በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር መገር ወረዳ መንግስት ኮምንኬሽን ጉ/ጽ/ቤት

በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር መገር ወረዳ መንግስት ኮምንኬሽን ጉ/ጽ/ቤት

Share

ዓላማችን የመንግስት ፖሊሲ እና ስትራቴጂዎችን ለህብረተሰቡ ማሳወቅ፣ ወቅታዊ አቋሞችን መግለጽ፣

Photos from በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር መገር ወረዳ መንግስት ኮምንኬሽን ጉ/ጽ/ቤት's post 30/05/2026

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ በዞኑ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ የካፒታል ወጪ እየተገነባ ያለውን የዞኑ የአስተዳደር ህንፃ ያለበት ደረጃን ምልከታ አደረጉ!!

ግንቦት 22/2018 ዓ/ም

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በ2000 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈውና (B+G+9) የሆነው ግዙፍ ህንፃ በተያዘው በጀት ዓመት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል!!

የመስክ ምልከታው ዋና ዓላማ ህንፃው እንዲጠናቀቅ ከተያዘለት ጊዜ አንፃር የደረሰበትን ደረጃን ከመከታተል ባሻገር በባለፉት ጊዜያት የተሰጡ አስተያየቶች ስለመታረማቸው ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል።

ህንፃው የዘመኑ የህንፃ ቴክኖሎጂ በደረሰበት ደረጃና መጪውን ጊዜ ባለመ መልኩ እየተገነባ ያለ ሲሆን እስካሁን 85 በመቶ የሚሆነው ዋናው ስራ መጠናቀቁን እና 74 በመቶ ክፍያ መፈፀሙን ተጠቁሟል!!

ህንፃው ሲጠናቀቅ የዞኑ አብዛኛው መስሪያ ቤቶችን መያዝ የሚችል ሲሆን፣ የተገልጋዮችን እንግልት ከመቀነስና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ከማዘመን አንፃር ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል!!

ህንፃው በውስጡ ከ160 ቢሮዎች ባሻገር 8 ደረጃቸውን የጠበቁ የስብሰባ አዳራሾች፣ዲጂታል የእሳት አደጋ መከላከያ፣ሁለት ዘመናዊ ሊፍቶች፣ግሪነሪዎች፣የዳታ ማዕከል፣ ካፊቴሪያዎች፣ የህፃናት ማቆያና ሌሎችም አገልግሎቶች የሚኖሩት ሲሆን የሊፍት አገግሎትም የሚገጠምለት እንደሆነ ተመላክቷል!!

ከዋናው ህንፃም በተጨማሪ በሁለተኛ ፌዝ ዘማናዊ ቴክኖሎጂዎች የተገጠሙለትና ከአንድ ሺህ ባላይ ሰዎችን የሚይዝ አዳራሽም እንደሚሰራ ተማላክቷል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት በበጀት ዓመቱ የዞኑ መንግስት ከሚያስፈፅማቸው ከፍተኛ ፕሮጀክቶች አንዱና ቀዳሚው ነው!!

የዞኑ አብዛኛው አገልግሎት መስጫ ቢሮዎች ደረጃቸውን ያልጠበቁ፣ላአገልጋይም ሆነ ተገልጋይ ምቹ ያልሆኑ፣ ተበታትነው ያሉ፣ ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር የማይሄዱና ጉራጌን የማይመጥኑ መሆናቸውን የገለፁት አቶ ላጫ እየተሰራ ያለው ህንፃ ግን እነዚህን ችግር የሚቀርፍ መሆኑን አስገንዝበዋል!!

የዞናችን የፕሮጀክቶች የማስፈፀም አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል ያሉት ክቡር አስተዳዳሪው ለዚህም የአመራሩ ተከታታይነት ያለው የአካል ምልከታና ግብረ መልስ አስተዋፅዎ ማበርከቱን ገልፀዋል!!

ግንባታዎች በፍጥነት ማለቃቸው ብቻ ሳይሆን ጥራትና የሚመጣውን ዘመን ቴክኖሎጂን ሊሸከሙ የሚችሉ ስለመሆናቸው ልዩ ትኩረት ይሻሉ ያሉት አቶ ላጫ ችግሮች እንዳይገጥሙ ከመነሻው ጀምሮ መከታተል ትርጉም አለው ብለዋል።

በመስክ ምልከታው የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ እና የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ናስር ሀሰን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ ከፍተኛ አመሮች ተሳትፈዋል!!

Photos from በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር መገር ወረዳ መንግስት ኮምንኬሽን ጉ/ጽ/ቤት's post 30/05/2026

ግንቦት 22/2018 ዓ.ም
በእኖር ኤነር መገር ወረዳ 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ለፀጥታ አካላት የስራ መመሪያ ኦሬንቴሽን ተሰጠ።

የእኖር ኤነር መገር ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ፣ ነፃ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ሁኔታ እንዲካሄድ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት የስራ መመሪያ ኦሬንቴሽን ሰጥቷል።

በመድረኩ የተገኙት የእኖር ኤነር መገር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሰበ ካብቱ እንደገለጹት ለሀገር ሰላምና መረጋጋት የፀጥታ ኃይሎች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ 7ኛ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫ በሚካሄድበት ወቅት በገለልተኝነት፣ በህግ አክባሪነት እና በኃላፊነት ስሜት መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

እንደ አስተዳዳሪው ገለፃ የሚሊሻ አባላት ከህዝቡ ጋር በአብሮነት የሚኖሩ በመሆናቸው የአካባቢው ሰላም ጠባቂዎች እና አምባሳደሮች ሆነው በማገልገል 7ኛ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በታማኝነት ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

አክለውም ሰላም የሁሉም ዜጋ የጋራ ሀብት በመሆ የፀጥታ አባላት ለአካባቢያቸው ህዝብ የሰላም አምባሳደር በመሆን በታማኝነት እና በቁርጠኝነት ሊያገለግሉ እንደሚገባ አመላክተዋል።

የወረዳው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አብድልፈታ ነጅሙ በበኩላቸው ሰላም የልማት እና የዴሞክራሲ መሠረት በመሆኑ የፀጥታ አካላት 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እና እምነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ ሀላፊው ገለፃ የተዘጋጀውን መድረክ የምርጫ ሂደቱ ያለምንም የፀጥታ ስጋት ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት የሚጫወቱትን ወሳኝ ሚና የበለጠ ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

አያይዘውም በምርጫ ወቅት ማንኛውም የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች የተደረጉ ሲሆን የፀጥታ አካላትም ህግን በማክበር እና የህዝብን መብት በመጠበቅ ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ አሳስበዋል።

የወረዳው ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባቡ ድንቁ እንደገለጹት የሚሊሻ አባላት ከህዝቡ ጋር በአብሮነት የሚሰሩ የሰላም አጋሮች በመሆናቸው በምርጫ ወቅት ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል።

አክለውም በማንኛውም ፖለቲካዊ አቋም ሳይወግኑ ገለልተኛ ሆነው በመስራት የህዝቡን ደህንነት እና የምርጫ ሂደቱን ሰላማዊነት ማረጋገጥ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

በመድረኩ የተሳተፉ የፓሊስ እና የሚሊሻ አባላትም በበኩላቸው መንግስት እና ህዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው ምርጫው በሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ከህዝቡ ጋር በመተባበር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

Photos from በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር መገር ወረዳ መንግስት ኮምንኬሽን ጉ/ጽ/ቤት's post 29/05/2026

ባህላዊ ጎዳና ጀፎሮ/ጀፎረ

አንድ ማህበረሰብ ከሌሎች የኅብረተሰብ ክፍል የሚለየው የራሱ መገለጫ የሆኑ እሴቶች ባለቤት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡

ይህም ማህበረሰብ የሚከተለው የህይወት ፍልስፍናና የአኗኗር ዘይቤውን መነሻ በማድረግ ሲሆን በዚህም ውስጥ የማህበረሰቡ ባህላዊ፣ ትውፊታዊ፣ ሥነ-ጥበባዊ፣ ቁሳዊና ሀይማኖታዊ ክዋኔዎቹ በዋንኛነት ይጠቀሳሉ፡፡

የጉራጌ ማህበረሰብ ልክ እንደሌሎቹ የአገራችን ብሔር ብሄረሰቦች ውብና ማራኪ ባህልና ወግ ባለቤት ነው።

ከነዚህ ውስጥ ብሔረሰቡ በዋነኛነት ከሚታወቅባቸው ሀብቶቹ መካከል የመንደር አመሰራረቱ አንዱ ነው።

የጉራጌ የመንደር አመሰራረትም መሰረት የሚያደርገው ጀፎሮ/ጀፎረ ሲሆን ይህም አረንጓዴ ሳር ለብሶ ውብና ማራኪ ገጽ ያለውና ባህላዊ ጎጆ ቤቶች ታጅቦ በሁለት መንደሮች መካከል በትይዩ የሚገኝ ነው።

የአካባቢው ነዋሪዎች የጋራ መጠቀሚያ፣ መተላለፊያ፣ መግቢያና መውጫ የሆነ ሰፊ መሬት ነው።

በጉራጌኛ ጀፎሮ ማለት ባህላዊ አውራ መንገድ ማለት ነው። የጉራጌ የመንደር አመሰራረት ያኔ እንደዛሬው የኢንጅነሪንግ ጥበብ ባልተስፋፋበት ዘመን የብሔረሰቡ አባቶች የጥበብ አሻራ ያረፈበትና ዛሬ የደረስንበት የስልጣኔ እርከን የኢንጂነሪንግ ጥበብ የጉራጌ አባቶች ከረጅም ዘመናት በፊት ሲተገብሩት መቆየታቸውንም ጭምር ያሳያል፡፡

አባቶች ምንም አይነት የዘመናዊ ምህንድስና ቀለም ሳይቆጥሩ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴያቸው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው የቀየሱበት የመንገድ አይነት ነው።

ለጉራጌ መንደሮች ትልቅ ውበት መላበስ አንዱ ምክንያቱ ባህላዊ ጀፎረ ነው። ለጉራጌ ኅብረተሰብ ጀፎሮ የዓይን ብሌን ነው ብለን ብንናገር ማጋነን አይደለም።

ጀፎሮ በጉራጌ ኅብረተሰብ ዘንድ ብዙ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች አሉት።

ሰው ሲሞት የለቅሶ ስነ ስርአት ይከናወንበታል ፣በሰርግ የሙሽሪትና ሙሽራው አጃቢዎችና ዘመዶች በባህላዊ ዘፈን በማጀብ ይሞጋገሱበታል፣ ሕጻናት ይጫወቱበታል ፣ወጣቶች የገና ጨዋታ ይጫወቱበታል፣ በቅሎ እና ፈረስ ይገራበታል፣ ባህላዊ የእርቅ ስነ ስርአት ይከናወንበታል ፣ወንዶችና ሴቶች የደቦ ስራ ለመስራት ቁጭ ብለው ይመካከሩበታል፣ በመስቀል በአል አዛውንቶችና ወጣቶች የበአሉ እለት የደመራ ሥነ- ስርአት ያከብሩበታል ፣ተሰብስበው ይመራረቁበታል፣ አዛውንቶች ተቀምጠው ጊዜያቸውን ያሳልፉበታል።

ለሰው መሰብሰቢያ፣ ከብቶች ጠዋት ከመሰማራታቸው፤ ማታ ደግሞ ወደየበረታቸው ከመግባታቸው በፊት የጋራ ማቆሚያ ስፍራ ከመሆኑም ባሻገር ለመንደሮች ውበትም የላቀ ሚና ይጫወታል።

ስለዚህም ጀፎረ /አውራ ጎዳና / ለጉራጌ ህዝብ ካለው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አንፃር በተገቢው ጠብቀን ለተተኪው ትውልድ ልናወርስ ይገባል።

እንዲሁም ቅርሳችን እንደ መሆኑ መጠን ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶት የቱሪስት መስህብ ሊደረግ ይገባል።

28/05/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ

ግንቦት 20/2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ እና 6ኛ ክፍል ማጠናቀቂ ክልላዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በዚሁም መሠረት የ6ኛ ክፍል ማጠናቀቂ ክልላዊ ፈተና ሰኔ 8 እና 9/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የ8ኛ ክፍል ማጠናቀቂ ክልላዊ ፈተና ደግሞ ሰኔ 11 እና 12 /2018 ዓ.ም ይሰጣል።

እንዲሁም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁ ይታወሳል።

በመሆኑም ተፈታኝ ተማሪዎች ይህ አውቃችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ማሳሰቡን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

28/05/2026

ለምርጫ የተመዘገቡ እጩዎች ልዩ መብቶች

1. ለምርጫ የተመዘገቡ እጩዎች ከባድ ወንጀል ሲፈፅሙ እጅ ከፍንጅ ካልተያዙ በስተቀር ምርጫው እስከሚጠናቀቅ ድረስ በወንጀል ተጠርጥረው አይያዙም፡፡

2. እጅ ከፍንጅም ባይሆንም ዕጩዎች ሕገወጥ ድርጊት የፈፀሙ እንደሆነ ሕጋዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው የሚችለው፣ የምርጫው ውጤት በቦርዱ አማካኝነት በይፋ ለህዝብ ከተገለፀ በኋላ ብቻ ይሆናል፡፡

3 እጩው በምርጫ ካሸነፈ፣ አሸናፊው ሰው በምርጫ ወቅት በፈፀመው ወንጀል የሚጠየቀው በሚመለከተው ምክር ቤት የሕግ ከለላው ሲነሳ ብቻ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ትመርጣለች!

Photos from በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር መገር ወረዳ መንግስት ኮምንኬሽን ጉ/ጽ/ቤት's post 28/05/2026

በተያዘው ምርት ዘመን በጉራጌ ዞን እኖር እና እኖር ኤነር መገር ወረዳዎች የአርሶ አደሩን ጉልበትና በሜካናይዜሽን የታገዘ እርሻ በማሳረስ እስካሁን ታርሶ የማይታወቁ ለዘመናት የቆዩ ማሳዎች የማሳረስ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የዞኑ የምርት እድገት ባለፉት ጥቂት አመታት ብቻ ከ5ሚሊየን ኩንታል በላይ እድገት አሳይቷል!!

ይሄንን እድገት በተሻለ መልኩ ለማስቀጠልና የዞኑ ሁሉም ወረዳዎች ትርፍ አምራች እንዲሆኑ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

ትርፍ አምራች ለመሆን የግብርና ቴክኖሎጂን ከመጠቀም ባሻገር ተጨማሪ መሬቶችን ማረስ አስፈላጊ ነው።

በክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) በበጀት አመቱ መግቢያ ላይ ከተቀመጡ የ"0" ግቦች አንዱ ምንም አይነት ያልታረሰ መሬት እንዳይኖር ማድረግ ነው!!

የዞናችን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማና የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ ከአዲስ እርሻ ጋር በተያያዘ የተቀመጡ ግቦችን ተፈፃሚነትን ለማረጋገጥና ወቅታዊ የግብርና ስራዎች እንቅስቃሴን ለማየት በእኖር ኤነር መገርና በእኖር ወረዳዎች የመስክ ምልከታ አድርገው ነበር!!

በመስክ ምልከታ የታዩት ነገሮች ተስፋ ሰጪ ብቻ ሳይሆኑ ተሞክሮም ሊቀሰምባቸው የሚገባ እንደሆኑ ተናግረዋል!!

ምንም አይነት ያልታረሠ መሬት አይኖርም በሚል መሪ ሀሳብ እና ለእርሻ ምቹ ሆነው በባህር ዛፍ የተሸፈኑ መሬቶችን ባህር ዛፉን በመመንጠር የማረስ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል!!

27/05/2026

=======የአፋልጉኝ ማስታወቂያ=======
ይህ ከታች በፎቶ የምትመለከቱት ወንድማችን ስሙ አዳነ ተሰጋ ሲዶ ይባላል ተወልዶ ያደገው በእኖር ኤነር መገር ወረዳ ላንካ ቶሬ ቀበሌ ልዩ መንደር ማሀል ቶሬ ሲሆን ይህ ወንድማችን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የአዕምሮ ህመም የገጠመው ሲሆን ዕለተ አርብ በቀን 13/09/2018 ዓ.ል ከቀኑ 9:00 ጀምሮ ከቤት እንደወጣ አልተመለሠም።

ቤተሰቦቹም የልጃቸውን መጥፋቱን ተገንዝበው በአካባቢው ህዝብና በፖሊስ ጣቢያዎች ቢፈልጉም እስካሁን ሊያገኙት አልቻሉም።

ወጣቱ በወቅቱ ከቤት ሲወጣ የለበሰው ነጭ የሹራብ፣ጥቁር ሱሪ የለበሰ በመሆኑ ወጣቱ እድሜው 35 ዓመት ሲሆን ወጣቱ ማንነቱ በተጠየቀ ሰዓት ማንነቱን የሚያስረዳ/የሚናገር ስለሆነ ወጣት አዳነ ተሰጋ ሲዶ ያየ ወይንም ያለበት የሚያውቅ በተመላከቱት ስልክ ቁጥሮች

➝ 09-17-23-74-72
➝ 09-13-68-84-27 ያየ የሰማ ከስር በተቀመው አድራሻ ቢያሳውቀን ወሮታውን ከፋይ ነን ይላሉ ፈላጊ ቤተሰቦቹ

ሼር በማድረግ መረጃው የማዳረስ ስራ ሰርተን የወላጅ አንጀት ከጭንቀት እንታደግ ሲል የእኖር ኤነር መገር ወረዳ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት የአፋልጉኝ ማስታወቂያውን ያስተላልፋል።

Photos from በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር መገር ወረዳ መንግስት ኮምንኬሽን ጉ/ጽ/ቤት's post 27/05/2026

በጉራጌ ዞን 1447ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርአት በድምቀት እየተከበረ ነው።

ግንቦት 19/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት አንዱ የአረፋ በዓል ሲሆን የዘንድሮ የ1447ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓልን የኢድ እየተካሄደ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በዓሉ በሚያከበሩበት ወቅት የተቸገሩ ወገኖች የሚረዱበት ፈጣሪን የሚለመንበት፣ አንድነትን፣ ወንድማማችነትን የሚሰበክበት በዓል ነው።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን እንኳን ለ1447ተኛው የኢደል-ዓድሃ (አረፋ)በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

ዒድ ሙባረክ!!

Photos from በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር መገር ወረዳ መንግስት ኮምንኬሽን ጉ/ጽ/ቤት's post 26/05/2026

በጉራጌ ዞን ለወቅታዊ የግብርና ስራዎች ትኩረት በመስጠት በዘርፉ እየታዩ ያሉ ውጤቶች አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል፦ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ

ግንቦት 18/2018

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ ጨምሮ ሌሎች የዞኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በእኖር ኤነር መገር ወረዳ በመገኘት በግብርና ልማት ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች የመስክ ምልከታ አካሂደዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማ እንደገለጹት፣ ከሀገራዊ ምርጫ ዝግጅት ጎን ለጎን በግብርናው ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር የህብረተሰቡን ምርታማነትና የኢኮኖሚ አቅም ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢኒሼቲቭ የተጀመረውን ያልታረሰ መሬት የማረስ እንቅስቃሴ በማጠናከር አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የእኖር ኤነር መገር ወረዳ ለተለያዩ የግብርና ስራዎች ምቹ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህንን ፀጋ ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ አቅም ለመቀየር በትኩረት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

በተጨማሪም አዳዲስ የግብርና ምርቶችን ማስጀመርና መሬትን በወቅቱ ማረስ ለምርታማነት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፣ በመንግስት፣ በተደራጁ ወጣቶች፣ በማህበራት እና በአርሶ አደሮች በቡናና ቅመማ ቅመም ምርት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

አቶ ላጫ አክለውም በአንዳንድ አካባቢዎች የታዩ ሞዴል የግብርና ስራዎችን በሁሉም የአርሶ አደር ጓሮዎች በማስፋፋት የተሻለ ምርታማነትና የገቢ አቅም መፍጠር እንደሚቻል ገልጸዋል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ እንዳሉት በዞኑ በተቀናጀ የግብርና ልማት፣በሌማት ትሩፋት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ፣ በቡና ልማት እንዲሁም ቀደም ሲል ያልታረሱ መሬቶችን ወደ ምርት በማስገባት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ በስፋት እየተሰራ ነው።

የበልግ እርሻ ስራዎችን በተገቢው ወቅት በማጠናቀቅና ለመጪው የመኸር ወቅት የተሻለ ምርት መሠረት ለመጣል ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል።

በዘንድሮ አመትም በ30 40 30 ኢኒሼቲቭ እንደዞን ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የፍራፍሬ ችግኞች ይተከላሉ ነው ያሉት አቶ አበራ።

በመስክ ምልከታውም በእኖር ኤነር መገር ወረዳ እየተከናወኑ ያሉ የእርሻ ስራዎች፣ የቡና ችግኝ ዝግጅት፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማቶች፣ በመኸር ቅድመ ዝግጅቶች የተገኙ ውጤቶች አበረታች መሆናቸው ጠቁሟል።

የቤተሰብ ብልጽግና ለማረጋገጥ ግብርናው አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለው በዘንድሮ መኸር ወቅት 178 ሺ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለማልማት ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የእኖር ኤነር መገር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሰበ ካብቱ በበኩላቸው የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በግብርና ዘርፉ በትኩረት እየተሰራ ነው።

በተለይ ድንች ፣በቆሎና ጤፍ በኩታገጠም እየተመረተ መሆኑን ጠቁመው በዘርፉ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየተፈጠረ መሆኑን ጠቁመዋል።

በወረዳው ያሉ የቡና አቅምና ጸጋ ከፍ በማድረግ የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ብለው ያልታረሱ መሬቶችም በስፋት መታረሳቸው አስታውቀዋል።

አቶ መላኩ ሳህሌ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ እንዳሉት በቀጣይ በወረዳው ለመኸር ወቅት ሰፊ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን በዘንድሮ አመትም 4ሺ 700 ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በተቀናጀ የግብርና ስራ የሚተዳደሩት አርሶ አደር ክንፈ ደሳለኝና አርሶ አደር ብዙነህ ሰፊ መሬታቸውን አስቀድመው በማለስለስና በኩታ ገጠም በማረስ ከግብርናው ዘርፍ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ሆነዋል።

በተለይም በቡና ልማት የተሻለ ውጤት እያስመዘገቡ ያሉት አርሶ አደሮቹ፣ የተቀናጀ የግብርና አሰራር ለምርታማነትና ለገቢ እድገት ያለውን ጠቀሜታ በተግባር እያዩ መሆኑ አመላክተዋል።

Photos from በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር መገር ወረዳ መንግስት ኮምንኬሽን ጉ/ጽ/ቤት's post 26/05/2026

ግንቦት 18/2018 ዓ.ም
''ኧሽርሽርየ" "ኧሽረኘ ገያ" ኧወኸመያ (የኢደል-ዓድሃ (አረፋ)በአል ገያ" በጉራጌ ማህበረሰብ በድምቀት ከሚከበሩ በአላት መካከል አንዱ ነው።

ይህንን በአል ተከትሎ በብዙ ሁነቶችና ገጠመኞች ታጅቦ የሚመጣ የመጨረሻ ገበያ ፥ ኧሽርሽርየ"፣ "ኧሽረኘ ገያ"በእኖር ኤነር መገር ወረዳ በወይራ ከተማ

''ኧሽርሽርየ ገያ" ገበያ ከፈጠሩት ብልሆች መንደር፣ ከጠበብቶች ሃገር በማህበረሰብ የስነልቦና ልህቀት ተገርቶ፣ በባህል ዕሴት እደጥበብ ተሽቆጥቁጦ፣ በበአል ድባብ ታጅቦ፣ ከገበያነት ይልቅ ፌስቲቫል መስሎ የሚውልበት እለት ነው።

የዕለቱ ገበያ ከባድ የሚያደርገው ባለፉት የበአል ገበያዎች ወቅት በተለያየ ምክንያት የሚፈልገውን ሳይሸምት የቆየ ሸማች የሚርመሰመስበት እለት ሲሆን ለበአል ገበያ ሩቅ ተጉዞ ምርት ያቀረበ ነጋዴ ትሩፏንና ኪሳራውን የሚለይበት ዕለት እንደመሆኑ ሁለቱም የመወሰን ስልጣናቸው በጊዜ ዳኝነት ከመቀማት ለመትረፍ የሚያደርጉት እሽቅድምድም ልዩ ስሜት ይፈጥራል።

መረጋጋት ከጎደለው እንዲሁ የገበያ ሁኔታን መቆጣጠር የሚያስችል የስሜት ብልህነት በሸሸው የግብይት ሂደት የሚውል ገበያ በመሆኑ የእብድ ገበያ "ኧሽረኘ ገያ" የሚል ማህበረሰባዊ መጠሪያ ይዟል።

በአይነትና በመጠን ተመሳሳይ የሆኑ ምርቶች በሰአታት ውስጥ የዋጋ መጨመር የሚታይባቸው ሲሆን መልሶ በሰአታት ውስጥ ሲጋሽብ የነበረ ዋጋ ድንገት ማሽቆልቆል ይጀምራል፣ ምንም አይነት የተረጋጋ የዋጋ ተመንና ልክ የለም።

ሸማች የገበያው ሁኔታ በንቃት ይከታተላል። ሻጭም የሸማቹን አመጣጥና የፍላጎት መጠን ካቀረበው ምርት ጋር እያመዛዘነ ይወስናል። ሸማቹ መቀነስን እየጠበቀ ሻጩ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችልበትን ሁኔታ ለመፍጠር ሲጥር ፉክክሩ ይደራል።

''ኧሽርሽርየ ገያ" የተባለው በቀጣይ ቀናት አማራጭ የግብይት ወቅት ስለማያገኝ የዕለቱ ገበያ ያቀረበውን ብቸኛ አማራጭ ለመሸመት የሚጣደፍ ሸማች እና የያዘውን ሽጦ ለመጨረስ በተገደደና ለመሸጥ በሚጓጓ ነጋዴ መካከል የሚደረግ የግብይት ሂደት በመሆኑ ኧሽርሽርየ ገያ የሚል ስሜትንም ግብይቱንም የሚገልጥ መጠሪያ ይዟል።

መግዛትና መሸጥ ማህበራዊና ስነልቦናዊ እንዲሁ ኢኮኖሚያዊ ግዴታ በሆንበት የመስቀል (የወኸመያ) ገበያ ፣ የበዓል ትዝታን በሚያጭሩ የግብይት ሁነቶችን ታጅቦ አልፏል።

መረጃው የእኖር ኤነር መገር ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

Photos from በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር መገር ወረዳ መንግስት ኮምንኬሽን ጉ/ጽ/ቤት's post 26/05/2026

ግኖድ 18/2018 ዘቨር
እእኖር ኤነር መገር ወረዳ ቡር ዳኘ አቨቃጥ አሰበ ካብቱ ቦኽይም አት ሺ አርዋት መቶ አራዋአ ሰአተኛ(1447)
የኢደል-ዓድሃ (አረፋ)በዓል ቦኸይ አሰናናሁም ቲኑዋ ወሄ ጭመቸህኖ አሰኖም።

ኧዋድረ የኢደል-ዓድሃ (አረፋ)በዓል ኧወገሬት፣ኧርመጀ፣ጎቸ ይኸረኸ እእኖር ኤነር መገር ወረዳ ቡር አቨቃጥ አሰበ ካብቱ ዝሬኮም።

ወረዳንራ በኖአራ ልማት ከሰ ወሄ ሜና ኧቴፔ ዘቨር ኧኸኔ ኧዋድረ የኢደል-ዓድሃ (አረፋ)በዓል በአል ድርብ ወሄ ዘቨርን ቲኑዋ አበቃጥ አሰበ አሰኖም።

ኧ1447ተኛ የኢደል-ዓድሃ (አረፋ)በዓል ትናከብረነዳ ደረገ ኤነኖ ሰቭ በኦጉዥት የትራከሰ ሰቭ ባሰታሩቁት ያሲእ ቲብሮ ጭሞጨሁኖዋ ኤኤጁም።

ቡር ዳኘ ደቦርኮታ ገኘኛ ናልማ የባረ ሰብ እንሞሗ በገኘሗ ያለማኸ ዝሬኮምታ ገኘንራ እማቴ ናልማነ ቲኑዋ ዝሬኮም።

ኢናይ ወረደ እን ሜና ኢኖኮኸ ኢትመችካ አየር አነን ኧኸነይ በወረዳንራ ኢንቨስት ኢናካ ሰቭ በነፐረ ወረዳንራ ኢቴኤፐር ቲኑዋ አትሄሩም።

ኧዋድረ ኧ1447ተኛ የኢደል-ዓድሃ (አረፋ)በዓል ኧወገሬት፣ኧርመጀ፣ኧዝፓና ይኸረኸ እእኖር ወረዳ ቡር አቨቃጥ አሰበ ቴጋአሩም።

ወሄ የኢደል-ዓድሃ (አረፋ)በዓል ኧህር ባነ አበሩስንራ ሰላም ታሁዋ ኧህን አት በሄም አሰናንረ አሰናናሁም እእኖር ኤነር መገር ወረዳ ቡር አቨቃጥ ቢድ!!

ትትሄተርንረዳ አበሩስንራ ተዋአካሞሃ ኧኬር፣ ኧርማጀ፣ ኧሽኛት፣ እእማትነድ፣ ኧዝፓና በአል ኧህር ባርነ።

መስራጀ ሁና ሽካከተታ አቀረበናሁዋ ሁዳ እእኖር ኤነር መገረ ወረዳ መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቢድን

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Addis Ababa