14/02/2026
Waw it great post
TikTok · የጣይቱ ልጅ 🦅 3119 likes, 182 comments. “ #ሒሩትበቀለ @ሸገር”
The blue nile must be used by ethiopians there is no genourausity without our feeling we wrre foolis
14/02/2026
Waw it great post
TikTok · የጣይቱ ልጅ 🦅 3119 likes, 182 comments. “ #ሒሩትበቀለ @ሸገር”
14/02/2026
ስልኩን አንሥቶ ቅርብ ጓደኛው ጋር ደወለና "እናቴ ስለታመመችብኝ ለመድኃኒት የሚሆን ገንዘብ አበድረኝ" ብሎ ጠየቀው።
ጓደኛውም "እማማ ምን ሆኑ?" አለ።
"አቅም አንሷታል መድሀኒቱ የግድ ያስፈልጋታል" በማለት አስረዳው።
ጓደኛውም "እሺ እፈልጋለሁ ከአንድ ሰአት በኋላ ደውልልኝ" ብሎት ስልኩ ተዘጋ።
ደቂቃዎችን በስስት እየቆጠረ አንድ ሰዓት ሆነ። በቀጠሯቸው መሠረት ዳግም ደወለ። ስልኩ ዝግ ነበር! ደጋግሞ ደወለ ስልኩ ግን አይሰራም። ያ የቅርብ ጓደኛው ያ መደገፊያው ችግሩን አስረድቶት ስልኩን ጠርቅሞ መዝጋቱ ቅስሙን ሰበረው። አማራጭ እንደሌለኝ እያወቀ እንዴት ስልኩን ዘግቶ ይጠልፋ ሲል ራሱን በአግራሞት ጠየቀ። ቢያንስ አልቻልኩም አይለኝም ነበር ብሎ በጓደኛው በጣም አዘነ። ምድር ጠበበችው። የሚደገፍበት ሰው አጣ። የሚወዳትን እናቱን እንዴት ይታደጋት?! ምድር ተከፍታ ብትውጠው ተመኘ። በአጽናፈ ሰማይ መጠለል እንደማይችል ያህል ተሰማው። ስለእናቱ በጣም አዘነ። አምርሮም አለቀሰ.......
ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ እየተጋባ በጓደኛው አለመታመን ብስጭትና እናቱን መድሀኒት ገዝቶ መታደግ ባለመቻሉ በሐዘን ተሞልቶ በዕንባ እየታጠበ ወደ ቤት ተመለሰ።
እናቱ በሰላም ተኝታለች። ፊቷ ላይ የእረፍት ስሜት ይነበባል። አጠገቧ ሊገዛው ፈልጎ ገንዘብ በማጣቱ ምክንያት ሳይገዛው የተመለሰው የመድሀኒት ብልቃጥ ተቀምጧል። ሁኔታው ግራ ቢገባው እህቱን "መድሃኒቱን ማን ገዛው?" አላት ብሎ ጠየቃት።
"ጓደኛህ እየሮጠ መጥቶ ማዘዣውን ወስዶ መድሀኒቱን ገዝቶ አመጣው። እማም መድሀኒቱን ስትወስድ ወዲያው ተሻላት።" አለችው።
ዓይኖቹ የደስታ እንባን አቀረሩ። ድብልቅልቅ እያለበት ወደ ጓደኛው ቤት በሩጫ ገሰገሰ። በሩን ከፍቶ ወደ ውስጥ ገባ።
"ደግሜ ደጋግሜ ደወልኩልህ ስልክህ ግን ዝግ ነበር?" አለው።
"አዎ ስልኬን ሸጬ ለእማማ መድኃኒት ስለገዛሁበት ነው ዝግ የሆነው" ሲል መለሰለት።
ለሁላችሁም እንዲህ ያለ ጓደኛ ይስጣችሁ!
ከተመቻችሁ👉
29/11/2025
One of the sight in Bale mnp
21/11/2025
It is well known
19/09/2025
that is true
kne yemeeskral
27/03/2025
በ100 ሄክታር ሰብል መሀል ላይ በድብቅ የተዘራ አደንዛዥ እፅ...
ቤት ለቤት በተደረገ ፍተሻ 158 ኪሎ የካናቢስ ዘር ተይዟል፡፡
**********
በምዕራብ አርሲ ዞን ባሉ ሶስት ወረዳዎች በአንድ መቶ ሄክታር መሬት ላይ በድብቅ በሰብሎች መካከል የተዘራ አደገኛ ዕፅ እንዲወገድ መደረጉ ተሰምቷል::በሻሸመኔ ፣ በነጌሌ አርሲ እና በሾላ ወረዳዎች ላይ ባሉ አስራ ሁለት ቀበሌዎች ላይ ከበቆሎ እና ማሽላ አዝርቶች ጋር በድብቅ በመቶ የተዘራ አደንዛዥ ዕፅ በዘመቻ መልክ ተመንጥሮ እንዲቃጠል መደረጉን የምዕራብ አርሲ ዞን ፖሊስ አሳውቋል፡፡
በድብቅ የተዘራ አደገኛ አደንዛዥ ዕፅ ከማሳው ላይ እንዲወገድ ከመደረጉ በተጨማሪ በአርባ ስምንት ሄክታር መሬት ላይ ተዘርቶ የተከማቸ እና 157 ኩንታል የደረቀ አደገኛ ዕፅ በቁጥጥር ስር ውሎ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት እንዲቃጠል ተደርጓል::በነጌሌ አርሲ እና በሻላ ወረዳዎች በመንግስት ተሽከርካሪ ጭምር ሲጓጓዝ የነበረ አደገኛ አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገለፁት ኃላፊው በሻሸመኔ ወረዳ ከሸቀጣሸቀጥ ቁሳቁሶች ጋር በመደባለቅ 60 ኩንታል ሀሺሽ በድብቅ ሲጓዝ በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡
ቤት ለቤት በተደረገ ፍተሻ 158 ኪሎ ግራም ለዘር የተቀመጠ አደገኛ ካናቢስ የተሰኘ ዕፅ በቁጥጥር ስር ውሎ እንዲቃጠል የተደረገ ሲሆን የአደገኛ ዕፅ ዝውውር የምርት ሂደቱ ላይም ከመንግስት መዋቅር አንስቶ ነጋዴዎች አሽከርካሪዎች እና የፀጥታ አካላት ጭምር በተዋረድ እጃቸው መኖሩን የምርት ሂደቱ እና ዝውውሩ እንዳይቆረጥ እንዳደረገው የተናገሩት ኃላፊው አርሶ አደሩ ከሰብል ምርት ይልቅ ከአደገኛ ዕፅ የሚያገኘው ጥቅም የተሻለ እንደሆነ በተደራጁ ነጋዴዎች ስለሚነገረው ምርቱን ከሰብል ጋር እያመረተ እንደሚገኝም ተገልጾአል፡፡
በማሳ ላይ አደገኛ ዕፅ በድብቅ የሚያመርት አርሶአደር እርሻ መሬቱ እስከማጣት የሚያደርስ ቅጣት እንደሚያጋጥመው በማስጠንቀቅ አደገኛ ዕፁን በማምረት እንዲሁም በማዘዋወር ተጠያቂ የሆኑ ግለሰቦች የምርመራ መዝገባቸውን ለሚመለከተው የፍትህ አካል ተልኮ በቅርብ ቀን ውሳኔ እንደሚያገኝም የአርሲ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
https://www.youtube.com/c/ShegerTimesMedia
16/08/2024
waw hileye
"የምንፈልገው ክርክር ሳይሆን በእኛ ምክንያት ህዝቡ ውጤት አጥቷል ብለው ስልጣን እንዲለቁ ነው" - ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ
***************
ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ "ለበርካታ ዓመታት ችግሩ ሳይታረም በመቆየቱ በሶስት ኦሎምፒክ ሶስት የወርቅ ሜዳሊያ ብቻ ለማግኘት ተገደናል" በማለት በኢትዮጵያ የውጤት ቀውስ የተሰማውን ቁጭት ገልጿል።
የፓሪስ ኦሎምፒክ ውጤት ላይ የታዩ ችግሮች እና ዘላቂ የመፍትሄ ሀሳቦች በሚል ርዕስ ኢቢሲ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የቀጥታ ውይይት አዘጋጅቷል።
የሁለት ኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቱ ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ በውይይቱ ላይ "የእኛ ተፎካካሪዎች በሶስት ኦሎምፒክ 14 ወርቅ ወስደዋል፤ እኛ ደግሞ አሁን ኦሎምፒክ ለተሳትፎ ነው እየተባልን ነው" ሲል ተናግሯል።
"አንድን ስፖርተኛ ሂድና አሸንፍ ብለን ከመላካችን በፊት የሚመራህ አካል ፍትሃዊ ነው ብለን ማሳመን አለብን ያለው ኃይሌ ኢ-ፍትሃዊ የሆነ አስተዳደር የስፖርተኞችን በራስ መተማመን እና የማሸነፍ ፍላጎት ይቀንሳል" ብሏል።
"የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ በቻሉት ልክ ሞክረዋል ነገር ግን አልተሳካም" ብሏል ሻለቃ ኃይሌ።
"አሁን ከአሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) ጀምሮ ካሉት የተቋሙ አመራሮች የምንፈልገው ክርክር ሳይሆን ህዝቡን አስቀይመናል፣ በእኛ ምክንያት ህዝቡ ውጤት አጥቷል ብለው ስልጣን እንዲለቁ ነው" በማለት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ የመፍትሔ ሀሳቡን ጠቁሟል።
በሐዋርያው ጴጥሮስ
waw
10/08/2024
my turkish group on a tour on the way to ADADI .Marian All are T embessy member
Spotlight on a day 2 new items · Memory by Tsegaye Tirfe