18/08/2021
ነሃሴ 11/2013ዓ.ም
የወረዳ 01 ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤትና የውኃና ፍሳሽ መካኒሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በጋራ በመሆን በጣቢያ 02 የአቅመ ደካማ ቤት የማደስ ስራ በዛሬው ዕለት ተጀመረ‼️
በወረዳ 01 ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ጽ/ቤት አስተባባሪነት የዘንድሮ የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ 12 ቤቶች ለማደስ በእቅድ ተይዘው እየተሰሩ መሆኑን ይታወሳል።
በዛሬው እለት በጣቢያ 02 የቤት እድሳት መርሐግብርን በማስመልከት የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል አበበ፣ የኮ/ቀ/ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዘይኑ አህመድ እና የወረዳው ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ወይንሸት ጎሳ፣ የወረዳው የወጣቶች እና በጎ ፍቃድ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ዘመን ሽመልስ እንዲሁም የውኃና ፍሳሽ መካኒሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስተባባሪዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት ጣቢያ 02 የሚገኘውን ስድስት ቤተሰብ ያለው የአካል ጉዳተኛ ቤት የእድሳት ስራ አስጀምረዋል። የቤቱ እድሳት እስከ 215ሺ ብር እንደሚፈጅ ተገልጿል።
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል አበበ በበጎ ተግባር ላይ የተሳተፉ የውኃና ፍሳሽ መካኒሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በማመስገን በእንዲህ አይነት ተግባር ላይ መሳተፍ ለሚፈልጉ ግብረሰናይ ድርጅቶች በወረዳው ስር የሚገኙ የአቅመ ደካማ ቤቶችን በማደስ ተግባር ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አስተላልፈዋል‼️
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 የመንግስት መረጃና ኮሚኒኬሽን ጉዳዩች ጽ/ቤት ዘግቧል።

12/08/2021