12/10/2026
🇪🇹 በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ 19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በድምቀት ተከበረ! 🇪🇹
''ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና አንድነታችን!" በሚል ታላቅ ሀገራዊ መሪ ቃል 19ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ በደነባ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጋር በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሪት አመዘነች ሀይሉ ባደረጉት ንግግር "ሰንደቅ ዓላማችን የአንድነታችን፣ የሉዓላዊነታችንና የሀገራዊ ኩራታችን ህያው ምልክት ነው። ኢትዮጵያ ሀገራችን ጀግኖች እናትና አባቶቻችን ህይወታቸውን የገበሩላት ታላቅና ድቅድቅ ሀገር ናት።" የዛሬውን የባንዲራ ቀን ስናከብር የሀገራችንን ሉዓላዊነት ያስከበሩልን አባቶቻችን ደማቸውን አፍስሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው ያስረከቡንን አደራ እኛም ጠብቀን ለሚቀጥለው ትውልድ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል ብለዋል።
በተላለፋ መልዕክቶችም ሰንደቅ ዓላማ ቀን አከባበር የሀገርን ታሪክ፣ ክብርና የሉዓላዊነት ገድል የሚያስታውስ ታላቅ ሀገራዊ ኩነት ነው፤ ዜጎች ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅር፣ አገራዊ አንድነትና የዜግነት ኃላፊነት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው፤ የተከፈለውን መስዋዕትነት በመዘከር ለነገዋ ኢትዮጵያ በጋራ የመቆም ቁርጠኝነት የተገለፀበት ዕለት ሆኖ አልፏል ።