04/06/2026
በሁሉም ፈጣሪ አምላክ ረድቶን 7ኛውን ዙር ምርጫ ባጠናቀቅንበት ማግስት ዛሬ 8ኛውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ክፍት አድርገናል።
ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት ዛሬ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ባለ 7 ወለል ህንፃ ገንብተን በቴክኖሎጂ ተደራጅቶ 96 ተገልጋዮችን በአንድ ጊዜ የሚያስተናግዱ መስኮቶች ያሉት፣ በ22 ተቋማትና በ114 አገልግሎቶች ስራ አስጀምረናል።
ማዕከሉ ከፍ ባለ ጥራት እጅግ ውብ፣ ፅዱ፣ አካታች የሆነ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ፣ የህፃናት ማቆያ ያለው፣ ለሰራተኞችም ለተገልጋዮችም ምቹ ሆኖ የተገነባ ነው።
በቀጣይም በርካታ አገልግሎቶችን ወደ መሶብ ማዕከል በማስገባት ነዋሪዎች ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት እንዲያገኙ እናደርጋለን።
የከተማችን ነዋሪዋች መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አግልግሎት ለዘመናት አስልቺ ከነበረውና ውጣ ውረድ ከበዛበት እና በእጅ መንሻ ከተማረራችሁበት ቢሮክራሲ የሚያላቅቃችሁ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ! በማዕከላቱ በቦታ ሳትገደቡ በሚቀርባችሁ በየትኛውም ማዕከል በመገኘት ተገልገሉ።
ይህ ማዕከል ተጠናቆ ስራ እንዲጀምር ያስተባበራችሁትን በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
03/06/2026
ዛሬ በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ከሆኑት ንስቲያን ክርስተንሰን ጋር ውይይት አድርገናል።
በመጪው መስከረም በኢትዮጵያ በሚካሄደው የኖርዲክ - አፍሪካ ኢቪ ሰሚት (Nordic Africa EV Summit) ላይ በጋራ በምንሰራቸው ጉዳዮች ላይ ከአምባሳደሩ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። ከተማችን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶችን የማስተናገድና በብቃት የመወጣት ልምድ ያካበተችና ተመራጭ እየሆነች የመጣች በመሆኗ ይህንንም ጉባኤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እናሳካዋለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!
Today, we held discussions with H.E. Stian Christensen, Ambassador of Norway to Ethiopia.
We had a productive exchange with the Ambassador on areas of mutual cooperation in preparation for the upcoming Nordic Africa EV Summit, which will be held in Ethiopia this September.
During our discussion, I emphasized that our city has developed considerable experience and capacity in successfully hosting major continental and international events and is increasingly emerging as a preferred destination for such gatherings. I assured the Ambassador that, in close collaboration with all relevant stakeholders, we will organize this summit with the highest standards of professionalism and excellence.
Royal Norwegian Embassy in Addis Ababa
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
02/06/2026
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ ቆጠራው ተጠናቅቆ ጊዜያዊ ውጤቶች እየተገለፁ ነው።
የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችም በየምርጫ ጣቢያዎች የተለጠፈውን ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት እየተመለከቱ ይገኛሉ።
02/06/2026
ኢትዮዽያ አሸነፈች!!!
የሀገረ መንግስቱን ግንባታ ከዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አቅጣጫ ውጭ ባንዳና ባዳ ጥምረት ፈጥረው በአመፅና በኃይል ሀገራችንን ወደ ጥፋት መንገድ ለመክተት ያሴሩትን ደባ ሕዝቡ በዴሞክራሲያዊው ምርጫ እምቢተኝነቱንና ለሀገር ያለውን ፅኑ ፍቅር በተግባር በማሳየት አክሽፎታል።
በተለይ በአዲስ አባባ ረጃጅም ሰልፍ ቢፈጠርም ህዝቡ በእንቅልፍ እና በብርድ ሳይበገር ተራ እስኪደርሰው እስከ ለሊቱ 10:30 ሰአት ድረስ ተሰልፎ በሚገርም ጨዋነት፣ መሰጠት፣ ቁርጠኝነትና ፅናት መርጧል።
የሀገራችን ፖለትከኞችና ልሂቃን ይህንን ታላቅ ጽኑ ጨዋና ቆራጥ ሕዝብ የምንረዳውና የሚንመጥነው መሆን ይጠበቅብናል።
ፈጠሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
02/06/2026
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝቡ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠበት ነው!
የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
7ኛው ሃገራዊ ጠቅላላ ምርጫ መራጩ ሕዝብ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነትና ፍላጎት በተግባር ያረጋገጠበት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ።
ምክር ቤቱ የ7ኛው ሃገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ሂደት መጠናቀቁን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።
የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ማሩ ጃኔ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ ምርጫው ግልጽነት እና ፍትሐዊነት ከመላበሱም ባሻገር በመራጩ የከተማዋ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ቅቡልነት ያሳየ ነው።
ምክር ቤቱ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጋር በመቀናጀት ለምርጫው ስኬታማነት መሥራቱን አስታውሰው፤ ይህም ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አብራርተዋል።
የምርጫ ሂደቱም እጅግ የተረጋጋ፣ የሰለጠነ እና የዴምክራሲ ሥርዓት ትግበራ ሂደትን ያጠናከረ ሆኖ ማለፉንም ጠቅሰዋል።
መገናኛ ብዙሃንም ለፓርቲዎች የሰጡት የአየር ሰዓት ፍትሐዊ፣ ግልጽና ለሁሉም ፓርቲዎች እኩል የመወዳደሪያ ሜዳ የሰጠ ነው ያሉት አቶ ማሩ፤ ይህም እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ ያሉትን የፖሊሲ አማራጭ ሀሳቦች ያለምንም ገደብና ጫና ለሕዝቡ የሚያቀርብበት ዕድል መፍጠሩን አስረድተዋል።
የጸጥታ አካላትም ያለምንም ወገኝተኝነት ፍጹም ገለልተኛ በሆነና ሙያዊ አካሄዶችን በተከተለ መንገድ የአዲስ አበባ ምርጫ ጣቢያዎችንና የመራጩን ሕዝብ ደህንነት ሲጠብቁ መዋላቸውን ያስታወሱት ሰብሳቢው፤ የጸጥታ አካላት ያከናወኑት ተግባር ሊመሰገን የሚገባው ነው ብለዋል።
የድምጽ ቆጠራውና ውጤቱን የማደራጀት ሥራ የሚያከናወነው በሕጉ መሰረት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በመሆኑም ውጤቱ በከተማ ደረጃ በኦፊሴላዊ መልኩ እስኪገለጽ ድረስ በትዕግስት እንዲጠበቅ ምክር ቤቱ ጥሪውን ያቀርባል ነው ያሉት።
ማንኛውም ወገን የምርጫ ውጤቱን በጸጋ የመቀበል ታሪካዊና ሞራላዊ ግዴታ እንዳለበት አመልክተው፤ ቅሬታዎች ቢኖሩ እንኳን በሕጋዊ እና በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ዘሪሁን ኮርሜ በበኩላቸው፤ በምርጫው አረጋዊያን፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ያሳዩት ተሳትፎ እና ቁርጠኝነት ተምሳሌታዊ መሆኑን ተናግረዋል።
ለምርጫው ስኬት አስተዋጽኦ ላደረገው መራጩ ሕዝብ፣ ለምርጫ ቦርድ፣ የከተማዋ የጸጥታ አካላት ጨምሮ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት በምክር ቤቱ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
የምርጫ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን የሕዝብ ድምጽ ልናከብር ይገባል ያሉት ምክትል ሰብሳቢው፤ የሰለጠነና ብስለት የተሞላበት የፖለቲካ አካሄድም ይሄው መንገድ ነው ብለዋል።
!
02/06/2026
የረዳን ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!!
ዛሬ በምርጫ ማግስት የእንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የአገልግሎት መስጫዎች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ተመርቀው ለህዝብ ክፍት አድርገናል።
በከተማችን ለሚገኙ ለብዙዎቹ ወንዞች መነሻና የከተማችን ሳምባ የሆነው ደን የሚገኝበት ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ ያለው አካባቢ ወደ ተፈጥሯዊ ይዘቱ ተመልሶ የአካባቢውን ማህበረሰብ አኩሪ የስራ ባህል የሚዘክሩ ሃውልቶችና ቅርሶች ተገንብተውለት አካባቢው ፍፁም ማራኪ እና የሚያስደንቅ ገፅታን ተላብስሶ ተጠናቋል።
የቀጨኔ አካባቢ ከዚህ ቀደም ለሰው ኑሮ ምቹ ያልሆነ፣ ለአደጋ የተጋለጠ እና የተጎሳቆለ አካባቢን መልሶ በማልማት ውስን የሆነውን የከተማዋን የመሬት ሀብት ለብዙሃን አገልግሎት እንዲሰጥ በሚያስችል መልኩ ለምቶ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
597 ሄክታር ቦታ እና 9.6 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የእንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት ለመዝናኛ፣ ለንግድና ለተለያዩ ማህበራዊ ኩነቶች ተስማሚ በሆነ መልኩ የተገነባ ሰፊ የከተማ መናፈሻ ሆኗል።
በከተማ ግብርና ስራዎች 15 ሄክታር ቦታ በአረንጓዴ የተሸፈነ ሲሆን፣ ቀሪው ደግሞ በ210 ቀፎ ዘመናዊ ንብ እርባታ፣ በአበባ ጋርደን እና በእፀዋት ጋርደን ለምቷል።
እንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ያካተታቸው ሌሎች መሰረተ ልማቶች፦
6.4 ኪሎ ሜትር የተሽከርካሪ መንገድ፣ 8 ኪሎ ሜትር የሳይክል መንገድ፣ 22 ክሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፣ 4 ኪሎ ሜትር ሃይኪንግ መንገድ፣ 39 ቼክ ዳም ተገንብተዋል።
2 አዲስ የተሽከርካሪ ድልድዮች ሲገነቡ፣ 3 ነባር የተሽከርካሪ ድልድዮች እድሳት ተደርጎላቸዋል። እንዲሁም ሌሎች የእረንጓዴ ልማት ጥንቅቅ ብለው ለምተዋል።
የከተማችን ነዋሪዎችን እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ፣ ይህንን ልዩ ሆኖ የተጠናቀቀ የእንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት አዕምሮችሁን ዘና አካላችሁን ፈታ እያደረጋችሁ እንድትገለገሉበት እና ረጅም አገልግሎት እንዲሰጥ እንድትንከባከቡት አደራ እላለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያና እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
02/06/2026
ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች!
ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችዉን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀገር ናት፡፡ ለሀገራቸዉ የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ ኮርታለች፡፡ ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ፣ ከመሻቷ በላይ ተሳትክቶላታል፡፡ ዛሬ የተደገመዉም ይኸው ነው፡፡
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲን ማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን መምረጥ፣ ሕገ መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ማስያዝ ትሻለች፡፡ ለዚህ ደግሞ 7ኛዉን ሀገራዊ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም አስፈልጓት ነበር፡፡
በምላሹም ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው የዛሬዋን ቀን ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ እነሆ የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበል ዜጎች በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ ውለዋል፤ ሌሊቱንም አጋምሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈዉ ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫም ነው፡፡
ምርጫዉ እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተዉ ያልቆፈሩት ጉድጓድ፣ ያልደረደሩት እንቅፋት አልነበረም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር አልነበረምና በስኬት ተጠናቅቋል፡፡ ኢትዮጵያውን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ አሸንፋለች፡፡
የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃዉ ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫዉን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናለች፡፡
የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ግንቦት 25 2018፣አዲስአበባ፣ኢትዮጵያ
01/06/2026
የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-
• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤
በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።
The people of Ethiopia are an extraordinary and remarkable people. Other than the Creator, who can truly know and assess our people in their entirety? Through this year’s election, Ethiopians have once again shown the world that they are a people with a rich culture, deep patriotism, and the ability to safeguard the common good.
On this historic day:
* Citizens who were not intimidated by the cold and darkness of the night,
* Who were not deterred by the midday sun or sudden rain,
* Whom weddings, funerals, childbirth, and other social obligations did not prevent from participating,
* Who were not wearied by long lines,
* Whose physical disabilities did not stop them from casting their vote,
* Those whose illness and old age did not prevent from witnessing the hope of their country,
* Who were not exhausted by carrying their infant children; the future inheritors of the nation,
* And above all, whom the shouting and threats of enemies could not intimidate or stop;
The perseverance you demonstrated amid many challenges and hardships, against all odds, was a contribution made for democracy and for the very survival of the nation. For this, you deserve heartfelt gratitude.
It is a privilege to serve such a people. Therefore, may those who have been elected honor the trust placed in them and serve this people, with integrity and sincerity! A people who have paid a great price for the democratic system. May you be worthy of that responsibility.
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
01/06/2026
ድምፅ ሳንሰጥ ወደ ቤት መግባት የማይታሰብ ነው ሲሉ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ::
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ኢትዮጵያን ለማጽናት በምሽትም ድምፃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ::
በክፍለ ከተማው በሚገኙ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ የመስጠት ሂደቱ አሁንም በከፍተኛ መነሳሳት ቀጥሏል።
01/06/2026
ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ነዋሪ ከማለዳ ጀምሮ ድምፁን በመስጠት ላይ ሲሆን በተፈጠረው የሲስተም መስተጓገል ሳይበገር፣ ምርጫ ቦርድ በሰጠው የሰዓት ማሻሻያ በመጠቀም ድምፁን ለመስጠት በየምርጫ ጣቢያው በፅናት እንደቆመ ነው::
#ኢትዮጵያእየመረጠችነው