የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የኮልፌ ቀራንዮ ቅርንጫፍ

የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የኮልፌ ቀራንዮ ቅርንጫፍ

Share

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈ? ስለመንጃ ፈቃድ በተመለከተ --- 0113-69-79-23
ስለተሽከርካሪ (መኪና) በተመለከተ --- 0113-69-72-52

25/04/2022

የአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሸከርካሪ መረጃ ማዕከል ሚያዚያ 17/08/2014ዓ.ም አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሸከርካሪ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ኮድ 02 አአ ሰሌዳ ″B″ በማለቁ ምክንያት ከቀን 17/08/2014ዓ.ም ጀምሮ ኮድ 02 አአ ሰሌዳ ″C″ መስጠት የጀመረ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

መረጃ ፡-የአዲስ አበባ አሽከርካሪ ተሸከርካሪ መረጃ ማዕከል

telegram ገፃችን፡- https://t.me/AddisAbabaDVInfocenter_bot
የFaceBook ገፃችን፡- https://www.facebook.com/AADVInfoCenter
ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Photos from የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን AA Driver and Vehicle Authority's post 23/03/2022
22/02/2022

ለክቡራን ተገልጋዮቻችን በሙሉ
በአሽከርካሪና ተሽርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅርቡ አገልግሎት ለማስጀመር ቅድመ ስራ እየተከናወነ ሲሆን የፋይል ዝውውር ስራ በመከናወን ይገኛል፡፡
በመሆኑም ከዚህ ቀደም በቦሌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ተሽርካሪችሁ የተመዘገበና፡-
ከ ኮድ 2 - B 22459 – B 89030 AA
ከ ኮድ 3- B 00983 - B 30284 AA
ፋይላችሁ ወደ ለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የተዛወረ መሆኑን እያሳወቅን ከዚህ በኋላ አገልግሎት የምታገኙት በተዛወረበት ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ይሆናል፡፡
ይሁንና ከላይ በተጠቀሰው የሰሌዳ ቁጥር ውስጥ የምትገኙና ከቦሌ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ውጭ ያላችሁና በሌላ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ተሽርካሪያችሁ የተመዘገበ ተገልጋዮች ፋይላችሁ ባለበት ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አገልግሎት ማግኘት የምትቀጥሉ ይሆናል፡፡
ወደ ለሚ ኩራ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ፋይላችሁ የተዛወረ ተገልጋዮቻችን ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱን የማደራጀት ስራው በቅርቡ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር መሆኑን እያሳወቅን ስራ ሲጀምር አስቀድመን የምናሳውቃችሁ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የአሽከርካሪና ተሽርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን

11/02/2022

ክቡራን ተገልጋዮቻችን ነገ ማለትም ቅዳሜ 5/6/2014 የአሽከርካሪዎች መረጃ ቋት ላይ ማሻሻያ ስለሚደረግ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ህትመት የማንሰጥ መሆኑን በ አክብሮት እንገልፃለን፡፡

01/10/2021

አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን መልካም የእሬቻ በዓል እየተመኘ ቅዳሜ መስከረም 22 /2014 ዓ ም አገልግሎት የማንሰጥ መሆኑን ለክቡራን ተገልጋዮቻችን አስቀድመን እናሳውቃለን።
የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን

22/09/2021

የኮልፌ ቀራንዮ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ዘርፍ እውቅና ተሰጠው፡፡

22/09/2021

ለክቡራት ተገልጋዮቻችን የኢትዬጲያ ብሄራዊ ባንክ ለጊዜው ማንኛውም ህንፃ ፣ቤት ፣መሬት እና "ሌሎች" በመያዣነት ተጠቅመው ብድር እንዳይሰጥ ለባንኮች መመርያ ማስተላለፉን ተከትሎ ሌሎች በሚለው ተሽከርካሪንም ይመለከታል በማለት በባንኮች እና የአነስተኛ ብድር ተቋማት ተሽከርካሪን በማያዣነት ተጠቅመው ብድር ሲሰጡ ተሽከርካሪ እንዳይሸጥና እንዳይለወጥ በማድረግ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ከቀን 10/12/2013ዓ.ም ጀምሮ የተሽከርካሪ ብድር ዕግድ አገልግሎት ማቆሙን የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን ማሳወቁ ይታወቃል።
ሆኖም ክልከላው ተሽከርካሪ በመያዣነት የሚሰጥ ብድር የማይመለከት በመሆኑ ከቀን 11/01/2014ዓ.ም ጀምሮ የተሽከርካሪ የባንክ ብድር ዕግድ አገልግሎት መስጠት መጀመራችንን እናሳውቃለን፡፡

07/08/2021
Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Kolfe Keranyo
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 16:00
Tuesday 08:00 - 16:00
Wednesday 08:00 - 16:00
Thursday 08:00 - 16:00
Friday 08:00 - 16:00
Saturday 08:00 - 12:00