Addis Ketema Youth & Sport Office

Addis Ketema Youth & Sport Office

Share

የወጣቶችን ጉዳይ በወጣቶች የላቀ ተሳትፎ እናረጋግጣለን

Photos from Addis Ketema Youth & Sport Office's post 06/05/2025

የአዲስ ከተማ እግር ኳስ ቡድን በ3ኛ ዙር የውድድር መርሐ ግብር 1ኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋገጠ::
*****************
ሚያዚያ 28-2017ዓም

በኢትዮጵያ 1ኛ ሊግ እየተሳፈ የሚገኘዉ የአዲስ ከተማ የወንዶች እግር ኳስ ክለብ በ1ኛ እና በ2ኛዉ ዙር ዉድድር 2ኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ የቻለ ሲሆን ወደ ከፍተኛ ሊግ ለመቀላቀል የ3ኛ ዙር የውድድር መርሃ-ግብር 1ኛ ደረጃ በመያዝ ወደ ቀጣዬ ዙር ማለፉን አረጋግጧል።

የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዮናስ ስዩም እንዳሉት በ1ኛ ሊግ ዉድድር መርሀ ግብር ተሳታፊ ከነበሩ ክለቦች አዲስ ከተማ ከአቃቂ ቃሊቲ ጋር ለዋንጫ በማለፉ የተደለደለ መሆኑን እና ለዋንጫ ወይም ለደረጃ ከደረሰ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የሚቀላቀል ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ዮናስ አክለውም መርኬዎቹ እያስመዘገቡት ያለው ውጤት የሚገባቸውና የልፋታቸው ውጤት መሆኑን ጠቅሰው ባስመዘገቡት ውጤት ሳይኩራሩ ለበለጠ ውጤት መትጋትና መረባረብ እንደሚገባቸውና የስፖርቱ ማህበረሰብ በየጫወታው በመገኘት የተለመደውን ሞራላዊ ድጋፍ እንዲሰጡ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል::

30/03/2025

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታይ የክ/ከተማችን #ወጣቶች እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የዒድ አል ፈጥር በዓል ሙስሊሙ ወገናችን ታላቁን የረመዳን ወር በፆም እና ፀሎት በማሳለፍ ከራሱ አልፎ ለሀገራችን ሰላም ፣ ፍቅር እና አንድነትን እንዲሁም በረከትን ከፈጣሪዉ ሲጠይቅ ቆይቶ የፆሙ ወቅት መገባደዱን ተከትሎ የሚከበር ታላቅ በዓል ነው፡፡

በእስልምና አስተምህሮ ሰላም ፣ ኅብረትና አንድነት ልዩ ስፍራ እንደሚሠጠዉ ይታወቃል ፥ ስለሆነም በፆሙ ወቅት ልዩነቶቻችንን ሳይገድቡን የኢፍጣር ማዕድን በአብሮነት እንደተቋደስነዉ ሁሉ ፣ ሁለንተናዊ ብልፅግናችንን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ግባቸዉን እንዲመቱ ከወትሮዉ በተለየ ሁኔታ የሂደቱ ዳር ተመልካች ሳይሆን ተዋናያን ጭምር መሆን የሚገባን ምዕራፍ ላይ መሆናችንን መገንዘብ ይኖርብናል ፡፡

በተመሳሳይም ይህ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ #ህብረታችን #መተባበራችን እና #መደጋገፋችን አስፈላጊ የሆነበት እንደ መሆኑ በዓሉን ስናከብር ለዘመናት የገነባነውን የሰላም ፣ የመቻቻል ፣ የመደጋገፍ እና የአንድነት እሴቶቻችንን በሚያጠናክር መልኩና የተቸገሩ #ምስኪኖችን በመደገፍና በመዘየር እንዲሆን እያስታወስኩ በዓሉ የሀሴት ፣ የፍቅር ፣ እና የመተሳሰብ እንዲሆን ልባዊ ምኞቴን በራሴ እና /ቤት ስም እገልጻለሁ 🙏

!

Photos from Addis Ketema Youth & Sport Office's post 12/02/2025

"የላቀ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለከተማችን ወጣት"

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ወጣት ማህበር 8ኛ መደበኛ ጉባኤዉን አካሄደ።

በፕሮግራሙ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ኤርሚያስ ወንድሙ ወጣት ማህበሩ ባለፉት ጊዜያት የወጣቱን ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከከተማ እስከ ወረዳ ወጣቶች በማሳተፍ በርካታ ተልዕኮዎችን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፤ ወጣቶች በሀገራቸው የለውጥ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ሚና እንዲኖራቸው በማድረግ ግዜውን የዋጀ ጠንካራ ማህበር ለመፍጠር መቻሉን ገልፀዋል።

የወረዳ 1 ወጣት ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት ወጣት አብዱራህማን ካሱ በበኩላቸዉ ወጣት ማህበራችን የተለያዩ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን በመስራት የሚታወቅ ሲሆን የወረዳውን ወጣቶች ከማሳተፍ አኳያ እጅግ አመርቂ ስራዎችን እየሰራ ያለ ማህበር ሲሆን በቀጣይም ከዚህ የበለጠ እንሰራለን በማለት መልክት አስተላልፈዋል።

ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች የወረዳዉ አመራሮችና ከወጣት ማህበሩ ሰብሳቢ በቂ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የወጣት ማህበሩን ስራ አስፈፃሚዎች መርጠዋል።

በመጨረሻም ወጣት ማህበሩን በተለያዩ ስራዎች ላይ እገዛ ሲያደርጉ ለነበሩ አካላት የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

የካቲት 5/2017ዓ.ም
የአዲስ ከተማ ወጣቶች ማህበር ኮሚኒኬሽን

Photos from Addis Ketema Youth & Sport Office's post 11/02/2025

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሰራተኞች እግር ኳስ ውድድር ዛሬም እንደቀጠለ ነው።
ቀን 04/06/2017
⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሰራተኞች እግር ኳስ ውድድር ተፋላሚው ቡድን እልክ አስጨራሽ እና በማራኪ ጨዋታ መለየቱ ታውቋል። ዛሬ በነበረው ፕሮግራም ወረዳ 11 ከወረዳ 8 እና ዋና ስራ አስፈፃሚ (ሹፌሮች) ከወረዳ 12 ለዋንጫ ለማለፍ በነበረው ፍልሚያ ውጤት የመጀመሪያው ጨዋታ ሙሉ ሰዓት 1ለ1 በመለያየታቸው በፍፁም ቅጣት ምት ወረዳ 11 7-6 ወረዳ 8
በሁለተኛው ጨዋታ ዋና ስራ አስፈፃሚ (ሹፌሮች) ከወረዳ 12 በነበረው ጨዋታ የክፍለ ከተማው ተወካይ ቡድን በሰፊ የጎል ብልጫ 7ለ2 ማሸነፍ ችሏል።

Photos from Addis Ketema Youth & Sport Office's post 04/02/2025

⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️
ወረዳ 12 እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፑል(ሹፌሮች) ግማሽ ፍፃሜ መግባት ችለዋል።
ቀን 27/05/2017
⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️
ተጠባቂው ደርቢ በዋና ስራ አስፈፃሚ ፑል (ሹፌሮች) አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሰራተኞች እግር ኳስ ውድድር እልክ አስጨራሽ በሆነ መልኩ ግማሽ ፍፃሜ የሚገቡ ቡድኖች ተለይተዋል። ዛሬ በተደረጉ ውድድሮች ወረዳ 9 ከ ወረዳ 12 እና ፐብሊክ ፑል ከዋና ስራ አስፈፃሚ ፑል(ሹፌሮች) ያገናኘ ሲሆን ውጤት ወረዳ 12 በፍፁም ቅጣት ምት ማሸነፍ ሲችል የክፍለ ከተማው ደርቢ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፑል(ሹፌሮች) 2-1ፐብሊክ ፑል በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

Photos from Addis Ketema Youth & Sport Office's post 03/02/2025

የአዲስ ከተማ ክፉለ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት በሀገር አቀፉ እና በከተማ አቀፉ ብቸኛ የሆነዉ የባንኮች ካኘ እግር ኳስ ዉድድር የ3ኛ ሳምንት መርሀ ግብር ዉድድር 4 ጨዋታወች በአበበ ቢቄላ መታሰቢያ ስታዲየም እና ጀኔራል ዊንጌት ኮሌጅ ተካሂዷል።
-ግሎባል ኢትዮጵያ ባንክ -2ለ1- ዳሽን ባንክ
-ዘምዘም ባንክ -3ለ0-ወጋገን ባንክ
-አዋሽ ባንክ -2ለ0-አብሲንያ ሲያሸንፉ ኦሮሚያ ህብረት ባንክ -4ለ1- ኦሮሚያ ባንክ በማሸነፉ የ4ኛ ሳምንት በሰላም መጠናቁቁን የወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዮናስ ስዮም አረጋግጠዋል።

Photos from Addis Ketema Youth & Sport Office's post 17/01/2025

የኢትዮጵያ የሴቶች ከፍተኛ ሊግ 11ኛ ሳምንት

⌚️ 85'

✅ 2-4
58' ቤተልሄም ቤዛዬ 32' ምህረት ተካልኝ
70' ቤተልሄም ደበበ 45' ሠላም ለማ
56' ሠላም ለማ
60' ሠላም ለማ

🏟ሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም

Photos from Addis Ketema Youth & Sport Office's post 12/01/2025

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት የሚካሄደው የባንኮች እግር ኳስ ውድድር በይፋ ተጀመረ::
******
ጥር 4-2017ዓም

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተጀመረው የባንኮች ካፕ እግር ኳስ ዉድድር 10 ባንኮች የሚሳተፉበት ሲሆን የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በሐገር አቀፍም ሆነ ከተማ አቀፍ ብቸኛ የሆነው 3ኛ ዓመታዊ ዉድድር በይፋ ተጀምሯል::

ዉድድሩን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዮናስ ስዩም መንግስትና ገዥዉ ፓርቲ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በማስፋፋት ለሁሉም ማህበረሰብ ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በሀገር አቀፉም ይሁን በከተማ አቀፉ ደረጃ ስፖርቱ ተደራሽ ያልሆነባቸዉን ተቋማት በመለየት እንዲህ አይነት ዉድድሮችን ማካሄድ ዜጎች ጤናማ፣ ብቁና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ አይነተኛ ሚና ይኖረዋል ሲሉ ገልፀዋል።

አጠቃላይ የዉድድሩን ሁኔታ አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የአዲስ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት የስፖርት ማህበራት ማደራጀትና ዉድድር ቡድን መሪ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዳኝነት አበበ በበኩላቸዉ ጽ/ቤቱ በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በአመቱ ከ20 በላይ ክፍለ ከተማ አቀፍ የኩነትና ዉድድሮችና 6 ከተማ አቀፉ መደበኛ ዉድድሮች አቅደን እያከናወን ሲሆን ዛሬ በ2015 ለመጀመሪያ ጊዜ በ6 ባንኮች የተጀመረዉ አዲስ ከተማ የባንኮች ካኘ ዉድድር ዛሬ በ2017 10 ባንኮች የተሳተፉበት ዉድድር ተጀምሯል።

በመክፈቻው ቀን ሁለት ዉድድሮች የተካሄዱ ሲሆን ወጋገን ባንክ -ከ- ከኦሮሚያ ባንክ በተደረገ ጨዋታ ኦሮሚያ ባንክ 4ለ2 ሲያሸንፍ እንዲሁም አብሲንያ ባንክ ዘምዘም ባንክን 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

Photos from Addis Ketema Youth & Sport Office's post 18/12/2024

የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ

⏰ የሙሉ ሰዓት ውጤት'

✅ 3-0
21' ገዛሽኝ የኋላሸት
35' ምህረት ተካልኝ
88' ቃልኪዳን ፈይሳ

የዋናው ስፖርት የጨዋታ ኮከብ
🏆 ከአዲስ ከተማ

ምንጭ :-

👉 https://t.me/Dagu_Sport

Photos from Addis Ketema Youth & Sport Office's post 17/12/2024

በበጀት ዓመቱ የመንግስት ሰራተኞች እግር ኳስ ውድድር ተጀመረ።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በስፖርት ተሳትፎና አካል ብቃት ቡድን አስተባባሪነት 12ቱም ወረዳ እና ከክፍለ ከተማ 4ቱ ፑል በድምሩ 16 ቡድን የተሳተፉበት በአራት ምድብ በዛሬው እለት በኒኮላ ሜዳ በመክፈቻው ወረዳ 8 ከወረዳ 6 ያገናኘ ሲሆን ውጤቱም ወረዳ 8 6ጎል በማስቆጠር ወረዳ 6 ማሸነፍ ችሏል!!!

Photos from Addis Ketema Youth & Sport Office's post 10/12/2024

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ወጣቶች ማህበር ከሰው ተኮር ተግባራት አንዱ የሆነውን የአንድ አቅመ ደካማ ቤት እድሳት አስጀመረ።

በሰው ተኮር የቤት እድሳት ማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ የክ/ከተማው ወጣቶች ማህበር ም/ሰብሳቢ ወጣት ኢሳ ሰኢድን ጨምሮ የወረዳው የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የወረዳው ወጣት ማህበር አመራሮችና አባላት በተገኙበት ተከናውኗል።

ሰው ተኮው ተግባራት በማህበረሰባችን የመረዳዳት፣ የመተጋገዝ፣ የአብሮነትን እሴትና ባህል ከማጎልበት ባለፈ በተጨባጭ የማህበረሰባችንን ማህበራዊ መስተጋብሮች ለማስቀጠል ትልቅ ሚና ያላቸው ከመሆን ባለፈ ለማህበረሰብ ለውጥ መሰረት የሆኑ ተግባራት በመሆናቸው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ወጣት ኢሳ ሰኢድ መልዕክቱን አስተላልፏል።

ህዳር-30-2017 ዓ.ም
ምንጭ :- የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶች ማህበር ኮሚኒኬሽን

Photos from Addis Ketema Youth & Sport Office's post 06/12/2024

አለም አቀፍ የትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች መታሰቢያን አስመልክቶ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የደም ልገሳ ተካሄደ፡፡
***************
ህዳር 27-2017ዓም
በክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አስተባባሪነት አውቶብስ ተራ አካባቢ በተካሄደው የደም ልገሳ ፕሮግራም በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች አለማቀፉን የትራፊክ ተጎጂዎች ቀን በማስመልከት ደም ልገሳ ተደርጓል፡፡

በእለቱ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዮናስ ስዩም የትራፊክ ሕግን የማክበር ጠንካራ ባህል መገንባት እንደሚገባ ገልፀው መላው ህዝባችን የትራፊክ ህግጋትን በማክበር ከአደጋ የሚቆጠብበትን ሁኔታ ለመፍጠር ተከታታይነት ያላቸው ተግባራት መከናወን ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን እንደሚያጡ የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት መረጃ ያሳያል፡፡

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Addis Ababa