ልደታ ወረዳ 08 ንግድ ጽቤት Lideta Wereda 08 Trade office

ልደታ ወረዳ 08 ንግድ  ጽቤት Lideta Wereda 08 Trade office

Share

Trade license registration
Trade regulatory

23/01/2026

የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት ለተጨማሪ 15 ቀናት ተራዘመ።

የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት በበጀት ዓመቱ ከሀምሌ 1/2017 እስከ ታህሳስ 30/ 2018 ዓ/ም ድረስ ያለቅጣት የሚታደስበት ጊዜ እንደሆነ ይታወቃል።

አመታዊው የንግድ ፈቃድ እድሳት ያለቅጣት የሚታደስበት ጊዜ ካበቃበት ታህሳስ 30/2018 ዓም ጀምሮ የማደሻ ጊዜው ለተጨማሪ 15 ቀናት ተራዝሞ እድሳት ሲከናወን ቆይቷል።

ይሁን እንጂ በተሰጠው ጊዜ እድሳታቸውን ያላጠናቀቁ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን እድሳት ማከናወን እንዲችሉ ለመጨረሻ ጊዜ ለተጨማሪ15 ቀናት መራዘሙን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

በተሰጠው ተጨማሪ ጊዜ መሰረት የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት ያለቅጣት የሚከናወንበት ጊዜ ጥር 30/2018 ዓም የሚያበቃ ይሆናል።

ለቀኑ መራዘም ምክንያት ነጋዴዎች የክሊራንስ አሰጣጥ ላይ መጓተቶች በመኖራቸው ክሊራንስ አለመጨረሳቸውን በመግለጽ ቅሬታ በማቅረባቸው ምክንያት መሆኑን ተገልጿል።

ቅሬታቸው በንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተቀባይነት በማግኘቱ ለተጨማሪ 15 ቀናት እስከ ጥር 30/2018 ዓም ድረስ ለመጨረሻ ጊዜ እንዲራዘም መወሰኑን ቢሮው አሳውቋል።

እንደ ንግድ ቢሮው መረጃ እስካሁን 295 ሺ 810 የሚሆኑ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት እድሳት አከናዉነዋል።

የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ከሠኞ-ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 2፡30 በኦንላይን እየተሠጠ የሚገኝ ሲሆን በቀሩት ቀናት ንግድ ፈቃዳቸውን ያላሳደሱ ነጋዴዎች እንዲያሳድሱ ቢሮው ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

Photos from ልደታ ወረዳ 08 ንግድ  ጽቤት Lideta Wereda 08 Trade office's post 13/09/2025

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ንግድ ፅ/ቤት እና ህብረት ስራ ፅ/ቤት በጋራ የማህበረሰቡን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ የተጀመረው የእሁድ ገቢያ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የነዋሪውን የኑሮ ጫና ለመቀነስ የተጀመረው የእሁድ ገበያ ተደራሽ ለማድረግ በተሻለ ሁኔታ ምርት እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን በቅዳሜ ገበያውም የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን ለነዋሪው በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብ መሆኑን ለማየት ተችሏል ።

ልደታ ወረዳ 08 ንግድ ጽ/ቤት ማህበረሰቡ ወደዚህ ቦታ በመምጣት ምርቶችን በተመጣጣኝ ዎጋ በመግዛት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ያቀርባል።

መስከረም 03/01/2018 ዓ.ም

Photos from ልደታ ወረዳ 08 ንግድ  ጽቤት Lideta Wereda 08 Trade office's post 27/07/2025

የእሁድ ገበያ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ንግድ ፅ/ቤት እና ህብረት ስራ ፅ/ቤት በጋራ የማህበረሰቡን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ የተጀመረው የእሁድ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የነዋሪውን የኑሮ ጫና ለመቀነስ የተጀመረው የእሁድ ገበያ ተደራሽ ለማድረግ በተሻለ ሁኔታ ምርት እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን በቅዳሜ ገበያውም የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን ለነዋሪው በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብ መሆኑን ለማየት ተችሏል ።

የእለቱን የእሁድ ገቢያ ማህበረሰቡ ወደዚህ ቦታ በመምጣት ምርቶችን በተመጣጣኝ ዎጋ በመግዛት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።

ሐምሌ 20/11/2017 ዓ.ም

Photos from ልደታ ወረዳ 08 ንግድ  ጽቤት Lideta Wereda 08 Trade office's post 12/07/2025

የቅዳሜና እሁድ ገበያ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር የማህበረሰቡን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ የተጀመረው የቅዳሜና እሁድ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የነዋሪውን የኑሮ ጫና ለመቀነስ የተጀመረው የቅዳሜና እሁድ ገበያ ተደራሽ ለማድረግ በተሻለ ሁኔታ ምርት እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን በቅዳሜ ገበያውም የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን ለነዋሪው በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብ መሆኑን ለማየት ተችሏል ።

የእለቱን የቅዳሜ ገቢያ ማህበረሰቡ ወደዚህ ቦታ በመምጣት ምርቶችን በተመጣጣኝ ዎጋ በመግዛት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።

ሐምሌ 5/11/2017 ዓ.ም

Photos from ልደታ ወረዳ 08 ንግድ  ጽቤት Lideta Wereda 08 Trade office's post 29/06/2025

የቅዳሜና እሁድ ሰንበት ገቢያ ዛሬም በደመቀ ሁኔታ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በልደታ ክፋለ ከተማ ወረዳ 08 ንግድና ህብረት ስራ ጽ/ቤት አዘጋጅነት የኑሮ ውድነትን እና ገበያውን ለማረጋጋት አቦ ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዎጋ ለህብረተሰቡ አቅርበዋል።

የእለቱን የእሁድ ገቢያ ማህበረሰቡ ወደዚህ ቦታ በመምጣት ምርቶችን በተመጣጣኝ ዎጋ በመግዛት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።

ሰኔ 22/10/2017 ዓ.ም

28/06/2025

የሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ

የሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከዛሬ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሰኔ ወር ሲሸጥ በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የነዳጅ ማደያዎች እና ኩባንያዎች በነዳጅ ውጤቶች ግብይት አዋጁና በአሠራር መመሪያው መሠረት ውሳኔውን ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጥብቅ ያሳስባል፡፡

Photos from ልደታ ወረዳ 08 ንግድ  ጽቤት Lideta Wereda 08 Trade office's post 22/06/2025

" በነዳጅ ማደያዎች ላይ ያልተገባ ወረፋ እየተስተዋለ ያለው በማህበራዊ ሚዲያ በተሰራጨ የተሳሳተ መረጃ ነው " - ሚኒስቴሩ

➡ " የድጎማም ሆነ የታክስ ክፍያ አይኖም !! "

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከነዳጅ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ማብራሪያ ሰጥቷል።

በዚህም " መንግስት በሀገር ውስጥ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ ያደርግ የነበረውን የጥቅል ድጎማ በሂደት በመቀነስ እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም. መጨረሻ ከድጎማ ሥርዓት በመውጣት በዓለም ገበያ ልክ እንዲሆን አድርጎ ነበር " ብሏል።

" ሆኖም ግን መንግስት ተግባራዊ ያደረገውን የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የውጭ ምንዛሬ መጠን በማደጉ የሀገር ውስጥ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል " ሲል ገልጿል።

" ይህ በመሆኑ መንግስት ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍል ኑሮ አንዳይጎዳ በማሰብ ከሐምሌ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የጥቅል ድጎማ አድርጎ በማቅረብ ላይ ነበር " ብሏል።

" ሆኖም ግን ከጎሮቤት ሃገራት ጋር ያለው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ልዩነቱ ሰፊ ስለሆነ ለኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ግብይት እንዲጋለጥ ከማድረጉ በተጨማሪ በመንግስት ላይ ያለው ጫና በከፍተኛ ሁኔታ በማደጉ በሂደት ከድጎማ ለመውጣት ባለፉት 11 ወራት ሰፋፊ ስራዎች ተከናውነዋል " ሲል አስረድቷል።

" ይህን ተከትሎ ቤንዚንና የአውሮፕላን ነዳጅ ከግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ፣ ነጭ ናፍጣና ሌሎች የነዳጅ ውጤቶችን ከግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ የጥቅል ድጎማውን በማስቀረት በዓለም የነዳጅ ዋጋ መሰረት እንዲሆን ተደርጓል " ሲል አሳውቋል።

ነዳጅ ከድጎማ መውጣቱንና በዓለም የነዳጅ ዋጋ መሰረትም እንደሚሆን ነው ያብራራው።

" ነገር ግን በያዝነው ሳምንት ውስጥ መንግስት ከድጎማው እንዳልወጣና ተጨማሪ የታክስ ክፍያዎችን አንደሚተገብር በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተሳሳቱ መረጃዎች መሰራጨታቸውን ተከትሎ በነዳጅ ማደያዎች ላይ ያልተገባ ወረፋ እየተስተዋለ ነው " ብሏል።

ሚኒስቴሩ " ህብረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያዎቹ የሚናፈሰውን ከእውነት የራቀ አሉባልታ መሆኑን ይገንዘብ " ያለ ሲሆን " የድጎማም ሆነ የታክስ ክፍያ እንደማይኖርና ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ እየቀረበ መሆኑን ተገንዝቦ ተረጋግቶ እንዲገበያይ " ሲል ገልጿል።

ከመጭው ሐምሌ ወር ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በዓለም አቀፉ ዋጋ መሰረት ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ፤ ላለፉት ወራት ቀስ በቀስ የነዳጅ ድጎማን እያነሳ ያለው መንግስት ሙሉ በሙሉ ድጎማውን ከማቆም ባሻገር ተጨማሪ እሴት ታክስ ሊያስከፍል ማቀዱ ከሰሞኑን ተዘግቦ ነበር።

ይህ መረጃም ዋቢ የተደረገው የገንዘብ ሚኒስቴር ለተወካዮች ምክር ቤት ካቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2018 ረቂቅ በጀት ከሚያብራራ ሰነድ ላይ ነው።

መንግሥት ከነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች 15 በመቶ ቫት በማስከፈል ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ማቀዱ ተዘግቧል።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ግን በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጩት መረጃዎች የተሳሳቱ መሆናቸውን በመግለፅ የድጎማም ይሁን የታክስ ክፍያ እንደማይኖር አሳውቋል።

Photos from ልደታ ወረዳ 08 ንግድ  ጽቤት Lideta Wereda 08 Trade office's post 20/06/2025

የእርስ በርስ ልምዶችን በመለዋወጥ የተሻለ ተቋም ለመገንባት ያስችል ዘንድ ከመሰል ተቋምና ሴክተሮች ጋር የልምድ ልውውጥ በማድረግ የተሻሉ ልምዶችና ተሞክሮዎችን ለማስፋት የሚስችል አቅም መሆኑ ግልጽ ነው::
በቀን 13/10/2017 ዓ.ም የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ንግድ ጽ/ቤት ከአቻው ተቋም ከልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ንግድ ጽ / ቤት ጋር የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።

በልምድ ልውውጡ የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ንግድ ፅ/ቤት በተቋሙ በሚገኙ ቡድኖች የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት በማቅረብ የንግድ ተቋሙን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የሚደረጉ ጥረቶች የቀረቡና ተግባራቶች በውጤት ለማጀብ የእርስ በርስ ቅንጅትና አቅምን አሟጦ መጠቀም ለውጤታማነት ጉልህ እገዛ እንደሚሰጥ በርስ በርስ የልውድ ልውውጡ የቀረበ ሲሆን
በተጨማሪም ለልምድ ልውውጥ የመጡት የኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 9 ንግድ ጽ/ቤት ባለሙያዎችም ከአቻ ተቋማቸው የተሰጣቸው ልምድ ልውውጥ አመስግነው የንግድ ተቋም ጤናማ የሆነ የንግድ ስርዐት እንዲኖር ከማድረግ አንጻር እንደዚሁም ከኑሮ ውድነት ጋርና ከንግድ ቁጥጥር ስራዎች ጋር ያሉት ልምዶች ተሞክሮዎችም በቀጣይም በቅርበት መለዋወጥ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

Photos from ልደታ ወረዳ 08 ንግድ  ጽቤት Lideta Wereda 08 Trade office's post 14/06/2025

የቅዳሜ ገቢያ ዛሬም በደመቀ ሁኔታ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በልደታ ክፋለ ከተማ ወረዳ 08 ንግድና ህብረት ስራ ጽ/ቤት አዘጋጅነት የኑሮ ውድነትን እና ገበያውን ለማረጋጋት አቦ ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች እንድውም ጤፍ በተመጣጣኝ ዎጋ ለህብረተሰቡ አቅርበዋል።

የእለቱን የቅዳሜ ገቢያ ማህበረሰቡ ወደዚህ ቦታ በመምጣት ምርቶችን በተመጣጣኝ ዎጋ በመግዛት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።

ሰኔ 7/10/2017 ዓ.ም

Photos from ልደታ ወረዳ 08 ንግድ  ጽቤት Lideta Wereda 08 Trade office's post 07/06/2025

የቅዳሜና እሁድ ገበያ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ንግድ ጽ/ቤት በአቦ ቤተክርስቲያን አካባቢ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
*
ግንቦት 30/2017

የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለማቅለል በተመጣጣኝ ዋጋ የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን የማቅረብ ስራ በአቦ ቤተክርስቲያን አካባቢ ከህብረት ስራ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን እንዲሁም በንግድ ጽ/ቤት ትስስር ከተፈጠረላቸው ነጋዴዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በወረዳው በሚገኘው አቦ ቤተክርስቲያን አካባቢ የሰንበት ገበያ የሰብል ምርቶች፣የኢንዱስቱሪ ምርቶች፣ የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶቶች በአቅራቢ ነጋዴዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ማሕበረሰብ ቀርበው በመገበያያት ላይ ይገኛል።
የእለቱን የቅዳሜ ገቢያ ማህበረሰቡ ወደዚህ ቦታ በመምጣት ምርቶችን በተመጣጣኝ ዎጋ በመግዛት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።

ግንቦት 30/09/2017 ዓ.ም

18/02/2025

አስደሳች የውጤት ዜና

የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ንግድ ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የ6 ወር ሥራ አፈጻጸም ከ10 ወረዳዎች ተመዝኖ 1ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና ሰርተፍኬት ተሸላሚ የሆነ ሲሆን ይህ ውጤት እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ ያደረጉ የወረዳው አስተባባሪ፣አመራሮች፣ቡድን መሪዎችና ፈጻሚዎች እንዲሁም የህዝብ አደረጃጀቶች የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ንግድ ጽ/ቤት ምስጋናውን ያቀርባል።

08/02/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Hirut Daniel, Ridwan Sebre, Lemi Dereje

Welcome!!

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Around Bisrate Gebreal
Addis Ababa