2 ቀን ብቻ ቀረው
ለደረጃ ሐ ግብር ከፋዬች በሙሉ
የግብር መክፈያ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት በመምጣት ግብርዎን ያለ ቅጣት ያሳውቁ
Kolfe Keranyo Sub City Small Tax Payers Branch Office
Revenue Bureau
ለኮልፌ ቀራንዬ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች በሙሉ
የአድራሻ ለውጥን ይመለከታል
ቀድሞ ሞቢል 3ቁጥር ማዞሪያ አካባቢ የነበረውን ቢሮ ወደ ጦርኃይሎች ወረድ ብሎ ካልዲስ ኮፊ አጠገብ ወይንም ኢብራሂም ሕንጻ በስተጀርባ ባለው አዲስ ሕንጻ ላይ ያዛወረ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።
የኮልፌ ቀ/ክ/ከተማ አ/ግ/ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
25/06/2022
" ዒድ አልፈጥር "
ውድ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆናችሁ ግብር ከፋዮቻችችን እንኳን ለ1443ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ በዓሉ የሰላም የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህላችንን የምናፀባርበቅበት እና የጤናና የሰላም ይሁንላችሁ።
ዒድ ሙባረክ !
የኮ/ቀ/ክ/ከ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ግብር ከፋዮቻችን በሙሉ እንኳን ለፋሲካ በዓል በሠላም አደረሳችሁ በዓሉ የመተሳሰብ የመረዳዳት እንዲሁም የሠላም ይሁንላችሁ መልካም በዓል
የኮ/ቀ/ክ/ከ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት
08/04/2022
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አነስተኛ ግ/ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ 30/07/2014ዓ.ም ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ እና የወጪ መጋራት በተመለከተ በድርጅቶቻቸው ውስጥ ሠራተኞችን ቀጥረው ለሚያሰሩ ግብር ከፋዬች ስልጠና ተሰጠ።
23/03/2022
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የግብር ከፋዮች የመልካም ስነ ምግባር መገንቢያ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ፡፡
መጋቢት 14/2014 ዓ.ም በተጀመረው የንቅናቄ መገንቢያ መድረክ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሕግ ተገዥነት ም/ሥራ አስኪያጅ አቶ መኮንን ገመቺስ መድረኩን ያስጀመሩ ሲሆን ወ/ሮ ዘቧ ሀይሉ በሰነድ በማስደገፍ በአጭር ግልጽ እና ሳቢ በሆነ መልኩ በተቋሙ የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን እና በግብር ከፋዩም በኩል የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በመዘርዘር እነዚህን ችግሮች እርስ በእርስ ተጋግዘን ለመፍታትና በሠራተኞች ስነ ምግባር ላይ የሚታዩ ጉድለቶች ለማረም የግብር ከፋዮች ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ግብር ከፋዮች የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች እና ጥያቄዎቻቸውን ካለ ማንም ጣልቃ ገብነት በየደረጃው ለሚገኘው አመራር በማቅረብ ምላሽ ለማግኘትና መብታቸው በገንዘብ ሳይሆን በህግ ለማስከበር የራሳቸው ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋዮችን ሰብስቦ ውይይት ባደረገበት ወቅት በአነቃቂ ንግግራቸው እና በሐገር ወዳድነታቸው ታዋቂ የሆኑትን አቶ መሀመድ ካሣ ተጋባዥ እንግዳ በማድረግ ግብር/ታክስ ከራስ ቆርሶ ለራስ መሆኑን በአነቃቂ አንደበታቸው ለውይይቱ ተካፋይ አስረድተዋል፡፡በመጨረሻም ከመድረኩ በተነሱ ሀሳቦች አስተያየት እና ጥያቄ ተነስተው በአግባቡ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን የውይይቱ ተካፋዮችም ከዚህ በኋላ ላሉ ጊዜያቶች ግብር ከፋዩ እና ግብር አስገቢው መ/ቤት መካከል ካለማንም ደላላ ወይም አውቅልሃለሁ ባይ ውጪ እየተቀራረቡ የሚከሰቱ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ተግባብተው መድረኩ ባማረ መልኩ ተጠናቋል፡፡
23/03/2022
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በቀን 12/07/2014ዓም March 8 የሴቶች ቀንን በታላቅ ድምቀት አክብሮ ዋለ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Telephone
Website
Address
Torhaloch
Addis Ababa
