Addis ketema Wereda 13 Communication

Directions Contact the organization

Addis ketema Wereda 13 Communication This is Addis Ketema Sub-city wereda 13 Communication Offical page,Come and join us!

የመደመር መንግሥት"በግንባርም፣ በሚዲያም፣ በሰይፍም በሰልፍም ፣ በውሸትም፣ በሀሜትም፣  በተንኮልም፣ በሽረባም፣ ባገኙት የትግል ሜዳ ሁሉ ከጉዟችን ሊያደናቅፉን መከራቸውን አዩ፤ ኢትዮጵያን ግ...
06/10/2026

የመደመር መንግሥት

"በግንባርም፣ በሚዲያም፣ በሰይፍም በሰልፍም ፣ በውሸትም፣ በሀሜትም፣ በተንኮልም፣ በሽረባም፣ ባገኙት የትግል ሜዳ ሁሉ ከጉዟችን ሊያደናቅፉን መከራቸውን አዩ፤ ኢትዮጵያን ግን አልቻሏትም፤ አይችሏትም!"

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

#የመደመርመንግሥት

የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስነ-ሥርዓት - በምስል  #የመደመርመንግሥት
06/10/2026

የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስነ-ሥርዓት - በምስል


#የመደመርመንግሥት

አቶ ሙሉቀን  ታሪኩ ከቀድሞ የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ከነበሩት  አቶ ሃፍታይ  ገብረግዚኣብሔር ጋር  የስራ ርክክብ  አደረጉ! አዲስ የተሾሙት የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ...
06/10/2026

አቶ ሙሉቀን ታሪኩ ከቀድሞ የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ከነበሩት አቶ ሃፍታይ ገብረግዚኣብሔር ጋር የስራ ርክክብ አደረጉ!

አዲስ የተሾሙት የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ታሪኩ ከቀድሞ የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ከነበሩት አቶ ሃፍታይ ገብረግዚኣብሔር ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል ።

በዛሬዉ ዕለት በተደረገዉ የስራ ርክክብ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገብረግዚኣብሔር እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ታሪኩ የመልካም የስራ ዘመን ምኞታቸዉን የተለዋወጡ ሲሆን፤ ቢሮዉም ለሁለቱም ተሿሚዎች መልካም የስራ እና የስኬት ዘመን እንዲሆንላቸዉ ተመኝቷል።

ወደ ነገ መሻገር የሚያስችል ታሪካዊ አተያይ በተግባር እየተገነባ ነው፡- ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  ከትናንት መልካሙን በመውሰድና ዛሬ ላይ አስፈላጊውን እሴት በመጨመር ወደ ነ...
06/10/2026

ወደ ነገ መሻገር የሚያስችል ታሪካዊ አተያይ በተግባር እየተገነባ ነው፡- ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ከትናንት መልካሙን በመውሰድና ዛሬ ላይ አስፈላጊውን እሴት በመጨመር ወደ ነገ መሻገር የሚያስችል ታሪካዊ አተያይ በተግባር እየተገነባ መሆኑን ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክክር ቤት በትናንትናው ዕለት ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ መፍትሄዋን ከራሷ ማህጸን ማውጣት እንደጀመረች አብስረዋል።

የውጭ ሀገራትን ርዕዮተ ዓለም ገልብጦ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ለመትከል የተደረጉ የዘመናት ሙከራዎች፣ ከመልካም ሰብል ይልቅ አረም እያበቀሉ ሀገራችንን ለችግር መዳረጋቸውን አመላክተዋል።

የአውሮፓና የእስያ ስልጣኔዎች የራሳቸውን ባህል መሠረት አድርገው እንደተገነቡት ሁሉ፣ ኢትዮጵያም በራሷ እሴት ላይ የታነጸ 'የመደመር' እሳቤ መከተሏን አብራርተዋል።

ይህ ሀገር በቀል እሳቤ፣ የሕዝቦችን ብዝኃነት ከአንድነት፣ አካባቢያዊነትን ከሀገር እንዲሁም የግል ፍላጎትን ከቡድን ጋር አስተሳስሮ የሚያስኬድ የስልጣኔ ማሰቢያ ቋንቋ መሆኑን አስረድተዋል።

ከባሕር ማዶ የሚመጡ ዕሳቤዎችን አጠቃቀም በተመለከተም ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ለሌሎች ዕሳቤ ኢትዮጵያን ከመቀየር ይልቅ ለኢትዮጵያ ሲባል የሌሎችን ዕሳቤ አቃንቶ መቀበል ተገቢ አካሄድ ነው" በማለት ጠንካራ ፖለቲካዊ አቋማቸውን አንጸባርቀዋል።

በዚህም መሠረት ትናንትን ሙሉ በሙሉ እንደ እርኩስ ወይም እንደ ቅዱስ ከሚቆጥረው የጽንፍ ፖለቲካ በመውጣት፣ ከትናንት መልካሙን በመውሰድና ዛሬ ላይ አስፈላጊውን እሴት በመጨመር ወደ ነገ መሻገር የሚያስችል ታሪካዊ አተያይ በተግባር እየተገነባ መሆኑን ተናግረዋል።

"መጪውን ዘመን ቀድመው አስበው የሚመጣውን አዲስ ነገር በተጠንቀቅ ለሚጠብቁ ብርቱዎች ምንዳው ብዙ ነው፤ በአንጻሩ  ተዘናግተው ለሚቆዩ ደካሞች እዳው እልፍ ነው።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕ...
05/10/2026

"መጪውን ዘመን ቀድመው አስበው የሚመጣውን አዲስ ነገር በተጠንቀቅ ለሚጠብቁ ብርቱዎች ምንዳው ብዙ ነው፤ በአንጻሩ ተዘናግተው ለሚቆዩ
ደካሞች እዳው እልፍ ነው።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ/ር)

ወንድሜን ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛን በደስታ ተቀብያለሁ።‎ ዛሬ የመደመር መንግሥት ምሥረታን ስናከብር ላስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ኢትዮጵያ እና ደቡብ ...
05/10/2026

ወንድሜን ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛን በደስታ ተቀብያለሁ።
‎ ዛሬ የመደመር መንግሥት ምሥረታን ስናከብር ላስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ ለአህጉሩ አንድነት፣ ሰላም፣ ልማት እና ብሩህ ተስፋ ባላቸው የጋራ ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ እና ታሪካዊ ግንኙነት አላቸው። አጋርነታችንን ይበልጥ ለማሳደግ እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የወዳጅነት ትስስር እንደምናጠናክር ተስፋ አለኝ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

"ሥርዓት በአንድ ጀምበር አይገነባም" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)*****************ሀገራዊ የሥርዓት ግንባታ በአንድ ጀምበር ተገንብቶ የሚያልቅ ሳይሆን ጥበብን፣ ስክነ...
05/10/2026

"ሥርዓት በአንድ ጀምበር አይገነባም" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*****************

ሀገራዊ የሥርዓት ግንባታ በአንድ ጀምበር ተገንብቶ የሚያልቅ ሳይሆን ጥበብን፣ ስክነትን፣ ትዕግሥትን እና ትጋትን በተመጣጠነ መልኩ የሚጠይቅ የረጅም ሂደት ጉዞ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የ2010 ዓ.ም ሀገራዊ ለውጥ እንዲመጣ ዋነኛ ገፊ ምክንያት የነበረው "እንዴት ወደ ኋላ እንቀራለን?" የሚል ጥልቅ ሀገራዊ ቁጭት እንደነበር አስታውሰዋል።

ይሁን እንጂ ቁጭት የጉዞ መነሻ እንጂ መዳረሻም ሆነ ማድረሻ ሊሆን እንደማይችል ገልጸው፤ የቁጭት ማድረሻው ጠንካራ ሥርዓት፣ የመጨረሻ መዳረሻው ደግሞ ሥልጣኔ መሆኑን አብራርተዋል።

ይህን የሕዝብ ቁጭት ወደ ጠንካራ ሥርዓት አዋላጅነት ለመቀየር ሰክኖ ማሰብ፣ ማሰላሰል፣ መሞከር፣ የተሻለውን መምረጥ እና ዘወትር ማሻሻል ግድ እንደሚልም አጽንኦት ሰጥተውበታል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሥርዓት የመገንባት ሙከራ ሲደረግ የቁጭት እጥረት አጋጥሞ እንደማያውቅ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ በተቃራኒው ስክነት ማጣት እና ለአዳዲስ ሐሳቦች ዝግ መሆን ጠንካራ ሥርዓት መሠረት እንዳይይዝ ማድረጉን አስረድተዋል።

በተለይም ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታን በሚገባ በመገንዘብ ለኢትዮጵያ አዋጭ የሆነውን መንገድ መርጦ ከመተግበር ይልቅ፣ የኢትዮጵያን ችግር በውጭ ሀገራት ዕይታ ለመፍታት መሞከር በሂደቱ ከፍተኛ ዋጋ ማስከፈሉን አብራርተዋል።

"ምንጩን የሚረሳ ወንዝ እንደሚደርቀው ሁሉ፣ ከሥሩ የተነጠለ ሕዝብ መጨረሻው አያምርም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መሠረቱን፣ ባህሉን፣ ልማዱን እና ሀገራዊ እሳቤውን በመጣል የሚጀመር የሥልጣኔ ጉዞ ሩቅ ሊጓዝ እንደማይችል ገልጸዋል።

ባለፉት ስምንት ዓመታት ኢትዮጵያን ከዚህ አዙሪት ለማውጣት በርካታ ጥረቶች ተደርገው ውጤት መገኘቱን ጠቅሰው፤ በዚህም የኢትዮጵያዊነት መሠረት የሆነውን የመደመር እሳቤ ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉን ተናግረዋል።

“ጥያቄው ታላቁን ርዕያችንን ማሳካት ይቻላል ወይስ አይቻልም የሚለው አይደለም፤ እንደሚቻል እርግጠኞች ነን!” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ኢትዮጵያ አሁን ላይ የጀመረችው አዲስ ...
05/10/2026

“ጥያቄው ታላቁን ርዕያችንን ማሳካት ይቻላል ወይስ አይቻልም የሚለው አይደለም፤ እንደሚቻል እርግጠኞች ነን!” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ አሁን ላይ የጀመረችው አዲስ የብልጽግና እና የስልጣኔ ጉዞ ባዶ ፉከራ ሳይሆን በመሬት ላይ በተጨባጭ የሚገለጥ የትውልድ ቃል ኪዳን መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አረጋገጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ባላንጣዎች በተናጠል ተከፋፍለው ሊያጠቁ ሲከብዳቸው ለክፋትና ለሴራ ማበራቸውን በማስታወስ፤ አዲሱን የኢትዮጵያ ስልጣኔ የመገንባቱ ሂደት በመላው ሕዝብ ዘንድ ጽኑ እምነት የተጣለበት ታላቅ ሀገራዊ እውነት መሆኑን አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያን የማድረግ አቅም በጽኑ መንፈስ ያበሰሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ “ጥያቄው ይቻላል ወይስ አይቻልም የሚለው አይደለም፤ እንደሚቻል እርግጠኞች ነን!” ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል።

አክለውም ትልቁ ፈተናና ዋነኛው ትኩረት የሚሻው ጉዳይ ራዕዩን በምን መልኩና እንዴት አድርገን በተግባር እናሳካዋለን ለሚለው ስልታዊ ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ መስጠት ላይ መሆኑን አብራርተዋል።

በመደመር እሳቤ ተጉዞ የታለመውን ሀገራዊ የከፍታ ማማ ለመጨበጥ ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ እንደሌለ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለተቀመጠው ግብ መሳካት የሚያግዙ ቁልፍ መሣሪያዎችን በዝርዝር አመልክተዋል።

በዚህም መሠረት እምቅ ሀገራዊ አቅሞችን በጥልቀት መረዳት፣ የአካሄድ ስልቶችን ከግብርና ከንባብ ጋር ማጣጣም፣ ከዓለም አቀፍ የተሻሉ ተሞክሮዎችን ወስዶ ከራስ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ማስማማት፣ በብሔራዊ አንድነት ላይ ጸንቶ መቆም፣ የቡድን እና የግል መብቶችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ማስጠበቅ እንዲሁም ጠንካራ ሲቪክ ማንነትን ገንብቶ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ምህዳርን በሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ላይ ማጽናት ወሳኝ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ በመንግሥትና በሕዝብ የማይበገር አብሮነትና በጽናት የያዘችውን የብልጽግና ርዕይ ከዳር በማድረስ፣ የነገዋን የበለጸገችና ሉዓላዊ ክብሯ የተጠበቀ ታላቅ ሀገር ለትውልድ ማውረሷ የማይቀር ታሪካዊ እውነታ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ አስታውቀዋል።

! ! !

ለዚህ ያበቃን ፈጣሪያችንን እናመሠግናለን !!መላው  ሰላምና ልማት ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ!!እንኳን ደስ አለን!!ጀግናው ፣ ሀገር ወዳድና የኢትዮጵያ ስጦታ  ክቡር ጠቅላ...
05/10/2026

ለዚህ ያበቃን ፈጣሪያችንን እናመሠግናለን !!

መላው ሰላምና ልማት ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ!!
እንኳን ደስ አለን!!
ጀግናው ፣ ሀገር ወዳድና የኢትዮጵያ ስጦታ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን መልካም የስራ ዘመን!!

ባለፉት ዓመታት ሀገራችንን ከገጠማት ዘርፈ ብዙ ውጣ ውረድ ታድገን፣ በተግባር ባረጋገጥነው የማይበገር ጽናት እና ሌት ተቀን ባከናወንናቸው ጠንካራ የልማት ሥራዎች የሕዝባችንን አመኔታና ድምፅ በማግኘት በድጋሚ በሕዝብ ይሁንታና ድምፅ ጠንካራ የመደመር መንግሥት ለመመሥረት ችለናል።

ለኢትዮጵያችን ዳግም ማንሰራራት አርአያ የሆኑን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት ለሀገር ሉዓላዊነት፣ ለፍትሐዊነትና ለዜጎች ሁለንተናዊ ብልጽግና በፅናት እንቁም፤ እንተባበር!!

ትናንት ፈተናዎችን በብቃት ተሻግረናል፤ በተግባር የተፈተነው አቅማችንና የተስፋ አድማሳችን እጅግ የገዘፈ ነው። ኢትዮጵያችን በእርግጠኝነት የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ታሳካለች! በመላው ኢትዮጵያውያን ጽኑ ትብብር፣ የጋራ ርብርብ፣ ወንድማማችነትና የማይበጠስ አንድነት የታላቅነት ጉዟችን በእርግጥም ከጫፍ ይደርሳል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ ነገር ዕዳም ምንዳም ያለው በመሆኑ ለሀገራችን የሚበጀውን መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)አዲስ ነገር ዕዳም ምንዳም ያለው በመሆኑ ...
05/10/2026

አዲስ ነገር ዕዳም ምንዳም ያለው በመሆኑ ለሀገራችን የሚበጀውን መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ ነገር ዕዳም ምንዳም ያለው በመሆኑ ለሀገራችን የሚበጀውን መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ እንደማይኖራትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሰየሙ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ 7ኛውን ምርጫ በቀላሉ እንዳልመረጠ ጠቁመዋል።

ነገር ግን ህልውናውን ለማጽናት ፈተናዎችን ሁሉ በጽናት አልፎ ውሳኔውን ማሳወቁን እና በዚህም ጠንካራ የመንግሥት ሥርዓት ለመሥራት የሚያስችል መሠረት መጣሉን ገልጸዋል።

ዓለም በተለያየ መልኩ እየተቀያየረች እና አይገመቴነት በሰፈነበት በአሁኑ ወቅት ሀገራችንን በጽኑ መሠረት ላይ ማቆም ወሳኝ ሥራ መሆኑን ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ማንኛውም አዲስ ነገር ዕዳም ምንዳም ያለው በመሆኑ ለሀገራችን የሚበጀውን መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ዓለም በርካታ የኢንዱስትሪ አብዮቶችን ሲያሳልፍ ለሀገራችን የደረሳት ትራፊው ብቻ እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እንደ ሀገር ቀድሞ ካለመዘጋጀት የሚመጣውን ችግር ለመቋቋም አሁናዊ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

Address

Winget
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis ketema Wereda 13 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis ketema Wereda 13 Communication:

Shortcuts

Share