Balderas ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ

Balderas ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ

Share

የፓለቲካ ድርጅት | Political Party

Photos from Balderas ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ's post 20/04/2026

ሚያዚያ 12/2018 ዓ.ም.
ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፓርቲው የስራ አስፈፃሚ እና የምክር ቤት አባላት የተሰጠ መግለጫ

የፓርቲ ስራ አስፈፃሚን እና ምክር ቤትን ያገለሉ ውሳኔዎች እና ተግባራት ተቀባይነት የላቸውም

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ቀደም ሲል እንደ ሲቪክ ተቋም ከዛም እንደ ፓርቲ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በመተዳደሪያ ደንብ እና በውስጡ ባሉ መዋቅራት እንደሚመራ ይታወቃል። በዚህም ተቋማዊ አሰራር አምባገነኑን የብልፅግና መንግስትን ከየትኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ በላይ ሲታገል እንደቆየ ህዝብ የሚያውቀው የአደባባይ ሀቅ ነው። ባልደራስ የትግል አድማሱን በማሳደግ በነሀሴ 23/2016 ዓ.ም ወደ ሀገር አቀፍነት አድጓል።

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በነዚህ የትግል አመታት ውስጥ በርካታ የውጪ እና የውስጥ ተፅዕኖዎች እና ፈተናዎች ደርሰውበታል። የችግሮቹ ምንጭ የፀጥታ ሀይሎች፣ ሰርጎ ገቦች፣ የግልን ጥቅም (የስልጣን፣ የገንዘብ) በሚያሳድዱ፣ አላማቸውን የሳቱ ታጋዮች ... ወዘተ ናቸው። አብዛኛዎቹ እነዚህ ተግባራት የስልጣን እና የገንዘብ ጥማት በአጭሩ የተቀጩ መስለውን ነበር ዳሩ ግን ካለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ፤ የፓርቲው ፕሬዝዳንት ሁለት ግለሰቦችን በመያዝ ፓርቲውን ህገወጥ በሆነ መንገድ ለመምራት፤ የፓርቲውን የስራ አስፈፃሚ፣ ምክርቤት እና ሌሎች መዋቅሮችን ከጨዋታ ውጪ በማድረግ ውሳኔዎችን ከህግ ውጪ በራሳቸው በመወሰን ፍቃድ የሌላቸውን እና ደንብን ባላከበሩ ሁኔታ ስራዎችን እየተገበሩ ይገኛል። ከአብዛኛዎቹ ተግባራት ውስጥ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል፦

1. ስራ አስፈፃሚም ሆነ ምክር ቤቱ ባልተሰበሰበበት እና ውሳኔ ባልሰጠበት ሁኔታ ምርጫ ተሳትፎ ማድረግ፤

2. ያለ ስራ አስፈፃሚ እና ምክር ቤት ውይይት እና ውሳኔ መስፈርቱ ባልታወቀ እና ስርአት በሌለው መንገድ የምርጫ እጩዎች ማስመዝገብ፤

3. የትኛውም የተቋሙ መዋቅር ባልመከረበት እና ውሳኔ ባልሰጠበት ሁኔታ ማኒፌስቶ ማውጣት፤

4. የትኛውም ስልጣን ያለው አካል ባልመከረበት እና ውሳኔ ባልሰጠበት ሁኔታ በተቋማት ላይ ክስ መመስረት እና ስራ አስፈፃሚው ያልመከረበት መልስ ለፍርድ ቤት መስጠት፣

5. ስልጣን ያለው አካል ባልመከረበት ሁኔታ የፓርቲውን ዋና ፅ/ቤት አድራሻ መቀየር፣

6. ስራ አፈፃሚው ያላፀደቀውን ገንዘብ ማንቀሳቀስ፤ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ህጋዊ ያልሆኑ ውስጣዊ ጉዳዮችን ግለሰቦቹ እየፈፀሙ ይገኛሉ።

እነዚህ ፍፁም ህገወጥ የሆኑ ስራዎች እንዲቆሙ የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ እና የምክር ቤት አባላት ስንታገል የቆየን ሲሆን አሁንም እየታገልን እንገኛለን። እነዚህ ፍፁም ህገወጥ የሆኑ ተግባራት በአስቸኳይ ቆመው ፓርቲው ወደ ህጋዊ እና መዋቅራዊ ስራዎች እንዲመለስ በፅኑ እናሳስባለን። እነዚህ ተግባራት በጊዜ የማይፈቱ ከሆነ ግን፣ ዝርዝር ጉዳዮችን ከነ ማስረጃ ይዘን ለመውጣት እንገደዳለን።

10/04/2026

እንኳን ለስቅለት እና ትንሳኤ በአል አደረስዎ!
መልካም በአል!

20/03/2026

እንኳን ለዒድ-አልፈጥር በዓል አደረስዎ!
ዒድ-ሙባረክ!

05/03/2026

እንኳን ለካራማራ የድል በአል አደረሰን!

ክብር ለጀግኖች አባቶቻችን!
ድል ለኢትዮጵያ!

02/03/2026

#አድዋ
የድል ታሪክ!

01/03/2026

#አርሲ

01/03/2026

ዓፄ ምኒልክ ወደር የለሽ ኢትዮጵያ ጀግና

✊ዳግማዊ ምኒልክ ወደር የለሽ አፍሪካዊ ጀግና ናቸው!
✊ዳግማዊ ምኒልክ የአፍሪካ ኩራት ምንጭ የሆነውን የአድዋ ድል የመሩ የጀግኖች ጀግና ናቸው!

በርሊን ከተማ ውስጥ የጀርመን ግዛት አስተዳዳሪ (ቻንስለር) በነበረው ኦቶ ቫን ቢስማርክ (Otto von Bismarck) መኖርያ ሳሎን ፌሽታ በፌሽታ ሆኗል። እለቱ እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር (እ.አ.አ) የካቲት 16 ቀን 1885 ሶስት ወር ሙሉ አሰልቺ ውይይት የተደረገበትና ዋና ዋናዎቹ የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ተሰብስበው ”አንተ ይሄን ያዝ አንተ ያንን ያዝ” ተባብለው ከወታደራዊ ዘመቻ በፊት አፍሪካን የተቃረጡባት ነበረች።

በስብሰባው ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነውን የአፍሪካ መሬት የሃሳብ መስመር እያሰመሩ ያለከልካይ ተከፋፈሉት። ከሦስት ወራት በላይ (እ.አ.አ ከኅዳር 15 ቀን 1884 እስከ የካቲት 26 ቀን 1885) ሲካሄድ የነበረው የበርሊን ጉባዔ (Berlin Conference) መደምደሚያ የነበረው ‘የበርሊን ጉባዔ ጠቅላላ ግብአተ ሰንድ’ (General Act of Berlin conference) በታሪክ አጥኚዎችና ፖለቲካ ተመራማሪዎች ዘንድ በአብዛኛው “አፍሪካን የመቀራመት ጉባዔ” (“The Division of Africa” ወይም “Scramble of Africa”) ተብሎ ይታወቃል። በጉባዔው ላይ የጀርመን፣ ኦስትሮ-ሀንጋሪ፣ ቤልጅየም፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታንያ፣ ጣልያን፣ ኔዘርላንድስና ፖርቱጋል ተወካዮች ተገኝተዋል።
አውሮፓውያን አፍሪካን ለመቀራመት በበርሊን ስምምነት ሲያደርጉ፤ አፍሪካዊያን ደግሞ የውጭ ወራሪዎችን ለመከላከል ከዚህ አለፍ ሲልም እርስ-በርሳቸው መተነኳኮስ የጀመሩበት ጊዜ እንደነበር ታሪክ ያስረዳል። ወቅቱ በአራቱም የአህጉሪቷ አቅጣጫዎች የሚገኙ ነገስታት እና የጭፍራ አለቆች በተናጠል ከአውሮፓውያኑ ጋር በገጠሟቸው ውጊያዎች ትርጉም ያለው ስኬት ሳያገኙ፤ አፍሪካውያን በቅኝ ግዛት መውደቅ የጀመሩበት ነው።

ይህን ተከትሎ ጣልያንም ኢትዮጵያን በቁጥጥሯ ስር ለማድረግ ብትነሳም እምቢተኛው ጥቁር ሕዝብ ማንነቱንና ክብሩን አሳልፎ ላለመስጠት በመወሰኑ ያልተመጣጠነ ውጊያ ቢገጥሙም አሳፍሮ መልሷታል። ዘመናዊ የጦር መሣሪያ የታጠቀው የጣልያን ጦር የቅኝ ግዛት ተልእኮውን እውን ለማድረግ የተመመው በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ በአግባቡ የሰለጠኑ ወታደሮችን ይዞ ነው። ነገሩ እንደታቀደው ሳይሆን ቀርቶ የጣልያን ጦር በአድዋ ድል ተነሳ። ታሪክም ይህን ጦርነት (The Battle of Adwa) በማለት፣ ለጥቁር ሕዝቦች ታላቅ መነቃቃትና ተስፋ የሰጠውን የጦርነቱን ድል ደግሞ (The Victory of Adwa) ብሎ ሲገዝበው ይኖራል።
የታሪክ ሊቃውንት እንደሚያስቀምጡት የአድዋ ጦርነት በአፍሪካ ምድርና ታሪክ ከተከናወኑት ጦርነቶች ከፍተኛውን የዋጋና የክብር ስፍራ ይዟል።

የአድዋ ድል ለኢትዮጵያ ነጻነትና ኩራትን፣ በዓለም ዙሪያ በተለይ በአሜሪካዎቹ ሰፋፊ እርሻዎች ለ500 አመታት በባርነት ለተጋዙ ጥቁር ሕዝቦች ደግሞ፥ የማንነት ማረጋገጫ፣ የዘመናት ጭቆናና የስነ-ልቦና ቁስልን አውልቆ የመጣያ የተስፋ ትንሳኤ ሆኖም ነበር።
የታሪክ ተመራማሪና ደራሲውፖል ሄንዝ በጻፉት ንብረ ጊዜ፥ የኢትዮጵያ ታሪክ (Layers of Time: A History of Ethiopia, by Paul B. Henze) በተሰኘው የታሪክ ድርሳናቸው “አውሮፓውያን የፈለጉትን ገድለዋል፣ ባሪያ ፈንግለዋል፣ አካባቢን፣ ሀብትን፣ ጉልበትን መዝብረዋል፤ ምክንያቱ በግልጽ ባይታወቅም ‘ኢትዮጵያን በጦር ከማስገበር ይልቅ እንቃረጣት ብለው’ ብሪታኒያ፣ ፈረንሳይና ጣልያን የሦስትዮሽ ስምምነት (Tripartite Agreement) ተፈራርመው አጼ ምኒልክን ‘እወቁልን’ ብለው ጦማር ሰደዋል። አጼ ምኒልክም ‘ስለነገራችሁኝ አመሰግናለሁ፣ ነገር ግን እኔ በሌለሁበት የተወሰነውን አላውቅም’ በማለታቸው ጣልያን ኢትዮጵያን በወረራ ያዘች።

ወረራውን ለመቀልበስ በአጼ ምኒልክ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት ሰላማዊ ትግል ቢያደርግም የወራሪዎቹ ብልጣብልጥነት ጦርነቱን አይቀሬ አደረገው። ወደ ጦርነት ተገዶ የገባው የኢትዮጵያ የጦር ኃይል በአምባላጌ፣ በመቀሌና በአድዋ በተከታታይ ባደረገው ጦርነት የበላይነት ወስዶ የካቲት 23 ቀን 1988 ዓ.ም. ላይ በአድዋ የድል ባለቤት መሆኑ ተበሰረ። የድሉ ዜና እንደናኘ በአፍሪካ ተስፋ፣ በአውሮፓ ድንጋጤ ፈጠረ። የኢትዮጵያ ድል አውሮፓውያን በዓለም የነበራቸውን ልዕለ ኃያልነት ለመጀመሪያው ጊዜ ጥያቄ ውስጥ ከቷል። ፖል ሄንዝ ”ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው” የኢትዮጵያ ድል የአውሮፓ ተሰሚነት የቁልቁለት ጉዞ መነሻ ነበር” ሲሉ በጽሁፍ አስፍረዋል።

ድሉ ታላቋ ብሪታንያን ኢትዮጵያን በእኩል ዓይን ዓይታ ”የምስራቁን የደቡቡን የምእራቡን ድንበራችንን እንካለል” ብላ በፊርማ እንድታጸድቅ አስገድዷታል። ከዚህ በተጨማሪ በአውሮፓ ቅኝ ግዛት መዳፍ ስር ሲማቅቁ የነበሩትን አፍሪካውያን እና ካሪቢያን ጥቁሮች ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ብርታት እና ምሳሌ ሆኗቸዋል። ለጥቁር አሜሪካውያን ምሁራን ከፍተኛ የመንፈስ መነቃቃት እንዲያገኙ አድርጓል።
የአድዋ ድል (ማለትም፥ በአውሮፓውያን ዘንድ የአድዋ ጦርነት ሽንፈት) በተሸናፊ የአውሮፓ ገዢዎች ዘንድ ቁጭት ፈጥሮ ከ30 ዓመት በኋላ ፋሺዝም በጣልያን ውስጥ ስር እንዲሰድ እና መሪ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም (አይዲዮሎጂ) እንዲሆን ምክንያት ሆኗል። ለኢትዮጵያ ደግሞ የተረጋጋ መንግስታዊ አስተዳደር አስገኝቷል። በዚህ የከሸፈ የቅኝ-ግዛት ዕቅድና የአውሮፓውያን ተስፋፊነት የተደሰቱ ሶሻሊስት አመለካከት ያላቸው ወገኖች በጣልያን፣ በብሪታንያና በፈረንሣይም ነበሩ።

ዕውቁ የታሪክ ተመራማሪና የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰር የነበሩት ሪቻርድ ፓንክረስት እና ሌላው ኢትዮጵያዊ የታሪክ ተማራማሪ ዶ/ር አብዱልሳማድ አህመድ በጋራ በጻፉት ስለ አድዋ ድል በጻፉት መጽሐፍ (Adwa Victory Centenary Conference, 26 February – 2 March 1996) ውስጥ እንዳሰፈሩት የኢጣሊያኑ ክሪቲካ ሶሻሌ (Critica Sociale) ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ፊሊፖ ቱራቲ (Filippo Turati) በወኔና በምልዓት ለእውነት ስለእውነት ጻፈ። “ጣልያን ወደ አድዋና ወደ ሌሎችም ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ተደረጉት ጦርነቶች የገባችው፣ ለእንግሊዛውያን አገልጋይና አሽከር ሆና ነው። በዚህም የተነሳ የጣሊያናውያን ሀብትና ደም ያላግባብ ፈሰሰ” ሲል ወረራውን በማውገዝ ድፍረት የተሞላበት ጽሁፉን ማስነበቡን ይገልጻሉ። ጋዜጠኛው በጽሁፉ “የጣልያንና የእንግሊዝ መንግሥታት በአፍሪካ ስለተቀዳጁት የቅኝ-ግዛትና የተስፋፊነት ድል እንደጽጌረዳ የፈካ ውሸት እየፈበረኩ ይመጻደቁ እንጂ፣ በእርግጥ ኢትዮጵያ ድል አድርጋለች… ቪቫ ምኒልክ! ቪቫ ኢትዮጵያ!” ሲል አወድሷል።

በአጼ ምኒልክ መሪነት የኢትዮጵያ ኃይል በጣልያን ወራሪ ኃይል ላይ በአድዋ የተቀዳጀው ድል ድልድይ ሆኖ የጥንታዊቷን ኢትዮጵያ የታላቅነት ክብር ከዘመናዊ ዓለም ጋር ያገናኘ ድልድይ ሆኗል። ታዲያ ይህ ድልድይ በ1890ዎቹ ግንባታው የተጀመረው የተቀረው የአፍሪካ ክፍል በውጭ ኃይሎች አገዛዝ ቀንበር ስር ሲወድቅ ኢትዮጵያውያን ብቻ በተከታታይ የተሰነዘረባቸውን ወረራ በድል ሲመልሱ ነበር።
በዚያው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያውያን ለውጭ ወራሪዎች የማይንበረከኩ መሆናቸውን ማሳየታቸውን ማስታወስ ይቻላል። በ1870ዎቹ የግብፃውያንን፣ በ1880ዎቹ የመሃዲስቶችን ተደጋጋሚ ጥቃቶች መክተው መልሰዋል።

የአድዋ ድል ደግሞ ይህን የነፃነት ቀናዒነት ይበልጥ ከማድመቅ አልፎ የዓለምን ትኩረት ስቧል።
የአውሮፓ መንግሥታት ዲፕሎማቶቻቸውን ወደአዲስ አበባ እንዲልኩ፣ ከኢትዮጵያ ጋር 19 ድንበርን የሚመለከቱ ስምምነቶችን እንዲፈራረሙ አደረጋቸው ። በአርነት ትግሉ መስክ በቅኝ ግዛት ሥር ለነበሩት እህት የአፍሪካ አገሮች ታጋዮችም ኢትዮጵያ ፋና ወጊ መብራታቸውና የራዕይ ምንጫቸው ነበረች።

የአድዋ ድል የፓን አፍሪካን ንቅናቄ መሠረት መሆኑን የኢትዮጵያውያንን የአድዋ ውሎ ከዘከሩ የታሪክ ጠበብት መካከል የዋሽንግተኑ የታሪክ ሊቅ ፕሮፌሰር ራየሞንድ ጆናስ፥ “የአድዋ ጦርነት – የአፍሪካውያን ድል በዘመነ ግዛት” (The Battle of Adwa: African Victory in the Age of Empire, by Raymond Jonas” በሚለው መጽሐፋቸው አስፍረዋል፡፡ በዚህ ጽሁፋቸው

“የአድዋ ድል ለአፍሪካውያን ቅኝ አገዛዝን ታግሎ መጣል እንደሚቻል ያሳየ፣ የኢትዮጵያንም ታላቅነት ያስመሰከረ” ስለመሆኑ ደጋግመው አውስተዋል። ለዚህም ነው የናይጄሪያ ድኀረ ነፃነት የመጀመሪያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶ/ር ናምዲ አዚኪዊ (Nnamdi Azikiwe) “ኢትዮጵያ ጥቁር ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርባት አገር ነች። በዚህ ክፍለ አህጉር ላይ የአፍሪካ ቀደምት አባቶች የመሠረቱት መንግሥት የታሪክ ዋቢ ነች። ኢትዮጵያ ከዘመን ወደ ዘመን እየተሸጋገረች ህልውናዋን ጠብቃ መኖሯ የሚደነቅና መደነቅም ያለበት ነው” በማለት የተናገሩት።

ከአድዋው ድል አርባ ዓመት በኋላ ጣልያን ቂሟን ልትወጣ ወረራ ስታካሂድ በግልጽም ይሁን በተዘዋዋሪ የአውሮፓና የአሜሪካ መንግሥታት ከእሷ ጎን ቆመዋል። በተቃራኒው ድሉ በአፍሪካም ይሁን በተቀረው ዓለም የተቀጣጠለውን የአፍሪካዊነት የትግል ስሜት አነሳስቷል፤ እልህ አጭሯል። በአጠቃላይ መላው ጥቁር ሕዝብ፣ በቁጥር አነስተኛ ቢሆኑም ለፍትህ የታመኑ አውሮፓዊያን ነጮችም ለኢትዮጵያ ያላቸውን ወገናዊነት እንዲያጠናክሩ ጥርጊያውን አመቻችቷል። የነኝህም ጥረት በውጭ የነበረውን ሕዝባዊ ድጋፍ ወደ ኢትዮጵያ ያደላ እንዲሆን አድርጎታል። ባህላዊ እሴቶቻቸውን ያልጣሉ የአፍሪካ ምሁራን ከነበሩባቸው የአህጉሩ ከተሞች፣ ከካርቢያን ደሴቶች፣ ከጥቁር አሜሪካዊያን በኩል ተሰባስበው ወረራው ያጫረባቸውን የመጠቃት ስሜት በይፋ አንጸባርቀዋል።

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ለነበሩት የአፍቃሪ ኢትዮጵያዊነት እንቅስቃሴ መሪዎችም የአድዋው ድል የሞራል እርሾ ሆኗቸዋል። ከእንቅስቃሴው ግንባር ቀደም መሪዎች አንዱ ጀምስ ድዋኔ (James Mata Dwane) ግብጽና ሱዳን ውስጥ ያሉትን ክርስቲያን አፍሪካዊያን ሁኔታ ትኩረት ሰጥተው መፍትሄ ይፈልጉለት ዘንድ ለአጼ ምኒልክ ደብዳቤ የፃፉት የአድዋውን ድል ተከትሎ ነበር።
ስለአድዋ ድል የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ዊንስተን ቸርችል “የካቲት 23 ቀን 1888 የአድዋ ጦርነት ተካሂዶ፥ ጣልያን በኢትዮጵያውያን ሽንፈት ደረሰባት። (ይህም) ሌሎች ሕዝቦችን የሚነካ ሁለት ውጤቶች አስከተለ፤ አንደኛ፥ ሰሜን አፍሪካ ላይ አውሮፓዊ ክብርን ትልቅ ምች መታው። ሁለተኛ፥ በአውሮፓ ፖለቲካ ማንነት ረገድ የኢጣልያ ዋጋ ወደታች ወረደ” ብለው ጽፈዋል።

ዊንስተን ቸርችል ስለ ኢጣልያ ሽንፈትና ውጤቱ ከመጻፍ ይልቅ ስለ ኢትዮጵያ ድልና በአፍሪካና በሌሎቹ ጭቁን አገሮች ዘንድ የኢትዮጵያን ማንነት ሽቅብ መናሩን መግለጽ አልፈለጉም። ይህ ሊሆን የቻለው ምናልባትም አድዋ ላይ የተገኘው ድል ለጥቁር ሕዝቦች ከነጻነት ለመውጣት የተስፋ እርሹ በመሆኑ፣ ለአውሮፓውያኑ የቅኝ ግዛቶቻቸውን ሊያጡ የሚችሉበት ጅምር በመሆኑ ሊሆን ይችላል።
የሆነ ሆኖ አድዋ ላይ የተለኮሰው የድል ችቦ በቅኝ ግዛት ስር ለነበሩት የአፍሪካ አገሮች ቀንዲል ሆኗል። ለዚህም ክብር ለመስጠት 17 የአፍሪካ አገሮች የሰንደቅ ዓላማ ቀለማቸውን ከኢትዮጵያ ወስደዋል። አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ የሆነው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለም ማሊ፣ ጋና፣ ካሜሩን … አገሮች በተለያየ ቅርጽ የአገራቸው መለያ ሰንደቅ አላማ እንዲሆን አድርገዋል።

የቀድሞው የአሜሪካ ፕረዘዳንት ጆንኦፍ ኬኔዲ " በምድር ላይ ጀግና ጥራ ብትሉኝ ቀድሜ ምጠራው የንጉስ ሚኒሊክን ነው ደርባባና ደፋር ናቸው። የነጭ ቅኝ ገዥን በአፍሪካ ምድር ያንበረከኩ ቆራጥ ሰው ። ኢትዮጵያውያን ጀግንነታቸው የመነጨው ከሌላ ሚስጥር አይደለም ከሚኒሊክ ነው። ለዚህም አገሬ አሜሪካ በክብር እዚህ ድረስ ታሪካቸውን በሙዚየም አስቀምጣለች" በማለት ገልፀዋቸው ነበር። . የፈረንሳዊ የቀድሞው መሪ ዣክ ሽራክ"የት አለ ጀግና ለዛውም በአፍሪካ ምድር ከንጉስ ሚኒሊክ በላይ" በማለት ዘክረዋቸው ነበር። . የሊቢያው መሪ ጋዳፊ ከመኖሪያ ሰገነታቸው ባንዱ ክፍል የንጉስ ሚኒሊክ ፎቶ ነበር ከስሩም " ታላቁ ሰው " ይላል። በመላው የአፍሪካ አገራት የንጉስ ሚኒሊክ ታሪክ ትልቅ የመንፈስ መነቃቂያ ነው። . ሪቻርድ ግሪንፊልድ አፄ ምኒልክን "ነገር ከዐይነ-ውኃ የሚያውቅ ብልህ ፖለቲኛ(ዲፕሎማት)" ሲል ይገልፃቸዋል። . አፄ ምኒልክ በታመሙ ጊዜ አንድ ዋሽንግተን ጋዜጣ እንዲህ የሚል ፅሁፍ አወጣ "the most Democratic emperor is sick" ነገስታት በዲሞክራሲ በማይታወቁበት በዚያ ዘመን አፄ ምኒሊክ ግን በአለም ላይ ከነበሩት ነገስታት በሙሉ ዲሞክራሲያዊ የሆነ ንጉስ በፅኑ ታሟል አውሮፓዊያን አሁን አገሩን ሊቀራመቱ እየሞከሩ ነው። ንጉሰ ነገስቱ ምኒልክ እና ንግስቷ እቴጌ ጣይቱ በራሳቸው አገር እና ህዝቦች ዘንድ የሚገባቸውን ክብር እንዳያገኙ 27+ አመት አሻጥር ሲሰራ ቆይቷል... አሁን ግን ያ አብቅቷል! የጥቁር ህዝብ ኩራቶች ዛሬም ወደ ፊትም ከትውልድ ትውልድ ይዘከራሉ!

ለሀገር ልማት ያደረጉትን ተዘርዝሮ የማያልቅ ውለታቸውን መካድ የማይቻል ሆኖ፣ በአሁኑ ጊዜ የአፍሪካ መዲና ለመሆን የበቃችውን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባን በዘመናዊ መዋቅር የቆረቆሩት አፄ ምኒልክ፤ በኢትዮጵያ በርካታ አዳዲስ ጅማሮዎችን በመፍጠር ጉልህ ሚና ነበራቸው፡፡

በግብፆች አስተዳዳሪነት “አቢሲኒያ ባንክ” በሚል ስያሜ የመጀመሪያውን ባንክ፤ የመጀመሪያውን ፖስታ ቤት “አራዳ ፖስታ”፤ በኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ትብብር የተሰራው የመጀመርያው የባቡር መንገድ፣ የመጀመርያዎቹ የስልክና የቴሌግራፍ አገልግሎቶች፤ የመጀመርያው የሞተር መኪና፤ የመጀመርያው የውሃ ቧንቧ እንዲሁም በመንግሥት አስተዳደር የመጀመርያው የሚኒስትሮችን ካቢኔ አቋቁመዋል፡፡

⭐ ስለ ርህራሄያቸው እና ሰባዊነታቸውን በሁለት ምሳሌ ላስረዳ

“አፄ ምኒልክ ደም መፈሰስን እናስቀር ብለው ንጉሥ ጦናን ለመኑት። ንጉሥ ጦና ግን ኃይሉን አሟጦ መዋጋት ስለመረጠ በምኒልክ ሠራዊት ላይ ከባድ ጉዳት አደረሰ። በመጨረሻ ግን ቆሰለና ተማረከ። ዳግማዊ ምኒልክ ጦናን አይቀጡ ቅጣት ከመቅጣትና መንግስቱንም አሽቀንጥረው
ጥለው ሥልጣኑን ለጦር መሪዎቻቸው ከመስጠት ይልቅ ደግነት የተሞላበት ምህረት አድርገውለት እንደሚገብርላቸው ቃል ካስገቡት በኃላ ወደ ሥልጣኑ መለሱት። ምኒልክ ተበቃይ አልነበሩም። ይቅር ባይ፣ በተጨባጭ እውነታ ላይ የተመሰረተ ምክንያታዊ አስተሳሰብ የነበራቸው እና ራሳቸውን እነደ ጥሩ ክርስቲያን የሚያዩ ሰው ነበሩ።

የጎጃሙ ንጉሥ ተክለሃይማኖት አምጸው ጦርነት አነሱና ቆስለው ተማረኩ። ምኒልክ የቆሰለውን ምርኮኛ ገድሎ በመጨረስ ፈንታ ቁስላቸውን ራሳቸው አክመው፣ አጠገባቸው አስቀምጠው አብረዋቸው እንዲመገቡ በማድረግ ፍቅር ነው ያሳዪአቸው። ሥልጣናቸውንም አልወሰዱባቸው፤ ያለማመንታት መልሰውላቸዋል። በርግጥ ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ሩኅሩኅ ነበሩ። አገራቸውን ለመውረር የመጡ ምርኮኞች ጣልያኖችን እንኳ በርኅራኄና በደግ አያያዝ ነበር የያዟቸው።

እኒህን በደግነታቸው፣ በሩህሩህነታቸው፣ በተለይ በይቅር ባይነታቸው የተነሳ ‘እምዬ‘ የተባሉትን ታላቅ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ ላይ የውሸት ትርክት ሲጠጣ የኖረው ጎጠኛ ከመቶ አመት በኋላም የፓለቲካ አጀንዳ አድርጎ ጥላቻውን እየደሰኮረ ተከታይ ሲያራባ ማየት ኢትዮጵያዉያንን ምን ነካቸው የሚያስብል ነው።

ከምኒልክ ሌላ የጋራ ብሔራዊ ጀግና ሊኖረንስ ይችላልን?

ምንጭ ፦ የተለያዩ ፅሁፎች

19/02/2026

አዲስ አበባ ፋሽስት-ጣሊያኖች በለኮሱት እሳት ተቃጥላ ስትጨስ ቀን አይተው ነበር። ሌሊት ደግሞ በቃጠሎዋ ነበልባል እንደ ኮከብ ስታበራ አይተው አንድ ጊዜ አለቀሱ። ዕንባቸው በቁስላቸው ወረደና ፈጃቸው። ለበለባቸው።

“አምላክ ቦታውንና ሕዝቡን ትቶት ሔዷል” አሉ።

የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ/ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

13/02/2026

የግፍ እስረኞቹ አንድ አመት ሞላቸው

በአገዛዙ ታፍነው ያሉበት ቦታ እንኳን እንዳይታወቅ የተደረጉ የአዲስ አበባ ወጣቶች ዛሬ ድፍን አንድ አመት ሞላቸው።
▶ እስከዛሬ ያሉበት አይታወቅም።
▶ ፍርድ ቤት አልቀረቡም።
▶ ለቤተሰቦቻቸው ስላሉበት ሁኔታ የሚያሳውቅ አካል የለም።

ፍትሕ ለወጣቶቻችን!
ፍትሕ ለግፍ እስረኞች!

18/01/2026

እንኳን ለከተራ እና የጥምቀት በአል አደረስዎ!
መልካም በአል!!

12/01/2026

#መረጃ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ 'በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚይዘውን አቋም' የሚገልፀው፤ ከ287 ሺህ በላይ ተከታይ ባለው የፓርቲው የተረጋገጠ (verified) ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ላይ ብቻ ነው።

በሌላ የሚዲያ አማራጮች በቡድንም ሆነ በግል፣ በአመራሩ እና በአባላቱ የሚሰጡ አስተያየቶችም ሆኑ ትንታኔዎች፤ በፓርቲው የተረጋገጠ የፌስቡክ ገፅ ደግመው እስካልተጋሩ ድረስ አስተያየቱ የፓርቲው ዋና አካላት የሆኑት የስራ አስፈፃሚውና የምክር ቤቱ አቋም እንደሆኑ አይቆጠርም።

ድል ለዲሞክራሲ!
#ኢትዮጵያ
Balderas ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ

06/01/2026

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረዎ!
መልካም የገና በአል!

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Address


Addis Ababa