Boloso Bombe Wereda Chief Administration /ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና አስተዳደር

Boloso Bombe Wereda Chief Administration /ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና አስተዳደር

Share

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር

Photos from Boloso Bombe Wereda Chief Administration /ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና አስተዳደር's post 13/10/2025

የዳኝነት እና የፍትህ ጥመርታ ፍትህን ለማስፈን የሚሰጠው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው:- ክቡር ፕረዚዳንት አምሳሉ አበራ

❇❇❇❇❇❇❇❇❇❇❇❇❇
ቦምቤ:-ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ፍርድ ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም የወረዳ እና ከተማ ፍትህ ተቋማት ጋር ግምገማ አካሄደዋል።

መድረኩን የመሩት የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት ክቡር አምሳሉ አበራ የዳኝነት እና የፍትህ ጥመርታ ፍትህን ለማስፈን የሚሰጠው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት የህዝቦችን መብት ማስከበር እንደሆነ የገለፁት ክቡር ፕረዚዳንት ባለድርሻዎች ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመግባባት መሥራት ይገባል ሲሉ አብራርተዋል።

በ2018 በጀት ዓመት በ1ኛ ሩብ ዓመት ፍትህን ለማስፈን በተደረገው ጥረት ብዙ መሻሻሎች ቢኖሩም የህዝባችንን ተጠቃሚነት እና ፍትህን ከማረጋገጥ ጋር በተያዜ በሚደረገው ጉዞ ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል።

ዳኞችና ዓቃቢያን ፍትህን ለማስፈን አቅምን ከፍ አድርገው መንቀሳቀስ ግድ ይለዋል ያሉት ክቡር ፕረዚዳንት አምሳሉ በፍርድ ቤት ውስጥ የሚሰሩ ዳኞች በሕግ አተረጓጎም ረገድ ያላቸውን እውቀት እርስ በርስ በመረዳዳት አቅማቸውን የሚያጎለብቱበት ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል።

በወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ደረጃ በየጊዜው የሚፈጸመው ወንጀል እና ወንጀል ነክ ጉዳዮች በመርመር እና ፍትሃዊ ዉሳኔ መስጠት ጋር በተያዘው መርማሪ ፖሊስ ቀልጣፋና ውጤታማ ሥራ በማድረግ ተገቢ ዉሳኔ መስጠት ይገባል።

የዳኞች እና የፍትህ ተቋማት ጥመርታ ለቀልጣፋና አስተማማኝ ፍትህ ማረጋገጥ የሚሰጠው ሚና ወሳኝ እንደሆነ በመገንዘብ ሁሉም ባለድርሻዎች ከሚመለከታቸው ጋር በቅንጅትና በመግባባት መሥራት ያስፈልጋል ተብለዋል።

በወረዳና ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ተቋማት ዉስጥ የነበረው አለመግባባት የህዝቦችን መብትና ፍትህን ለማረጋገጥ ሲል ቅሬታቸውን በዕርቅ እንድያልቅ ተደርጓል።

በመድረክ ላይ የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት የተከበሩ አምሳሉ አበራ፣ የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር ፍትህ ተቋማት ኃላፊዎች፣ የሁለቱ መዋቅር ፖሊስ አዛዦች፣ ዓቃቢያን እና ሌሎች አካላት ተሳትፈዋል።

ምንጭ:- #የቦሎሶ-ቦምቤ-ወረዳ-ፍርድ-ቤት-ነው

13/10/2025

ብሔራዊ መግባባት የሀገራችን ለውጥ ማነቆዎች የሆኑ ጉዳዮችን የምንፈታበት መንገድ ነው፡፡ የረጅም ጊዜ ችግሮቻችንንና ስብራቶቻችንን በመጠገን በአንድ ላይ ወደፊት የምንሻገርበት መንገድ ነው፡፡ በፖለቲካ ወደፊት ሳይሻገሩ በኢኮኖሚ ሙሉ ለሙሉ ወደፊት መሻገር የማይታሰብ ነው፡፡

የመደመር መንግሥት ገጽ 4ዐ3

Photos from Boloso Bombe Wereda Chief Administration /ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና አስተዳደር's post 13/10/2025

18ኛው የኢትዮጵያ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ በተለያዩ ክንዋኔ ተከብሮ ዉለዋል።

‎ቦምቤ:- ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ 18ኛዉ ሰንደቅ ዓለማ ቀኑ ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጲያ ሕዳሴ’ በሚል መሪ ሃሳብ ተከብሯል።

‎የወረዳ ም/አስተዳዳና ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታርኩ ይመር ሰንደቅ ዓላማችን ቅድመ አያቶቻችን በተለያየ አውደ ውግያ ፊት ለፊት ተዋግተው ያስረከቡን የነጻነት ምልክት ነው ብለዋል።

‎የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የስኬቶቻችን ከፍታ ማሳያ ነው ያሉት ምክትል አስተዳዳሪ ሀገራችን ኢትዮጵያ የዘመናት ቁጭት የነበረውን የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ አጠናቃ፣ የተፈጥሮ ጋዝ ለማውጣት፣ የአፈር ማዳበሪያ ለማምረትና ስራ በጀመረችበት ወቅት መሆኑ በዓሉ የተለየ መሆኑን ገልፀዋል።

‎ሰንደቅ ዓላማ አንድ ሀገር በዓለም የሚወከልበት የሀገርና ህዝብ ምልክት መሆኑንም ተናግረዋል።

‎የሰንደቅ ዓላማ ቀኑን የወረዳ አስተባባሪ አካላት፣ የወረዳ መካከለኛ አመራር አካላት፣ የወረዳ የጸጥታ አካላት፣ የመ/ሠራተኞች እና አከባቢዉ ማህበረሰብ ተሳትፈዋል።

‎ #ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጲያ ሕዳሴ

Photos from Boloso Bombe Wereda Chief Administration /ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና አስተዳደር's post 13/10/2025

በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ባሉት በሁሉም መ/ቤቶች 18ኛው የኢትዮጵያ የሰንደቅ ዓላማ ቀን የፓናል ዉይይት መድረክ ተካሄደ ።

‎ቦምቤ ፣ጥቅምት 3/2/2018 ዓ/ም በወላይታ በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ባሉት በሁሉም መ/ቤቶች 18ኛው የኢትዮጵያ የሰንደቅ ዓላማ ቀን የፓናል ዉይይት መድረክ ተካሂደዋል ።

‎የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የስኬቶቻችን ከፍታ ማሳያ ነው ሀገራችን ኢትዮጵያ የዘመናት ቁጭት የነበረውን የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ አጠናቅቃ፣ የተፈጥሮ ጋዝ ለማውጣትና የአፈር ማዳበሪያ ለማምረት ስራ በጀመረችበት ወቅት መሆኑ በዓሉ የተለየ የሚያደርገው መሆኑን ተገልፀዋል።

‎ሰንደቅ ዓላማ አንድ ሀገር በዓለም የሚወከልበት የሀገርና ህዝብ ምልክት መሆኑንም ተጠቁመዋል ።

Photos from Boloso Bombe Wereda Chief Administration /ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና አስተዳደር's post 13/10/2025

18ኛው የኢትዮጵያ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ተከበረ

ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም

ቀኑ ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጲያ ሕዳሴ’ በሚል መሪ ሃሳብ በወላይታ ሶዶ ማዕከል ተከብሯል፡፡

የክልሉ መንግስት ተጠሪ እና የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመስቀል ጫላ እንደገለፁት ሰንደቅ ዓላማችን ቅድመ አያቶቻችን በተለያየ አውደ ውግያ ፊት ለፊት ተዋግተው ያስረከቡን የነጻነት ምልክት ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የስኬቶቻችን ከፍታ ማሳያ ነው ያሉት አቶ ገብረመስቀል ሀገራችን ኢትዮጵያ የዘመናት ቁጭት የነበረውን የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ አጠናቃ፣ የተፈጥሮ ጋዝ ለማውጣት፣ የአፈር ማዳበሪያ ለማምረትና ስራ በጀመረችበት ወቅት መሆኑ በዓሉ የተለየ መሆኑን ገልፀዋል።

ሰንደቅ ዓላማ አንድ ሀገር በዓለም የሚወከልበት የሀገርና ህዝብ ምልክት መሆኑንም ተናግረዋል።

የክልሉ ባንዲራ በክልሉ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች አንድነት ማሳያ መሆኑን አንስተው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአንድነት እና የመቻቻል ምሳሌ መሆኑን አስረድተዋል።

ክልሉ ኢትዮጵያ ለጀመረችው የብልጽግና ጉዞ ያለውን የተፈጥሮ እምቅ አቅም እና የሰው ኃይል ተጠቅሞ አበርክቶውን እንደሚቀጥል አበክረዋል።

ሰንደቅ ዓላማ መስቀል መርሀግብሩን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የክልሉ መንግስት ተጠሪ እና የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመስቀል ጫላ እና የክልሉ ርዕሰ መስተድድር ጽ/ቤት ኃላፊ በጋራ በመሆን ያከናወኑ ሲሆን ቃለመሀላ በማድረግ ተጠናቋል።

የሰንደቅ ዓላማ ቀኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የክልሉ መንግስት ተጠሪ እና የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገብረመስቀል ጫላን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የክልሉ የጸጥታ አካላት፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ማርሽ ባንድ እንዲሁም የወላይታ ሶዶ ክላስተር የክልል ተቋማት ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በድምቀት ተከብሯል።

Photos from Boloso Bombe Wereda Chief Administration /ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና አስተዳደር's post 13/10/2025

ሰንደቅ ዓላማችን የትናንት የጋራ ታሪካችን፣ የዛሬ የጋራ ጥረታችንና የነገ ተስፋችንን አጣምሮ የያዘ የክብራችንና የማንነታችን ማህተም ነው፦ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ

ቦምቤ፤ጥቅምት 3/2018 በወላይታ ዞን 18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ወቅታዊ ሀገራዊ እና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ በድምቀት ተከብሯል።

በአከባበሩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ ሰንደቅ ዓላማ የሉዓላዊነታችን መግለጫ፣ የነፃነታችን አርማ ነው ብለዋል።

ህብረ ብሔራዊ አንድነትንና ዘላቂ መግባባትን የሚያጠናክር የጋራ ዓርማችን እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለዜጎቿ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ጥቁር ህዝቦች ነፃነት ተምሳሌት የሆነ ሰንደቅ ዓላማ ባለቤት ነችም ብለዋል።

የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከባበር ልዩ የሚያደርገው የሁሉም ዜጎቻችን አሻራ ያረፈበት፣ የደም፣ የላብ፣ የዕንባ ጠብታ ውጤትና የአገራችን ማንሰራራት ብስራት የሆነው የህዳሴ ግድብ ግንባታው በተጠናቀቀበት ማግስት እና ወደ ባህር በር ጉዞ በጀመርንበት ጊዜ የሚከበር መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ሲሉም ተናግረዋል።

ብዙዎች ለሰንደቅ ዓላማ ክብር በየጦር ግንባሩ ተዋድቀዋል፣ አገራችን ሉዓላዊነቷን ጠብቃ እንድትቀጥል መስዋዕትነት ከፍለዋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፥ በደም በአጥንታቸዉ አጥረዉ ያልተደፈረች ሀገር ለእኛ አስረክበዋል ብለዋል፡፡

አትሌቶቻችን በየዓለም አደባባይ በሰንደቅ ዓላማ ስም ሮጠው አሸንፈዋል፣ በሰንደቅ ዓላማ ፊት የአሸናፊነት ዕንባ ለአገራቸው ሲያነቡ አብረን አንብተናል ነው ያሉት።

እኛ ኢትዮጵያዊያን መጀመር ብቻ ሳይሆን ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በራሳችን አቅም አቅደን ማጠናቀቅ እንደሚንችል አረጋግጠናል ብለዋል፡፡

አባቶቻችን በጦርነት ድል በማድረግ ሉዓላዊ ሀገር እንዳስረከቡን ሁሉ የዚህ ትዉልድ አርበኝነት የሚጠይቅ ዘርፈ-ብዙ ጉዳይ እንዳለውም አስገንዝበዋል፡፡

በሀገራችን የቆየ ከፋፋይ ትርክትን በብሔራዊ ገዥ ትርክት መተካት፣ ብሔራዊነትን ማጽናት፣ በድጅታል ሚዲያ የሚደረገዉን የስነ-ልቦና ጦርነትና በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨዉን ሀሰተኛ መረጃዎችን በመመከት ዳግም ታሪክ መስራት ያስፈልጋል ሲሉም አንስተዋል፡፡

ከተረጅነት ወደ ምርታማነት በሚናገርገዉ ጉዞ አመራሩ ተግባራትን አቀናጅቶ መምራት፣ የተቋማትን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅምን ማሳደግና ከሌብነትና ከብልሹ አሠራር የፀዳ አገልግሎት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በዛሬው ዕለት የሰንደቅ ዓላማ ቀን ስናከብር ለሀገራችን ማንሰራራት፣ ለሉዓላዊነቷ እና ህዳሴ የሚጠበቅብንን ለመወጣት ቃል የምንገባበት ሊሆን ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

የወላይታ ዞን ምክርቤት ዋና አፌ-ጉባኤ ወ/ሮ ጤናዬ ትራንጎ በበኩላቸው ሰንደቅ ዓላማችንን ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ መጠቀም ይኖርብናል ብለዋል።

Photos from Boloso Bombe Wereda Chief Administration /ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና አስተዳደር's post 13/10/2025

በወላይታ ዞን ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው

ቦምቤ፤ጥቅምት 3/2018 በወላይታ ዞን 18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ወቅታዊ ሀገራዊ እና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

"ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችን እና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ" በሚል መሪ ቃል ወቅታዊ ሀገራዊ እና ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል።

ዜጎች በሰንደቅ ዓላማ ፊት ቆመው ቃለ መሃላ በመፈፀም ለሀገራቸው እና ለሰንደቅ ዓላማቸው ያላቸውን ክብር እና ፍቅር ዳግም የሚገልጹበት፤ የሀገራቸውን አንድነት እና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ቃላቸውን የሚያድሱበት ቀን ነው።

የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዜጎች ስለ ሰንደቅ ዓላማ ምንነት፣ ክብር እና ትርጓሜ በተገቢው መንገድ እንዲረዱ በማድረግ ረገድ የራሱ አስተዋፅኦ እንዳለውም ተገልጿል።

ሰንደቅ ዓላማችንን ስናከብር ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን እና ሌሎች ፀጥታ አካላት ዕውቅና እና ክብር መስጠት እንዲሁም ለሀገር አንድነት፣ ሉዓላዊነት፣ ክብር እና ጥቅም የተከፈለውን መሥዋዕትነት ማሰብ አስፈላጊ ነው።

በአከባበሩ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ፣ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር አማረ አቦታን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ የፀጥታ አካላት እና ሌሎች ህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

13/10/2025

➡ ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ማንሠራራት፤የአዲስ ዘመን ድል ብስራት!

Photos from Boloso Bombe Wereda Chief Administration /ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና አስተዳደር's post 12/10/2025

የሕዝቡን ፍላጎት ለማሟላት እና መልካም አስተዳደር ለማስፈን የህዝብ ተወካዮች በመፍትሔው ላይ መወያየትና አቅጣጫ ማስቀመጥ ያስፈልጋል:- አቶ አማን ከበደ

ቦምቤ፣ ጥቅምት 02፣2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ምክር ቤት አፌ -ጉባኤ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት 4ኛ ዙር 13ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት የ11 ቀበሊየት የጋራ ምክክር ፎሬም መድረክ ተካሂደዋል።

በማጠቃለያው መርሃግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማን ከበደ እንደተናገሩት የሕዝቡን ፍላጎት ለማሟላት እና መልካም አስተዳደር ለማስፈን የህዝብ ተወካዮች በመፍትሔው ላይ መወያየትና አቅጣጫ ማስቀመጥ ያስፈልጋል ሲል ገልጿል።

የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች አፈጻጸም በመከታተልና በመቆጣጠር ህዝብን ተጠቃሚ ማድረግ የሚችል ለውጥ ለማምጣት መትጋት እንዳለበት ጠቁሟል።

የሕዝቡን አዳጊ ፍላጎቶች ለማሟላት በየአከባቢዉ ለዉጥ እንዲመጣ ለማድረግ ሁሉም ሰው በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ተብሏል።

የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ አፌ ጉባኤ ምክር ቤት ምክትል አፌ ጉባኤ አቶ ተመስገን ጎኣ በምክክር ፎረሙ እስካሁን ያለው አፈጻጸም ዙሪያ ሪፖርት በቀረበው መነሻ ዉይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ በሚሰራው ተግባራት ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በለውጡ የተገኙ የልማት ትሩፋቶች በዘላቂነት ለማረጋገጥ የፈጠሩት መተማመን፣ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት መመዝገቡ እንዲሁም የአመራር ክትትልና ድጋፍ መጠናከሩና የዜጎችን ግንዛቤ የማሳደግ ስራዎች የተቋማችን ተልዕኮ ነው ብለዋል።

ምክክር መድረክ የልምድ ልውውጥ የምናደርግና የመማሪያ ነው ያሉት አቶ ተመስገን እንደክፍተት የታየውን በመለየት እና መፍትሔ ሊሆን የሚችል ሀሳብ መስጠት የምክር ቤቱ ዋነኛ ተግባር ነው ብለዋል።

በመድረክ የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማን ከበደ ጨምሮ ሌሎች አስተባባሪ አካላት፣የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ምክትል አፌ- ጉባኤ አቶ ተመስገን ጎአ ፣አጠቃለይ የወረዳ መካከለኛ አመራሮች የ11ቀበሊያት አስተዳዳሪዎች፣ ሥ/አስክያጆች፣ ዋናና ምክትል አፌጉባኤዎች ተሳትፈዋል።

Photos from Boloso Bombe Wereda Chief Administration /ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና አስተዳደር's post 12/10/2025

የዘንድሮውን ምርት ዘመን የቡናው ምርት በጥራት እና በመጠን ለዓላም ገበያ ለማቅረብ ማነቆ የሚሆኑ ጉዳዮችን የመለየትና ህገወጥ ነጋዴ እንቅስቃሴን መግታት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅት ይፈልጋል:- አቶ አማን ከበደ

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ቦምቤ፤ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ እና ቦምቤ ከተማ አስተዳደር የቡና ምርት ጥራት ቁጥጥርና ግብይት አስተባባሪ ግብረ ኃይል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የንቅናቄ መድረክ አካሂደዋል።

በማጠቃለያው ላይ ሀሳብ የሰጡት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማን ከበደ የዘንድሮውን ምርት ዘመን የቡናው ምርት በጥራት እና በመጠን ለዓላም ገበያ ለማቅረብ ማነቆ የሚሆኑ ጉዳዮችን የመለየትና ህገወጥ ነጋዴ እንቅስቃሴን መግታት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅት ይፈልጋል ብለዋል።

በ2018 የምርት ዘመን ጥራት ያለውን ቡና ለዓላም ገበያ ለማቅረብ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የቡና ጥራት እንዳይኖር የሚያደርጉ ብዙ ጉዳዮች መኖራቸውን የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው ለማሻሻል የግንዛቤ እጥረት ለመቅረፍ በትኩረት ይሰራል።

ህገወጥ ቡና ግብይት ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል ያሉት አቶ አማን በየደረጃው ያለው ግብረሃይል የቁጥጥርና ክትትል ስራ ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል። በሌላ በኩል ለህገወጥ ነጋዴዎች ክፍት በሚሆኑ አከባቢዎች ለቁጥጥር እንድመቺ በመተላለፊያዎች ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል።

በተግባር አፈጻጸም ማነቆዎችን ለመፍታት ሁለቱም መዋቅር በትብብርና በመተጋገዝ በመስራት ዉጤት እናመጣለን።

ጥረቱን የጠበቀ ቡና ለዓለም ገበያ ለማቅረብ በሚደረገው ጥረት የሚፈጠሩ ክፍተቶችን በጋራ በመታገል ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል ሲሉ አጠናቅቀዋል።

የቦምቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኤርዳቸዉ ታደሰ በበኩላቸው ቡና የኢኮኖሚ ዋልታ መሆኑን በመጠቆም ወቅቱን ጥብቆ ጥራቱ የተረጋገጠ ቡና ወደ ግብይት ማዕከል እንዲቀርብ ከፍ ያለ ርብርብ እንዲደረግ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ወላይታ ቡና የወላይታ ልዩ መለያ በመሆኑ በምርት ዘመኑ ጥራት ያለውን ቡና ለዓለም ገበያ በጥራት እና መጠን ለማቅረብ ባለድርሻ አካላት ከወዲሁ ቅንጅታዊ አሰራር እንዲዘረጉ ከንቲባ አበክረው ተናግረዋል።

ስለሆነም ማንኛውም ህገወጥ እንቅስቃሴ በመግታት መሠረታዊ ዓላማውን ለማሳካት በትብብር መስራት ያስፈልጋል ሲሉ የተናግረዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ከወረዳው ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር የ2018 የቡና ምርት ዘመን ውጤታማ ለማድረግ የሚሰራ መሆኑንም ገልጿል።

በመድረክ የ2017 ምርት ዘመን የዘርፉ አጠቃላይ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ዉይይት በማድረግ እንደክፍተት የተነሱትን በማረም እና ጥንካሬና በማስቀጠል ዘንድሮ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በዕቅዱ ላይ መግባባት በመፍጠር ተጠናቅቋል።

በመድረኩ የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ አስተባባሪ አካላትና የቦምቤ ከተማ አስተዳደር አስተባባሪዎች ፣ አጠቀላይ የከተማና ወረዳ አጠቃላይ አመራሮች፣ የቡና ጥራት ቁጥጥር ግብይት አስተባባሪ ግብረኃይል እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

Photos from Boloso Bombe Wereda Chief Administration /ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና አስተዳደር's post 12/10/2025

የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ እና ቦምቤ ከተማ አስተዳደር የቡና ምርት ጥራት ቁጥጥርና ግብይት አስተባባሪ ግብረ ኃይል ምክክር ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው:-

ቦምቤ:- ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም በወላይታ ዞን ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ እና ቦምቤ ከተማ አስተዳደር የቡና ምርት ጥራት ቁጥጥርና ግብይት አስተባባሪ ግብረ ኃይል የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረክ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማን ከበደ በሃሳባቸው ህገወጥ ቡና ግብይት ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመዉሰድ በየደረጃው ያለው ግብረሃይል የቁጥጥርና ክትትል ስራ ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።

የወላይታ ቡና የወላይታ ልዩ መለያ በመሆኑ በምርት ዘመኑ ጥራት ያለውን ቡና ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ባለድርሻ አካላት ከወዲሁ ቅንጅታዊ አሰራር እንዲዘረጉ ዋና አስተዳዳሪው አበክረው ተናግረዋል።

ቡና የኢኮኖሚ ዋልታ መሆኑን ያብራሩት አቶ አማን ወቅቱን ጥብቆ ጥራቱ የተረጋገጠ ቡና ወደ ግብይት ማዕከል እንዲቀርብ ከፍ ያለ ርብርብ እንዲደረግ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ወረዳ አስተዳደሩ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር የ2018 የቡና ምርት ዘመን ውጤታማ ለማድረግ የሚሰራ መሆኑንም አንስተዋል።

በየደረጃው ካሉት ከአርሶ አደሩ ጋር መግባባት በመፍጠር ከቡና ምርት የሚያገኙትን ኢኮኖሚ መጠን ከፍ እንዲያደርጉ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

በመድረኩ የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ አስተባባሪ አካላትና የቦምቤ ከተማ አስተዳደር አስተባባሪዎች ፣ አጠቀላይ የከተማና ወረዳ አጠቃላይ አመራሮች፣ የቡና ጥራት ቁጥጥር ግብይት አስተባባሪ ግብረኃይል እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

Photos from Boloso Bombe Wereda Chief Administration /ቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና አስተዳደር's post 12/10/2025

የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ምክር ቤት አፌ -ጉባኤ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት 4ኛ ዙር 13ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት የ11 ቀበሊየት የጋራ ምክክር ፎሬም መድረክ በመካሄድ ላይ ነዉ

‎ቦምቤ ፣ጥቅምት 2/2/2018 ዓ/ም በወላይታ ዞን የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ምክር ቤት አፌ -ጉባኤ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት 4ኛ ዙር 13ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት የ11 ቀበሊየት የጋራ ምክክር ፎሬም መድረክ እየተካሄደ ይገኛል ።

‎በማስጀመሪያ መርሃግብሩ ላይ ተገኝተው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማን ከበደ እንደተናገሩት የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች አፈጻጸም በመከታተልና በመቆጣጠር ህዝብን ተጠቃሚ ማድረግ የሚችል ለውጥ ለማምጣት መትጋት አለባቸው ብለዋል።

‎በምክክር ፎረሙ እስካሁን ያለው አፈጻጸም ዙሪያ ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት ተደርጎ በቀጣይ በሚሰራው ተግባራት ላይ ከወረዳ አፌ ጉባኤ ጽ/ቤት አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይታሰባል።

‎በመድረክ የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማን ከበደ ጨምሮ ሌሎች አስተባባሪ አካላት፣የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ምክትል አፌ- ጉባኤ አቶ ተመስገን ጎአ ፣አጠቃለይ የወረዳ መካከለኛ አመራሮች የ11ቀበሊያት አስተዳዳሪዎች፣ ሥ/አስክያጆች፣ ዋናና ምክትል አፌጉባኤዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


ቦምቤ
Addis Ababa