ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ፐብሊክ ሠርቪስና የሠው ሀይል ሀብት አስተዳዳር ጽ/ቤት

ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ፐብሊክ ሠርቪስና የሠው ሀይል ሀብት አስተዳዳር  ጽ/ቤት

Share

This is official page of Lemi Kura S/city worera 03 Public service and human resource manageme office

Photos from Lemi Kura wereda 03 Communication's post 15/01/2024
Photos from ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ፐብሊክ ሠርቪስና የሠው ሀይል ሀብት አስተዳዳር  ጽ/ቤት's post 13/01/2024

ልምድ ልውውጥ ለተሻለ ለውጥ።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 3 እና 2 የፐብሊክ ሰርቪና የሰው ሀብት ልማት ቤት አስተዳደሮች በጋራ በመሆን በቦሌ ወረዳ 12 በመሄድ ልምድ ልውውጥ ለተሻለ ተሞክሮ በሚል መሪ ሀሳብ የጋራ ልምድ ልውውጥ አደረጉ።

በልምድ ልውውጡም በተሻ ሁኔታ የሰው ሀይሉን የማስተዳደርና የአሰራር ብቃት፣የሰራተኛውን መብትና ግዴታውን የማስጠበቅና የመወጣት ተግባር እንዲሁም ልዩ ልዩ ተሞክሮ እንዳገኙ የገለፁ ሲሆን በቀጣይም ከዚህ ተሞክሮና ልምድ ልውውጥ የአገኙትን እውቀትና ግንዛቤ በጽ/ቤታቸው ወስደው ተግባራዊ በማድረግ ለሌሎች አሪያ የመሆን ስራ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

11/01/2024

በተሰጠው የምዘና ፈተና 6 ሺሕ 517 ሰራተኞች የማለፊያ ነጥብ አስመዘገቡ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተሰጠው የምዘና ፈተና ከ15 ሺሕ 151 ተፈታኞች 6 ሺሕ 517 የማለፊያ ነጥብ ማስመዝገባቸው ተገለፀ።

ከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ መዋቅሮች ለሚሰሩ ሰራተኞቹ የምዘና ፈተና መስጠቱ ይታወሳል።

በዚህም ፈተናውን ለመውሰድ የተመዘገቡ ሰራተኞችና አመራሮች 15 ሺሕ 592 ሲሆኑ ለፈተናው የቀረቡት 15 ሺሕ 151 ሰራተኞች መሆናቸውን የከተማ አስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ጣሰው ገብሬ (ዶ/ር) እንደገለፁት በምዘና ፈተናው 4 ሺሕ 213 አመራሮች የተፈተኑ መሆኑንና 1 ሺሕ 422 ማለፋቸውን ገልፀዋል። ይህም ከተፈተኑት 34 በመቶ መሆኑንም አንስተዋል።

10 ሺሕ 257 ሰራተኞች በፈተናው መሳተፋቸውንና ከዚህም ውስጥ 5 ሺሕ 95 ማለፍ መቻላቸውንም አክለው ገልፀዋል።

በሰራተኞቹ በኩል 681 የሚሆኑት በተለያዩ የደንብ ጥሰቶች ምክንያት ፈተናውን ወስደው ያልታረመላቸው እንደሆኑም ተጠቅሷል።

ፈተናውን እንዲወስዱ ከተጠበቁ ሰራተኞች መካከል 441 ሰራተኞች እንዳልተገኙም ተገልጿል።

ፈተናው ፍፁም ደህንነቱንና ሚስጥራዊነቱን በጠበቀ መልኩ መካሄዱንም ፈተናውን ያስተናገዱት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ገልፀዋል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Ayat In Front Of Lemi Kura Sub City Zureyash Moll 5th Floor
Addis Ababa