Addis Ababa Burn Emergency and Trauma Hospital/SPHMMC- አቤት ሆስፒታል

Addis Ababa Burn Emergency and Trauma Hospital/SPHMMC- አቤት ሆስፒታል

Share

AaBET Hospital – SPHMMC’s Center for Burn, Emergency, Critical Care and Trauma.

Renowned for homing postgraduate trainings in Orthopedic & Traumatologic Surgery, Neurosurgery, Plastic & Reconstructive Surgery, and Emergency & Critical Care Medicine. Addis Ababa Burn, Emergency & Trauma Hospital (AaBET Hospital) is an affiliate of St. Paul’s Hospital Millennium Medical College and is inclusive of four major departments; Emergency Medicine and Critical Care, Plastic Reconstruct

26/10/2025
Photos from Addis Ababa Burn Emergency and Trauma Hospital/SPHMMC- አቤት ሆስፒታል's post 24/10/2025

13/02/2017
የሆስፒታሉ ሴቶች ፎረም አመታዊ እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ
የቅ.ጳ.ሚ.ሜ.ኮ ያዲስ አበባ የቃጠሎ፣ የአደጋ እና የድንገተኛ ሆስፒታል/አቤት/ በዛሬው እለት አመታዊ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለአባላቱ አቅርቧል፡፡
የሆስፒታሉ ስራ አስኪጅ ዶር ጸጋዬ ገ/ሃናንያ በእለቱ ባስተላለፉት መልእክት የሴቶች ፎረም የመንግስት አቅጣጫ ስለሆነ መጠናከር ያለበት ሲሆን እኛም የምንፈልገው ነው፡፡ አንዳንድ መሃበረሰብ አቀፍ ስራዎችንም በቅንጅት የምንሰራ ይሆናል፡፡ የሴቶች ተሳትፎም እንዲጎላ ተጠናክራችሁ እንድትሰሩ እንደግፋለን ብለዋል፡፡
የሴቶቸና መህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ገነት በየነ በደረጉት ንግግር ፎረሙ ከተቋሙ ፕሮግራሞች ጋር ተቀናጅቶ በበጎ ስራዎች ላይ በግንባር ቀደምነት እንዲሳተፍ ለማስቀጠል አባላት እንዲሳተፉ ጥሪ አድርገዋል፡፡ አክለውም የሴቶች አቅምን ማጎልበት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሰራት አለበትም ብለዋል፡፡
ከሪፖርቱ መመልከት እንደተቻለው ፎረሙ በ2017 በጀት አመት አባላትን ቁጥር ከ240 ወደ 262 ማሳደግ ተችሏል፡፡ አጠቃላይ ገቢውም 402.541.86 ሲሆን ወጪው ደግሞ 196.284.84 ነው፡፡ በአካውንቱ የሚያሳየው ባላንስ ደግሞ 206.257.00 ነው፡፡ በበጀት አመቱ ሰራተኛውን ተጠቃሚ ለማድረግ በ6 ወር ክፍያ የመመገቢያ ሳህን፣ የሽንኩርት እና የጁስ መፍጫ ቀርቧል፡፡ ለተጨማሪ የፎረሙ ገቢ ደግሞ የቡና፣ ሻይ፣ ብስኩትና ውሃ ሽያጭ ተከናውኗል፡፡
በእለቱ ደጋፊ ወንዶች 3 እና ሴት አባላት 22 በድምሩ 25 የሆስፒታሉ ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

Photos from Addis Ababa Burn Emergency and Trauma Hospital/SPHMMC- አቤት ሆስፒታል's post 20/10/2025

10/02/2018
አመራሩ ከዲፓርትመንት ሀላፊዎች እና ከስራ አስፈፃሚዎች ጋር ተወያየ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የ.ቅ.ጳ.ሚ.ሜ.ኮ የአዲስ አበባ የቃጠሎ፣ የአደጋ እና የድንገተኛ ሆስፒታል/አቤት/ አዲሱ ስራ አስኪያጅ እና የማኔጅመንት አባላት በዛሬው እለት ከሆስፒታሉ ዲፓርትመንት ሀላፊዎች እና ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ተወያይተዋል።

በአቤት በስራስኪያጅነት የተመደቡት ዶር ፀጋዬ ገ/ሀናንያ በሆስፒታሉ ያሉ አጠቃላይ ሁኔታዎችን ለመለየት እና በቀጣይ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ይቻል ዘንድ ከበተቋሙ ካሉ አጠቃላይ የዲፓርትመንት ሀላፊዎች እና ስራ አስፈፃሚዎች ጋር የየክፍሉን ስራዎች እና ያሉ ክፍተቶችን አስመልክቶ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል።

ከውይይቱ በፊትም በሆስፒታሉ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ለመረዳት ያስችላቸው ዘንድ አጠቃላይ ጉብኝት አድርገዋል።

ከየክፍሉ የመጡ አመራሮች በየክፍላቸው የሚታዩ አጠቃላይ የቁሳቁስ፣ የሰው ሀይል፣ የመድሀኒት እንዲሁም በቡድን የመስራት እና ከአመራሩ ጋር ተናቦ በመስራት ሂደት ያሉ ክፍተቶችን አቅርበዋል።

ዶር ፀጋዬም በሆስፒታሉ የሚታየውን የቁሳቁስ እና የስራ ቦታ ጥበትን ለማስተካከል ጥረት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል። የአገልግሎት አሰጣጡ የተገልጋይን እርካታ የሚያመጣ መሆን አለበትም ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ፤ በተቋሙ የሚታየውን የበጀት እጥረትም በጋራ ለመፍታት ጥረት እናደርጋለን። ለሰራተኛው ቅርብ በመሆን ማወያየት አለብን። ለሰራተኛው ጥያቄ ምላሽ መስጠት ይጠበቅብናል። ሆስፒታሉን መስመር እስከምናስይዝ ድረስ ጠንክረን ሌት ተቀን መስራትም ይጠበቅብናል ብለዋል።

Photos from Addis Ababa Burn Emergency and Trauma Hospital/SPHMMC- አቤት ሆስፒታል's post 17/10/2025

17/02/2018
ሰራተኞቹ በሀገራዊ ጉዳዩች እና የእቅድ አፈጻጸም ላይ ተወያዩ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊንየም ሜዲካል ኮሌጅ እና የአዲስ አበባ የቃጠሎ፣ የአደጋ እና የድንገተኛ ሆስፒታል/አቤት/ ሰራተኞች "ብሄራዊ ጥቅምና ጂኦ ስትራቴጂያዊ ቁመና!" በሚል ርእስ በቀረበ ሀገራዊ ሰነድ እና የተቋማቱ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱም የአመራሩ ቆራጥ የለውጥ ተነሳሽነት በሰራተኛው ውስጥ ትልቅ አዎንታዊ ስሜትን የፈጠረ ሲሆን፤ በየተቋማቱ ያሉ ጥንካሬዎችና ድክመቶች በነፃነት ተነስተው ውይይትም ተደርጎባቸዋል።

ለለውጥ አብሮ ለመስራት በአመራሩ እና በሰራተኛው መካከል ከፍተኛ ፍላጎት የታየበት የውይይት መድረክ ነበር።

17/10/2025

ዶር ፀጋዬ ገብረሀናኒያ ሀጎስ በቅ.ጳ.ሚ.ሜ.ኮ በአዲስ አበባ የቃጠሎ፣ የአደጋ እና የድንገተኛ ሆስፒታል/አቤት/ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ተመድበዋል። ዶር ፀጋዬ የኢመርጀንሲ እና ክሪቲካል ኬር ስፔሻሊስት ሲሆኑ በህክምናውም ሆነ በሆስፒታል አስተዳደር ዙርያ የካበተ ልምድም አላቸው።
በአቤት ሆስፒታል የሚኖራቸው የዋና ስራ አስኪያጅነት ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን በመመኘት እንኳን ደህና መጡ!!!

Photos from Ethiopian News Agency's post 30/09/2025
Photos from Addis Ababa Burn Emergency and Trauma Hospital/SPHMMC- አቤት ሆስፒታል's post 26/09/2025

16/01/2018
የቅ.ጳ.ሚ.ሜ.ኮ አዲስ አመራሮች ከአቤት አመራርና ሰራተኞች ጋር ተወያዩ
*****************************************
የቅ.ጳ.ሚ.ሜ.ኮ አዲስ አመራሮች ከአቤት አመራርና ሰራተኞች ጋር በዛሬው እለት በአቤት ሆስፒታል ውይይት አድርገዋል።

አዲሱ አመራርን በሆስፒታሉ ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎችን መረዳት እንዲያስችላቸው የተቋሙን ነባራዊ ሁኔታ የሚያሳይ ሰነድ በሜዲካል ዳይሬክተሩ በዶር ወልደሰንበት ዋጋነው ቀርቧል።

የተቋሙ ሰራተኞችም ሆስፒታሉ የራሱ ህንፃ እንዲኖረው፣ በየክፍላቸው ያሉ የቁሳቁስ ችግሮች፣ የሕክምና ግብአቶች እጥረት፣ የባለሙያ ጥቅማጥቅም እና ስልጠና፣ በተቋም የሚታዩ እና በአመራሩ ዘንድ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች አንስተዋል።

አዲሱ አመራርም በቀጣይ በቅርበት ከሰራተኛው ጋር በመስራት ያሉ ችግሮች ለመቅረፍ ጥረት እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


AaBET Hospital
Addis Ababa