27/05/2026
Yeka Woreda 12 Communication-የካ ወረዳ 12 ኮሙኒኬሽን
This is the official page of Yeka Woreda 12 Communication!!
27/05/2026
26/05/2026
የካ የብልፅግና ከፍታ ማሳያ!
ቃልን በተግባር ያረጋገጠ የበጎነት መንደር በየካ ፈረንሳይ ለጋሲዮን!
22/05/2026
ዛሬ በከተማችን መሃል ፒያሳ ላይ ያስገነባነውን የአድዋ የገበያ ማዕከልና የትራንስፓርት ተርሚናል ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።
ፒያሳ በቀድሞ አጠራሩ “ዶሮ ማነቂያ” አካባቢን አፍርስን መልሰን አልምተን፥ አዘምነንና አስውበን ከ 101 በላይ የመሸጫ ሱቆች፥ ከመሬት በታች ሁለት ደረጃ ፓርኪንግ ፣ የታክሲ እና የአውቶቡስ ተርሚናል፥ ካፌ እና ሬስቶራንት፥ የመኪና የኤሌክትሪክ ቻርጅ አገልግሎት መስጫ፥ እንዲሁም ኘላዛና ፋውንቴን ጨምሮ 2 ዘመናዊ ሊፍት፥ ቢሮዎች፥ ክሊኒክ እና ፋርማሲ፣ ዘመናዊ የእሳት አደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፥ የደህንነት መቆጣጠርያ ተገጥመውለት ሱቆቹና ካፍቴሪያዎቹ ለአካባቢው ለተነሽዎች በእጣ አስተላልፈናል።
የአድዋ የገበያ ማዕከልና የትራንስፓርት ተርሚናል በመጨናነቅ፣ ግፊያ፣ እንግልት፣ በፀሀይ፥ በዝናብ እና አቧራ ላይ ሲንገላታ ለነበረዉ ህዝባችን ንፁህ ምቹ እና ስርዓት ያለው የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫም አድርገነዋል ።
ፒያሳ ኣካባቢ የኮሪደር ልማት የጀመርንበት ነው። ዛሬ ፒያሳ የጋራ ታሪካችንን “የአድዋ ድል መታሰቢያን” የገነባንበት እና የአገራት መሪዎች ለጀግኖች ሰማእቶቻችን የአበባ ጉንጉን የሚያኖሩበትን ጨምሮ በርካታ የጋራ መገልገያ እና የቱሪስት ስበትን የጨመሩ መሰረተ ልማቶች የሰራንበት ታሪካዊ ቦታ ሆኗል።
ይህ የዛሬውን ፕሮጀክት በተቀመጠለት ጊዜና የጥራት ደረጃ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ላደረጋችሁ በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Addis Ababa
