Yeka Communication-የካ ኮሙኒኬሽን
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yeka Communication-የካ ኮሙኒኬሽን, Government Organization, Addis Ababa.
01/06/2026
የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-
• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤
በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።
The people of Ethiopia are an extraordinary and remarkable people. Other than the Creator, who can truly know and assess our people in their entirety? Through this year’s election, Ethiopians have once again shown the world that they are a people with a rich culture, deep patriotism, and the ability to safeguard the common good.
On this historic day:
* Citizens who were not intimidated by the cold and darkness of the night,
* Who were not deterred by the midday sun or sudden rain,
* Whom weddings, funerals, childbirth, and other social obligations did not prevent from participating,
* Who were not wearied by long lines,
* Whose physical disabilities did not stop them from casting their vote,
* Those whose illness and old age did not prevent from witnessing the hope of their country,
* Who were not exhausted by carrying their infant children; the future inheritors of the nation,
* And above all, whom the shouting and threats of enemies could not intimidate or stop;
The perseverance you demonstrated amid many challenges and hardships, against all odds, was a contribution made for democracy and for the very survival of the nation. For this, you deserve heartfelt gratitude.
It is a privilege to serve such a people. Therefore, may those who have been elected honor the trust placed in them and serve this people, with integrity and sincerity! A people who have paid a great price for the democratic system. May you be worthy of that responsibility.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
01/06/2026
01/06/2026
በምሽት ተሰልፈው ለሚገኙ መራጮች ወ/ሮ መሪማ ታደሰ በነፃ ምግብና ውኃ እያቀረቡ ነው
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ መሪማ ታደሰ፤ የምርጫ ቦርድ የድምፅ መስጫ ሰዓቱን ማራዘሙን ተከትሎ በምሽት ተሰልፈው ድምፃቸውን ለመስጠት እየተጠባበቁ ላሉ ነዋሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ምግብና ውኃ በነፃ እያቀረቡ ነው፡፡
ወ/ሮ መሪማ መራጩ ሕዝብ ሳይሰለችና ሳይደክም የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ ለማበረታታት ቆሎ፣ ውኃ፣ ዳቦ እና ሌሎች ቀለል ያሉ ምግቦችን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡
በአሁኑ ወቅትም በክፍለ ከተማው የምርጫ ክልል 28 ሥር በሚገኙት የምርጫ ጣቢያዎች በርካታ መራጮች አሁንም ድረስ ተሰልፈው ተራቸውን እየተጠባበቁ መሆናቸው ታውቋል፡፡
01/06/2026
በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የምርጫ ክልሎችና የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች ድምጽ እየሰጡ ይገኛሉ::
01/06/2026
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሂደት በማስፈጸም ላይ መሆኑ ይታወቃል። ቦርዱ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ 12:00 ሰዓት ሠልፍ ላይ የነበረው ድምፅ ሰጪ ድምፅ ሰጥቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እንደሚቀጥል ያሳውቃል።
ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 49 (4) መሠረት ቦርዱ በልዩ ሁኔታ የድምፅ መስጫ ሰዓት ሊያራዝም እንደሚችል ይደነግጋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Address
Addis Ababa
1000
