Mehur Tutorial Program - ምሁር ቱቶርያል ፕሮግራም

Mehur Tutorial Program - ምሁር ቱቶርያል ፕሮግራም

Share

Mehur Tutorial Program is a Tutorial Service providing wing of Mehur Ethiopia Social Enterprise.

We provide Academic as well as Language Tutorials for KG - 12 students. A well trained and highly qualified Tutors of both genders which can make the learning environment very easy, practical and enjoyable are available with us.

26/04/2023

Equipping your children with both Academic Knowledge and Life Skills needs high Experts. Mehur Tutors are ready to help you on this.

ልጆችዎን በአካዳሚክ እውቀት እና በህይወት ክህሎቶች ማስታጠቅ ብቁ ባለሙያዎችን ይፈልጋል። የምሁር አስጠኚዎች በዚህ ላይ እርስዎን ለማገዝ ዝግጁ ናቸው።

contact us: 0924222272/ 0964222272

26/04/2023

"Sometimes, you just have to start all over differently." Bernard Kelvin Clive

Congratulations for the team who accomplished the rebranding process successfully. After taking a long working time on rebranding our Company, finally Mehur Tutorial Program - ምሁር ቱቶርያል ፕሮግራም is here and we will keep posting valuable articles and posts regarding to Empowering the Generation with Transformative Education.

This page will be used to create awareness about Transformative Education, Effective Parenting, proper Child Growth and other important topics

We are the Tutorial Service Providing wing of Mehur Ethiopia, a youth led Social Enterprise based in Ethiopia. (Visit Mehurethiopia.com)

Stay Tuned to get our first post in our page. It will be released at 08:30 PM tonight.

We really appreciate your patience as being our audiences. In the mean time please send us your feedbacks , comments and suggestions since it is very crucial for our growth and fullfil your needs with our services.

Mehur Ethiopia Team




20/11/2021

20th November World children's day ―ህዳር 11 የአለም የልጆች ቀን

ኢትዮጵያዊው የልጆች አባት አባባ ተስፋዬ በዘወትር ፕሮግራማቸው ላይ «ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች» ይሉ ነበር።ልክ ነው ልጆች ዘር ተዘርቶ እንደሚፈሩ ፍሬዎች ናቸው። ዘሩን የምንዘራው እኛ ወላጆች፣ በአካባቢያችን የሚገኘው ማኅበረሰብ እንዲሁም ት/ቤቶች ናቸው። ለመሆኑ እየዘራንባቸው ያሉት አዝርዕት ምንድን ናቸው? ተወያዩበት!! ለማንኛውም መልካም ፍሬ ለማፍራት መልካም ዘር አስፈላጊ ነው ፤ በአሽዋማ መሬት ላይ ጠጠር ዘርቶ የመብል ፍሬ መጠበቅ ሞኝነት ነውና የዛሬ አበባ የሆኑ ልጆቻችንን መልካሙን እሴቶቻችንን ዘርተንባቸው ፍቅር ፣ መተሳሰብ፣ አንድነት ፣ ለጋስነት፣ ቸርነት ፣ ኢትዮጵያዊነት የተባሉ ፍሬዎችን እንዲያፈሩ የበኩላችንን ድርሻ እንወጣ።

ውድ ወላጆች ልጆቻችንን እቅፍ አድርገን እንዲህ እንበላቸው

«አንተ/ አንቺ እኮ ዕንቁዬ ነሽ ፤ የአንተ/አንቺ ወላጅ በመባሌ ሁሌም እኮራለሁ፤ ከራሴ አስበልጬ እወድኃ/ሻለሁ እንደ ዓይኔ ብሌንም እሳሳልኃ/ሻለሁ፤ አምላክ አንተን/አንቺን ልጅ አድርጎ ስለሰጠኝ ሁሌም አመሰግነዋለሁ፤ በጥበብ ፣ በሞገስ ያሳድግልኝ በጤናም ጠብቆ ትልቅ ደረጃ ያደርስልኝ ዘንድ የዘወትር ጸሎቴ ነው። ሁሌም ቢሆን እኔ ወላጅህ/ሽ ከጎንህ/ሽ እንዳለሁ አስብ/ቢ ። ልጄ ሆይ ውድድድድ አደርግኃ/ሻለው።» ከዚያም እንሳማቸው

መልካም የልጆች ቀን! !

Happy children's Day!!

«ኑ በሥነ ምግባርና ፣ በዕውቀት የታነጸ ምሁር ትውልድን ለኢትዮጵያችን ለማፍራት በጋራ እንስራ!»

ምሁር የእናንተው ቤተሰብ




Photos from Mehur Tutorial Program - ምሁር ቱቶርያል ፕሮግራም's post 19/11/2021

ሠላም ውዶች

ልጆቻችን ትምህርት ከጀመሩ ሰነባበቱ አይደል? ኸረ እንደው አንዴት ይዟቸዋል? ፈተናውም ተቃረበ አይደል? እኛ ወላጆችስ በምን ያህል ቅርበት እየተከታተልናቸው ነው? «አዪ የእኛን ወላጆችስ ነገር ተዉት ፤ ሕይወታችን ሩጫ ብቻ ሆኗል፤ ጠዋት ወጥቶ ማታ አምሽቶ ልጆች ከተኙ በኋላ መግባት፤ ዘንድሮስ የልጆቼ ትምህርት እንጃልኝ» ያላችሁ አላችሁ አይደል? አንዳንዶች ደግሞ «ይገርማችኋል ልጆቼን ለማስጠናት እሞክራለሁ ነገር ግን የሚያስተምሯቸው ነገር ጫን ብሏል፤ ካንዳንዱ ሀሳቦች ጋርማ ተፋጠን ነው የሚመሸው» ያላችሁም ትኖራላችሁ። ስለዚህ ታዲያ መፍትሔው ምንድን ነው?

መልካም……… ያዙ እንግዲህ

ምሁር የትምህርት ማማከር አገልግሎት በህጋዊ መልኩ ብቃት ያላቸውን የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን አስጠኚዎችን በመሰብሰብ የእናንተን ጭንቀት በመረዳት በተመጣጣኝ ዋጋ ለልጆችዎ በቤታቸው የማስጠናት አገልግሎት መስጠት ከጀመረ አመት አልፎታል። አሁንም አቅማችንን እና ተደራሽነታችንን ከመቼውም ጊዜ በላይ በማጠናከር ልጆችዎን እንደ ወንድም እና እህት በመሆን ለማገዝ ለመርዳት ተዘጋጅተናል። በማስታወቂያው ላይ በተገለፁት ስልክ ቁጥሮች ወይም ቢሮኣችን በአካል በመገኘት የልጆችዎ ደኅንነትን ታሳቢ አድርገው የሚፈልጉትን አስጠኚ በመቅጠር ይስተናገዱ።



«ኑ በሥነ ምግባር እና በዕውቀት የታነጸ ምሁር ትውልድን ለኢትዮጵያችን ለማፍራት በጋራ እንስራ!!!»

ምሁር ቤተሰብዎ





15/09/2021

በአዲስ አበባ የ2014 ዓ.ም የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት ትምህርት ጥቅምት 1 ቀን 2014 እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

ከትምህርት ቢሮው የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው፥ የ2014ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት ትምህርትን ለማስጀመር መምህራን በየትምህርት ቤታቸው እስከ መስከረም 18 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ሪፖርት በማድረግ የመምህራን ጉባኤ ይደርጋል፡፡

በሁሉም ትምህርት ቤቶች የ2014 ዓ.ም የትምህርት ሳምንት ከመስከረም 24 እስከ 28 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚካሄድም ገልጿል፡፡

የ2014 ዓ.ም የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት የማጠቃለያ ፈተናም ከየካቲት 14 እስከ የካቲት 18 የሚሰጥ ሲሆን፥ ከየካቲት-21 እስከ የካቲት-25 ቀን 2014 ዓ.ም ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ዝግ ሆኖ እንደሚቆይም አመላክቷል።

የሁለተኛው መንፈቅ ዓመት ትምህርት ከየካቲት 28 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ መሆኑን የትምህርት ቢሮው የትምህርት ካላንደር ያሳያል፡፡

ትምህርት ቢሮው አባሪ አድርጎ በላከው ደብዳቤ ላይ ያለው ካላንደር እንደሚያሳየው እያንዳንዱ መንፈቅ ዓመት 99 የትምህርት ቀናት የሚኖሩት ሲሆን ይህም የትምህርት ቀናት በሳምንት 5ቱን ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ያለፈረቃ የሚከናወን መሆኑን ያመለክታል።

ምሁር የእናንተው ቤተሰብ ልጆችዎን በጥናት እና ቤት ውስጥ በሚኖር ክትትል በብቁ አስጠኚዎቹ ሊደግፋቸው ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ሲገልፅ በደስታ ነው።

«ኑ በሥነ ምግባር እና በዕውቀት የታነፀ ትውልድን ለኢትዮጵያችን ለማፍራት በጋራ እንስራ!!!»

ምሁር እፎይታዎ

13/09/2021

እንኳን ለ 2014 ዓ·ም በሰላም አደረሳችሁ እያልን ትውልድን በእውቀት እና ስነ ምግባር አንፆ በት/ቤቶች እና በወላጆች መካከል ድልድይ በመሆን የትምህርት አቀባበል ላይ እንዲሁም በበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ የሚሰማራ ሀገር ወዳድ ትውልድ ለማፍራት የሚሰራው የዘወትር አጋራችሁ ምሁር የትምህርት ማማከር አገልግሎት በአዲሱ አመትም አገልግሎቱን በማስፋት በሚፈለገው መልኩ ተደራሽ ለመሆን ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ እናንተ መጥቷል።

በማንኛውም ደረጃ ላይ ላሉ ልጆችዎ ብቃት እና ልምድ ያላቸው የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ሴት እና ወንድ አስጠኚዎችን በህጋዊ መንገድ ይቅጠሩ። ምሁር ልጆችዎ በቤት ውስጥ የሚደረግላቸውን የትምህርት ጥናት እና የሰብዕና ግንባታ ድጋፍ ከጥብቅ ክትትል ጋር በስነ ምግባር በታነፁ ትጉህ ምሁራን ባለሙያዎቹ የወላጆች እፎይታ ለመሆን ተዘጋጅቷል።

ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? አሁኑኑ ወደ ቢሮኣችን በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥሮቻችን በመደወል ለልጆችዎ የሚፈልጉትን አስጠኚ ይውሰዱ። ህጋዊነታችን ላይ ስለምናተኩር ለደህንነትዎ አይጨነቁ።

ቅድሚያ የመጣ ቅድሚያ ይስተናግዳል!!!

«ኑ በሥነ ምግባር እና በዕውቀት የታነፀ ትውልድን ለኢትዮጵያችን ለማፍራት በጋራ እንስራ!!!»

ምሁር እፎይታዎ

Happy New year!!! Your all time partner Mehur Educational Consultancy which is dedicated to give support on academic performance and personal growth of your children is ready to serve you well in this bright year too.

Hire well experienced , highly educated as well as very disciplined university graduate male and female personal tutors from our office LEGALLY. Mehur is ready to take responsibility of following up seriously and help students to find best version of themselves.

Hurry up!!!!! Book your order by coming to our office or make a call to us.

"Let us work together to create an energetic, intellectual , disciplined and changemaker generation to our Ethiopia."

Photos 02/05/2021

📌 አማርኛ -- ክርስቶስ ተነስቷል! በእውነት እሱ ተነስቷል!

📌 ግዕዝ -- ክርስቶስ ተንስአ! በአማን ተንስአ!

📌 English – “Christ is risen! He is risen, indeed!”

📌 Hebrew: Ha Mashiyach qam! – Ken hoo qam!

📌 Greek: Χριστός ἀνέστη Ἀληθῶς ἀνέστη!
(Christos Anesti Alithos Anesti)

📌 French – Le Christ est ressuscité! En verité il est ressuscité! or Le Christ est ressuscité! Vraiment il est ressuscité!

📌 Italian – Cristo è risorto! È veramente risorto!

📌 Turkish – Hristós diril–Dí! Hakíkatén diril–Dí!

📌 Mandarin Chinese – 基督復活了 他確實復活了 (Jīdū fùhuó le! Tā quèshí fùhuó le!)

📌 German – Christus ist auferstanden! Er ist wahrhaftig auferstanden!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

መልካም በዓል ይኹንላችሁ!!

ምሁር የትምህርት ማማከር አገልግሎት

https://t.me/mehurconsultancy

Photos 11/03/2021
02/03/2021

ዓድዋ

የጥቁር ውብት፣ የነፃነት ድል፣ የማንነታችን መድመቂያ ፣ የሀገር ፍቅር ፣ ዛሬም ነገም ለመላው የዓለም ሕዝብ በኩራት የምንናገረው ነጮችን አንገት ያስደፋ ሁሌም እያስደፋ የሚዘልቅ በየበላይነት ስሜት ላይ የነጠበች ደማቅ እና የማትጠፋ ጥቁር ነጥብ አሻራ የዛሬዋ ቀን ናት።

ስለነፃነት የብዙዎች ደም የፈሰሰበት፣ የአያሌ ጀግኖች አጥንት የተከሰከሰበት ዛሬ ላለነው መስዋዕት ሆነዉ ብዙዎች ያለፉበት ነው።

ዛሬ ካለው ትውልድ ምን ይጠበቃል? የአዲሱ ትውልድ ወይም የልጆቻችን ድርሻስ ምንድን ነው?

መልካም!!! ይሄ ሁሉ ዋጋ የተከፈለው ስለ ሀገር ፍቅር ነው። ስለ ነፃነት ነው። ስለ ማንነት ነው። ስለሆነም ይህን ተረደተን አሁን ያለነው እኛ ጥላቻን አስወግደን በፍፁም ፍቅር፣ መተሳሰብ እና መተባበር የተሻለ ኢትዮጵያዊ መሆንን ይጠይቃል።

ኢትዮጵያዊ??? ምን ማለት ይሆን

ኢትዮጵያዊነት ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሀሳብ ከመስጠት፣ ከመተቸት፣ ከመኮነን በላይ ተግባርን ይጠይቃል። ወገን እናስተውል።። ኢትዮጵያ ሀገራችን እኔ፣ አንተ፣ አንቺ፣ እኛ፣ እናንተ እንዲሁም ሁላችንም በኅብረት በጎ ስራዎችን ስንሰራ ፣ በተሰማራንበት ዘርፍ ሁሉ ስለሀቅ፣ ስለእውነት፣ ስለፍቅር ፣ ስለቅንነት ስንኖር፤ መልካምነትን በወሬ ሳይሆን በተግባር ስናሳየው የዚያን ጊዜ ኢትዮጵያችን በእኛ ውስጥ ፈክታ እና ደምቃ ታበራለች።

እናሳ ስለዚህ በዓል ለልጆቻችን ምን ብለናቸው ይሆን? ምንስ ተምረው ይሆን?? ሀሳባችሁን እንወያይበት አጋሩን

ምሁር የትምህርት ማማከር አገልግሎት

Adwa!!!! The pride of blacks , the sign of freedom, dignity and sovereignty.......

How we explain the history to our children?? Share us what you feel we are ready to listen from parents ......

Photos 01/03/2021

የጥቁር ህዝቦች ሁሉ ኩራት ለሆነዉ ለታላቁ የአድዋ ድል 125ኛ ዓመት የመታሰቢያ ክብረ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!

ምሁር የትምህርት ማማከር አገልግሎት

https://t.me/mehurconsultancy

Photos 19/02/2021

Teach your children value of lives rather than value of things. Because when they grow up, they will always be helpful to everyone.

https://t.me/mehurconsultancy

15/02/2021

ውድ ወላጆች

ትምህርት ምንድን ነው?

ትምህርት ቤት መሄድ ነው? ፈተና ማለፍ ነው? ዩኒቨርስቲ መግባት ነውን ? ዲግሪ መያዝ ነውን?

በፍፁም………………

ትምህርት ሁለንተናዊ ሂደት ነው። ትምህርት ዲግሪ መያዝ ሳይሆን በሂደቱ ውስጥ የምንሠንቃቸው የሕይወት እሴቶች እና ዘዴዎች ናቸው። ያልተገለጠውን ለመግለጥ፣ ለፈተና ከሚያስፈልገው በላይ ለማወቅ ያለን ጥማት እና ተግባራዊ ክንዋኔዎች ትምህርትን በሚፈለገው መልኩ ይገልጹታል። በአጠቃላይ ትምህርት በተግባራዊ ዕውቀት በመታገዝ ያካበትነውን ብቃትና ብልሃት በገሃዱ አለም ያሉ የሕይወት ውጣ ውረድ እና ፈተናዎችን ለማሸነፍ የምንጠቀመው ጥበብ ነው።

በሚያሳዝን ሁኔታ በሀገራችን ያለው የትምህርት አሰጣጥ ሂደት ፈተና ተኮርና ሁሉም ተመሳሳይ ውጤት እንዲያመጡ መልፋት ነው። ይህም በእያንዳንዱ ልጆች ላይ የለውን የግል ብቃት መደበቅ ተፈጥሮኣዊ የፈጠራ ክህሎታቸውን ሸፍኖ ማሳለፍ ነው።

ውድ ወላጆች እስኪ ራሳችንን እራሳችንን እንጠይቅ

ልጆቻችን እየተማሩ ነው ወይስ ትምህርት ቤት ደርሰው እየመጡ??

መልሱን ለእናንተ ተውን!!!!! እስኪ ምን እናድርግ????? በይበልጥ ስለ ልጆች ቀርበን እንወያይ ይላል ምሁር የትምህርት ማማከር አገልግሎት። የመፍትሔዎ ሀሳቦች አሉን እነርሱ ላይ እንነጋገር።

ሠናይ ጊዜ

Dear Parents

What is Education ?

Is it just attending school, passing exams, attending university and getting a degree.?????

Definitely not. Education is a holistic process. It is not just about earning degrees, it is about the values and life lessons you imbibe in the process. It is about exploring the unknown, and about having the thirst to learn more than what is required of your exam. It is about hands-on learning. Education is about gaining practical knowledge and also should equip you to use your intelligence and capabilities to face real-life situations.

But unfortunately our current system aims to measure all children on the same parameters and expect similar results.
THAT IS WHERE WE KILL THE INDIVIDUALITY and CREATIVITY OF CHILDREN

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Address


Bole Medhanealem, Alem Dessu Building , 5th Floor 503
Addis Ababa