FDRE Gov't Whips' Office-የመንግስት ተጠሪ

FDRE Gov't Whips' Office-የመንግስት ተጠሪ

Share

This is Official page of FDRE House of People's Representatives Government whip's Office.

05/02/2023

በወቅታዊ ጉዳይ ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ ‼️

ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ በውስጣዊ አሠራር መፈታት እንዳለበት መንግሥት ያምናል።

ሀገራዊ ተቋማት አንድነታቸውንና ጥንካሬያቸውን ጠብቀው እንዲዘልቁ ከዚህ በፊትም ሆነ ችግሮች በተፈጠሩ ጊዜ ሁሉ መንግሥት የሚጠበቅበትን ሲወጣ ቆይቷል። ይሄንን ጥረቱን አሁንም አጠናክሮ ይቀጥላል። የተቋማቱን አንድነት የሚፈታተኑ ችግሮች ከውስጥ ሲነሡ በውይይትና በውስጣዊ አሠራር እንዲፈቱ ድጋፍ ሲያደርግ ነበር። በተጨባጭ ውጤት አምጥቷል።

ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት በሰላማዊ መንገድ በውይይትና በቤተ ክርስቲያኒቱ አሠራር መሠረት እንዲፈታ ሁሉም አካላት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት ይኖርባቸዋል። የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ሁለቱን ወገኖች በማቀራረብ ችግሩ በሰከነ መንገድ እንዲፈታ ማድረግ አለባቸው።

አማኞች ችግሩን ከማወሳሰብና ለሌሎች አካላት መጠቀሚያ ከመሆን በመታቀብ ገንቢ ሚና ሊጫወቱ ይገባል። የጸጥታ አካላት የየአካባቢውን ሕዝብና የእምነት ተቋማት ሰላምና ጸጥታ ማስከበር ግዴታቸው ነው። ግጭት የሚያባብሱ አካላትንም ሥርዓት ማስያዝ አለባቸው።

የሚዲያ አካላት ችግሩን የሚያባብሱ ነገሮችን ከማቅረብ መቆጠብ ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም መላው ሕዝብ ለችግሩ መፈታት የሚጠበቅበትን እንዲያደርግ መንግሥት ያሳስባል።

በሌላ በኩል እምነትና ብሔርን ተገን አድርገው ግጭት ለመፍጠር የሚያስቡ፣ ሀገር ለማፍረስ በተለያዩ መንገዶች ሞክረው ያልተሳካላቸው ኃይሎች፣ ችግሩ እንዲባባስና እንዳይፈታ ለማድረግ እየሠሩ መሆኑ ተደርሶበታል። መንግሥት ይሄንን ፈጽሞ አይታገሥም።

ችግሩን ለማባባስና በሕዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር፣ ብሎም ሀገርን ወደፈተና ለማስገባት በሚጥሩ አካላት ላይ መንግሥት ሕግ የማስከበር ሥራውን እንደሚሠራ በዚሁ አጋጣሚ ያሳውቃል።

ጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Photos from FDRE Gov't Whips' Office-የመንግስት ተጠሪ's post 03/02/2023

የሕዝብ ተወካዮች፤ ከመረጣቸው ሕዝብ ጋር በመወያየት ለጥያቄዎቻቸው መፍትሄ እንዲያገኙ እየሰሩ ያለውን ስራ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ተባለ

(ዜና ፓርላማ)፣ ጥር 26፣ 2015 ዓ.ም፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከተሰጣቸው ተልዕኮ መካከል የሕዝብ ውክልና ሥራ ቁልፍ ተግባራቸው በመሆኑ፤ የመረጣቸውን ሕዝብ በማወያየት ለሚነሱ ጥያቄዎችና ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ በቅንጅት መሠራት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በዓመት ሁለት ጊዜ ከመረጣቸው ሕዝብ ጋር በመገናኘት በሚሰሩት የውክልና ስራ ዙሪያ ገለፃ ተደርጓል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር የተከበሩ አቶ ተስፋዬ በልጂጌ በዚህ ወቅት እንዳሉት በሕዝብ የተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች የሕዝቡን የልብ ትርታ በቅርበት በማድመጥ ለሚነሱ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች ምላሽ እንዲያገኙ ተወካዮች የማይተካ ሚና እንዳላቸው አውቀው ሊሠሩ ይገባል ብለዋል፡፡

የተከበሩ አቶ ተስፋዬ በልጂጌ አክለውም አባላቱ የሰላም ግንባታ፣ የፀጥታ እና የህግ ማስከበር ሂደቶች፣ በወጡ ህጎች አፈፃፀም፣ የፕሮጀክትና አጠቃላይ የልማት ስራዎች አፈፃፀሞች በውክልና ስራው ትኩረት ሊሰጡባቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል። ህጋዊነትን ከማረጋገጥ አኳያ አባላቱ ልዩ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ የተከበሩ ወ/ሮ መሰረት ኃይሌ በበኩላቸው አባላት በውክልና ስራቸው ወቅት ሊከተሏቸው የሚገቡ አሰራሮች ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ወደመረጣቸው ሕዝብ በመሄድ በሚሠሩት የውክልና ስራ ከክልል ምክር ቤት አባላት እና በየደረጃው ካሉ ምክር ቤቶች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በዓመት ሁለት ጊዜ በየካቲት ወር እንዲሁም ምክር ቤቱ ሰኔ 3ዐ ተዘግቶ እስኪከፈት ባለው ጊዜ የምክር ቤቱ አባላት ወደ ተመረጡበት አካባቢ በመሄድ የውክልና ሥራ እንደሚሠሩ የሚታወቅ ነው፡፡

Photos from FDRE Gov't Whips' Office-የመንግስት ተጠሪ's post 23/10/2022

በግብርናው መስክ የተጀመሩ የልማት ስራዎች በምግብ ራስን ከመቻል ባሻገር ለኢኮኖሚ ሉዓላዊነት መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ገለጹ

በግብርናው መስክ ምርታማነትን ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች በምግብ ራስን ከመቻል ባሻገር ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች በጅማ ዞን እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ የልማት ስራዎችንና የቦንጋ ዩኒቨርሲቲን የልማት እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉ ሚኒስትሮች በጉብኝት መዳረሻዎቹ እየተከናወኑ ያሉ የግብርና ልማት ስራዎች እንደ ሀገር ትልቅ የሽግግር አቅም መሆናቸውን ገልጸዋል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ፤ በተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ የግብርና እና ሌሎችም የልማት ስራዎች በምግብ ራስን ለመቻል ለሚደረገው ጥረት የስኬት መንገድ ማሳያዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዳሉት፤ በቦንጋ የታየው አስደናቂ ስራ በሌሎች ተቋማትም ተመሳሳይ የልማት ስራ ከተከናወነ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ስኬት የሚረጋገጥ መሆኑን ያመላከተ ነው።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የመንግሥት ተጠሪ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በበኩላቸው፤ በጉብኝታችን በአካባቢዎቹ ቀደም ሲል ያልተለመዱ አዳዲስ የግብርና ልማት ስራዎችን በስፋት ተመልክተናል ብለዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዛዲግ አብረሃ፤ በሁሉም መስክ የተመለከትናቸው የልማት እንቅስቃሴዎች ኢትዮጵያ ከዝቅተኛ አምራችነት በመሸጋገር ላይ መሆኗን የሚያመላክቱ ናቸው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Photos from FDRE Gov't Whips' Office-የመንግስት ተጠሪ's post 22/09/2022

(ዜና ፓርላማ)፣ መስከረም 4፣ 2015 ዓ.ም.፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመሬት ወረራና በፀጥታ ስራ ላይ ትኩረት መስጠት እንዳለበት ከአዲስ አበባ የተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጠቁመዋል፡፡

አባላቱ ዛሬ ከከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በአስተዳደሩ በተከናወኑ ተግባራትና በሕዝብ እየተነሱ ባሉ ጥያቄዎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በዚሁም ወቅት ከተማ አስተዳደሩ ሕዝቡ የሚያነሳውን የኑሮ ውድነት ለማቃለል እያደረገ ያለው የምገባ ስርዓት፣ ሰላምና ፀጥታ ለማሻሻል የሚደረገው ጥረት፣ የግንባታ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም፣ የአካባቢ ፅዳትና ውበት አፈፃፀም ላይ እያከናወናቸው ያሉትን ተግባራት በአዎንታዊ ያነሱት አባላቱ አሁንም በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በኑሮ ውድነት፣ በግንባታ አቅርቦት እንዲሁም በመሬት ወረራና በፀጥታ ችግር ዙሪያ አመራሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት አመላክተዋል።

የከተማው ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው በየደረጃው ያለው አመራር እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በተለያዩ ጊዜያት በመውረድ ከሕዝቡ ተቀራርቦ እንዲሰራ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን ጠቁመው ከተማ አስተዳደሩ ከነዋሪው ለተነሱ ጥያቄዎች በየደረጃው መልስ እየሰጠ መሆኑንም ተናግረዋል።

አባላቱ በቀጣይ ከሕዝብ በሚያደርጉት ውይይት የሚነሱ ጥያቄዎችንና ሀሳቦችን ለመመለስ ከተማ አስተዳደሩ በሁሉም መዋቅር ግብረ-መልሶቹን የዕቅዱ አካል ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራም ከንቲባዋ አረጋግጠዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በቀጣይ ቀናት በየምርጫ ክልላቸው በመውረድ ከመራጮች ጋር እንደሚወያዩም ተጠቁሟል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament

በዩቲዩብ https://www.youtube.com/watch?v=cp_8F5TEeFE

በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews

በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr

በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ

Photos from FDRE Gov't Whips' Office-የመንግስት ተጠሪ's post 22/09/2022

(ዜና ፓርላማ)፤ ነሐሴ 10፣ 2014 ዓ.ም.፣ አዲስ አበባ፤ በጎፋ ዞን ምርጫ ክልሎች የፌዴራል ፓርላማ ተወካዮች እና የክልል ምክርቤት አባላት ከመራጩ ሕብረተሰብ ጋር የውይይት መድረክ አካሄደዋል፡፡

የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚንስትር የተከበሩ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ መራጩን ሕዝብ በየጊዜው ማወያየት እና ለሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ለማሰጠት የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

በሀገሪቱ በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች የዴሞክራሲ ባህል እየተገነባ እንዲሄድ፣ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍንና ልማት እንዲፋጠን የማይተካ ሚና እንዳላቸው የገለፁት ደግሞ የጎፋ ዞን ነዋሪዎች ናቸው፡፡

ነዋሪዎቹ ይህንን የገለጹት የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት እና የክልል ምክር ቤት አባላት በጎፋ ዞን ምርጫ ክልሎች ከሕብረተሰቡ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡

በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በተካሄደው የመራጭ ተመራጭ ውይይት፤ ለረጅም ዘመናት ከሕብረተሰቡ ዘንድ ይነሱ ለነበሩ ጥያቄዎች ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በየደረጃው ያሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሰጧቸውን ምላሾች በዝርዝር ተብራርተዋል።

በተመሳሳይም የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመቅረፍ፣ የልማት ስራዎችን ከማፋጠን እና የኑሮ ውድነትን ከመቆጣጠርና የገበያ ዋጋን ከማረጋጋት አንፃር እርምጃዎች የተወሰዱ እንደሆነም በውይይቱ ተነስቷል።

እስከ አሁን የተከናወኑ አፈፃፀሞችን ያደነቁት የውይይቱ ተሳታፊዎች፤ በቀጣይ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ መፍታት ካለበት አበይት ጉዳዮች መካከል የመሰረተ ልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና የኑሮ ውድነት መሆናቸውን ተናግረዋል።

የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር የተከበሩ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በውይይቱ ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት የአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያዊያን ከምንጊዜውም በላይ አንድነታችንን በማጠናከር እያጋጠሙን ያሉ ፈተናዎችን በድል ለመወጣት መረባረብ የሚጠበቅብን ወቅት ነው ብለዋል።

በሀገሪቱ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር፣ የሰላምና ፀጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ ህዝቡ ከመንግስት ጎን በመቆም የተለመደውን ድጋፍ ማጠናከር እንደሚገባውም የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም እንደ ሀገር እየገጠመን ያለውን የኑሮ ውድነት ፈተና ለመቋቋም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በህዳሴ ግድባችን ላይ ባሳየነው ኢትዮጵያዊ አንድነትና ቁርጠኝነት ልንረባረብ ይገባል በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።

አክለውም ሕዝቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በየደረጃው ለሚገኘው የመንግስት አስፈፃሚ አካል እንደሚያደርሱ እና አፈፃፀሙን እንደሚከታተሉም አፅዕኖት ሰጥተው ገልፀዋል።

ዘጋቢ፡- የመንግስት ተጠሪ ፅ/ቤት
ቀን፡- ነሐሴ 10፣ 2014 ዓ.ም

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ https://youtu.be/kiCsgFwJzho
በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ

Photos from FDRE Gov't Whips' Office-የመንግስት ተጠሪ's post 22/09/2022

(ዜና ፓርላማ)፤ መስከረም 10፣ 2015 ዓ.ም.፤ የአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በከተማዋ ነዋሪዎች የሚነሱ የልማትና የጸጥታ ጥያቄዎች በሚፈቱበት ሁኔታ ተወያይተዋል።

ነዋሪዎቹ የከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ የድጎማ ስርዓት በመዘርጋት በእሁድ ገበያ በማስፋፋት ሸማችና አምራችን የማገናኘት፣ የተቀናጀ የከተማ ግብርና እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች እና ተማሪዎችን የምገባ መርሃ ግብር ማድረጉ የሚደነቅ ቢሆንም መሠረታዊ የሸቀጦች ዋጋ ንረት እንዲረጋጋ ለማድረግ ተጨማሪ ተግባራት እንዲከናወኑ ጠይቀዋል።

ህገ-ወጥ የመሬት ወረራና የወጣቶች የስራ አጥነትንም ለመቅረፍ በልዩ ትኩረት እንዲሰራ ነዋሪዎቹ አሳስበዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በበኩላቸው የከተማው አስተዳደር የህብረተሰቡን ህይወት ለመለወጥና ከተማዋን ለነዋሪው ምቹ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን መገንዘባቸውን ገልፀው የነዋሪውን የእለት ተእለት ኑሮ እየተፈታተነ ያለውን ኑሮ ውድነት ለመቅረፍና ከተማዋን ምቹ ለማድረግ የከተማው አስተዳደር የበለጠ አቅዶ መሥራት እንዳለበትም አሳስበዋል።

በከተማው በተካሄዱት ውይይቶች የየሴክተር ኃላፊዎች በህብረተሰቡ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ የሰጡ ሲሆን ተሳታፊዎች ወቅታዊ ሀገራዊ ችግሮችን ለመፍታትና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ የተጀመሩ ተግባራትን አጠናክረው ለመቀጠል ቃል ገብተዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament

በዩቲዩብ https://www.youtube.com/watch?v=cp_8F5TEeFE

በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews

በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr

በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Ethiopian Parlament
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 23:30