10/07/2026
እ.ኤ.አ ከጁላይ 11 እስከ 20/2026 (ሐምሌ 4 እስከ ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ በውሃ ዘርፍ ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅዕኖ
/////////
በሚቀጥሉት በጁላይ የሁለተኛ አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ ተፋሰሶች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው የገጸምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸው ይጠበቃል። በመሆኑም የሚኖሩ መልካም አጋጣሚዎችን ለመጠቀምና አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመቀነስ ከታች የቀረቡትን ቦታ ተኮር የውሃ ሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሃሳብ ከወዲሁ ማከናወን ያስፈልጋል፡፡