17/03/2026
ደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል/south Ethio peopls' region_Follow
idea exchaing media ግልጽ የሆነ ዉይይት የምናደርግበት ገጽ ነዉ
17/03/2026
22/01/2026
"ጊፋታ" በዓል በዓለም ቅርስነት (UNESCO) መመዝገቡን ተከትሎ ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋር የደስታ ማብሰሪያ በአደባባይ ይከበራል፡፡
የደስታ ማብሰሪያ በዓል "የጊፋታ ብስራቶች፤ ለህዝባችን ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል የፊታችን ዕለተ ማክሰኞ ጥር 19/2018 ዓ.ም ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋር በአደባባይ በወላይታ ሶዶ ከተማ በድምቀት ይከበራል።
ጊፋታ የኢትዮጵያ ኩራት ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም የጋራ ሀብት ሆኗል።
በሕንድ፥ ኒው ዴልሂ የተካሄደው 20ኛው የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (UNESCO)፥ የማይዳሰሱ የባህል ቅርሶች ጥበቃ ኮሚቴ ጉባኤ ኢትዮጵያ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ያቀረበችውን የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በሰው ልጅ የማይዳሰሱ የባህል ቅርሶች ስር መመዝገቡን ይታወቃል።
የደስታ ማብሰሪያ ጥር 17/2018 ለማክበር የተገለጸ ቢሆንም በሀገር ደረጃ የተያዘ ልዩ ፕሮግራም ከመኖሩ የተነሳ በጉጉት ስንጠብቅ የነበረውን የደስታ ማብሰሪያ በዓልን ጥር 19/2018 ዓ.ም ማክሰኞ ዕለት ለማክበር መግለጹንም ይታወሳል።
10/12/2025
የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ
አዲስ አበባ፣ ታሕሳስ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ፡፡
በሕንድ፣ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ጥበቃ ኮሚቴ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ያቀረበችው የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በሰው ልጅ የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ዝርዝር ስር ተመዝግቧል።
"ጊፋታ" በወላይታ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ በዓል ሲሆን፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የሕዝቡ የማንነት መገለጫ የሆነ የአሮጌው ዓመት ማብቂያና የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ የመሸጋገሪያ በዓል ነው፡፡
ጊፋታ እድሜ፣ ጾታ፣ ሃይማኖት ወይም ሌላ ማኅበራዊ ደረጃ ሳይለይ ለሁሉም ሠላም እና ማኅበራዊ ትሥሥር አስተዋጽኦ በማድረግ በዩኔስኮ የተለዩትን ዘርፎች ያካተተ ሁሉን አቀፍ ተግባራትን በማበረታታት የሚከበር በዓል መሆኑ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ አስችሎታል።
09/11/2025
አንጋፋው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ላዺሶ ጌ. ዴሌቦ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ማለፋቸውን ስንሰማ ኀዘን ተሰምቶናል። ነፍሳቸውን በዐጸደ ገነት እንዲያኖርልን እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንዲሰጥልን እንመኛለን።
20/09/2025
14/09/2025
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 50 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን አሳልፈዋል።
14/09/2025
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 48 ሺህ 929 ተማሪዎች ከ50 በመቶ በላይ በማምጣት አልፈዋል-ትምህርት ሚኒስቴር
መስከረም 4/2018 ዓ.ም
በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 48 ሺህ 929 ተማሪዎች ከ50 በመቶ በላይ በማምጣት ማለፋቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ይህም ከአምና ከነበረው 36 ሺህ 409 ተማሪዎች ጋር ሲነፃፀር 12 ሺህ ልዩነት እንዳለው ተገልጿል።
በ2017 የትምህርት ዘመን የተሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በተመለከተ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር) መግለጫ ሰጥተዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ በ2017 ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 48 ሺህ 929 ተማሪዎች 50 በመቶ በላይ አምጥተዋል።
ባለፈው አመት 5 ነጥብ 4 በመቶ ተማሪዎች ማለፋቸውን አስታውሰው፤ ዘንድሮ 8 ነጥብ 4 በመቶ ማለፋቸውን ተናግረዋል።
ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ 11 ነጥብ 4 በመቶ እንዲሁም በማህበራዊ ሳይንስ 5 ነጥብ 2 በመቶ መሆኑን ተናግረዋል።
በተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ከ600 ከፍተኛ ውጤት 591 ሲሆን ከሴት 579 መሆኑን ገልፀዋል።
በማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ከፍተኛ በወንድ 562 በሴት 548 መሆኑን ተናግረዋል።
ዘንድሮ 1 ሺህ 249 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ሲሆኑ 50 ትምህርት ቤቶች ደግሞ መቶ በመቶ ያሳለፉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ትልቁ ውጤት የመጣው ከአዳሪ ትምህርት ቤቶች አማካይ ውጤቱ 71 በመቶ መሆኑን ጠቁመው፤ ዝቅተኛ የመጣው ደግሞ በማታ ትምህርት ተማሪዎች መሆኑን ተናግረዋል።
በአጠቃላይ ፈተና የወሰዱት 585 ሺህ 882 ተማሪዎች ሲሆኑ 308 ሺህ 66ቱ ወንዶች እንዲሁም 277 ሺህ 816 ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል። #ኢዜአ
09/09/2025
ዛሬ ጳጉሜን 4 ህዳሴ የሚመረቅበት ቀን ነው
የእኛ የኢትዮጵያዊያን የድል ቀን
የኢትዮጵያ ከፍታ ማብሰሪያ
የማንሰራራት ዘመን መጀመሪያ
ከተስፋ ወደሚጨበጥ ብርሃን መሸጋገሪያ
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በጋራ የመወሰናችን፣ በህብረት የመትጋታችን፣ በአንድነት መቻላችን፣ በተስፋ የመፅናታችን የጀግንነት የኃያልነት ትዕምርት ነው።
ዳግማዊ አደዋ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ
በጋራ ችለናል፤ በጋራ እንመርቀዋለን!
08/09/2025
Proud to be part of this
Proudly Ethiopian
በኢትዮጵያ ሰማይ ስር
06/09/2025
የኢትዮዽያ ብሄራዊ ቡድን በግብፅ አቻው ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከግብፅ ብሄራዊ ቡድን ጋር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ 7ኛ ጨዋታውን አድርጓል።
በካይሮ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፈርኦኖቹ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ዋልያዎቹን አሸንፈዋል።
የፈርኦኖቹን የማሸነፊያ ግቦች ሞሀመድ ሳለህ እና ኦማር ማርሙሽ በመጀመሪያው አጋማሽ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥረዋል።
የኢትዮዽያ ብሄራዊ ቡድን የምድብ 8ኛ ጨዋታውን ጳጉሜ 4 ከሴራሊዮን ጋር ያከናውናል።
ምድቡን ግብፅ በ19 ነጥብ ስትመራ ቡርኪነፋሶ በ14፣ ሴራሊዮን በ9፣ ጊኒ ቢሳው በ7፣ ኢትዮዽያ በ6 እንዲሁም ጅቡቲ በ አንድ ነጥብ ከ2ኛ እስከ 6ኛ ያለውን ድረጃ ይዘዋል።
28/08/2025
ዛሬ ነሐሴ 22/2017 ዓ/ም
በክልላችን በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የውድ ወገኖቻችንን ህይወት አጥተናል።
በዚህ እጅግ ልብ ሰባሪ በሆነ ድንገተኛ አደጋ ባጣነዉ የወገኖቻችንን ህይወት የተሰማኝን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽኩ፤ ነፍሳቸዉን በአፀደ ገነት ፈጣሪ ያኑሪልን።
ለቀሪ ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለሁ።
በዚህ አጋጣሚ የክረምቱ ዝናብ መጠናከር ጋር ተያይዞ ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ተመሳሳይ አደጋ እንዳይከሰት ለአደጋዉ ተጋላጭ የሆኑ አከባቢዎችአስፈላጊዉ ጥንቃቄ እንዲደረግ የየራሳችን ኃላፊነት እድንወጣ አደራ እንላለን።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Telephone
Website
Address
A. A
Addis Ababa
