19/03/2024
State Minister Henos Worku - ሔኖስ ወርቁ
This is my official government Page for my office as Governor
19/03/2024
19/03/2024
#ኢትዮጵያ|🇪🇹
ከጉሙዝ አብራክ የወጣችው ፅግሽ ኢትዮጵያዊት የፅናትና የአይበገሬነት ተምሳሌታችን በዛሬው ዕለትም ዳግም በጋና አክራ የሀገራችንን የኢትዮጵያ ባንዲራ በአዲስ ድል እንደገና ከፍ አድርጋ ሰቅላ አስፈንድቃናለች። ለኔ በተከታታይ እያስመዘገበች ባለችው አኩሪ ድል በተናጠል ሀገሩን እንደሚወድ ዜጋ ከሚሰጠኝ ደስታ በተጨማሪ ከወጣንበት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለይም ከጉሙዝ ማህበረሰብ አንፃር እርሷን ተመልክተው በተለያየ የህይወት መስክ ስኬታማ መሆን ለካ ይቻላል የሚል ተስፋን የሚሰንቁ እምቦቀቅሎች፣ ወንድና ሴት ብላቴኖችን ሳስብ ነው።
#አለገና ❗
16/08/2023
#ኢትዮጵያ|🇪🇹
በአንድ ሀገር ውስጥ የሀሳብ ልዩነቶች ይኖራሉ። የሀሳብ ልዩነት እርግማን አይደለም። ልዩነቱ እንዳለ ሆኖ መደማመጥና በመርህ ላይ ተመስርተን መግባባት ስንችል የሀሳብ ልዩነት በረከት ይዞልን ይመጣል። በሀሳብ ፍጭት ውስጥ መፍትሄ ይገኛል። በመተባበር ውስጥ ኃይል አለ። ስንደመር እንጠነክራለን። አንድነት የማይፈታው ችግር አይኖርም… አገር ይገነባል።
የኔ ሀሳብ ካላሸነፈ ሞቼ እገኛለሁ ማለት ግን እንኳን አገርን ሊያቆም ቤተሰብን ያፈርሳል። ያለችን ኢትዮጵያ ነች ከየትኛውም የፖለቲካ አመለካከት በላይ ሀገራዊ አንድነት ይበልጣል። አንድነት ማለት ግን አንድ ዓይነትነት ማለት እንዳልሆነ ሊሰመርበት ይገባል። አንድነታችን ልዩነቶቻችንን ያቀፈ ብዝሃነታችንን በህብረ-ብሔራዊነት ያደመደቀ መሆን አለበት።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
08/08/2023
#ኢትዮጵያ|🇪🇹
እንደሚታወቀው ሀገራችን ኢትዮጵያን ለሶስት አስርት አመታት ገደማ ሲያስተዳድር የቆየው ስርዓት ከስልጣን ተወግዶ በኢትዮጵያ ሠማይ ስር በታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ ሠላማዊ የስልጣን ሽግግር በስኬት በማጠናቀቅ እንዲሁም የለውጥ ሀይሉ የሚመራው የብልፅግና ፓርቲ ከሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ፍትሀዊ፣ አካታችና ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ውድድሩን በአሸናፊነት በማጠናቀቅ ቅቡልነት ያለው መንግስት መመስረቱ የሁላችንም የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።
ምንም እንኳን የለውጡ መንግስት ወደፊት ይምጣ እንጂ ታዲያ በጊዜው እዚህም እዝያም ለውጡ ያልተመቻቸው ቡድኖችና የአራት ኪሎ የወንበር ናፋቂዎች የለውጡን ጉዞ ለማደነቃቀፍ እንዲሁም ሴራ ለመሸረብ ጊዜ አልወሰደባቸውም ነበር። በዚህም ለውጡን በስጋት የተመለከቱት እነዚህ አካላት በውጭ ሀይሎች ጭምር እየታገዙ በየጊዜው በሚሸርቡት ሴራ ምክንያት የበርካታ ዜጎችን ህይወት የቀጠፉ፣ ለብዙዎች መፈናቀል ምክንያት የሆኑ፣ ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ያመጡ የተቀነባበሩ ጥፋቶች መጠኑ ይለያይ እንጂ በመላ ሀገሪቷ ላይ ተከስተዋል።
አሁንም እነዚህ ፅንፍ የረገጡ አካላት መልካቸውን ቀይረውና አጀንዳ ቀምረው እንዲሁም የተለያዩ ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶችን በመጠቀም ጭምር በዚህ ዕኩይ ተግባራቸው ቀጥለዋል። ከሀሳብ ሙግትና በአመክንዮ ላይ የተመሠረተ ሰላማዊ የፖለቲካ ስልትን ቀይሶ ሀሳቡንም ሸጦ ህዝብ ከማሰለፍ ይልቅ ኋላ ቀር በሆነ መንገድ በትጥቅ ትግል አንዳች ተዓምራዊ ለውጥ እንደሚመጣ በቅዠት አለም የሚንከላወሰውን የጃዊሳውን ቡድን እንደማየት፣ በዚህ ቡድንም ተሰብኮ በስሜት እየተነዳ በአሁኑ ጊዜ ውድ ህይወቱን የሚገብርን ኢትዮጵያዊ ወጣት እንደመመልከት የሚያሳዝን ነገር ግን የለም።
አንዳንድ እናውቅልሀለን ባዮችም በተደላደለ መንገድ ኑሯቸውን በውጭ ሀገራት ጭምር እየመሩ በመንግስትም ይሁን በመሪዎች ላይ ባላቸው የግል ጥላቻ፣ የፖለቲካ የሃሳብ ልዩነት፣ ኩርፊያና ቁርሾ ብቻ ህዛባዊ ሳይሆኑ እንደሆኑ በመለፈፍ ወጣቱን አምራች ሀይል የእነርሱን ጦርነት እንዲዋጋ ለማይጠረቃ የፖለቲካ አጀንዳ ማሳኪያ በመቀስቀስ መማገድ ግዜው ያለፈበት ብቻ ሳይሆን አሳፋሪም፣ አስነዋሪም ተግባር ነው።
የትላንቱ ሳያንስም ከህዝብ አብራክ የወጣውንና የሀገር አለኝታ የሆነውን መላከያ ሰራዊታችንን በመውጋት ለማዋረድ ብዙ እርቀት የመሄዳቸውን ዜና ለሰማና ለተመለከተ ድርጊታቸው ቅስም ሰባሪ ነው። ይሁንና የኢትዮጵያ ብልፅግና በፈጣሪ ዕገዛ፣ በቆራጥ ልጆቿ ፅናትና በህዝባችን ድጋፍ ዕውን እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። እኛ ግን ጦርነት አንገሽግሾናል፣ ህዝባችንም ሰልችቶታል፣ ሰላምንም እንሻለን።
ሠላም ለሁሉም
ሁሉም ለሠላም‼
27/04/2023
#ኢትዮጵያ|🇪🇹
በወንድማችን ግርማ የሺጥላ ህልፈተ-ህይወት ከፍተኛ ሀዘን ተሠምቶኛል። እጅግም ልብ ይሠብራል፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ለትግል አጋሮቹ ከልብ የሆነ መጽናናትን እመኛለሁ‼️
27/04/2023
#ኢትዮጵያ|🇪🇹
ሠላም የሁሉ መሠረት፣ ካለፈው ስህተት ተምሮ ልዩነቶችን በመነጋገርና በድርድር መፍታት ብልህነት፣ ህብረብሄራዊ ወንድማማችነትና እውነተኛ ፌደራሊዝም ደግሞ
ለሀገረ መንግስት ግንባታና ለኢትዮጵያ ብልፅግና መሠረት ነው‼
20/04/2023
#ኢትዮጵያ|🇪🇹
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወንድሞቼና እህቶቼ እንኳን ለኢድ አል-ፈጥር ዐዓል በሰላም አደረሳችሁ‼️
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
8845
