Kirkos Communication-ቂርቆስ

Kirkos Communication-ቂርቆስ

Share

ይህ ትክክለኛው የቂርቆስ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት የፌስቡክ ፔጅ ነው

Photos from Kirkos Communication-ቂርቆስ's post 30/10/2025

የፕሮዳክሽን ስራዎችን ጥራት በማሳደግና አዳዲስ ሀሳቦችን በመጨመር የመረጃ ተደራሽነትን ለማስፋት ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት አስታወቀ።
*******
ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም

በዛሬው እለትም ለዚሁ ስራ ግብአት ይሆን ዘንድ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት የተገነባውንና ሙሉ ግብአት የተሟላለትን ዘመናዊ የብሮድካስት ስቱዲዮ በቦታው በመገኘት የፅህፈት ቤቱ የዘርፉ ባለሙያዎች ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በዘርፉ ከሚገኙ ተቋማት ጋር የጉብኝትና የልምድ ልውውጥ ማድረግ ለተቋም ስራዎች ውጤታማነት ከፍተኛ ሚና እንዳለው የገለፀው ተሞክሮ ወሳጁ ጽህፈት ቤት በልምድ ልውውጡ የስቱዲዮ ግንባታ ፕሮጀክት ስራና ተያያዥ ስራዎችን ምልከታና የልምድ ልውውጥ እንደተደረገ ገልጿል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሠርካለም ተፈሪ እንደተናገሩት አቻ ተቋማት የልምድ ልውውጥ በማድረግ አንዱ ላይ ያለውን የተሻለ ስራ ለሌላው በማካፈል ለነዋሪው ማህበረሰብ ጥራት ያለው መረጃ በስፋት ተደራሽ በማድረግ የተቋሙን አላማ ከግብ ማድረስ ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የከተማዋ እምብርት ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ያንን የሚመጥን ዘመናዊ ሁለገብ ስቱዲዮ እንዲኖራትና ጥራት ያለው አጫጭር ፕሮግራሞችን፣ ቶክ ሾዎችን፣ የገፅ ለገፅ ውይይቶችን፣ የክፍለ ከተማውን እለታዊ ዘገባዎችን፣ የፕሮዳክሽን ዜናዎችን፣ በጥራት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው፤ ያንን ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚረዳ ሀሳብና መሬት የነካ፤ ዘመኑን የዋጀ የፕሮዳክሽን መተግበሪያ ሁለገብ ብሮድካስት ስቱዲዮ ከነሙሉ ግብአቱ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ተመልክተናል፤ ያንን ተሞክሮ በመውሰድ በክፍለከተማው እንዲኖር ጥረት ይደረጋል ሲሉ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

30/10/2025

አዲስ አበባ፡
የአፍሪካ የውበት ፈርጥ ፣ የእድገት ተምሳሌት፣ የለውጥ መዲና

Addis Ababa:
Africa’s iconic image of Beauty, fast growth and real Transformation

Photos from Kirkos Communication-ቂርቆስ's post 30/10/2025

የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ለ10 ቀናት የሚያደርገውን ክትትልና ድጋፍ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዛሬ ጀመረ።
*******
ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም

ድጋፍና ክትትሉ ለበለጠ ጥንካሬ ክፍተትን አውቆ ፈጥኖ ለማረም የሚረዳን ነው ሲልም የክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ገልጿል፡፡

ይህ የክትትልና ድጋፍ ቡድን የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ያዋቀረው ሲሆን እስከ ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም ለ10 ቀናት የሚቆይ እንደሆነም በክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ብርሀኑ ለኮሙዩኒኬሽን ገልፀዋል፡፡

ቡድኑ የ2018 በጀት አመት 2ኛ ሩብ አመት የድጋፍና ክትትል መርሀ-ግብሩ እንደሆነ የጠቆሙት ምክትል ሀላፊው የክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ጽህፈት ቤት የሁሉም ወረዳ የጽ/ቤት ሃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ባሉበት በማስፈጸሚያ ሰነዱ እንዲሁም ቡድኑ በክትትልና ድጋፉ በሚቆይበት ወቅት ምን መደረግ እንዳለበት ግንዛቤ ተሰጥቷል፡፡፡

የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በ10 ቀናት ቆይታውም የክፍለ ከተማውን ስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት እንቅስቃሴ ጨምሮ በተመረጡ ወረዳዎች ላይ ያሉ አፈፃፀሞችን የሚመለከትና የቆይታ ማጠቃለያም የጋራ መውጫ ግብረ መልስ የሚሰጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝ ድጋፍ ዘርፍ ዳይሮክትሬት ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ደበላ ተናግረዋል፡፡

30/10/2025
Photos from Kirkos Communication-ቂርቆስ's post 30/10/2025

12ኛ ክፍል ላጠናቀቁ ተማሪዎች በሙያና ቴክኒክ ስልጠና ዙሪያ በዛሬው እለት ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መስራቱንና የመስክ ጉብኝት ማድረጉን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ገለፀ፡፡
*********
ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም

"የሙያ ስልጠና እንደ አንድ አማራጭ ተወስዶ በዛም በመሳተፍ የተመቻቸውን መልካም እድል መጠቀም እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡

ፅህፈት ቤቱ በክፍለ ከተማው ከሚገኘው ከማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ጋር በመሆን 12ኛ ክፍል ላጠናቀቁ ተማሪዎች በሙያና ቴክኒክ ስልጠና ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መሰራቱን የፅህፈት ቤቱ ምክትል ሀላፊ አቶ ብርሀኑ ለኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ገልፀዋል፡፡

ኮሌጁ የ2018 ዓ.ም መደበኛ ሰልጣኞች ቅበላ በማድረግ በጥራት ትምህርቶችን ለመስጠት መዘጋጀቱን የገለፁት አቶ ብርሀኑ በዘንድሮው አመትም በሙያ ተኮር ዘጠኝ ዘርፎች ላይ ለተማሪዎቹ የማስገንዘብ ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

ኮሌጁ ብቃት ባላቸው መምህራን እየታገዘ አምራች ትውልድ እያፈራ ነው ያሉት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ምክትል ሀላፊና የስልጠና ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ታደሰ ናቸው። በዘንድሮው አመትም ወደኮሌጁ ለሚገቡ ተማሪዎችም በ9 ዘርፎች ላይ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

በቀን (ሁለት አመት)፣ በማታ (ሁለት አመት ተኩል)፣ በቅዳሜና እሁድ (ሁለት አመት ተኩል) ምዝገባ በመካሄድ ላይ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

ተማሪዎችም የሚማሩባቸውን ክፍሎችና የመማሪያ ግብአቶችን ጎብኝተዋል፡፡

Photos from Kirkos Communication-ቂርቆስ's post 30/10/2025

የቂርቆስ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ጽ/ቤት የ2018 1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀምን ከ100% በላይ ማሳካቱን አስታወቀ።
*****
ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም

ጽ/ቤቱ በዛሬው እለት የ1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀሙን አስመልክቶም ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄዷል።

ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የበጀት አመቱን ሲጀምር “አገልጋይነት ለተገልጋይ ከፍታ እና አመኔታ” በሚል መሪ ቃል መሆኑን ያስታወሱት ስራ አስኪያጁ ለተገልጋይ እርካታ፣ ሙያዊ ስነ-ምግባር እና ተቋማዊ ውጤታማነት ያለውን ጠንካራ ቁርጠኝነት አሳይቷልም ብለዋል።

የቂርቆስ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ጽ/ቤት 529,230,841.84 ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡንም የገለጸ ሲሆን የተሽከርካሪ ፍቃድ አገልግሎት በ1ኛ ሩብ ዓመት ዉስጥ 529,230,841.84 መሰብሰብ መቻሉንም አስታውቋል በተያዘዉ እቅድ መሰረት በስኬት ማጠናቀቁን በመግለጽ።

ጽህፈት ቤቱ በ2018 በጀት አመት በ1ኛ ሩብ ዓመት ዉስጥ የቀረበ ቅሬታ አለመኖሩንም የጽህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ አሰፋ ገልጸዋል።

ተቋሙ ለዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጥ፣ ቀልጣፋ አሰራር እና የተገልጋይ እርካታን ለማሻሻል ያለውን ቁርጠኝነት በማሳደግ ከ42 መሰረታዊ አገልግሎቶች መካከል በ35ቱ በዲጂታል ሲስተም በመታገዝ በአጠቃላይ የ1ኛ ሩብ ዓመት ዉስጥ 41,627 ተገልልጋዮች አገልግሎት መስጠት መቻሉንም አቶ ደረጄ ተናግረዋል።

በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተደረገው ለውጥ ቅልጥፍናን እና ግልጽነትን በእጅጉ አሳድጓል ነው ያሉት ስራ አስኪያጁ፡፡

ተቋሙ ከ232,332 በላይ ፋይሎች በኢ-ፋይል ወደ ሲስተም በማስገባት የወረቀት ስራን በመቀነስ የአገልግሎት ፍጥነት እና ትክክለኛነትን በማሻሻልና የወረፋ ስርዓትን በማስጠበቅ ፍትሃዊ አገልግሎት እንዲሰጥ አድርጓል።

ጽህፈት ቤቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የVIP አገልግሎት፣ ዘመናዊ የቅሬታ አቀራረብ ስርዓት፣ ለተገልጋይና ለአገልግሎት ሰጭ ባለሙያዎች ምቹ የቢሮ ሁኔታን በመፍጠር የስራ አካባቢን የበለጠ አሻሽሏል ፤እንደ ባንክ፣ኢንሹራንስ እና የመንገድ ፈንድ ያሉ አገልግሎቶች በአንድ ቦታ በመስጠት የአገልግሎት ፍጥነትን ከፍ አድርጓል፡፡

የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እያስመዘገበ ያለውን ለዉጥ ተከትሎ የ1ኛ ሩብ ዓመት ውስጥ፣ በቂርቆስ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደር፣ በክልሎች እና በአለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ተቋማትና የስራ ሃላፊዎች ጉብኝቶች ተካሂደዋል።

የተገኘው ውጤት የተሻሻለ የአገልግሎት አሰጣጥ፣የስራ ክፍሎች የተሻለ ቅንጅታዊ አሰራር እና ቴክኖሎጂን ውጤታማ በሆነ መንገድ በመጠቀም የተገኙ ውጤቶች መሆናቸውን ተመላክቷል።

በዉይይት መድረኩ ላይም ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተዉ ማብራሪያ የተሰጠባቸው ሲሆን አጋርነትን ለማጠናከር እና አገልግሎት ጥራት ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቱ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

Photos from Kirkos Communication-ቂርቆስ's post 30/10/2025

ሀገር በቀል የሰላምና የመቻቻል እሴቶችን ለመገንባት የሴቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ።
*******************
ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ጋር በመተባበር ሃገር በቀል ሰላምና መቻቻል እሴቶች ለትውልድ ግንባታ ያላቸው ፋይዳና ከሴቶች የሚጠበቅ ሚና በሚል መሪ ቃል ኮንፍረንስ ተካሄደ ።

በዉይይት መድረኩ ላይም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ሰመሀል ገ/መድህን እና የክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሃዊ ጌታቸዉ ተገኝተው ውይይት አካሄደዋል።

Photos from Kirkos Communication-ቂርቆስ's post 30/10/2025

የተቋሙ ውጤታማነት ከህዝብ እርካታ አንጻር እየተለካ መሄድ እና መስራት እንደሚገባ የቂርቆስ ክፍለ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ ።

ጥቅምት 20/2018
በዛሬው ዕለትም ጽህፈት ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ከባለድርሻ አካላት ፣ በቅንጅት ከሚሰሩ ተቋማትጋር የተሰሩ ስራዎችን እና በመልካም አስተዳደር የተፈቱ ችግሮች በጋራ ገምግሟል ።

ጽህፈት ቤቱ ለተከታታይ ዓመታት ውጤታማ ተቋም መሆኑን በመግለፅ ይህንን የተቋሙ ውጤታማነት ብቻ ሳይሆን ውጤቱ ከህዝብ እርካታ አንጻር እየተለካ መኬድ እንዳለበት የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ በለጠች ተሰማ ተናግረዋል ።

ጽህፈት ቤት ኃላፊዋ አክለውም ከሌማት ትሩፋት በተያያዘም የኬጂ እና የደሮ ስርጭት ተደራሽነት ላይ በትኩረት ሰጥቶ በመስራት በሕብረተሰቡ የኑሮ ሁኔታ ተጨባጭ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ መስራት እና ለዚህም ለእያንዳንዷ የከተማ ግብርና ስራ የተጠያቂነት ስርዓት ማስፈን እንደሚገባ ገልፀዋል ።

በዚሁ የውይይት መድረክም አጠቃላይ በሩብ ዓመቱ የነበሩ ጥንካሬዎች እና መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች በዝርዝር ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸው መግባባት ላይ ተደርሷል ።

Photos from Kirkos Communication-ቂርቆስ's post 30/10/2025

የብልፅግና ፓርቲ ዓመታዊ ስልጠናውን ማካሄድ ጀመረ

የብልፅግና ፓርቲ የ2018 ዓመታዊ የከፍተኛ አመራሮች ስልጠናውን ማካሄድ ጀምሯል።

ስልጠናው "በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እምርታ" በሚል መሪ ሀሳብ ለሚቀጥሉት 10 ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።

ስልጠናው የአመራሩን እውቀት፣ ክህሎትና አቅም የሚገነቡ ልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች የሚቀርቡበት ነው።

በስልጠናው ከ2000 በላይ ከፌዴራልና ከክልል የተወጣጡ ከፍተኛ አመራሮች ይሳተፋሉ።

ከስልጠናው በተጓዳኝ የተግባር የመስክ የልማት ስራ ጉብኝቶች የሚካሄድ ይሆናል።

Photos from Kirkos Communication-ቂርቆስ's post 30/10/2025

የአዲስ አበባ አሁናዊ የቀን ገፅታ !

Photos from Kirkos Communication-ቂርቆስ's post 29/10/2025

ከተረጂነት ወደ አምራችነት የሚደረገው ጉዞ በቂርቆስ ተጠናክሮ መቀጠሉን የክፍለ ከተማው ስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
***************
ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም

በዛሬው እለትም በሴፍቲኔት ተጠቃሚ ከነበሩት ከ170 ያላነሱ ሰዎች ጋር ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ወደሚሸጋገሩበት ሁኔታ ላይ ምክክር መደረጉን የፅህፈት ቤቱ ምክትል ሀላፊ አቶ ብርሀኑ ሀይሉ ለቂርቆስ ኮሙዩኒኬሽን ገልፀዋል፡፡

በንግድ፣በአገልግሎት እና በእድገት ተኮር ተደራጅተው ወደ ስራ ለማስገባት ታስቦ የተደረገው ውይይት ከወረዳ ተመልምለው የመጡትን የክፍለ ከተማ ስትሪንግ ኮሚቴዎች የጋራ በማድረግ የማጽደቅ ስራ ተሰርቷል ብለዋል ምክትል ሀላፊው ።

በቀጣይ ከከተማ አስተዳደሩ በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት በፍትሃዊነት ወደ ስራ የማስገባት ስራ ይሰራል ያሉት አቶ ብርሀኑ ለዛ የሚሆን መስሪያ ቦታ በክፍለ ከተማው ወረዳ 04 በአለም ባንክ ድጋፍ የተገነባው G+4 ለዚሁ አላማ እንደሚውልም አመላክተዋል፡፡

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Mariot Hotel
Addis Ababa