Disaster Risk Management Commission የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን

Disaster Risk Management Commission  የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን

Share

Ethiopian Disaster Risk Management Commission የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን

01/06/2026

የህብረተሰቡ ተሳትፎና ዝግጁነት ባህል እንዲጠናክር ይመከራል
***************************************************

እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 10/2026 (ግንቦት 24 እሰከ ሰኔ 3/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ አዝማሚያ
//////////////////
በጁን የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለይም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ከዚሁ ጋር በተያያዘም እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተስፋፋ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸዉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
በሚቀጥሉት ቀናቶች ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች እና የደቡብ እና የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ ከባድ (ከ1-30 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ በውሃ አካላትና በከባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛወ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በጁን የመጀመሪያው አስር ቀናት ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ሀይል ጋር በተያያዘ በተለይም የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር ክልል፣ በሰሜንና በደቡም ምዕራብ የሀገሪቱ ሥፍራዎች ሊይ ከ32 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ ትንበያዎች ያመላክታሉ፡፡

Photos from Abiy Ahmed Ali's post 01/06/2026

በቦረና ዞን ጎሞሌ ወረዳ የተጠናቀቁ የመስኖ ግድብ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት ተግባር የሚያጠናክሩ ሲሆን የምግብ ሉኣላዊነትን፣ በዘላቂ የውሃ አቅርቦት በማረጋገጥ ከ14,500 ሄክታር በላይ መሬትን በመስኖ በማልማት፣ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር እና የዜጎችን መልሶ የመቋቋም አቅም ለማሳደግ ጉልህ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ።

Photos from Disaster Risk Management Commission  የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን's post 30/05/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት ኢንሼቲቪስ ተግባራዊ የመልሶ ማቋቋም ሥራዎችን እያጠናከረ ነው::

ግንቦት 19/2018 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት ኢንሼቲቪስ ተግባራዊ የመልሶ ማቋቋም ሥራዎችን ጉብኝት በአባላ አባያ ተካሂዷል።

በጉብኝቱ ከአንድ ዓመት በፊት በካዎ ኮይሻ ወረዳ በደረሰ የመሬት ናዳ ምክንያት ተፈናቅለው የተቋቋሙ ወገኖችና ለአዲስ ሰፋሪዎች የተዘጋጁ መኖሪያ ስፍራዎች እንዲሁም የተገነቡ መሠረተ ልማቶች ተጎብኝተዋል።

በተለይም ከስድስት ወራት በፊት የተቋቋሙ ወገኖች በምርትና በኑሮ መልሶ ማቋቋም ሥራዎች አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ መሆናቸው ተመልክቷል። በተጨማሪም ለሰውና ለእንስሳት የሚያገለግሉ የጤና ተቋማት ግንባታ ተጠናቆ ወደ አገልግሎት ለመግባት በዝግጅት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ ሥራ ኢትዮጵያ በሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት ማዕቀፍ ውስጥ ከአስቸኳይ ዕርዳታ ባሻገር ወደ ዘላቂ መልሶ ማቋቋምና የዜጎች አቅም ግንባታ እየተሸጋገረች መሆኗን በተግባር የሚያሳይ ነው።

በጉብኝቱ ወቅትም ቀሪ የቁሳቁስና የድጋፍ ማሟያ ሥራዎችን በማጠናከር ተፈናቃዮችን ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ ኑሯቸው ለመመለስ ተጨማሪ ትኩረት እንደሚደረግ ተጠቁሟል።

ምንጭ፡ መሪሁን ፍቅሩ መጃ (ዶ/ር) – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በምክትል ርዕሰ መስተዳዳር ማዕረግ የግብርና ቢሮ ኃላፊና የዲላ ክላስተር አስተባባሪ










Photos from Abiy Ahmed Ali's post 29/05/2026
27/05/2026
Photos from Disaster Risk Management Commission  የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን's post 24/05/2026

Very important!

የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የእርጥበት እጥረት
ቅድመ ማስጠንቀቂያ መፅሄት ቁጥር-2
ግንቦት 22/2026
የ2018 ዓ.ም ክረምት ድርቅ ቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅድመ እርምጃ ማጠቃለያ ሰንጠረዥ

በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎችን ጨምሮ የደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝና 23/05/2026

በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎችን ጨምሮ የደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ::

News source: Ethiopian News Agency

በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎችን ጨምሮ የደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝና አዲስ አበባ፤ ግንቦት 14/2018 (ኢዜአ)፦በሚቀጥሉት አስር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎችን ጨምሮ የደቡብ ምዕራብ እና የምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች በርካታ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀ...

Photos from Disaster Risk Management Commission  የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን's post 22/05/2026

ግንቦት 14/2018 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን “የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት በኢትዮጵያ፡- እሳቤዎች፣ ማስፈንጠሪያዎችና መለኪያዎች” በሚል ርዕስ ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሥራ ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጠ፡፡

በሁለተኛው ቀን ሥልጠናውን የሰጡት የሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ማስተባበሪያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሻግሬ ተሾመ ሲሆኑ፣ በሥልጠናውም የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት ጽንሰ ሃሳብ፣ ምቹ ሁኔታዎች፣ መርሆዎች፣ ፍኖተ ካርታዎች እና የትግበራ ፓኬጆች ዙሪያ ሰፊ ገለጻ ተደርጓል፡፡

አቶ አሻግሬ በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም እና ሉዓላዊነት ዘርፍ የተመዘገቡ አመርቂ ውጤቶችን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን፣ በመደጋገፍና በመረዳዳት ረገድ የማህበረሰቡ መልካም እሴቶችና ተሞክሮዎችም ተዳሰዋል፡፡

በሥልጠናው ወቅት የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለማሳካት የተረጅነትና የልመና አስተሳሰብን መቀየር እንደሚገባ እና ዘላቂ የግንዛቤ ለውጥ ማምጣት አስፈላጊ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ድረስ ደስይበለው በማጠቃለያ ንግግራቸው፣ በተያዘው ዕቅድ መሠረት የተሰጠውን ሥልጠና እስከ ዞንና ወረዳ መዋቅሮች ድረስ በማውረድ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን እንደሚያከናውኑ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ፖሊሲውን መሠረት ያደረገ ሥራ በቅንጅትና በኃላፊነት መንፈስ መፈጸም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የሥልጠናው ተሳታፊ የሥራ ኃላፊዎችም በበኩላቸው የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተግባር ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል፡፡

@@@@@@@@@@@@@@@
ምርጫችሁ በማድረግ ስለምትከታተሉን እናመሰግናለን፡፡
The Commission expresses its heartfelt appreciation to all who continue to follow and support its efforts.
በፌስ ቡክ
https://web.facebook.com/profile.php?id=100080363110015
************************
ቴሌግራም፡ https://t.me/+JncBcJ9i3EBjYmI8
************************
በቲውተር: https://x.com/EDRMC_info
************************
በድረ ገጽ: https://edrmc.gov.et
************************
በቲክቶክ: edrmc_Ethiopia
************************
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/channel/UCG6KuvTtBptmEJO1i1pEMTg See less

Photos from Disaster Risk Management Commission  የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን's post 22/05/2026

ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም፡- በአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ፖሊሲ፣ በአዋጁ እና በሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ኢኒሼቲቭ ዙሪያ የአሰልጣኞች ሥልጠና ተካሂዷል፡፡

መድረኩን የከፈቱት የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ነሲቡ ያሲን ሲሆኑ፣ በ2030 የአይበገሬነት ሥርዓትን ለመገንባት እንደ ሀገር የፀደቀውን የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ፖሊሲ መሠረት ያደረገ የተቀናጀ ሥራ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሠረት የአሰልጣኞች ሥልጠና መሰጠቱን ጠቅሰው፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ የሚወርድ፣ በዕቅድ የተደገፈ እና በኃላፊነትና በባለቤትነት መንፈስ የሚመራ የተቀናጀ ሥራ ማከናወን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ምክትል ኮሚሽነሩ በተጨማሪም፣ ፖሊሲውን ለማስፈጸም የተለያዩ ተቋማት ኃላፊነት እንዳለባቸው በፖሊሲው ማዕቀፍ መካተታቸውን ገልጸው፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ራሱን የቻለ ሥልጣንና ተግባር ቢኖረውም በፖሊሲው ውስጥ ኃላፊነት ከተጣለባቸው ተቋማት አንዱ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለማሳካት የሚደረገውን የተቀናጀ ርብርብ ለማጠናከር የአሰራር ሥርዓትን ማዘመንና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በመድረኩም በኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ፖሊሲ ጽንሰ ሐሳብ፣ ማዕቀፍ፣ መርሆዎች፣ ዋና ዋና ዓላማዎች እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የኮሚሽኑ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ታደሰ በቀለ ጥልቅና ግንዛቤ ሰጪ ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡

ሥልጠናውን የተሳተፉት ከክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ዋና መሥሪያ ቤትና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች መሆናቸው ታዉቋል፡፡

@@@@@@@@@@@@@@@
ምርጫችሁ በማድረግ ስለምትከታተሉን እናመሰግናለን፡፡
The Commission expresses its heartfelt appreciation to all who continue to follow and support its efforts.
በፌስ ቡክ
https://web.facebook.com/profile.php?id=100080363110015
************************
ቴሌግራም፡ https://t.me/+JncBcJ9i3EBjYmI8
************************
በቲውተር: https://x.com/EDRMC_info
************************
በድረ ገጽ: https://edrmc.gov.et
************************
በቲክቶክ: edrmc_Ethiopia
************************
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/channel/UCG6KuvTtBptmEJO1i1pEMTg

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


EDRMC/Nifas Silk Near To Gotera Complex Road On The Debre Zeyt Road, Before Mulege Bld
Addis Ababa
251

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30