Lemi Kura woreda 04 Communication

Directions

Lemi Kura woreda 04 Communication Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Lemi Kura woreda 04 Communication, Government Organization, Bole Arabsa Road, Addis Ababa.

06/10/2026
ወደ ነገ መሻገር የሚያስችል ታሪካዊ አተያይ በተግባር እየተገነባ ነው፡- ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  ከትናንት መልካሙን በመውሰድና ዛሬ ላይ አስፈላጊውን እሴት በመጨመር ወደ ነ...
06/10/2026

ወደ ነገ መሻገር የሚያስችል ታሪካዊ አተያይ በተግባር እየተገነባ ነው፡- ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ከትናንት መልካሙን በመውሰድና ዛሬ ላይ አስፈላጊውን እሴት በመጨመር ወደ ነገ መሻገር የሚያስችል ታሪካዊ አተያይ በተግባር እየተገነባ መሆኑን ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክክር ቤት በትናንትናው ዕለት ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ መፍትሄዋን ከራሷ ማህጸን ማውጣት እንደጀመረች አብስረዋል።

የውጭ ሀገራትን ርዕዮተ ዓለም ገልብጦ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ለመትከል የተደረጉ የዘመናት ሙከራዎች፣ ከመልካም ሰብል ይልቅ አረም እያበቀሉ ሀገራችንን ለችግር መዳረጋቸውን አመላክተዋል።

የአውሮፓና የእስያ ስልጣኔዎች የራሳቸውን ባህል መሠረት አድርገው እንደተገነቡት ሁሉ፣ ኢትዮጵያም በራሷ እሴት ላይ የታነጸ 'የመደመር' እሳቤ መከተሏን አብራርተዋል።

ይህ ሀገር በቀል እሳቤ፣ የሕዝቦችን ብዝኃነት ከአንድነት፣ አካባቢያዊነትን ከሀገር እንዲሁም የግል ፍላጎትን ከቡድን ጋር አስተሳስሮ የሚያስኬድ የስልጣኔ ማሰቢያ ቋንቋ መሆኑን አስረድተዋል።

ከባሕር ማዶ የሚመጡ ዕሳቤዎችን አጠቃቀም በተመለከተም ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ለሌሎች ዕሳቤ ኢትዮጵያን ከመቀየር ይልቅ ለኢትዮጵያ ሲባል የሌሎችን ዕሳቤ አቃንቶ መቀበል ተገቢ አካሄድ ነው" በማለት ጠንካራ ፖለቲካዊ አቋማቸውን አንጸባርቀዋል።

በዚህም መሠረት ትናንትን ሙሉ በሙሉ እንደ እርኩስ ወይም እንደ ቅዱስ ከሚቆጥረው የጽንፍ ፖለቲካ በመውጣት፣ ከትናንት መልካሙን በመውሰድና ዛሬ ላይ አስፈላጊውን እሴት በመጨመር ወደ ነገ መሻገር የሚያስችል ታሪካዊ አተያይ በተግባር እየተገነባ መሆኑን ተናግረዋል።

"መጪውን ዘመን ቀድመው አስበው የሚመጣውን አዲስ ነገር በተጠንቀቅ ለሚጠብቁ ብርቱዎች ምንዳው ብዙ ነው፤ በአንጻሩ  ተዘናግተው ለሚቆዩ ደካሞች እዳው እልፍ ነው።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕ...
05/10/2026

"መጪውን ዘመን ቀድመው አስበው የሚመጣውን አዲስ ነገር በተጠንቀቅ ለሚጠብቁ ብርቱዎች ምንዳው ብዙ ነው፤ በአንጻሩ ተዘናግተው ለሚቆዩ
ደካሞች እዳው እልፍ ነው።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ/ር)

"ዛሬን ከሰራንበት ትናንትን ማስተካከል ይቻላል፤ ዛሬን ከሰራንበት ነገን መተንበይ ብቻ ሳይሆን የፈለግነውን ዓይነት መንገድ መቅረጽ እንችላለን።"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
05/10/2026

"ዛሬን ከሰራንበት ትናንትን ማስተካከል ይቻላል፤ ዛሬን ከሰራንበት ነገን መተንበይ ብቻ ሳይሆን የፈለግነውን ዓይነት መንገድ መቅረጽ እንችላለን።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

05/10/2026
"ሥርዓት በአንድ ጀምበር አይገነባም" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)*****************ሀገራዊ የሥርዓት ግንባታ በአንድ ጀምበር ተገንብቶ የሚያልቅ ሳይሆን ጥበብን፣ ስክነ...
05/10/2026

"ሥርዓት በአንድ ጀምበር አይገነባም" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*****************

ሀገራዊ የሥርዓት ግንባታ በአንድ ጀምበር ተገንብቶ የሚያልቅ ሳይሆን ጥበብን፣ ስክነትን፣ ትዕግሥትን እና ትጋትን በተመጣጠነ መልኩ የሚጠይቅ የረጅም ሂደት ጉዞ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የ2010 ዓ.ም ሀገራዊ ለውጥ እንዲመጣ ዋነኛ ገፊ ምክንያት የነበረው "እንዴት ወደ ኋላ እንቀራለን?" የሚል ጥልቅ ሀገራዊ ቁጭት እንደነበር አስታውሰዋል።

ይሁን እንጂ ቁጭት የጉዞ መነሻ እንጂ መዳረሻም ሆነ ማድረሻ ሊሆን እንደማይችል ገልጸው፤ የቁጭት ማድረሻው ጠንካራ ሥርዓት፣ የመጨረሻ መዳረሻው ደግሞ ሥልጣኔ መሆኑን አብራርተዋል።

ይህን የሕዝብ ቁጭት ወደ ጠንካራ ሥርዓት አዋላጅነት ለመቀየር ሰክኖ ማሰብ፣ ማሰላሰል፣ መሞከር፣ የተሻለውን መምረጥ እና ዘወትር ማሻሻል ግድ እንደሚልም አጽንኦት ሰጥተውበታል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሥርዓት የመገንባት ሙከራ ሲደረግ የቁጭት እጥረት አጋጥሞ እንደማያውቅ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ በተቃራኒው ስክነት ማጣት እና ለአዳዲስ ሐሳቦች ዝግ መሆን ጠንካራ ሥርዓት መሠረት እንዳይይዝ ማድረጉን አስረድተዋል።

በተለይም ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታን በሚገባ በመገንዘብ ለኢትዮጵያ አዋጭ የሆነውን መንገድ መርጦ ከመተግበር ይልቅ፣ የኢትዮጵያን ችግር በውጭ ሀገራት ዕይታ ለመፍታት መሞከር በሂደቱ ከፍተኛ ዋጋ ማስከፈሉን አብራርተዋል።

"ምንጩን የሚረሳ ወንዝ እንደሚደርቀው ሁሉ፣ ከሥሩ የተነጠለ ሕዝብ መጨረሻው አያምርም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መሠረቱን፣ ባህሉን፣ ልማዱን እና ሀገራዊ እሳቤውን በመጣል የሚጀመር የሥልጣኔ ጉዞ ሩቅ ሊጓዝ እንደማይችል ገልጸዋል።

ባለፉት ስምንት ዓመታት ኢትዮጵያን ከዚህ አዙሪት ለማውጣት በርካታ ጥረቶች ተደርገው ውጤት መገኘቱን ጠቅሰው፤ በዚህም የኢትዮጵያዊነት መሠረት የሆነውን የመደመር እሳቤ ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉን ተናግረዋል።

“ጥያቄው ታላቁን ርዕያችንን ማሳካት ይቻላል ወይስ አይቻልም የሚለው አይደለም፤ እንደሚቻል እርግጠኞች ነን!” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ኢትዮጵያ አሁን ላይ የጀመረችው አዲስ ...
05/10/2026

“ጥያቄው ታላቁን ርዕያችንን ማሳካት ይቻላል ወይስ አይቻልም የሚለው አይደለም፤ እንደሚቻል እርግጠኞች ነን!” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ አሁን ላይ የጀመረችው አዲስ የብልጽግና እና የስልጣኔ ጉዞ ባዶ ፉከራ ሳይሆን በመሬት ላይ በተጨባጭ የሚገለጥ የትውልድ ቃል ኪዳን መሆኑን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አረጋገጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ባላንጣዎች በተናጠል ተከፋፍለው ሊያጠቁ ሲከብዳቸው ለክፋትና ለሴራ ማበራቸውን በማስታወስ፤ አዲሱን የኢትዮጵያ ስልጣኔ የመገንባቱ ሂደት በመላው ሕዝብ ዘንድ ጽኑ እምነት የተጣለበት ታላቅ ሀገራዊ እውነት መሆኑን አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያን የማድረግ አቅም በጽኑ መንፈስ ያበሰሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ “ጥያቄው ይቻላል ወይስ አይቻልም የሚለው አይደለም፤ እንደሚቻል እርግጠኞች ነን!” ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል።

አክለውም ትልቁ ፈተናና ዋነኛው ትኩረት የሚሻው ጉዳይ ራዕዩን በምን መልኩና እንዴት አድርገን በተግባር እናሳካዋለን ለሚለው ስልታዊ ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ መስጠት ላይ መሆኑን አብራርተዋል።

በመደመር እሳቤ ተጉዞ የታለመውን ሀገራዊ የከፍታ ማማ ለመጨበጥ ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ እንደሌለ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለተቀመጠው ግብ መሳካት የሚያግዙ ቁልፍ መሣሪያዎችን በዝርዝር አመልክተዋል።

በዚህም መሠረት እምቅ ሀገራዊ አቅሞችን በጥልቀት መረዳት፣ የአካሄድ ስልቶችን ከግብርና ከንባብ ጋር ማጣጣም፣ ከዓለም አቀፍ የተሻሉ ተሞክሮዎችን ወስዶ ከራስ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ማስማማት፣ በብሔራዊ አንድነት ላይ ጸንቶ መቆም፣ የቡድን እና የግል መብቶችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ማስጠበቅ እንዲሁም ጠንካራ ሲቪክ ማንነትን ገንብቶ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ምህዳርን በሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ላይ ማጽናት ወሳኝ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ በመንግሥትና በሕዝብ የማይበገር አብሮነትና በጽናት የያዘችውን የብልጽግና ርዕይ ከዳር በማድረስ፣ የነገዋን የበለጸገችና ሉዓላዊ ክብሯ የተጠበቀ ታላቅ ሀገር ለትውልድ ማውረሷ የማይቀር ታሪካዊ እውነታ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ አስታውቀዋል።

! ! !

ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!ለመላው ሰላምና ልማት ወዳድ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳንም ደስ አለን!የአለም የሰላም ሎሬት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን  ዐቢይ አሕመድ (ዶ...
05/10/2026

ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!

ለመላው ሰላምና ልማት ወዳድ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳንም ደስ አለን!

የአለም የሰላም ሎሬት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልካም የሥራ ዘመን!

ዛሬ የደስታ ቀን ብቻ ሳይሆን፣ የተስፋ፣ የድልና የኢትዮጵያን ስልጣኔ የመገንባት አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ነው!

ከብዙ ፈተናዎች በጽናት ተሻግረን፣ በጋራ ጥረታችንና በማይበገር አንድነታችን አዲስ የብልጽግና ጉዞ ጀምረናል።

ዛሬ ከሁሉም በላይ የሚጠይቀን አንድነት ነው፤ የሚጠይቀንም ሰላም ነው። ልዩነታችንን እንደ ጥንካሬ፣ አንድነታችንን እንደ ኃይል እንጠቀም። የትኛውም ልዩነት ከኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት አይበልጥም!

እጅ ለእጅ እንያያዝ፤ ልብ ለልብ እንቀራረብ፤ በሰላም እንደምር!

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን መሪነት፣ ለሀገራችን ሰላም፣ ሉዓላዊነት፣ ፍትሐዊነትና ሁለንተናዊ ብልጽግና በአንድነት እንቁም፤ እንተባበር፤ ተግተን እንሥራ!

ሰላም መሠረታችን ነው፤
አንድነት ጉልበታችን ነው፤
ኢትዮጵያ የጋራ ቤታችን ናት!

ስንደመር ኃይላችን ይጨምራል፤ ስንተባበር እንቅፋቶች ይሰበራሉ፤ በአንድነት ስንቆም የኢትዮጵያ ታላቅነት ይገለጣል!

ኢትዮጵያ ትበልጽጋለች!
ኢትዮጵያ በሰላም ትጸናለች!
ኢትዮጵያ በአንድነት ታሸንፋለች! 🇪🇹

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲሱ የመደመር መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ሲመሰረት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም  በሀገሪቱ የተካሄደው ምርጫ እንደ...
05/10/2026

አዲሱ የመደመር መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ሲመሰረት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም በሀገሪቱ የተካሄደው ምርጫ እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትኖ ያለፈ እና በብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ የኢትዮጵያን የዲሞክራሲ ባህል ያጠናከረ መሆኑን ገልጸዋል። በዲሞክራሲያዊ ውድድር ውስጥ የፓርቲዎች ማሸነፍና መሸነፍ ቢኖርም ኢትዮጵያ ግን አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ልጆች የሌሏት ሀገር መሆኗን አፅንኦት ሰጥተዋል። እንደ ሀገር የገጠሙንን ፈተናዎች ማሸነፍ የምንችለው እጅ ለእጅ ተያይዘን እንደ ወንድማማች ስንጓዝ እንደሆነ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዓለማችን በፍጥነትና በማይገመት ሁኔታ ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት መጪውን ዘመን በተጠንቀቅ መጠበቅ ትልቅ ምንዳ እንዳለው አስገንዝበዋል። ስለዚህም ለሀገር የሚበጀውን በጥበብ መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ታላቅ አደራ መሆኑን በንግግራቸው አስተላልፈዋል።
‎
‎
‎

Address

Bole Arabsa Road
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lemi Kura woreda 04 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share