ገልፀው ተሳታፊዎቹም ሶስት ዓመትና ከዚያ በላይ በድርጅቶቹ የተገለገሉ እንዲሆን መደረጉን ተናግረዋል። በዚህም የሚሰበሰቡ መጠይቆች ተዓማኒነት እና ሚዛናዊነትን እንዲጠብቁ ማድረግ ማስቻሉን አብራርተዋል።
ጥናቱ የተገልጋይ እርካታን ደረጃ ለመለየት የተቋሙ ሰራተኞች አገልግሎት ብቃት፣ ተገልጋዮች የሚያገኙት አገልግሎት ቀልጣፋነት፣ የሰራተኞች ስራ ሰዓት አከባበር እና ስነ ምግባር፣ የተገልጋዩን ፍላጎት በመረዳት የማገልገል ዝግጁነት፣ የድርጅቱ አገልግሎት ተደራሽነትና ሌሎች መስፈርቶችን እንደመለኪያነት ተጠቅሟል።
በዚህም በድርጅቶቹ የሚሰጡ አገልግሎቶች ሊጠናከሩና ፈጥነዉ ሊታረሙ የሚገባቸውን ጉድለቶች አመላክቷል ።
በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩት የሸገር ብዙሃን ትራንስፖርት ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ቢተው ደመላሽ ጥናቱ ገንቢና ያሉብንን ጉድለቶች አመላካች ሆኖ እንዳገኙት ገልፀው በቀጣይ በግብዓትነት በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ወሮ ዘይነባ ሽኩር በበኩላቸው ይህን መሰል ጥናት መካሄዱ ድርጅቶቹ በተጨባጭ ያላቸውን ጥንካሬና ድክመት ለመለየት ያስችላል። ይህም ለአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል አይነተኛ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።
በቀጣይም በሌሎች የልማት ድርጅቶችንም የመከታተል የመቆጣጠር እና አገልግሎት አሰጣጥ ሂደትንም የመፈተሽ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ዋና ስራ አስኪያጇ ተናግረዋል።
03/08/2021
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ሰራተኞች አዲስ አበባን እናልብስ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ መረሓ ግብር ላይ ተሳተፉ።
**********************************************
ባለስልጣን መስሪያቱ የሚቆጣጠራቸውን የልማት ድርጅቶች በማስተባበር በየካ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ሚሊንየም ፓርክ ውስጥ ከ8 ሺህ በላይ ችግኞችን ተክሏል።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ወሮ ዘይነባ ሽኩር የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙን ሲያስጀምሩ እንደገለፁት ተቋሙ ከዚህ ቀደም በነበሩ የችግኝ ተከላ ኘሮግራሞች ላይ ተሳታፊ እንደነበረው ሁሉ ዘንድሮም ከሚቆጣጠራቸው ሰባት የልማት ድርጅቶች ጋር በመሆን ከስምንት ሽህ በላይ ችግኞች እንደሚተከሉ ገልፀዋል።
የዘንድሮው አረንጓዴ ልማት ችግኝ መርሓ ግብር በአገር አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን እናልብስ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ሲሆን ከተማ አስተዳደሩም አዲስ አበባን እናልብስ በሚል መሪ ቃል በርካታ ችግኞች እየተተከሉ ይገኛሉ።
| Monday | 09:00 - 17:00 |
| Tuesday | 09:00 - 17:00 |
| Wednesday | 09:00 - 17:00 |
| Thursday | 09:00 - 17:00 |
| Friday | 09:00 - 17:00 |