14/08/2023
የሰላም ዋጋ ተመን የለውም!
======================
ስለ ሰላም አብዝቶና ደጋግሞ ማሰብና መጨነቅ ያስፈልጋል። ሰላም በመሻት ብቻም አይመጣም ሰላም ተግባራዊነትን ይጠይቃል፤ የራስን ምላስ አሉታዊ ነገሮችን ከመተኮስ መከልከልን ያሻል።
እጃችንን ቃታ ከመሳብ መቆጠብን ይፈልጋል። ስለ ሰላም ያለመሰልችት መወያየት የግድ ይላል።
የሰላም ዋጋ ተመን የለውም በሰላም እጦት ምክንያት አንድ ኢትዮጵያዊ ሊሞት ይችላል የአንድ ሰው ህይወት ዋጋስ ለመሆኑ ተመን አለው እንዴ? እንዲሁ የሰላም ዋጋ መተመን ያስቸግራል።
ቁጭ ብለው የሰቀሉት ቆሞ ማውረድ የሚያቅጥ ጊዜ ይመጣልና የሰላምን አስፈላጊነት ባለመረዳት አሊያም አርቆ ባለማሰብ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን እረፍት ባንነሳትና የተጀመረውን የብልፅግና ጉዞ ከግብ እንዳይደርስ ሳንካ ባንሆን መልካም ነው።
ሰላማችን እንዳይደፈርስ፣ ብዝሃነትን ያከበረ ዴሞክራሲያዊ አብሮነታችን እንዲጎለብት በጋራ እንቆማለን።
03/04/2023
ከአኩሪ ታሪኮቻችን ለቀጣይ ጉዟችን ተሞክሮ ሰንቀን፤ ከችግሮች ተምረን፣ ጥፋቶችን አርመን ወደ ፊት እንገስግስ !!
የብሔር፣ የባህል፣ የሀይማኖት እና መሰል ብዝሃነቶች የውበታችንና የጥንካሬያችን ምንጭ ናቸው። እነዚህ ብዝሀነቶች ተከብረው ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን የበለጠ እንዲጠናከር ለውጡ በከፈተው የዲሞክራሲ በር የሀሳብ ብዝሃነቶችን በአግባቡ ለማስተናገድ ዘርፈ ብዙ ጥረቶች ይደረጋሉ፣ እየተደረጉም ነው።
በመደማመጥ፣ በመሰማማት፣ ራስን በሌላው ቦታ አድርጎ በማየት፣ ላለመግባባት ሳይሆን ለመግባባት በመወያየት፣ የግልን ወይም የቡድንን ፍላጎት ሳይሆን ህብረ ብሔራዊነትን ታሳቢ በማድረግ የሀሳብ ብዝሀነትን ማስተናገድ ለምንገነባው ጠንካራ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ወሳኝ ነው።
ብሔራዊ መግባባት፣ ብሔራዊ የሽግግር ፍትህ እና ሌሎችም ሁሉን አካታች ጥረቶችም ህብረብሔራዊ አንድነታችንን የሚያጠብቁ በአግባቡ ከተጠቀምንባቸው በእርግጥም ኢትዮጵያውያንን ወደ ተሻለ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ ናቸው።
ተግባራዊ ለማድረግ የታሰበው ብሔራዊ የሽግግር ፍትህ አገራችን ጦርነት ውስጥ በነበረችባቸው ወቅቶች በዜጎች ላይ የተፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመለየት ለታሪካዊ ቁርሾ እንዳይዳርጉን እልባት ለመስጠት ከመደበኛው የፍርድ ቤት ተግባር በተጨማሪ የጎላ ጥቅም እንደሚያስገኝ እምነት ተጥሎበታል።
የሽግግር ፍትህ ረቂቅ ፖሊሲ ወደ ተግባር ሲገባ ተጠያቂነትንና ይቅር መባባልን አንድ እርምጃ በማራመድ እየተገነባ ላለው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት፣ ለህግ የበላይነት መከበር እና ለብሔራዊ መግባባታችን መጎልበትም ምቹ መደላድል ይፈጥራል ተብሎ ይታሰባል።
የፓርቲያችን አመራር፣ አባል፣ ደጋፊ እና አጠቃላይ ህዝባችን በዚህ ወሳኝ ወቅት በተሰማራበት ሁሉ ታሪካዊ አሻራችንን ከማሳረፍ በተጨማሪ የሀገራችን የብልፅግና ጉዞ ለማደናቀፍ ለሚጥሩና ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለማንም የማይበጁ ከፋፋይ አስተሳሰቦችን የሚያራምዱ አካላትን መመከትና ማረም ከሁላችንም ይጠበቃል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለፈችባቸውን አኩሪ ታሪኮች ለቀጣይ ጉዟችን ተሞክሮ ሰንቀን፣ ከችግሮች ተምረን፣ ጥፋቶችን አርመን ወደ ፊት ለመገስገስ በዚህ ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ለኢትዮጵያ ሰላምና ብልፅግና መሰረት የሚሆኑ ለትውልድ ተሻጋሪ ተግባራትን በሀገራዊ ስሜት መከወን ይገባል።
መልካም ሳምንት ይሁንልዎ ‼
Addis Ababa Prosperity Party - ብልፅግና
08/03/2023
መሀለኛዉ የፖለቲካ መንገድ፣ የጋራ መንገድ፣
የፖለቲካ እይታ ሚዛናዊ ሲሆን የሀገር ግንባታዉም ዉኃ ልክ የተደላደለና የተፋጠነ ይሆናል ። የ'መደመር' እሳቤዎች መሀለኛዉንና አካታቹን የፖለቲካ መንገድ የሚከተሉ በመሆናቸው የልዩነት ሀሳቦችን ለማስተናገድ መልካም ዕድል ይፈጥራሉ ።
በአገራችን የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ዉስጥ የተፈጠሩ ስብራቶች ወይም የልዩነትና የቁርሾ መነሻ የሆኑ ጉዳዮችን በ'መደመር ' መንገድ ፣ በፍቅርና በይቅር ባይነት መንፈስ በመሻገር የቁርሾና የጥላቻ ምዕራፍ ይዘጋ ዘንድ ብልጽግና ፓርቲ የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገ ይገኛል ።
አገር የሚገነባዉ በብሩህ ተስፋ፣ በለዉጥ ራዕይ ፣ በአዎንታዊ መንፈስ እና እሳቤዎች ታግዞ በመሆኑ ከፊት ለፊት ያለዉን ብሩህ ተስፋ ታሳቢ በማድረግ ስለትላንቱ ከመቆዘም ይልቅ የትላንትን ወረት አዳብሮ የዛሬንና የነገን መልካም በረከት ማስቀደም ጠቃሚ ነዉ። አዎንታዊ ትርክቶችን ማጠናከር ደግሞ አገርን ለማጠናከር ወሳኝ አቅም ይሆናል ።
የተዛቡ እና አሉታዊ ትርክቶች ደግሞ ከትልቁ ሀገራዊ የጋራ ጉዳይ ይልቅ በጥቃቅን ጉዳዮች እንድንጠመድ ይገፋፋሉ። ራዕያችንን ያስታሉ። ሰበብ እየጠነሰሱ ጥላቻን ማጉላት፣ ቁርሾ እየቀሰቀሱ ብሶትን ማባባስ የጀመርነዉን የለዉጥ ጉዞ ከማስተጓጎል ያለፈ ሀገራዊ ትርፍ አያበረክትም ። ይልቁንም ጠንካራ ሀገራዊ የጋራ ራዕይ እንዳይኖር ያደርጋል። አንድነትን ይሸረሽራል ።
ሚዛናዊ እና መሀለኛዉ የፖለቲካ ሀሳብና አማራጭ የቁርሾና የጥላቻ ሀሳብ የሚያራምዱ ጠርዝ ረገጥ አካሄዶችን ለማቀራረብ የሚያግዝ መሆኑን ብልጽግና ያምናል ። ለተግባራዊነቱም እየሠራ ይገኛል ። የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት እሴት እንዲያብብ ሚዛናዊነት መሠረታዊ ነዉ።
በአጠቃላይ ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን፣ የጋራ ልማትን ለማፈጠን ፣ በትብብርና በመግባባት ላይ የተመሠረተ ዲሞክራሲን ለመገንባት ከዋልታ ረገጥ አስተሳሰብና ተግባር ወደ ሚዛናዊ የመሀል መንገድ የመደመር እይታ መሸጋገር ሀገራዊ ፋይዳዉ ከፍተኛ ነዉ። ስለሆነም በሚያለያዩ ትርክቶች ላይ ከመጠመድ ይልቅ በሚያቀራርቡ ጉዳዮችና ሀገራዊ ተስፋዎች ላይ ማተኮር ለጋራ ሀገራዊ ዕጣፈንታችን ብሩህነት መሠረት ናቸው።
30/01/2023
የብልፅግና የእይታ መነፅሮች ፦
👉 እንችላለን !!
- አቅምን በማለምለም፣ ሀሳብን በመሰብሰብ፣ ፈጠራን በመሻት፣ ለውጥን በመቃረም ያሰብነውን መፈጸም፣ ያቀድነውን ማሳካት እንችላለን ።
👉 እንበለፅጋለን !!
- ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን በሁለመናዊ ብልፅግና የተሞሉ ማድረግ ።
👉 እንለወጣለን !!
- ለውጥ ዘወትር የምንተጋለት አውድ ነው። የመሻሻል፣ አዲስ ነገርን የመላመድ አውድ በብልፅግና እሳቤ ዘወትር ይለመልማል ።
👉 እናሳካለን !!
- ጀምረን አናቆምም፣ አቅደን ሳናሳካ አንቀርም፣ ግባችን ከመንገድ አይቀርም ።
👉 እንደርሳለን !!
- ነገን ከዛሬ የተሻለ ለማድረግ ብሩህ ተስፋን በሰነቀ ጉዞ ታጅበን ወደ ግባችን እንደርሳለን ።
መልካም የስራ ሳምንት ይሁንልዎ !!
28/01/2023
"የሀገራችን ብልፅግና በይደር የምናቆየው ጉዳይ ሳይሆን ሰርክ ልንናፍቀው የሚገባ እና እውን ለማድረግ የምንተጋለት ጉዳይ ነው።"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)
06/12/2022
የኢትዮዽያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች አላማዎች (Preamble):-
• በኢትዮዽያ ዘላቂ ሠላም
• ዋስትና ያለው ዲሞክራሲ እንዲሰፍን፤
• ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገቶች እንዲፋጠኑ፣
• የራስን እድል በራስ የመወሠን መብትን መጠቀም
• አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ በጋራ ለመገንባት መሻት (በነፃነትና በራስ ፈቃድ ላይ ተመስርቶ)
ይህን እና መሰል አላማዎችን ከግብ ለማድረስም የኢትዮዽያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ፅኑ እምነት እንዳላቸው በሕገ መንግስቱ መግቢያ ላይ ተመላክቷል፡፡
05/12/2022
ኢትዮጵያውያን አንድም ብዙም ነን!!
በአንድነታችን ውስጥ ህብረ ብሔራዊነታችን፣ በህብረ ብሔራዊነታችን ውስጥ ደግሞ አንድነታችን አለ። እንዲሁም የኢትዮጵያ ድምቀትና ጥንካሬ ምንጩ ብዝሀነቷ ነው።
ፓርቲያችን ብልፅግና ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ እና ከእውነታው በመነሳት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በመከባበርና በመቻቻል ላይ የተመሰረተ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ለመገንባት ከመጀመሪያው ጀምሮ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል።
አካታች የዴሞክራሲ ስርዓትን ለመትከልና እና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለሰለሰ ጥረት እያደረገ የሚገኘው ፓርቲያችን በቅርቡ በሀገራችን የተፈጠረውን አንፃራዊ የሰላም አየር ዘላቂ ለማድረግም ቁርጠኛ አቋም ሰንቋል። የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድምፅ የሚስተናገድበትና ያለፉ ቁርሾዎችን በይቅርታ በመዝጋት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እንደሚፈነጥቅ የሚጠበቀው ብሄራዊ ውይይታችንም ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላማችን የጎላ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።
ኢትዮጵያውያን አንድም ብዙም ነንና ዘላቂ ሰላማችን የሚረጋገጠው ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አጥብቀን በመያዝ ነው፤ ለዚህም እንዲያግዘን የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን "ህብረ ብሄራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም!!" በሚል መሪ ቃል የፊታችን ህዳር 29 ለ17ኛ ጊዜ በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ላይ በደማቅ ሁኔታ እናከብራለን።