21/10/2025
የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሳይፈቀድላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉ በሊዝ የሚተዳደሩ 2,969 ቦታዎች ወደሕጋዊ ሥርዓት እንዲገቡ የአገልግሎት ለውጥ ጥያቄዎችን ተቀብሎ ፈቃድ ሰጠ።
ሳይፈቀድላቸው የአገልግሎት ለውጥ አድርገው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሊዝ ባለይዞታዎች በተሻሻለው የከተማ መሬት ሊዝ ደንብ 162/2016 አንቀጽ 54 ንዑስ አንቀጽ 1-11 መሠረት የአገልግሎት ለውጥ አድርገው በሕጋዊ መንገድ
እንዲንቀሳቀሱ ቢሮዉ ፍቃድ ሰጥቷቸዋል።
በዚህም በእስካሁኑ ተፈቅዶላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉ ባለይዞታዎች 2,969 ሲሆኑ 2,581 (86%) የሊዝ ባለይዞታዎች የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ክፍያ ከፍለው በማጠናቀቅ ወደ ሕጋዊ ሥርዓት እንዲገቡ ወይም የንግድ ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ተደርጓል።
በበጀት ዓመቱ ከዚህ የአገልግሎት ለውጥ 2.4 ቢሊዮን ብር ገቢ ይሰባሰባል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ሳይፈቀድላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉና ለውጥ የተፈቀደላቸው የሊዝ ባለይዞታዎች የሚጠበቅባቸውን የሊዝ ቅድመ-ክፍያ እስከ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም ድረስ ከፍለው ማጠናቀቅ እንደሚጠበቅባቸውም ቢሮው አሳስቧል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት ና አስተዳደር ቢሮ
29/08/2025
በትክክለኛ አመራር ስለተመራን ታላላቅ ስኬቶችን ማምጣት ችለናል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላስመዘገበው ድል፣ እንኳን ደስ አላችሁ! ይህ ሽልማት ለሀገራችን ትልቅ ኩራት ነው። በተለይ በዓለም አቀፍ ደረጃ በብሉምበርግ በተዘጋጀው ውድድር የወርቅ ሽልማት ማሸነፍ፣ ከተማችን በፈጠራ እና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም የመንገድ ደህንነትን በማሻሻል ያሳየችውን ጠንካራ ቁርጠኝነት ያሳያል።
ይህ ደግሞ በአመራሩ ብቃት እና ራዕይ የተገኘ ድል ነው። ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና መላው ቡድን በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ ለውጥ በማምጣት የአገራችንን ስም ከፍ አድርገዋል።
ይህ ሽልማት አዲስ አበባ የተሻለ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ለማድረግ የተደረገው ጥረት ውጤት ነው። የተገኘው ሽልማት ደግሞ ለቀጣይ የልማት ስራዎች መነሳሻ መሆኑ ለሀገራችን ተጨማሪ ተስፋ ይፈጥራል።
ይህ የሚያሳየው በትክክለኛ አመራር እና ቁርጠኝነት ታላላቅ ስኬቶችን ማምጣት እንደሚቻል ነው። ለዚህም ነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሀገሪቱን ታሪክ እየቀየረ ነው የምንለው።
27/08/2025
ብለህ ፃፍበት “ታሪክ ተሰራ”!
ታሪክ ሰሪው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከቆራጡ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ጋር በመሆን ከዓድዋ ድል በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመላው አፍሪካ ምሳሌ የሚሆን የወል ታሪክ ሰርቷል። ይህ የኛ ዘመን ታሪክ የጦርነት ድል ታሪክ ሳይሆን የልማት፣ የጋራ ብልፅግና፣ የኢትዮጵያ ኃያልነት ማረጋገጫ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መቶ ፐርሰንት መጠናቀቅ ነው። ይህ ታሪክ ልክ እንደ የዓድዋ ድል ታሪክ ከትውልድ ትውለድ የሚሸጋገር አስደናቂ የዘመናችን የድል ታሪክ ነው። እንደ አንድ የዚህ ትውልድ አካል ሁላችንም ሊያኮራን የሚገባ ድል ነው።
#ዐቢቹ
#ኢትዮጵያ
26/08/2025
የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት የሆነችው ግብጽ በሀገር ውስጥ እና በጎርበት ሀገር ውስጥ ረብጣ ዶላሮችን በመመደብ ኢትዮጵያን እንዲያበጣብጡላት የምታደርጋቸው ዘመናዊ ፈረሶች የሚከተሉት ናቸው።
1. ሸዓቢያ (ጉዳይ አስፈፃሚ)
2. ወያኔ (ፈፃሚ እና ተላላኪ)
3. ፋኖ (ፈፃሚ እና ተላላኪ)
4. ሸኔ (ፈፃሚ እና ተላላኪ) እነዚህ ተላላኪ እና ጉዳይ አስፈጻሚ የሆኑት አካላት ኢትዮጵያ ሰላም እንዳትሆን እና ህዝቦቿ በሰላም ወጥቶ እንዳይገቡ ተልዕኮ በመቀበል በተለያዩ ስፍራዎች እሳት የሚለኩሱ የሰይጣን ቁራጮች ናቸው። እንደ እነሱ ሀሳብማ ቢሆን ኢትዮጵያን ልክ እንደ የመን እና ሶሪያ አፈራርሶ መንግስት አልባ ለማድረግ ያላደረጉት ነገር የለም ግን በጀግናው ሀገር መከላከያ ሰራዊት ጠንካራ ኦፕረሺኖች እና በሀገር ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠናካራ ስራ ሀገራችንን ከአውሬዎች አፍ ተርፋ ወደ ብልጽግና ተስፋዋ እያንሰራራች ትገኛለች! ወደዳችሁም ጠላችሁ ኢትዮጵያ ከሰይፋችሁ አምልጣ ትበለጽጋለች!!