Federal Law and Justice Institute የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት

Federal Law and Justice Institute  የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት

Share

#Towards Excellence!!!

Photos from Federal Law and Justice Institute  የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት's post 08/06/2026

የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ለመከላከያ የፍትሕ ኃላፊዎች በማኔጅመንት ስኪል ላይ ስልጠና መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ ሰኔ 01 ቀን 2018 ዓ.ም

የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት በበጀት ዓመቱ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ለመስጠት በያዘው ዕቅድ መሰረት፣ ከሁሉም ዕዞች፣ ኃይሎችና ዋና መምሪያዎች ለተውጣጡ የመከላከያ ፍትሕ ኃላፊዎች በአመራር ክሂሎት (Management Skills) በተለይም በውጥረት አያያዝ (Stress Management) እና በዕቅድ ዝግጅት (Planning) ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት ጀምሯል። ስልጠናው በሁሉም መስክ ለጋራ ዓላማ እና ግብ በትጋት በመስራት ዘመናዊ ተቋማትን ለመገንባትና ለማሻገር ያለመ ነው።

በስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የመከላከያ ፍትሕ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል አሰፋ ደበሌ ተቋሙ ከሪፎርም ወደ ትራንስፎርሜሽን ራሱን እየለወጠ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ፍትሕን የተከተለ አሰራር ለመተግበር አመራሩ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በመረዳት ስልጠናውን በትኩረት መከታተል እንዳለበት አሳስበዋል።

የመከላከያ ፍትሕ ዋና ዳይሬክቶሬት የወንጀል መከላከልና ስልጠና ዳይሬክተር ኮሎኔል ሰለሞን ግርማ በበኩላቸው፣ ለአመራሩ እየተሰጠ ያለው ስልጠና በተቋሙ የፍትሕ ሥርዓትን ለማዘመን አስተዋጽኦው የጎላ እንደሆነና ወደፊትም ቀጣይነት እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ስልጠናውን እየሰጡ ያሉት የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የተከበሩ ዶክተር ከበደ ገነቲ በበኩላቸው፣ አለም ተለዋዋጭ በመሆኗ በሰራተኞች መካከል ፍትሕን ለማንገስ፣ ኃይልን ለማሰባሰብና አቅጣጫ ለማሳየት ተፅዕኖ ፈጣሪ አመራር ማብቃት ያስፈልጋል ብለዋል።

ዛሬ የተጀመረው ይህ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
=================================
ምንጭ፦ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

08/06/2026
ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ 08/06/2026

https://www.ena.et/web/amh/w/amh_8995156

ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት የምርምርና የማኅበረሰብ አገልግሎት ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሰመራ፣ግንቦት 30/2018(ኢዜአ):-ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርንና ፍልሰትን ለመግታት የሚከናወኑ የምርምር ሥራዎችንና የማኅበረሰብ አገልግሎቶችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ....

Photos from Federal Law and Justice Institute  የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት's post 08/06/2026

ሕገ-ወጥ ስደትን እና የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የተዘጋጀ ሀገራዊ ሲምፖዚየም ተጠናቀቀ
ሰመራ /ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም
በፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት እና በሰመራ ዩኒቨርሲቲ በጋራ የተዘጋጀው “ህገ-ወጥ ስደት እና የሰዎች ዝውውር ላይ ትኩረቱን በማድረግ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ብሔራዊ ሲምፖዚየም በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
ይህ ሲምፖዚየም ከ44 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ የህግ ትምህርት ቤት ዲኖችን፣ ምሁራንን፣ የፖሊሲ አውጭዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ከመላው ሀገሪቱ አሰባስቧል።
በማጠቃለያፕሮግራሙ ላይ የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ ዶ/ር ዘካርያስ ኤርኮላ ፣ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሌሎች ባለድርሻ አካላት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ይህ ሲምፖዚየም በቆይታው ከሰው ማዘዋወር እና ከተደራጀ ህገ-ወጥ ስደት፣ ከኢትዮጵያ የፖሊሲ እና የህግ ማዕቀፎች፣ ከስደት አስተዳደር (migration governance)፣ ከሰው ማዘዋወር ጾታዊ ገፅታዎች፣ ለአስገዳጅ ስደት ከሚሰጡ ህጋዊ ምላሾች እና ችግሮችን በመፍታት ረገድ የሚዲያ ሚና ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚዳስሱ ምሁራዊ የምርምር ፅሁፎች ቀርበዋል።
ይህ ሲምፖዚየም በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚታዩት ህገ-ወጥ ስደት እና የሰው ማዘዋወር ችግሮች የሚሰጡ ህጋዊ፣ ማህበራዊ እና ተቋማዊ ምላሾችን ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራዊ ምክረ-ሀሳቦችን በማመላከት ፍጻሜውን ያገኘ ሲሆን ለሲምፖዚየሙ መሳካ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
=================================
ምንጭ፦ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
National Symposium Organized to Prevent Illegal Migration and Human Trafficking Concludes
Samara / June 7, 2026 (Ginbot 30, 2018 E.C.) The two-day national symposium focusing on "Illegal Migration and Human Trafficking," jointly organized by the Federal Law and Justice Institute and Samara University, has successfully concluded.
The symposium brought together law school deans from 44 public universities, scholars, policymakers, and other stakeholders from across the country.
The closing program was attended by H.E. Dr. Zekariyas Erkolla, Deputy Director General of the Federal Law and Justice Institute and Member of the House of Peoples’ Representatives, senior leaders of Samara University, and heads of various stakeholder organizations.
During its course, the symposium featured presentations of scholarly research papers covering issues related to human trafficking and organized illegal migration, Ethiopia’s policy and legal frameworks, migration governance, gender dimensions of human trafficking, legal responses t

06/06/2026

National Symposium Held to Combat Illegal Migration and Human Trafficking

Samara / June 06, 2026 (Ginbot 29, 2018 EC)

The Federal Law and Justice Institute, in collaboration with Samara University, hosted a national symposium aimed at curbing the severe challenges of illegal migration and human trafficking.

The symposium commenced with a welcoming speech by Mr. Ali Zeynu Adem, Vice President for Research (DRTTVP), followed by an opening speech from Dr. Abdurahman, Academic Vice President (AVP) of Samara University.

In his keynote speech, H.E. Dr. Zekarias Erkolla, Deputy Director General of the Federal Law and Justice Institute, emphasized the critical need to build strong linkages between academic research and practical law enforcement to effectively dismantle sophisticated, transnational human trafficking networks.
During the event, six research papers focusing on the current state of migration and human trafficking in Ethiopia were presented by various scholars:

Prem Sam Ponniah (Ph.D.) presented his research titled "Human Trafficking and Irregular Migration in Ethiopia: South Omo–Turkana Transits," highlighting localized vulnerabilities along major transit routes.

Mr. Abdushukur Nursela provided a comprehensive overview under the title "Addressing Illegal Migration and Human Trafficking: Policy, Legal, and Institutional Frameworks," identifying key areas requiring reform for legislative and law enforcement bodies.

Mr. Tsalafu Chaka presented a research paper titled "Ethiopia's Implementation of AU Migration Policy Framework across Moyale Border."

Mr. Solomon Anteneh shared his study with the audience, titled "Gendered Pathways of Migration and Trafficking in Ethiopia."

A paper tracing the transition from displacement to exploitation, titled "From Forced Migration to Human Trafficking: Risk Factors and Legal Responses," was presented by Mr. Shishigu Abi Adimasu.

Mr. Muluken Zemene presented a paper evaluating media responsibilities, titled "The Role of Media in Reducing Illegal Migration and Human Trafficking."
Following the presentations, participants raised numerous questions and constructive ideas, which were addressed with detailed explanations and responses from the presenters.
In its conclusion, the symposium underscored that ensuring sustainable prevention of illegal migration and human trafficking requires enacting policy reforms, strengthening legal responses, and significantly improving border control management.
This forum is an annual event hosted rotationally by selected universities incorporating Ethiopian law schools, drawing participation from prominent legal professionals, researchers, and policymakers.
=================================
Source: Public Relations and Communication Directorate

Photos from Federal Law and Justice Institute  የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት's post 06/06/2026

ሕገ-ወጥ ስደትን እና የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የተዘጋጀ ሀገራዊ ሲምፖዚየም ተካሄደ

ሰመራ /ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም

የፌዴራል የሕግና የፍትሕ ኢንስቲትዩት ከሰመራ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር ሕገ-ወጥ ስደትና የሰዎች ዝውውር አስከፊ ፈተናዎችን ለመግታት ያለመ ብሔራዊ ሲምፖዚየም በሰመራ ዩኒቨርሲቲ አካሄደ።

ሲምፖዚየሙ በDRTTVP ምርምር ምክትል ፕሬዚዳንት በአቶ አሊ ዘይኑ አደም የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት እና በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት በዶ/ር አብዱራህማን የመክፈቻ ንግግር ተጀምሯል።

የፌደራል ሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ ዶ/ር ዘካርያስ ኤርኮላ ባስተላለፉት የዕለቱ ቁልፍ መልዕክት ፤ የተቀናጁ ድንበር ተሻጋሪ የሰዎች ዝውውር መረቦችን ለመግታት በሚሰራ የአካዳሚክ ምርምር እና በተግባራዊ የሕግ ማስከበር ሥራ መካከል ጠንካራ ትስስር መፍጠር እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ ያለውን የስደት እና የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሁኔታ በተመለከተ በተለያዩ ምሁራን የተዘጋጁ ስድስት ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል።

በትራንዚት ኮሪደሮች ላይ ያተኮረ ትንታኔ በፕሬም ሳም ፖኒያ (Prem Sam Ponniah (Ph.D.) « በኢትዮጵያ ውስጥ የሰዎች ዝውውር እና ሕገ-ወጥ ስደት፦ የደቡብ ኦሞ–ቱርካና ትራንዚቶች" (Human Trafficking and Irregular Migration in Ethiopia: South Omo–Turkana Transits » በሚል ርዕስ ያደረጉትን ምርምር ያቀረቡ ሲሆን፤ በዋና ዋና የትራንዚት መስመሮች ላይ ያሉ አካባቢያዊ ተጋላጭነቶችን አመላክተዋል።

« ሕገ-ወጥ ስደትን እና የሰዎች ዝውውርን መግታት፦ ፖሊሲ፣ ሕግ እና ተቋማዊ ማዕቀፎች" (Addressing Illegal Migration and Human Trafficking: Policy, Legal, and Institutional Frameworks) » በሚል ርዕስ አቶ አብዱሹኩር ኑርሰላ አጠቃላይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፤ ለሕግ አውጪውና ሕግ አስከባሪው አካል ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸውን ቁልፍ ዘርፎችን ለይተዋል።

« ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረትን የስደት ፖሊሲ ማዕቀፍ በሞያሌ ድንበር ላይ ተግባራዊ ለማድረግ እያከናወነች ያለችውን እንቅስቃሴ / Ethiopia's Implementation of AU Migration Policy Framework across Moyale Border) » የተመለከተ ጥናታዊ ጽሑፍ አቶ ጻላፉ ጫካ (Tsalafu Chaka) አቅርበዋል።

« በኢትዮጵያ ውስጥ ከስደት እና ከሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር ተያይዞ የሚታዩ ጾታን መሰረት ያደረጉ ችግሮች / Gendered Pathways of Migration and Trafficking in Ethiopia) » በተመለከተ ያጠኑትን ጥናት ለታዳሚው ያጋሩት አቶ ሰለሞን አንተነህ ናቸው።

« ከግዳጅ ስደት ወደ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር / From Forced Migration to Human Trafficking: Risk Factors and Legal Responses » የሚደረገውን ሽግግር፣ ለዚህም መንስኤ የሚሆኑ አስጋጅ ሁኔታዎችንና ሊሰጡ የሚገባቸውን ሕጋዊ ምላሾች የሚዳስስ ጽሑፍ በአቶ ሽሽጉ አቢ አድማሱ አማካኝነት ቀርቧል።

« ሕገ-ወጥ ስደትን እና የሰዎች ዝውውርን በመቀነስ ረገድ የሚዲያ ሚና/ The Role of Media in Reducing Illegal Migration and Human Trafficking » በሚል ርዕስ የሚዲያዎችን ኃላፊነቶች የሚገመግም ጽሑፍ በአቶ ሙሉቀን ዘመነ ቀርቧል፡፡

የጥናት ጽሑፎቹ ከቀረቡ በኋላ በመድረኩ ተሳታፊዎች አማካኝነት በርካታ ጥያቄዎች እና ገንቢ ሐሳቦች የተነሱ ሲሆን፣ ለቀረቡት ጥያቄዎችና ሐሳቦችም በአቅራቢዎቹ አማካኝነት ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

በመድረኩ ላይ ሕገ-ወጥ ስደትንና የሰዎች ዝውውርን በዘላቂነት ለመከላከል የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ማድረግ፣ ሕጋዊ ምላሾችን ማጠናከር እና የድንበር ላይ ቁጥጥርን ይበልጥ ማሻሻል እንደሚገባ ተመላክቷል።

ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነው

ሰመራ፤ ግንቦት 29/2018 (ኢዜአ)፦ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጥናት እና ምርምር ተግባራት ማገዝ እንዳለባቸው የፌዴራል ህግና ፍትህ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዘካሪያስ ኤርኮላ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከፌዴራል የህግና ፍትህ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "ህገ-ወጥ ፍልሰት እና የሰዎች ዝውውር፤ የህግ፣ ማህበራዊ እና ተቋማዊ አመለካከቶች" በሚል መሪ ሀሳብ ያዘጋጀው አገር አቀፍ ሲምፖዚየም በሰመራ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ዘካሪያስ ኤርኮላ (ዶ/ር)፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና ፍልሰትን ለመከላከል የሚደረገውን ሀገራዊ ጥረት በጥናትና ምርምር ማገዝ አለባቸው ብለዋል።

የዚሁ አካል በሆነው በዚህ ሲምፖዚየም ላይ የቀረቡት የምርምር ፅሁፎች፣ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት የወጡ ህጎች አፈፃፀምና አተገባበር ላይ ትኩረት ያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በውይይቱ የሚገኙት ግኝቶች ለፖሊሲ አውጪዎችና ለህግ ማሻሻያ ስራዎች በግብአትነት እንደሚያገለግሉም ገልጸዋል።

ኢንስቲትዩቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በህጎች አተገባበር ላይ የግንዛቤና የምርምር ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፤ ይህም ችግሩን በዘላቂነት ለማስወገድና የፖሊሲ ግብአቶችን ለማፍለቅ ትልቅ እገዛ አድርጓል ብለዋል።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱረህማን ከድር (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው ህገ-ወጥ ፍልሰትና የሰዎች ዝውውርን ለመግታት የድርሻውን እያበረከተ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተለይም የአፋር ክልል ወደ የመንና ጅቡቲ ለሚደረገው ህገ-ወጥ ስደት እንደ መስመር የሚያገለግል በመሆኑ፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ተቋማቸው በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲው ለህብረተሰቡ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት፣ ለባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት እና ችግር ፈቺ ጥናቶችን በማካሄድ ረገድ በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ አክለዋል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ አገር አቀፍ ሲምፖዚየም ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ የህግና ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ክፍል ዲኖች፣ ተመራማሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
=================================
ምንጭ፦ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

Photos from Federal Law and Justice Institute  የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት's post 04/06/2026

ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሕግ ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ | ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም

የፌዴራል የሕግና የፍትሕ ኢንስቲትዩት ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሕግ ባለሙያዎች ላለፉት 20 ቀናት ሲሰጥ የነበረውን የአቅም ግንባታ ሥልጠና አጠናቋል።

በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ በመገኘት ለሰልጣኞቹ የሥራ መመሪያ የሰጡት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ ዶክተር ዘካርያስ ኤርኮላ፤ ኢንስቲትዩቱ በአዋጅ በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት በሥልጠና፣ በጥናትና ምርምር፣ በሕግ መረጃ ማዕከልነትና በሕግ ማሻሻያ ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። አክለውም፣ ሰልጣኞች በሥልጠናው የቀሰሙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመለወጥ ረገድ በትጋት መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ጋቨርናንስና ኮምፕሊያንስ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዱጉማ ነዳ በበኩላቸው፤ የሥልጠናው ዋና ዓላማ የሕግ ባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ ተቋሙን የሚመለከቱ ሕግ ነክ ተግባራት ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲከናወኑ ማስቻል መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ ሥልጠና በዋናነት “የማስረጃ ሕግ ፣የአሠሪና ሠራተኛ ሕግ፣ የግዢ ሕግ፣ የውል ሕግና ከውል ውጭ ኃላፊነት፣ የንግድ ሕግ ፣ የኮንስትራክሽን ሕግ፣ የፍትሐ-ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ፣ የታክስ ሕግ እንዲሁም የግልግልና ዳኝነት ሕግ “ላይ ያተኮረ ነበር፡፡
=================================
ምንጭ፦ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

Photos from Federal Law and Justice Institute  የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት's post 30/05/2026

የኢ-ለርኒንግ (e-Learning) የፓይለቲንግ ሥልጠና መካሄድ ጀመረ

(አዲስ አበባ፣ግንቦት 22/2018 ዓ.ም) የፌዴራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ሥልጠናዎችን በቴክኖሎጂ ለማዘመን ይቻል ዘንድ ለክልል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩቶች አሰልጣኞች፣ ዳኞችና የ(IT) ባለሙያዎች የተዘጋጀው የኢ-ለርኒንግ ፓይለቲንግ ሥልጠና በድሪም ላይነር ሆቴል መስጠት ተጀምሯል።

በሥልጠናው መክፈቻ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የዳኝነትና የፍትሕ አካላት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሠናይት አንዳርጌ እንደገለጹት፤ የዚህ የኢ-ለርኒንግ ሥልጠና ዋና ዓላማ የፍትሕ አካላት ሥልጠናን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ይበልጥ ቀልጣፋ ማድረግ መሆኑን አብራርተዋል።

ወ/ሮ ሠናይት አክለውም ሥልጠናው በዛሬውና በነገው ውሎ ወደ ዋናው ሥልጠና ከመገባቱ በፊት ለአሰልጣኞች ከይዘትና ከቴክኖሎጂ አኳያ የሙከራ (Piloting) ሥልጠና እንደሚደረግ ገልጸው፣ የዚህ የፓይለቲንግ ሥልጠና ዋና ዓላማም በሂደቱ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ቀድሞ በመለየት ተገቢውን ማስተካከያ መስጠት እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ኢንስቲትዩቱ በዚህ ዓመት ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር፣ ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ 6 የሥልጠና ሞጁሎችን ለኢ-ለርኒንግ በሚመች መልኩ በዘርፉ ምሁራን (Subject Matter Experts) እና በIT ባለሙያዎች እንዲበለጽጉ መደረጉን ገልጸዋል።

ሥልጠናው በሦስት ዋና ዋና ይዘቶች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰጥ የጠቀሱት ወ/ሮ ሠናይት፣ እነሱም፦ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተዘጋጀ የሬጅስትራሮች ሞጁል፣ የንብረት ማስከበርና እግድ (በፍርድ በፊት ስለሚሰጥ እግድ) እና የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ይህ የኢ-ለርኒንግ ሥርዓት የሕግና ፍትሕ አካላትን አቅም በዘመናዊ መንገድ ለመገንባት የተጀመረ ትልቅ እርምጃ ነው።
========================================
ምንጭ፦ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

28/05/2026

የጥናቱ ርዕስ
የሺናሻ፣ የሲዳማ፣ የመዠንገር እና የወላይታ ባህላዊ ህግ ጥናት ሪፖርት
የጥናቱ ዓላማ/ግብ
--------------------------------
በጥናቱ የቀረበ ምክረ ሀሳብ
1 በየአካባቢው ግጭቶችን ለመፍታት በተለይ በገጠሩ አካባቢ አግልገሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት ባህላዊ የግጭት መፍችያ ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት እና ተቀባይነት ከግምት በማስገባት (አሁን በስራ ላይ ባለው የኢፌድሪ ህገ መንግስት እውቅና የተሰጣቸው ቢሆንም) የባህላዊ ህጎችንና የባህላዊ ተቋማትን አሰራር በተመለከተ ዝርዝር ህግ በህግ አውጪው አለመውጣቱ በአፈፃጸም ረገድ በርካታ ችግሮችን አስከትሏል፡፡ የህገ መንግስቱ አላማና ፍላጎትም ሙሉ በሙሉ እንዳይተገበር አድርጎታል፡፡ በመሆኑም የህግ አውጪው አካል ዝርዝር ህግን በማውጣት ይህን ችግር ሊፈታው ይገባዋል፡፡ በዚህ ረገድ ሩቅ ሳይኬድ በአህጉራችን ከሚገኙት ሀገራት መሃከል የደቡብ አፍሪካ የዛምቢያ የቦትስዋና እና የሴራሊዮን ህገ መንግስት እና የህግ ስርአቶች በዚህ ዙሪያ የወሰዱትን አቋም መመልከቱና ልምድ በመቅሰም ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማዛነቅ ለችግሩ መፍትሄ መሻት ያስፈልጋል፡፡
ይህ ጥናት ማንኛውም የወንጀል ጉዳዮች በባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት መታየት አለባቸው የሚል አቋም የለውም፡፡ የባህላዊ ህግ እና የፍትህ ተቋማቱ አደረጃጀት ለምሣሌ ያህል፡
• እጅግ ውስብስብ እና የባለሙያ ዕውቀት የሚጠይቁትን በተላላፊ የገንዘብ ሰነዶች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን፣
• የሃገርንና የመንግስትን ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥለውን የሙስና፣ የኮንትሮባንድ እና ማኒ ላውንድሪ ወንጀሎችን፣
• የሽብርተኝነት፣ የዝርፊያ፣ የስርቆት እና የሃገር መክዳት ወንጀሎችን፣
• ከቴክኖሎጂ ዕድገትና ምጥቀት ጋር (ለምሣሌ ከኮምፒውተር አጠቃቀም) ጋር ተያይዞ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን፣
• በአለም አቀፍ ህግ ይቅርታ የማያሠጡ ወንጀሎችን፣
• በሴቶች እና በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወሲብ ነክ እና የመሣሠሉትን ለመዳኘት የሚያስችል ዘመናዊ አደረጃጀት፣ ዕውቀትም ሆነ ብቃት ላይኖራቸው ይችላል፡፡
እንደ እነዚህ አይነት ወንጀሎችን የመዳኘት ሥልጣን ይሠጣቸው ቢባልም ተገቢ ላይሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ከዚህ እና ከመሣሠሉት የወንጀል ድርጊቶች ባሻገር፡-
• በጎሣ በብሔር እና በሃይማኖት ተከታዮች መሃከል የሚነሱ ግጭቶችን፣
• በግድያ ምክንያት የሚከሰቱ ቅራኔዎችን፣
• በቤተሰብና በውርስ ጉዳዮች የሚነሱ አለመግባባቶችን
• በድንበር፣ በመሬት አጠቃቀም፣ በጋራ የግጦሽ፣ የውሃ እና መሰል የተፈጥሮ ሃብቶች አጠቃቀም እና የይገባኛል ጥያቄ ዙሪያ የሚነሱ አለመግባባቶችን ለዘለቄታው እና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመፍታት ባህላዊው የፍትህና የህግ ተቋም ከመደበኛው የፍትህ ተቋማት የበለጠ ተመራጭ ናቸው፡፡ የባህላዊ ህግ እና የፍትህ ተቋማቱን የስልጣን ዝርዝር እና አሰራርን በተመለከተ በተለይ የወጣ ህግ ባይኖርም እና ከላይ የተመለከቱት ወጀሎችን የማየት ስልጣን ያላቸው እንደሁኔታው የመደበኛ ፍርድ ቤቶች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቢሆንም አብዛኞቹ ከላይ የተጠቀሱት እና መሰል ቅራኔዎች በአብዛኛው እየተፈቱ ያሉት በባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴ እና በእርቅ ነው፡፡
በመሆኑም መደበኛው የፍትህ አካላት የሚያከናውኑትን ባህላዊ የፍትህ ተቋማትና እና የሃገር ሽማግሌዎች በተሻለ ውጤታማ እና ዘላቂ ሠላም በሚያመጣ መልኩ እየፈቱት ያለ መሆኑ በተጨባጭ እየታየ ከሆነ ስራቸውን የበለጠ ሊያቀላጥፍ የሚችል ዝርዝር ህግ እስካሁን ላለመውጣቱ ለባህላዊ የፍትህና የህግ ተቋማቱ ተገቢውን ትኩረት እና ቦታ ካለመስጠት የዘለለ ሚዛን የሚደፋ ምክንያት ማቅረብ አዳጋች ይመስላል፡፡ ስለዚህም ህገ-መንግስቱን መሠረት አድርጎ ይህንን የሚመለከት ዝርዝር ህግ በህግ አውጪው ሊወጣ ይገባል፡፡
ከዚህ በፊትም ሆነ ወደ ፊት በባህላዊ ህግ ዙሪያ ለተደረጉት እና ለሚደረጉት ጥናቶች የሚመለከታቸው አካላት ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጡ ይገባል፡፡ በተለይም በዚህ በኩል የትኞቹ የባህላዊ ህጎች እና ቷቋማት ናቸው ጠቃሚዎቹ? ህገ መንግስቱ ካስቀመጣቸው መሰረታዊ መርሆች ጋር ተጣጥመው መሄድ የሚችሉት እንዴት ነው? ባህላዊው ህግና መደበኛው የህግ እና የፍትህ ስርአት እንዴት ሊመጋገቡ ይችላሉ? ወዘተ… የሚሉትን በስፋት መርምሮ ጠቃሚ የሚባሉትን ለይቶ ለማወቅ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ከአካባቢ ባህላዊ የግጭት መፍቺያ ተቋማት ውስጥ ግጭቶቸን በመፍታት የጎላ ልምድ ያላቸውን የሀገር ሽማግሌዎች በመምረጥ የህግ፣ የፖለቲካ ሳይንስ፣ የታሪክ፣ የአንትሮፖሎጂ፣ የስነ ህዝብ ወዘተ ምሁራንን ያቀፈ ውይይት እና አገር አቀፍ ኮንፈረንስ በማዘጋጀት ብሄረሰቡ አንድ ወጥ በሆነ መልኩ ግጭትን የሚፈታበት፣ የማህበረሰቡን የፍትህ አመለካከት እና አተያይ መሰረት ያደረገ ዘመናዊ የግጭት መከላከያ እና መፍቻ ደንብ ከሀገሪቷ እና አለም አቀፋዊ ሁኔታ ጋር እየተገናዘበ በፖሊሲ ደረጃ የሚቀረጽበት ስልት መቀየስ እና ይህንንም ገቢራዊ የሚያደረግ ተቋም የሚቋቋምበትን መንገድ ማመቻቸት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ረገድ የዚህ ተቋም የባህላዊ ህግ ጥናት ቡድን “የደቡብ ብሔሮች፣ ብሄረሰቦች ምክር ቤት” እና የጋምቤላ ክልል “የሀገር ሽማግሌዎች ምክር ቤት” አርአያ እና መነሻ ሊሆን የሚችል ትልቅ ተግባር እያከናወኑ መሆኑን ለመረዳት ችሏል፡፡ በመሆኑም ይህ አይነቱ ጥረት በሌሎች ክልሎችና በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊተገበሩ እና ድጋፍ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
ግጭቶችን አስቀድሞ የመከላከል እና ሲከቱም በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ባህል ውጤታማ እና ቀልጣፋ የሚሆነው የህዝብ ተሳትፎ ሲኖር ነው፡፡ የማህበረሰቡ ወይም የህዝቡ ተሣትፎ መኖር የባህላዊ የግጭት አፈታት ስርአት አይነተኛ መገለጫ እንደመሆኑ መጠን በየደረጃው ያሉ የፖለቲካው ስርአትና የመደበኛው የፍትህ አካላት ግጭቶችን እንዴት መከላከል እና መቆጣጠር ብሎም መፍታት እንደሚቻል በግጭት ፈቺነት ከሚሳተፉት የሃገር ሽማግሌዎች ምክር የሚያገኙበትን አደረጃጀት፣ መዋቅር እና አሰራር መፍጠር፡፡
2 እያንዳንዱ ግጭት የራሱ ባህርይና መንስኤ እንዳለው በመረዳት ከግጭቱ ዓይነትና ከህዝቡ ባህል አንፃር እየታየ ከአካባቢው ባህላዊ ግጭት መፍቻ ተቋማት ጋር በህብረት በመስራት ግጭቶችን የመፍታት ልምድ ይበልጥ የሚዳብርበትን ሁኔታ መፍጠር እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮች እና ከምንጊዜም በላይ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
ጥናቱ የሚገኝበት ሁኔታ
ጥናቱ ተጠናቆ ለዋና ዳይሬክተር ቀርቧል
ጥናቱን ያከናወነው ባለሙያ ስም
ማዕረግ ገ/እግዚአብሄር፣ ይድነቃቸው ከበደ፣ ኢሳያስ አየለ፣ መስፍን እሸቱ
ጥናቱ የተከወነበት ጊዜ
የካቲት 2004

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

https://t.me/jlrtinet

Address


Addis Ababa
1000