29/05/2026
Mineral Industry Development Institute - Ethiopia
ማዕድናትን በጥሬ እቃነት ለሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች በምርምር፣ በስልጠና፣ በቴክኖሎጂ መረጣና ናመሳሰሉት በመደገፍ የጥናትና ምርምር ስራዎችን መስተዋወቅ
29/05/2026
27/05/2026
የከበሩ ማዕድናትን እሴት ተጨምሮባቸው ወደዉጭ ገበያ እንዲቀርቡ ለማስቻል የባለሞያዎችን የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ።
(ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም) የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በጌጣጌጥ ማዕድናት ልየታ፤ አያያዝ፤ ቆረጣና ማስዋብ ዙሪያ ተግባር ተኮር ስልጠና በሀዋሳ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።
በስልጠናው ላይ ከኦሮሚያ ክልል ከጉጂ ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረና፣ ምስራቅ ቦረና ዞኖች ውስጥ በጌጣጌጥ ማዕድናት ማውጣት ስራ ላይ የተሰማሩ አምራች ማህበራትና ከክልሉ የተውጣጡ ባለሞያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ ።
በስልጠና መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ማዕድን ልማት ባለስልጣን ምክትል ኃላፊና የፈቃድ አስተዳደር እና ቁጥጥር ዘርፍ ኃላፊ ጉታ ለገሰ (ዶ/ር) እንደተናገሩት የማዕድን ዘርፉን ለማሳደግና ሀገር ከዘርፉ ተጠቃሚ እንድትሆን በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው በተለይም የከበሩ ማዕድናትን እሴት ተጨምሮባቸው ወደውጭ ገበያ እንዲቀርቡ የባለሞያዎችን የአቅም ግንባታ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል ፡፡
በቀጣይ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር የተጀመሩ ስራዎች በማጠናክረ ማሰልጠኛ ማዕከላትን በማቋቋም በጌጣጌጥ ማዕድናት ልየታ፣ቆረጣ፣ማስዋብ እና ማጣመር ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስራዎችን በስፋት መሰጠት እንዳለበት ተናግረዋል።
ድህረገጽ፦https://www.miidi.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/midifacebook
Telegram: https://t.me/+UD8XZwAgQvYyZjg0
Email: [email protected]
26/05/2026
26/05/2026
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛ የኢድ አል-ዓደሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤
በዓሉ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡
መልካም በዓል
ድህረገጽ፦https://www.miidi.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/midifacebook
Telegram: https://t.me/+UD8XZwAgQvYyZjg0
Email: [email protected]
15/05/2026
Assosa University (May 15, 2026) — Assosa University is currently hosting its 11th Annual National Research Conference under the theme, "From Shelf to Society: Leveraging Research and Innovation for Community Transformation."
Distinguished keynote speaker Dr. Bisirat Kebede (Director General of Mineral Industry Development Institute, Ministry of Mines) highlights the importance of developing and transforming a community using mining resources, turning mineral wealth into long-term social and economic benefits rather than short-term extraction gains. The director also emphasized Strengthen local value addition, Invest mining revenue in public services, Build skills, Employment opportunities and Ensure environmental protection is among the key ways for ensuring the long term social economic benefit and converts non-renewable resources into sustainable development.
The University President Dr. Kemal Abdurahim officially opened the conference, welcoming distinguished guests and inviting them to enjoy their stay. In his remarks, Dr. Kemal emphasized that research and community engagement are the primary reasons for the gathering. He noted that since its founding, Assosa University has been dedicated to problem-solving, community-focused research in agriculture, health, mining, education, law, social sciences, and technology transfer.
A total of 40 research papers from different discipline will be presented during the upcoming sessions to an audience of researchers, directors, executives, and invited stakeholders.
ድህረገጽ፦https://www.miidi.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/midifacebook
Telegram: https://t.me/+UD8XZwAgQvYyZjg0
Email: [email protected]
14/05/2026
On May 15, 2026 Assosa University. Title of the keynote: Mineral Resource Potential and Industrial Development: The Strategic Role of Institutions
07/05/2026
በኢትዮጵያ የጌጣጌጥ ማዕድናት ዘርፍ ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡
(ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም) የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከወሎ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር እየተዘጋጀ ባለው የኢትዮጵያ የጌጣጌጥ ማዕድናት ዘርፍ ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ዝግጅት ዙሪያ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡
የውይይቱ ዋና አላማ የኢትዮጵያ የጌጣጌጥ ማዕድናት ፍኖተ ካርታ ረቂቅ ሰነድ ላይ ከሚመለከታቸው የክልል የኢንዱስትሪ የአምራቾች እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ግብአት ለማሰባሰብ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡
የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳሬክተር ብስራት ከበደ (ዶ/ር) በውይይቱ መክፈቻ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ ከወሎ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር በጌጣጌጥ ማዕድናት ላይ የሚታዩ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመፉታት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ጠቅሰው ይህም የኢትዮጵያ የጌጣጌጥ ማዕድናት ፍኖተ ካርታ ረቂቅ ሰነድ ዝግጅትም አንዱ እንደሆነ አንስተዋል፡፡
በሌላ መልኩ በዚህ ውይይት ላይም በጌጣጌጥ ማዕድናት ላይ ከምርት ጀምሮ እስከ መጨረሻው ተጠቃሚ ድረስ ያሎ ችግሮችን ለመፍታት የባለድርሻ አካላት እና የአምራቾች አስተያየት ወሳኝ እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡
የወሎ ዩኒቨርሲቲ የትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር አሳምን አያሌው (ዶ/ር) በበኩላቸው የወሎ ዩኒቨርሲቲ ከኢንስቲቲዩቱ ጋር በመተባበር በጌጣጌጥ ማዕድናት ላይ በርካታ የጥናትና ምርምር ስራዎችን እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው በተለይም በአቅም ግንባታ፤በቴክኖሎጅ አጠቃቀም እንዲሁም በማዕድናት ልየታ፤መረጃ አያየዝ እና እሴት ጭማሪ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ድህረገጽ፦https://www.miidi.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/midifacebook
Telegram: https://t.me/+UD8XZwAgQvYyZjg0
Email: [email protected]
03/05/2026
በጌጣጌጥ ማዕድናት ልየታ፤አያያዝ፤ቆረጣና ማስዋብ ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።
(ሚያዝያ 25 ቀን 2018 ዓም)የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ ሲሰጥ የቆየው ተግባር ተኮር ስልጠና ተጠናቀቀ።
ከሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የቆየው ተግባር ተኮር ስልጠና በጌጣጌጥ ማዕድናት ልየታና አያያዝ እንዲሁም ቆረጣና ማስዋብ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙት የደቡብ ወሎ ዞን የማዕድን ቢሮ ሀላፊ አቶ አህመድ መንግስት ለማዕድን ዘርፉ የሰጠው ትኩረት በተጨባጭ እየታየ መሆኑን እና በዘርፉም ውጤቶች መመዝገብ መጀመራቸውን ገልፀው እንደዚህ አይነት ተግባር ተኮር ስልጠና መሰጠታቸው መንግስት ወደ ውጭ በሚልካቸው የጌጣጌጥ ማዕድናት ላይ እሴት በመጨመር ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።
የወሎ ዩኒቨርሲቲ የኢንዱስትሪ የትስስርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር አሳምን አያሌው በበኩላቸው ወሎ ዩኒቨርሲቲው ከማዕድን ሚ/ር ጋር በገባው ውል መሰረት ሰፋፊ ስራዎችን እያከናወኑ እንደሚገኙ ጠቅሰው ለኢንዱስትሪው ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት አንዱ የትኩረት መስክ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የጌጣጌጥ ማዕድናት ዴስክ ሀላፊ አቶ ሰለሞን ዘለቀ በበኩላቸው በዘርፉ ያለውን እሴት ጭማሪ ለማበረታታት እንደዚህ አይነት ክህሎት መር የሆኑ ስልጠናዎች አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቅሰው የማዕድን ሀብት ባሉባቸው አካባቢዎች ለሚገኙ አምራቾችና የላፒደሪ ባለሙያዎች መሰል ስልጠናዎች የሚሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ይህ ተግባር ተኮር ስልጠና በማዕድን ምርት ላይ ለተሰማሩ ማህበራት ከፍተኛ መነሳሳት እንደፈጠረላቸው እና በሚያመርቱት ምርት ላይ እሴት በመጨመር ለገበያ ሊቀርብ እንደሚገባ ሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ሰልጣኞች በወሎ ዩኒቨርሲቲ እየተሰሩ የሚገኙ የጌጣጌጥ ማዕድናት ምርትና ምርታማነት ለመጨመር የሚያግዙ ፕቶታይፕ ቴክኖሎጂዎችን በመጎብኘት ስልጠናውን ተጠናቋል።
ድህረገጽ፦https://www.miidi.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/midifacebook
Telegram: https://t.me/+UD8XZwAgQvYyZjg0
Email: [email protected]
27/04/2026
በጌጣጌጥ ማዕድናት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፡፡
(ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓም) የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በጌጣጌጥ ማዕድናት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በዛሬው ዕለትም ኢንስቲቲዩቱ ከወሎ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ከአማራ እና ከአፋር ክልሎች ለተውጣጡ፣ በጌጣጌጥ ማዕድናት ቁፋሮ፣ ማስዋብ እና ተያያዥ ስራዎች ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና በኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የጌጣጌጥ ማዕድናት ትምህርት ክፍል እየተሰጠ ይገኛል።
ስልጠናው የጌጣጌጥ ማዕድናት ልየታ እና አያያዝ እና የጌጣጌጥ ማዕድናት መቁረጥና ማስዋብ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብስራት ከበደ (ዶ/ር) በስልጠና መክፈቻ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት መንግስት ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው የዘርፉን የግብይት ስርዓት ለማዘመን እና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ እንዲሁም የመሰረተ ልማት ችግሮችን ለመቅረፍ ሰፊ ስራዎችን እየተከናውኑ እንደሆነን አንስተዋል፡፡
የወሎ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ሃዋ ወሌ ( ዶ/ር) በበኩላቸው ወሎ ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰቡን ችግር በተግባር መፍታት የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰው በአማራ ክልል በተለይም የጌጣጌጥ ማዕድናት ሀብት በስፋት በሚገኝባቸው አካባቢዎች ለህብረተሰቡ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጡ ስራዎችን እየተሰሩ እንደሆነ ገልጸዋል።
የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ( ዶ/ር) መላኩ ታመነ በበኩላቸው የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ይህ ፕሮጀክት ወደ ተግባር እንዲለወጥ እየደረገ የሚገኘውን ድጋፍና ክትትል አድንቀው ይህ ተግባር ተኮር ስልጠና ማዕድናትን ከማውጣት ባሻገር እሴት ጨምሮ ለገቢያ ለማቅረብ እና በስራቸው ላይ ውጤታማ እንዲሁኖ እንደሚረዳቸው ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ስዓት በሀገራችን የጌጣጌጥ ማዕድናት በስፋት በጥሬው ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ሲሆን ከዘርፉ ሊገኝ የሚገባ የውጭ ምንዛሬ ከማሳጣት በተጨማሪ በእሴት ጭማሪ ሂደት ሊፈጠር የሚገባውን የስራ እድል እንዳንፈጥር ችግር ሆኖ ቆይቷል።
ድህረገጽ፦https://www.miidi.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/midifacebook
Telegram: https://t.me/+UD8XZwAgQvYyZjg0
Email: [email protected]
23/04/2026
በሃብት ምዝገባ የሲስተም አጠቃቀም እና በሰራተኞች የህግ ድንጋጌዎች ምንነት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
(ሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም) ለማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፤ለማዕድን ሚኒስቴር እና ለኢትዮጵያ ጂኦሎጅካል ኢንስቲትዩት አመራር እና ሰራተኞች በሃብት ምዝገባ የሲስተም አጠቃቀም እና በፌደራል የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ 1353/2017 ምንነት እና አተገባበር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ዋና አላማም ሰራተኛውና አመራሩ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሀብት ምዝገባ እንዲያከናውኑ ለማስቻል እና በቅርቡ በወጣው የፌደራል የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 ላይ በቂ እውቀት እና ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ ያለመ ነው።
ድህረገጽ፦https://www.miidi.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/midifacebook
Telegram: https://t.me/+UD8XZwAgQvYyZjg0
Email: [email protected]
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa/Ethiopia Lamberet Megenagna
Addis Ababa
486
