13/08/2025
#90ቀን
# ኮልፌ ወረዳ 10 ም/ቤት ዜና
#ቤት እድሳት
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት አስጀመረ።
ነሐሴ 07/2017 ዓ.ም
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት የ90 ቀን እቅድ አካል የሆነውን የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት የምክር ቤት አባላትን በማስተባበር በወረዳ 10 አስጀምሯል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማው ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ቦጋች ተድላ ጨምሮ የምክር ቤቱ አመራሮች ተገኝተዋል።
የዜናው ምንጭ ኮልፌ ወረዳ 10 ኮሚዩኒኬሽን
31/07/2025
#በመትከልማንሰራራት
#አረንጓዴአሻራ
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10 ምክር ቤት አመራሮችና የምክር ቤት አባላት የአንድ ጀንበር አረጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
10_Council
31/07/2025
#አረንጓዴዐሻራ
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ምክር ቤት አባላት በክረምት በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ላይ አሻራቸውን አሳርፈዋል
30/07/2025
#አረንጓዴዐሻራ
"በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል ነገ በሀገር አቀፍ ደረጃ 700 ሚሊዮን ችግኞች ይተከላሉ።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደርም በነገው እለት በሚካሔደው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የዚህ ታላቅ ንቅናቄ አካል ሲሆን፣ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርም ያካሂዳል።
አስተዳደሩም ነዋሪዎች ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በተዘጋጁ የመትከያ ቦታዎች በመገኘት በዚህ ታሪካዊ ቀን ተሳታፊ እንድትሆኑ ጥሪውን ያቀርባል።
The national level of national levels of the national level of the leader, "planting" is planted nationally.
Collee City Administration also completed the preparation of the green firmament program on the day.
Kolfyle City Sub-City is part of this great movement, including the nursery program in one beginning in different parts of the community.
The administration offers the call for people who are prepared by the ge***al days from 12:00 o'clock in the morning.
28/07/2025
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ የክፍለ ከተማው አስተዳደር የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ለምክር ቤት አባላት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ለምክር ቤቱ የተቋም ግንባታና አገልግሎነት አሰጣጥ በተመለከተ ካነሱት ዋና ዋና ሃሳቦች፡-
በክፍለ ከተማ ደረጃ በ9 ተቋማት እና በሁሉም ወረዳዎች 6 ተቋማትን በአደረጃጀት፣በአሰራር፣በቴክኖሎጂ፣በሰው ሃይል እና ምቹ የሥራ አካባቢ የመፍጠር ሪፎርም ተከናውኗል፡፡
በበጀት አመቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት ተከናውኗል፡፡
ለአብነትም የከፍለ ከተማችንን ገቢ አሰባሰብ ለማሻሻል የE-tax የE-filing እና የSIGTAS ቴሌ ብር ቴክኖሎጂን በመጠቀም ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ መክፈል እንዲችሉ የማድረግ ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በተጨማሪም የፈቃድ እድሳት፣ የጤና ዲጂታል ቴክኖሎጂ በማስፋትና በማጠናከር አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን በ 7ቱ ጤና ጣቢያዎች፣ በሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት፣ በንግድ፣ በግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር፣ በመሬት ልማትና አስተዳደር እና በትምህርት ዘርፍ ቀልጣፋና ግልጽ ዘመናዊ ስርአት በመገንባት የተገልጋዮችን እንግልት መቀነስ ተችሏል፡፡
የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ምቹ እና ሳቢ ከማድረግ አንፃር የ17 ተቋማት ሰራተኞች ካፍቴሪያ፣ በ15 ተቋማት የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና በ42 ተቋማት የሕፃናት ማቆያ ማእከላትን የማመቻቸት የ15 ተቋማት ምድረ ግቢን የማስዋብ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
28/07/2025
"ፍትሃዊ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሰፍን እና የአገልግሎት እርካታ ከፍ እንዲል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተሰሩ ስራዎች ስኬታማ ነበሩ" ክብርት ወ/ሮ ቦጋለች ተድላ
ኮልፌ ወረዳ 10 ምክር ቤት ሐምሌ 21 /2017 ዓ.ም
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ምርጫ ዘመን 12ኛ ዓመት የማጠቃለያ ጉባኤውን እያካሔደ ይገኛል።
በጉባኤው የመክፍቻ ንግግር ያደረጉት የክፍለ ከተማው ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ቦጋለች ተድላ በዘንድሮው የበጀት አመት የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ፍላጎትና ፍትሃዊ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሰፍን እንዲሁም የህዝባችን የአገልግሎት እርካታ ከፍ እንዲል ከምንግዚውም በተለየ መልኩ የተጠናከረ እንዲሆን ከክፍለ ከተማው አስተዳደር ጋር በመሆን የተሻለ የቅንጅት ስራ የተሰራበት ውጤታማ ዓመት እንደነበረ አብራርተዋል።
ክብርት አፈ ጉባኤዋ አክለውም ምክር ቤቱ የአስፈጻሚ አካላትን ዕቅድን ፣አፈፃፀምን፣ እንዲሁም ለክፍለ ከተማዉ ነዋሪዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች ተደራሽ መሆናቸዉንና መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥ እንዲቻል በም/ቤቱ ዘርፍ ኮሚቴዎች አማካይነት የመደገፍ፣ የመከታተል፤ የመቆጣጠር፣ የመገምገምና ግብረ መልስ የመስጠት ስራ መስራቱንም አመላክተዋል።
ክብርት አፈጉባኤዋ አያይዘው እንደገለፁት የተጀመሩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል፤ ደካማ ጎኖችን በማሻሻል እንዲሁም ቁልፍ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የአፈጻጻም አቅጣጫዎችን በማጎልበት በ2018 በጀት ዓመት የአስተዳደሩንና የምክር ቤቱን የቀጣይ የዕቅድ ተግባራትን ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ የነዋሪዎች ተሣታፊና ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከፍተኛ ርብርብ የምናደርግበት መሆን ይገባል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።
ምክር ቤቱ በጉባኤው የ2ኛ ምርጫ ዘመን 12ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ፤የክፍለ ከተማው አሰተዳደር የ2017 ዓ.ም በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀም በመወያየት ማፅደቅ፤የአስተዳደሩን የ2018 የበጀት ድልድል ተወያይቶ ማፅደቅ፣ሹመትን ተወያይቶ ማፀደቅ የጉባኤው አጀንዳዎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል ።
ምንጭ ኮልፌ ኮሙዩኒኬሽን
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
https://linktr.ee/kolfecommunication
https://linktr.ee/kolfecommunication ይጎብኙ
25/07/2025
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለወረዳ 10 ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅ/ቤት ተገልጋዮች በሙሉ
ከዚህ በፊት በወረዳ ደረጃ በግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅ/ቤት ሲሰጡ የቆዩ የጊዜያዊ ግንባታ ፈቃድ፣ የእድሳት ፈቃድ፣ የአጥር ፈቃድ 40% ማሻሻያ፣ የማፍረሻ ፈቃድ፣ የምሽት ፈቃድ፣ የG+0፣ የG+1፣ እና የG+2 ፈቃድና ቁጥጥር እንዲሁም የነባር ግንባታዎች የክትትልና ቁጥጥር አግልግሎቶችን ከሐምሌ 16/2017 ዓ.ም ጀምሮ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅ/ቤት አገልግሎቶችን የምታገኙ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
08/07/2025
የወረዳ 10 ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም ማጠቃለያ በወረዳው ስር የሚገኙ ተቋማት ምዘና ማካሄድ ጀምረዋል
27/05/2025
የክፍለ ከተማው ምክር ቤት 2ኛ ምርጫ ዘመን 12ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ፡፡
ኮልፌ ወረዳ 10 ምክር ቤት
ግንቦት 19/2017ዓ.ም
ምክር ቤቱ ጉባኤውን በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ጉባኤውን ማካሔድ የጀመረ ሲሆን በጉባኤው የክፍለ ከተማው አስፈፃሚ አካላት፤የምክር ቤት አባላት ፤የምክር ቤት ዘርፍ ኮሚቴዎች ፤የወረዳ ዋና አመራሮች ፤የወረዳ ዋና አፈጉባኤዎችና ፀሀፊዎች እንዲሁም የክብር እንግዶች በተገኙበት በክፍለ ከተማው አስተዳደር መሰብሰቢያ አዳራሽ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡
በጉባኤው የ2017 የ12ኛ አመት 2ኛ የምርጫ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለጉባኤ ተወያይቶ ማፀደቅ፣የክፍለ ከተማው አሰተዳደር የ2017 የ9 ወር የእቅድ አፈፃፀም በመወያየት ማፅደቅ የጉባኤው አጀንዳዎች ናቸው።
26/05/2025
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10 ምክር ቤት 2ኛ ምርጫ ዘመን12ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ።
ኮልፌ ወረዳ 10 ምክር ቤት
ግንቦት 18/2017ዓ.ም
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10 ምክር ቤት 2ኛ ምርጫ ዘመን 12ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ።በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ላይ 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ የማፀደቅ ስራ ተካሂዷል ።
በመቀጠልም የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቃሲም ሱሩር የ2017 በጀት ዓመት የወረዳ አስተዳደሩን የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም የነዋሪውን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ከመፍታት አንፃር የሚሆኑ ችግሮችን በመፍታትና ብልሹ አሰራር ላይም በልዩ ትኩረት በመስራት ውጤታማ ስራ መሰራቱን ፣በገቢ አሰባሰብ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራቱ ፣በህገ ወጥ ግንባታ ላይ ጥብቅ ክትትል ማድረግ ስለመቻሉ ፣ የበጎ ፍቃድ ተግባራት ፣ግብርና ስራ የሌማት ትሩፋት ፤የሴቶችን ተጠቃሚነት በማጉላት ብሎም በስራ እድል ፈጠራው ዘርፍ በስፋት በመስራት ለበርካታ ስራ አጥ ዜጎች የራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸው ማድረግ ከመቻሉም ጎን ለጎን በሰላምና ፀጥታው ዘርፍ ማህበረሰቡ የሰላም ባለቤት እንዲሆን ሰፊ ስራ መሰራቱ ገልጿል ።
በቀረበው ሪፖርት ላይም የምክር ቤቱ አባላት የመልካም አስተዳደር ችግሮች ናቸው ብሎ ላቀረቧቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች የሚመለከታቸው አስፈፃሚ አካላት ምላሽ የሰጡ ሲሆን የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ የማጠቃለያ ምላሽ የተሰጠው ስሆን በመቀጠልም የአስተዳደሩን የ9ወር ሪፖርት በተከበረው የምክር ቤት አባላት የማፅደቅ ስራ ተሰርቷል፡፡