እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from እናት ፓርቲ, Political Party, Addis Ababa.

🔴እናት ፓርቲ ድምጽ ለተነፈጋቸው መላ ኢትዮጵያውያን ያለአድሎ ድምጽ በመኾን አገዛዙ ከእኩይ ድርጊቱ እንዲታቀብ፣ ፍትሕና እድገት በምልዓት እንዲሰፍን ያለመታከት ይሠራል። ዜጎች በነጻነት ተንቀሳቅሰው እንዲሠሩ፣ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ከተጋረጠባቸው የሕልውና አደጋ ለማዳን አበክሮ ይሠራል፤
🔴እናት ፓርቲ ፈጣሪን መፍራት መርኁ አድርጎ ውሕድ ወግ ጠባቂ ማኅበራዊ ዴሞክራሲን ያራምዳል!
👉🏾ይቀላቀሉን!

29/05/2026

የበሬ ወለደ ሀሰት ዘመቻ የሥርዓቱን ነውር ቢገልጥ'ጂ ተጋግሮ ዳቦ አይወጣውም!
ከሰሞኑ በማኅበራዊ ሚዲያ በሚናፈሰው ውሸት ዙሪያ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ከሰሞኑ የእናት ፓርቲ ፕሬዝዳንትና የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ም/ፕሬዝዳንት የኾኑት ሰይፈሥላሴ አያሌው(ዶ/ር) ከ አንከር ሚዲያ ጋር ቆይታ አድርገው ጠንከር ያሉ ሀሳቦችን በሰጡ ማግስት የብልጽግናው ተቀላቢ እንደ እብድ ውሻ ከፊቱ የቆመውን ኹሉ የሚናከሰው ስብስብ(በዳቦ ስሙ ሚዲያ ሠራዊት ወይም ዲጂታል ሸኔ) ከዋና ማዘዣው በጉሽ ወይን የጠጣውን መርዝ ዐይኑን እያጉረጠረጠ በሬ ወለደ ለሃጩን እያዝረበረበ ይገኛል።

ክቡር ፕሬዝዳንቱ ጠንከር ያሉ ሀሳቦችን በሰነዘሩ ማግስት ባልዋሉበትና እጅግ በሚፀየፉት ተግባር ሲብጠለጠሉ ከርመዋል። የብር ነገር ከተነሳ ዶ/ር ሰይፈ ሥላሴ በተገኙባቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ባልኾኑ ስብሰባዎች እንኳን ፈርመው አበል የተቀበሉበት አንድ አይገኝም ድንገት ለጠሪዎቹ ክብር ሲባል ከተገኘም ወደ ፓርቲው ካዝና በደረሰኝ አስገብተውታል። ኹሉም የፓርቲው አመራር እንደሚያውቀው ፓርቲው የገንዘብ ችግር ከገጠመው የመሙላት ሸክሙ በእርሳቸው ላይ የወደቀ ነው። በዚኽም ያልተመለሰላቸው በ100 ሺህ የሚገመት ገንዘብ ፓርቲው አለበት። እኛም እንስጥ አላልን እሳቸውም አምጡ አይሉም። ቢሮም ቢኾን ፓርቲያችን ብዙ ሺህ ብሮች ሊያስወጣ የነበረን ራሳቸው በሚያስተዳድሪሩት ሕንጻ በነጻ ከ 7 ወራት በላይ በነጻ ተጠቅሟል።

እርግጥ ክቡር ፕሬዝዳንቱ በየዓመቱ እንደሚያደርጉት ለእረፍትና ለግል የቴክኖሎጂ ጋር የተገናኘ ቢዝነሳቸውን ኹኔታዎችን ለማስተካከል ያንንም ለአመራሩ በውል አሳውቀውና ተፈቅዶላቸው ከወራት በፊት ወደ አሜሪካ ሄደዋል። ከሣምንት በፊትም ከብዙ ልፋትና ጥረት በኋላ በፓርቲው እውቅና፣ በአሜሪካ መንግሥት ሕጋዊ ሂደትን አሟልቶ የፓርቲው የሰሜን አሜሪካ ቻፕተር በተገኙበት አስጀምረዋል።

ስለኾነም ፓርቲው ያለበት እንጂ ክቡር ፕሬዝዳንቱ የወሰዱትም ንብረት ኾነ ገንዘብ የለም፤ ኖሮም አያውቅም።
የሥምሪቱ የምትሰጡ ጌቶች እብድ ውሾቻችኹን አባቶቻችን ሲያደርጉ እንደኖሩት ብዙ ሰው ሳይበክሉ ክትባት ብትሰጧቸው ወይም ቫይረሱ ተሠራጭቶ የማይድን ከኾነም ከማዘዣው ብታስገልሏቸው። በሬ ወለደ ሥርዓትን ይበልጥ ከማዋረድ የዘለለ ዳቦ አይኾን፣ አገር አያድን።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ- ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት
ግንቦት ፳፩ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

28/05/2026


ዛሬ ሐሙስ፣ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ወረጃርሶ ወረዳ፣ ከጎሐጽዮን 6 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ቀሬቡሐ ቀበሌ ከጠዋቱ 4:30 አካባቢ ከአማራ ክልል ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ ታታ የሚባለው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ሙሉ ተጓዥ ታፍነው የተወሰዱ ሲኾን እስከአኹን ባለን መረጃ 6 ሰዎች ተገድለዋል። እነዚኽ ብቻ ሳይኾን ወደጫካ ሲወስዱ መሮጥ ያልቻሉትንም በርካቶች ሳይገድሏቸው አልቀረም ብለውናል። ቦታው ኹለተኛው አሊዶሮ ነው፤ በድርጊቱም ሙሉ የመንግሥት መዋቅር ይሳተፍበታል። በነዋሪው አቤቱታ የታሠሩ አካላት አሉ የሚሉት እማኞች 10ሺህ ብር የማይሞላ ደመወዝ ያላቸው አራት እና አምስት ቤት የሠሩ፤ ድንገት የሦስትና አራት ሲኖ ባለቤት የኾኑ አሉ ሕዝቡ ያውቃቸዋል ይላሉ እማኞች ጨምረው። እንዲያውም አኹን አኹን ሰው ሲታፈን የከተማው ሸኔ ነው የጫካው ያፈነው? የሚል ቀልድ መሰል እውነት እስከመነገር ደርሷል ይላሉ።

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ይኽን መሰል የነውር ተግባርና ማንነት ተኮር ግድያ በጽኑ ያወግዛል። የታፈኑ ንጹሓንም ያለምንም ቅድመ ኹኔታ እንዲለቀቁ ያሳስባል።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት - ለኢትዮጵያ
ግንቦት ፳ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
****
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድት- Coalition for Eth. Unity

27/05/2026

!
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ለመላው የእስልምና አምነት ተከታይ ወገኖቻችን እንኳን ለ1ሺህ 447ኛው የዒድ አል-አድሃ(አረፋ) በዓል አደረሳችኹ ሲል መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

የተከበራችኹ በውስጥም ከሀገር ውጭም የምትገኙ ይኽን ታላቅ በዓል የምታከብሩ ኢትዮጵያውያን ኹሉ አገራችን ዛሬ ከባድ ፈተና ውስጥ ወድቃለች። እንደልብ ተዘዋውሮ መኖር ብርቅ ኾኗል፣ ሴቶች፣ አቅም ደካሞች እና ወጣቶች በአሰቃቂ ኹኔታ ይገደላሉ። ታላላቅ ዑለማዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ካህናትና ገዳማውያን ምንም በማያቁት ይገደላሉ። በርካቶች ምን አልባትም በሚሊዮን የሚቆጠሩ በአራቱም ማዕዘን በተለይ በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ክልሎች በመጠለያ ጣቢያዎች በሰቆቃ ውስጥ ይገኛሉ።

ታላላቅ አባቶችና ዑለማዎች የሚካሄዱ ጦርነቶችን በድፍረት ወጥተው ማውገዝ መንግሥትም ታጣቂ ቡድኖችም ወደቀልባቸው ተመልሰው ስለሀገር ሲባል ወደጠረጴዛ ዙሪያ ድርድር እንዲመጡ አባታዊ ጥሪ ያቅርቡ። ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ባለው ሃይማኖታዊና ባህላዊ የዳበረ የማካፈል እሴት(ዘካ) እነዚኽን የዕለት ጉርስ የሚፈልጉ ወገኖች እንዲያግዝና ለሐጂሩም እንዲሠራ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ዛሬ ዕለቱ የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያና ውድ ቀን ቢኾንም ትብብራችን ዕለቱን በማክበር ትናንት ማክሰኞ ማጠቃለያውን በማድረግ በዓሉን በደስታና በፀጥታ ማሳለፍን መርጧል።

በድጋሚ መልካም የአረፋ በዓል

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት - ለኢትዮጵያ
ግንቦት ፲፱ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

👍 ገጾቻችንን ይወዳጁ👍
https://www.facebook.com/share/1JwwMKYDV1/
👍👍
https://t.me/tibibir_2018
👍👍
https://vt.tiktok.com/ZSuj3572y

26/05/2026

የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የምሥራቅ ኮከብ ድሬዳዋ ቅስቀሳ ፕሮግራም

በትብብር ከባንበት የሕልውና አደጋ እንዳን!

ምልክታችን አውራ ጣት ነው

26/05/2026
26/05/2026

ታላቁ አፄ ምኒልክ ሐውልት ዙሪያ

26/05/2026

የቅስቀሳ ማጠቃለያ ፕሮግራም ቀጥታ ሥርጭት አለን

26/05/2026

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ወላይታና አከባቢ ማስተባበሪያ ዳሞት ውይዴ ምርጫ ፩ ዕጩዎች

ምልክታችን አውራ ጣት ነው

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Address


Addis Ababa