08/12/2020
Bole wereda13 labour and social affairs office
wereda13
08/12/2020
24/08/2020
የወረዳው ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ለወረዳው ወጣቶችና በጎፈቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት የአልባሳት ድጋፍ አበረከተ 13 የወንዶች የአዋቂ ሱሪ የህፃናት 24 መሉ ልብስ የህፃናት 19 ጫማ
20/08/2020
ነሀሴ 11/2012 ዓ/ም
አሠሪዎች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክኒያት በማድረግ ድርጅቶችን ከመዝጋትና ሠራተኞች ከመቀነስ ይልቅ በሥራ ላይ እንዲከላከሉ የማድረግ ሥራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የኮሮና ቫይረስ ወርርሽኝ የመተላለፍ ፍጥነትን ከሚቀነሱ ስልቶች አንዱ እንደ ሆነ ከሚነገርለት በቤት ውስጥ ዘግቶ መቆየት ነው፡፡ ይሁን እንጅ ወረርሽኙ ከዓለም የሚጠፋበት ጊዜ አለመታወቁ በዜጎች ማኀበራዊና ኢኮኒሚያዊ ብሎም ፖለቲካዊና ስነ ልቦናዊ ጫናዎች ማስከተሉ በቤት ውስጥ መቆየት የሚለው አማራጭን ሀገራት በመተው አንደ አስፈላጊነቱ አንዴ ሲያላሉ እንዳንዴ ደግሞ ሲያጠብቁ ይስተዋላሉ፡፡ በኢትዮጵያም ሆነ በርዕሰ መዲናዋ አዲስ አበባ ከትምህርት ተቋማት ውጭ ወረርሽኙን በሥራ ላይ የመከለከል ላይ አትኩረዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘም የህግ ማዕቀፍ ወጥቶለት በትግበራ ላይ ነው፡፡ ስለ ተግባራዊነቱ የተጠየቁት በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የኢንዱስትሪ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት የሥራ ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ ስንታየሁ ለገሰ በከተማችን የሚገኙ የተለያዩ ፋብሪካዎች እና የግል ድርጅቶች በርካታ ሰራተኞች የሚሰሩባቸው ተቋማት በመሆናቸው ወረርሽኙን ለመከላከል የተለያዩ ተግባራት እያከናዎኑ መሆኑን ገለጸዋል፡፡
በተለይ ተቋማቱ ኮቪድ 19 የፈጠረውን ቀውስ ምክንያት በማድረግ ሰራተኞቻቸውን እንዳያግዱ፣ ከስራ እንዳይቀንሱ እና ያለ ደመወዝ እንዳይቀመጡ ተገቢ ክትትል የማድርግ እንዲሁም በርካታ ሰራተኞች ያሏቸው ተቋማት ሰራተኞች የዓመት እረፍት ወስደው እቤታቸው እንዲቀመጡና በተቃራኒ ፈረቃ እንዲሰሩ የማድረግ፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ እና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ለሰራተኞቻቸው እንዲያቀርቡ እና አካላዊ ርቀታቸውን ጠብቀው በመስራት የበሽታውን ስርጭት የመቆጣጠርና የመከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑን በክትትልና ቁጥጥር መረጋገጡን የስራ ቁጥጥር ቡድን መሪው አቶ ስንታየሁ ለገሰ ተናግረው ድርጅቱ የሰራተኞችን ደመወዝ መክፈል የማይችል ከሆነ ደግሞ ለሰራተኞቹ ብደር በመስጠት በረጅም ጊዜ ክፍያ እንዲከፍሉ በማድረግ ወይም ከሰራተኞች ጋር በውይይትና ስምምነት ላይ በመድረስ ሰራተኞችን መቀነስ እንደሚቻል አክለው ገልጸውልናል፡፡
በተጨማሪም ኮቪድ 19ኝን ለመከላከል በተለያዩ ድርጅቶች ኮሚቴዎችና ግብረ ሀይሎችን በማቋቋም ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸውልናል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
