በወሎ ሥም የሚቀነቀነው ክልላዊ ጩኸት‼️
አሳዬ ደርቤ
▬▬▬
➔ደቡብ ወሎ ላይ አዲስ ዞን በመመስረት ነባሩን ዞን በኦነግ ፖለቲካ የመሰልቀጥ ምኞት ያለው፤
➔በተመሳሳይ የፌስ ቡክ ሥም የተደራጀ የኦነግና የብልጽግና የሳይበር ጦር የሚያራግበው፤
➔ሕዝባዊ መሠረት የሌለው፤
➔አማራን ወደ ማይኖሪቲ አውርዶ ኦሮ፤ሚያን ብቸኛ ማጆሪቲ የማድረግ ሕልም ያለው ፤
➔የኃይማኖት ግጭት የመፍጠር ተልዕኮ የተሰጠው፤
➔የቤተ አማራዎች እትብት መቀበሪያ ምድር ወሎ መሆኗ የተዘነጋው፤
➔ትልቁን የአማራ ዞን አንዲት ወረዳ ከማታክል ልዩ ዞን ስር የማዋል እቅድ ያለው...
እናም እንላለን...
ብልጽግና ሆይ ያሰብከው ቅዠት በእኛና በፋኖዎች ዘመን ሊተገበር ስለማይችል በክልልነት ሥም ወሎን የመሰልቀጥ ምኞትህን ጥለህ ሕዝባዊ መሠረት ላለው የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ አፋጣኝ መልስ ስጥ።
(ከአሳየህኝ ደርቢ)
ዋርካው አማራ-Warkaw Amhara
አርበኝነት የማንነታችን አርማ ነው
20/01/2021
የአማራ ትግል ተግዳሮቶች!!!
+++++++++++++++++++
ክፍል አንድ:
++++++++++++++++++
ስለ አማራ የሚታገለው የአማራ ታጋይ ሁለት አይነት ቡድን ጋር ይታገላል!!
ውጫዊው ቡድን!!
+++++++++++++++++++++++
ውጫዊው ቡድን ህውሃትና ኦነግ ዛሬ ላለው የኢትዮጵያ ሕዝብ አማራ ጠላት ነው ብሎ ማኒፌስቶ ቀርጾ ከዛሬ ፵ ዓመታት በፊት በስውር አማራውን አታግሎ በአማራ ደም ተረማምዶ አማራ ከሰራው ቤተ መንግሥት ከገባ በኋላ አማራ ጠላት ነው የሚለውን የትግል ማኒፌስቶውን በሕገ መንግሥት አጽድቆ ዛሬ አማራን የሚገድሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚባሉትን ወለደ፡፡ ህውሃት በተንኮል በውሸት ትርክት ኦነግን ወለደ ኦነግ ደግሞ የግሙዝ ሽፍታን ወለደ፡፡ይህ ፍሬ አፍርቶ ዘሪዎች አዝመራቸውን እያጨዱ ነው፡፡ይህ ሁሉ ሲሆን 99.9% አማራ ግን ይህንን ጉዳይ ደግፎ ለምን የሚሉትን አማራዎች ከጠላት እኩል ሲገድሉ ሲያሳድዱ እስከ አሁን ቀጥለዋል፡፡
ውስጣዊ ቡድን!
+++++++++++
የአማራን ትግል በግንባር ቀደም የሚታገለው ራሱ አማራው ነው፡፡አማራ ነፍጡን አንስቶ ጫካ ከገባ ዘመናትን አስቆጥሯል ዳሩ ግን የአማራውን ትግል ፍሬ እንዳያፈራ አፈር ጋር የሚቀላቅለውና ወደ ኋላ ጎትቶ ለጠላት አሳልፎ የሚሰጠው ራሱ አማራው ነው፡፡የአማራ ትግል በጠላት ወድቆ አያውቅም፡፡
ከዲያስፖራው የሚመጣ ደመ ነፍስ ትግል
የመጀመሪያው የአማራውን ትግል የሚያደናቅፈው ከዲያስፖራው የሚወጣው አታጋይ ነኝ ባይ አማራ ነው፡፡ከዲያስፖራው የሚወጣው ከእውቀት ነጻ የሆነና አፈ ቀላጤ የአማራ ዲያስፖራ ከዲያስፖራው አማራ ኪሱን እያራቆተ ብር ይሰበስባል፡፡ ሀገር ቤት ገብቶ ለታጋዩ፣ ደሙን ለገበረው ገበሬ ሳይሆን እንደሱ ላለው አፈ ቀላጤ ፎቶ እየፖሰተ እኔ ጀግናው ለሚለው ከሰፈር ለማይወጣውና የገዛ ወገኑን ሲያሳድድ የሚውለውን ብር ያሳቅፋል፡ በዚህ ልክ ታጋዩን አንገት ያስደፋል ትግሉን ያቀጭጫል፡፡
የቅርቡን እንኳን ብናይ በወልቃይት ጠገዴ ግንባር ቀደም ሁነው የዘመቱት ነፍሳቸውን ሳይቀር አሳልፈው የሰጡ ጀግኖች፣ በወኔና በአንድነት እኔ ልሙት እኔ ልቅደም ብለው ተሰልፈው ሂደው ነው የጠላትን ድምጥማጥ ያጠፉት፡ ዲያስፖራው ግን ተዋግተው ያሸነፉትን ሳይሆን ፎቶ ተነስተው ለመጡት ከምስኪን አማራ ኪስ ሰብስበው የወዳጅ ማውጫ ሲያደርጉት አይተናል፡፡የሞቱት ሙተው የቆሰሉት ግን መታከሚያ አጥተው በየዶርሙ ወድቀዋል፡፡
1.1 ብር የሚሰበሰብበት ዲያስፖራ ምንአገባኝነት(ለዘብተኝነት)!
++++++++++++++++++
ዲያስፖራው ብር ከኪሱ በስሜት ማውጣቱን እንጅ ብር ተረካቢው የት እንደሚያደርሰው ለማን እንደሚሰጠው አያገናዝብም፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ጦርነት ውስጥ ላለው፣ የድረሱልኝ ጥሪ ለሚያቀርበው ታጋይ ሳይሆን ብሩ የሚጫነው ጦርነት መኖሩን እንኳን ለማያውቅ ግለሰብ ነው ይህን በተደጋጋሚ የታየና በመረጃም የተያዘበት ጉዳይ ነው፡፡ በ2008 ዓ. ም እነ ብርሌው ብቃለና ላመነው ታከለ ሲታገሉ እያለ ጭልጋ ላይ እነ ሸርብ አቸነፍ እየታገሉ ብሩ ይላክ የነበረው ግን ብር በመዝረፍ ለሚታወቁ ግለሰቦች አዲስ አበባ ለኮሌኔል እንትና ደንቢያና ደልጊ ለአርበኛ እንትና እየተባለ ቆቅ ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ ጫወታ ነበር፡፡
ሀገር ውስጥ ያለው የፎቶ አርበኛ!!!
+++++++++++++++++++
ሀገር ውስጥ ያለው የአማራ አርበኛ 95% በወገኑ ደም የሚቀልድና የፎቶ ጀግና ነው፡፡ አርበኛ ነኝ ባዩ ከሰፈሩ ተቀምጦ ፎቶውን እየላከ ፎቅ ይገነባል፡፡ ባለፎቶው አርበኛ ለልጆቹ ፎቅ ሲገነባ ካሜራ የማያውቀው ያ እውነተኛ ገበሬ፣ ያ እውነተኛ ታጋይ፣ያ እነተኛ አማራ ግን ከፊት ቀድሞ ሕይወቱን ለግሶ ልጆቹ በረሃ ተሰደዋል፣ የዛ ካሜራ የማያውቀው ጀግና ልጆች ግን አስታዋሽ አጥተው የዕለት ጉርስ ፍለጋ ይንከራተታሉ፡፡
በወልቃይት ዘመቻ ጃሎ ብሎ የተነሳው የአርማጭሆ፣ የቋራ መተማ፣ የበለሳ፣ ጃናሞራና በየዳ ጀግና ነው፡፡ሚዲያውን ያጥለቀለቀውና የተሸለለት ግን ከጦርነቱ ጀርባ ፎቶ የተነሳው ነው፡፡በተለይ ከ2011. ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ላይ በተደረጉ የውክልና እና ግልፅ የመንግሥት ጦርነቶች ብዞዎች መስዋዕት ሁነዋል፣ ብዙዎች አካላቸውን አጥተዋል፣ ብዙዎች በአማራው ተገፍተው ከትግል ወጥተው አንገታቸውን ደፍተዋል፡፡ በእነዚህ ግንባሮች የአማራ ዲያስፖራ ኪሱን ከማራቆት አንድም ቀን አላቋጠም፡ ዳሩ ግን በግለሰቦች ጥፋት ግቡ ዜሮ ሁኗል፡፡
ታጋይ አርበኞች ስግብግብነት!!
+++++++++++++++++
አማራ አርበኞች ውስጥ ግንባራቸውን ለጦር የሚሰጡ ታጋዮች አሉን እነዚህ አርበኞች ወደ ጦር ሜዳ ሲዘምቱ የአርበኛ እገሌ ጦር ተብሎ ብዙ አርበኞችን አስከትለው ይሄዳሉ፣ በግጥሚው የሚሞት፣ የሚቆስል፣ በሰላም የሚመለስ አለ፡፡ በእነዚህ መሪ አርበኞች ስም የሚመጣው ገንዘብ ግን አብሮ ለዘመተው፣ ለሞተው ለቆሰለው በሰላምም ለተመለሰው ለሞራሉ እንኳን ለሳሙና ሲባል አይታይም ይህ ድርጊት ብዙዎችን አጋሏል፣ ብዙዎችን አለያይቷል፣ ብዙዎችን ከትግል መስመር አውጥቶ በተቃራኒ ጎራ እንዲሰለፉ አድርጓል፡፡
በዲያስፖራው የሚቋቋም የሀገር ውስጥ ብር አድራሽ ኮሚቴ!!
+++++++++++++++++
በሀገር ውስጥ ፋኖን፣ አርበኞችን፣ ታጋዮችን የሚመራ፣ የተፈናቀለ እንዲረዳ፣ የሞተ እንዲቀብር ያዘነውን እንዲያረጋጋ ኮሚቴ ብለህ የምታቋቁመው ከሚስኪኑ አማራ የሚሰበሰበውን ብር ፎቅ ሲገነባበት፣ ኑሮውን ሲያሻሽልበት፣ ሄላንድ ሲጨብጥበት፣ ቁርጥ ሲበላበት ታያላህ ኮሚቴ በመሆኑ ለራሱ ትልቅ ስእል ሰጥቶ የተሻለ ሴፍቲ በመፈለግ መንገላታት አይፈልግም ፣ የወገኑ ሰቆቃ አይታየውም ይልቁንም በተለመነ ገንዘብ በተሻለ መኪና መንቀሳቀስ፣ በተሸለ አልጋ መተኛት ይፈልጋል፡፡ታጋይ አታጋይ በእግር ተጉዞ፣ ተርቦ ተጠምቶ፣ እንደ ወገኖቹ ሁኖ እንዲያስተዳድር ነበር አለማው ዳሩ ግን እንደ አለመታደል ሁኖ በተቃራኒው ተሰልፎ ትግሉን ይቀብራል፡።
"አርበኝነት የማንነታችን አርማ ነው"
ክፍል 2 ይቀጥላል
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
showa
Addis Ababa
