ETIDI Anti corruption office/ ኢጨኢልኢ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል

ETIDI Anti corruption office/ ኢጨኢልኢ  የሥነምግባር  መከታተያ ክፍል

Share

ሙስናን በመከላከል የጨርቃጨርቅ ኢንደስትሪን እድገት ማፋጠ?

30/11/2022
29/08/2022

ህንድ በሙስና ተገንብተዋል የተባሉ 100 ሜትር ከፍታ ያላቸውን መንትያ ህንጻዎችን አፈረሰች

በህንድ ዋና ከተማ ኒው ዴሊ ከተማ አቅራቢያ በቀጥታ ስርጭት በተላለፈ አስደናቂ ትዕይንት ለዘጠኝ አመታት ከዘለቀ የህግ ዉዝግብ በኋላ ሁለት የመኖሪያ ህንፃዎችን እንዲፈርሱ ተደርጓል፡፡100 ሜትር ከፍታ ያላቸው "መንትያ ህንጻ" መውደም ህንድ በሙስና ገንቢ እና ባለስልጣኖች ላይ ጠንካራ መሆኗን የሚያሳይ ነው ተብሏል።

ህንጻዎቹ ለዘጠኝ ዓመታት የዘለቀ የህግ ክርክር ውስጥ የነበሩ ሲሆን ነዋሪዎች እንዳልነበሩበት ብሎም በሴኮንዶች ልዩነት ውስጥ ወደ ፍርስራሽነት መቀየሩ ተነግሯል፡፡ከ3,700 ኪሎ ግራም በላይ ፈንጂ በማጥመድ ህንጻዎቹ በ12 ሰከንዶ ወደ ፍርስራሽነት ተቀይሯል፡፡

ህንፃዎቹ የተገነቡት ሱፐርቴክ ሊሚትድ የሪል እስቴት ድርጅት ሲሆን የግንባታ ደንቦችን በመጣስ ተከሷል።በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሁም ቤት አልባ ውሾች ከፍንዳታው በፊት ከአጎራባች ፎቆች ጭምር እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡

Via ዳጉ ጆርናል

Photos from Ministry of Urban  and Infrastructure/Ethiopia's post 11/12/2021
Photos from Federal Ethics and Anti-Corruption Commission's post 20/04/2021
22/10/2020

ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በሁሉም ተቋማት እንደሚከበር ተገለጸ
**************************************************************
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም አዳማ)፡- የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በሁሉም የመንግስት ተቋማትና ክልሎች ደረጃ እስከ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ተከብሮ እንደሚጠናቀቅ በኮሚሽኑ የሥነምግባር ግንባታና የህዝብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሐረጎት አብርሃ ገለፁ፡፡

ዳይሬክተሩ በአዳማ ከተማ ለሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች በተዘጋጀው ሥልጠና ላይ የበዓሉን ማስፈፀሚያ ዕቅድ ይፋ ባደረጉበት ወቅት በዓሉ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ17ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ “የትውልድ የሥነ-ምግባር ግንባታን በጠንካራ ዲሲፕሊን በመምራት ሌብነትንና ብልሹ አሠራርን በመታገል የብልጽግና ጉዟችንን እናፋጥናለን!” በሚል መሪ ቃል ተከብሮ እንደሚውል አብራርተዋል፡፡

በዓሉ በክልሎች፣በተለያዩ የህዝብ አደረጃጀቶች፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በልማት ድርጅቶችና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ደረጃ በሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች አስተባባሪነት የኮቪድ-19 መከላከያ ፕሮቶኮል ጠብቆ እስከ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ተከብሮ በመጠናቀቅ ለኮሚሽኑ ሪፖርት እንደሚደረግ አቶ ሐረጎት አክለው ገልፀዋል፡፡

በፌደራል ደረጃም እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም የማጠቃለያ በዓል ለማክበር መታቀዱን የገለፁት አቶ ሐረጎት የበዓሉን አከባበር በበላይነት የሚከታተል ሀገር አቀፍ ዓብይ ኮሚቴ መቋቋሙንም ጠቅሰዋል፡፡

22/10/2020

ተቋማት ለሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች ትኩረት ሊሰጡ ይገባል ተባለ
*******************************************************
(ፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም አዳማ)፡- የዕድገት ማነቆ የሆነውን ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል ተቋማት ለሥነምግባር መከታተያ ክፍሎቻቸው ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ የፌደራል የሥምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ አታክልቲ ግዳይ ገለፁ፡፡

ኮሚሽኑ ከ2012 በጀት ዓመት መጨረሻ ጀምሮ ካደረጋቸው ትላልቅ ሪፎርሞች መካከል በየተቋማቱ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎችን መልሶ የማደራጀት ሥራ አንዱ መሆኑን የጠቀሱት ም/ኮሚሽነሩ በሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች በኩል በየተቋማቱ የሚሰሩ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥራዎች ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል ከፍተኛ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡ የተቋማት የበላይ ኃላፊዎችም ለሥምግባር መከታተያ ክፍሎቻቸው የተሰጠውን ከፍተኛ ኃላፊነት በመገንዘብ ተገቢውን ዕገዛና ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባቸው ም/ኮሚሽነሩ በአዳማ ከተማ ለሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች በተዘጋጀው ሥልጠና ላይ አሳስበዋል፡፡

ኮሚሽኑ ለሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች ከሚያደርገው ድጋፍና ዕገዛ በበለጠ የተቋማት የበላይ ኃላፊዎች ለሥራ ክፍሉ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት በሰው ኃይል፣ በበጀትና ማቴሪያል እንደሚያደራጃቸውም ይጠበቃል፡፡

22/10/2020

የተቋማት ኃላፊዎች የመልካም ሥነምግባር ተምሳሌት መሆን እንዳለባቸው ተገለጸ
*************************************
(ፈ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም አዳማ)፡- የተቋማት የበላይ ኃላፊዎች ለሰራተኞቻቸውና ለሚያገለግሉት ማህበረሰብ በተግባር የሚገለጽ የመልካም ሥነምግባር ተምሳሌት መሆን እንዳለባቸው የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች በአዳማ ከተማ በተዘጋጀው የ10 ዓመት የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል መሪ ዕቀድ ሥልጠና ላይ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
እንደ አስተያየት ሰጭዎቹ ገለፃ የመንግስት ተሿሚዎች ከመሾማቸው በፊት የመልካም ሥነምግባር ጉዳይ እንደ ቅደመ ሁኔታ የሚታይበት የህግ ማዕቀፍ ሊኖር ይገባል፡፡ የተሾሙት የተቋማት የበላይ ኃላፊዎች ደግሞ በህዝብና መንግስት አደራ የተረከቡትን ተቋማት ከሙስናና ብልሹ አሰራር ችግሮች በፀዳ መልኩ መምራት እንዳለባቸው የሥልጠናው ተሳታፊዎች በውይይታቸው ወቅት ገልጸዋል፡፡

የተቋማት ኃላፊዎች አርኣያ የሚያደርጋቸውን የሥነምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ሥራዎችን በየተቋሞቻቸው ደረጀ በቁርጠኝነት በማከናወን ለሠራተኞቻቸውና ማህበረሰቡ ተምሳሌት፣ ለሀገሪቷም ኩራት መሆን እንዳለባቸውም የሥልጠናው ተሳታፊዎች አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

የተቋማት የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች በበኩላቸው ከየተቋማቱ የበላይ ኃላፊዎች ጋር በመቀናጀትና በመናበብ የተጀመሩ ተቋማዊና ሀገራዊ ለውጦች በሙስናና ብልሹ አሰራሮች እንዳይደናቀፉ ተግተው እንደሚሰሩ አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል፡፡

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Akaki Kality
Addis Ababa